Apostolic Vicariate of Meki

Apostolic Vicariate of Meki Ethiopian Catholic Church Apostolic Vicariate of Meki

11/09/2026

የብጹዕ አባታችን አቡነ አብርሃም ደስታ የመቂ ሀገረ ስብከት ጳጰስ የአዲስ ዓመት (2019) መልእክት

      ዮሐንስ ወንጌል 15 : 16"እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ አብም በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ እንደሚሰጣችሁ፥ እንድትሄዱና ፍሬ እንድታፈሩ ፍሬአችሁም እንዲኖር ሾምኋችሁ...
27/08/2026


ዮሐንስ ወንጌል 15 : 16
"እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ አብም በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ እንደሚሰጣችሁ፥ እንድትሄዱና ፍሬ እንድታፈሩ ፍሬአችሁም እንዲኖር ሾምኋችሁ።"

ቀን፦ ነሐሴ 23 ቀን 2018 ዓ.ም. (ቅዳሜ)

በሁሉን ቻይ አምላክ ፈቃድና ጸጋ፣ የምዕመናንን ጸሎትና ድጋፍ አግኝተው ወደ ቅዱስ የክህነት አገልግሎት ለመግባት የተዘጋጁት ዲያቆን ኢዮብ ተከሌ እና ዲያቆን ሐብተሙ ዋቄ የካህናት ሹመት በደስታና በምስጋና ለመቀባል ተዘጋጅቷል።
ስለሆነም በዚህ ታላቅና በረከት በተሞላበት የእምነት በዓል ላይ በመገኘት፣ በጸሎትና በመንፈሳዊ ድጋፍ ከእነርሱ ጋር እንድትሆኑ በአክብሮት እንጋብዛችኋለን።
በመቂ ሀገረ ስብከት በካቴድራል ቤተክርስቲያን የመቂ ሀገረ ስብከት ጳጰስ አቡነ አብርሃም ደስታ
ይህ የክህነት ሹመት ለዲያቆናቱ፣ ለቤተሰቦቻቸው እና ለመቂ ሀገረ ስብከት ታላቅ የደስታና የምስጋና ቀን ነው። በመሆኑም በዚህ ታላቅ መንፈሳዊ ዝግጅት ላይ በመገኘት ደስታችንን እንድትጋሩ እንጋብዛችኋለን።
ዲያቆን ኢዮብ ተከሌ እና ዲያቆን ሐብተሙ ዋቄ በክህነት አገልግሎታቸው ለቤተክርስቲያንና ለሕዝበ እግዚአብሔር በትሕትና፣ በፍቅር፣ በታማኝነትና በቅድስና እንዲያገለግሉ ጸሎታችንን እናቅርብላቸው። በጸሎትና በአክብሮት፣

26/08/2026

የወጣቶች ስልጠና በብሻን ጉራቻ

22/08/2026
 16/12/2018 "Manifesting Catholic Identity in Neighborhood" በምለው ላይ በአባ ቸርነት በየነ ለወጣቶች ተሰጥቷል join👇👇👇👇👇 🙏🙏🙏🙏
22/08/2026



16/12/2018

"Manifesting Catholic Identity in Neighborhood" በምለው ላይ በአባ ቸርነት በየነ ለወጣቶች ተሰጥቷል

join👇👇👇👇👇
🙏🙏🙏🙏

21/08/2026
የ2018 ዓ.ም  ! #"አይዟችሁ!_እኔ_ነኝ፤_አትፍሩ!" (ማቴዎስ 14:27) በምለው መሪ ቃል ከነሐሴ 14-17፣ 2018 ዓ.ም (August 20–23, 2026)በመቂ ሀገረ ስብከት በቢሻን ጉ...
21/08/2026

የ2018 ዓ.ም
!

#"አይዟችሁ!_እኔ_ነኝ፤_አትፍሩ!" (ማቴዎስ 14:27) በምለው መሪ ቃል
ከነሐሴ 14-17፣ 2018 ዓ.ም (August 20–23, 2026)

በመቂ ሀገረ ስብከት በቢሻን ጉራቻ/ ጥቁር ውኃ የቅዱስ ዮሐንስ 23ኛ የህንፀት ማዕከል የተዘጋጀው የወጣቶች ስልጠና ትናንት ማታ በቅዱስ ቁርባን ስግደት ፀሎት በይፋ የተጀመረ ሲሆን፣ ዛሬ ደግሞ በቅዳሴ እና በስልጠናው መርሃ ግብር ቀጥሏል።
በዚህ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ ከሀገረ ስብከቱ ስር ከሚገኙ ቁምስናዎች የተወጣጡ ወጣቶች በጋራ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

መልእክት፦ "በክርስቶስ አንድ ሆነን፤ በፍቅር እንገንባ!"

 ብሸን_ጉራቻ፣ ነሐሴ 14-16/ 2018 ዓ.ም. — የካቶሊክ ካሪታስ ኢትዮጵያ – መቂ የትምህርት ክፍል ዓመታዊ የሥራ ግምገማ ስብሰባ በብሸን ጉራቻ እያካሄደ ይገኛል።በመቂ ሀገረ ስብከት 46...
21/08/2026


ብሸን_ጉራቻ፣ ነሐሴ 14-16/ 2018 ዓ.ም. — የካቶሊክ ካሪታስ ኢትዮጵያ – መቂ የትምህርት ክፍል ዓመታዊ የሥራ ግምገማ ስብሰባ በብሸን ጉራቻ እያካሄደ ይገኛል።
በመቂ ሀገረ ስብከት 46 ትምህርት ቤቶች የሚገኙ ስሆን ከ46ቱ ትምህርት ቤቶች 18 ትምህርት ቤቶች እና 1 ኮሌጅ በስብሰባው ላይ ተገኝተዋል፡፡ የስብሰባው ዋና ዓላማ በ2018 ዓ.ም. የተከናወኑ የትምህርት ሥራዎችን በጥልቀት መገምገም፣ የተገኙ ውጤቶችንና ምርጥ ተሞክሮዎችን ማጋራት፣ ያጋጠሙ ችግሮችንና ክፍተቶችን መለየት እንዲሁም ለቀጣይ ዓመት የሥራ እቅድ ማዘጋጀት ነው።
በስብሰባው የተማሪዎች የትምህርት ውጤት፣ የመምህራን የማስተማር አፈጻጸም፣ የትምህርት ጥራት፣ የትምህርት ቤቶች አስተዳደር፣ የመማሪያ ሁኔታዎችና የተማሪዎች ድጋፍ የመሳሰሉ ጉዳዮች እየተገመገሙ ይገኛሉ።
በተጨማሪም የትምህርት አስተባባሪዎችና ሌሎች ቁልፍ ባለድርሻ አካላት በሥራቸው ያጋጠሟቸውን ተግዳሮቶች፣ የተገኙ ስኬቶችና ለወደፊት የሚያስፈልጉ የማሻሻያ አቅጣጫዎችን በመወያየት ላይ ናቸው።
የግምገማው ውጤት በመጪው ዓመት የትምህርት ሥራዎችን በተሻለ መልኩ ለማቀድ፣ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻልና የተማሪዎችን የመማር ውጤት ለማሳደግ እንደ መነሻ ያገለግላል።
“በጋራ ግምገማ፣ በጋራ ዕቅድ፣ ለተሻለ የትምህርት ጥራት” በሚል መንፈስ ስብሰባው ቀጥሏል።

14/08/2026

Address

P. O. Box 43
Mek'i

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Apostolic Vicariate of Meki posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share