Gospel for World Saves to All generation ወንጌል ለአለም መዳን ለሁሉም ትውልድ

  • Home
  • Ethiopia
  • Konso
  • Gospel for World Saves to All generation ወንጌል ለአለም መዳን ለሁሉም ትውልድ

Gospel for World Saves to All generation  ወንጌል ለአለም መዳን ለሁሉም ትውልድ
The Lord is my rock, my fortress and my deliverer;my God is my rock, in wh

እምነት ተራሮችን ብቻ አይደለም የሚያንቀሳቅሰው... እምነት ጊዜውንም ያቆማል!ኢያሱ በጦርነት መካከል ቆሞ ወደ ሰማይ እጁን ባነሳ ጊዜ፣ የጠየቀው ነገር ተራ አልነበረም። ፀሐይ እንድትቆም ጠየ...
06/07/2026

እምነት ተራሮችን ብቻ አይደለም የሚያንቀሳቅሰው... እምነት ጊዜውንም ያቆማል!
ኢያሱ በጦርነት መካከል ቆሞ ወደ ሰማይ እጁን ባነሳ ጊዜ፣ የጠየቀው ነገር ተራ አልነበረም። ፀሐይ እንድትቆም ጠየቀ። ጊዜ እራሱ እንዲታዘዝለት ጠየቀ። እና እግዚአብሔር መለሰለት። ፀሐይ ቆመች፥ ወርኅም ቆመ፥ እስራኤልም ድል ነሱ።
ይህ ታሪክ የሚያስተምረን አንድ ትልቅ እውነት አለ፦ ደፋር ጸሎት፣ ደፋር እምነትን ይፈልጋል። ኢያሱ ትንሽ ነገር አልጠየቀም። ትልቅ ነገር ጠየቀ፥ ምክንያቱም እግዚአብሔር ትልቅ አምላክ እንደሆነ ያውቅ ነበር።
ዛሬ በሕይወትህ ውስጥ ጊዜ የቆመ የሚመስልህ፣ ወይም በተቃራኒው ጊዜ በጣም ፈጣን ሆኖብህ የምትታገልበት ሁኔታ ካለ... እወቅ፣ ያ ፀሐይን ያቆመው አምላክ ዛሬም ተመሳሳይ አምላክ ነው። ለአንተም ጸሎትህን ይሰማል። ለአንተም ይታገልልሃል።
እግዚአብሔር ትናንት፣ ዛሬም፣ እስከ ዘላለምም ያው ነው።አሜን!!!

06/07/2026
እግዲህ ምን ይባላልከማነኛውም ነፍስና ህይወት አጥቂ ነገር ሊያድንና የዘላለምንም ሕይወት የሚሰጥ እግዚአብሔር ብቻ ነው፤ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ላደረገልን ስለማዳን ሥራው ልናመስግነው ...
06/07/2026

እግዲህ ምን ይባላል

ከማነኛውም ነፍስና ህይወት አጥቂ ነገር ሊያድንና የዘላለምንም ሕይወት የሚሰጥ እግዚአብሔር ብቻ ነው፤ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ላደረገልን ስለማዳን ሥራው ልናመስግነው የሚገባ ነው።
🙏🙏🙏🙏🙏🙏⛪🏥⛪🙏🙏🙏🙏🙏🙏

✟ ✞✞✞ ✝ ✞✞✞ ✟

✞🤔 የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና።
👉 የጥበበኞችን ጥበብ አጠፋለሁ የአስተዋዮችንም ማስተዋል እጥላለሁ ተብሎ ተጽፎአልና።
❓ ጥበበኛ የት አለ? ጻፊስ የት አለ? የዚች ዓለም መርማሪስ የት አለ? እግዚአብሔር የዚችን ዓለም ጥበብ ሞኝነት እንዲሆን አላደረገምን?
በእግዚአብሔር ጥበብ ምክንያት ዓለም እግዚአብሔርን በጥበብዋ ስላላወቀች፥ በስብከት ሞኝነት የሚያምኑትን ሊያድን የእግዚአብሔር በጎ ፈቃድ ሆኖአልና።
መቼም አይሁድ ምልክትን ይለምናሉ የግሪክ ሰዎችም ጥበብን ይሻሉ፥
🔊 እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ ይህም ለአይሁድ ማሰናከያ ለአሕዛብም ሞኝነት ነው፥

👉❤ ለተጠሩት ግን፥ አይሁድ ቢሆኑ የግሪክ ሰዎችም ቢሆኑ፥ የእግዚአብሔር ኃይልና የእግዚአብሔር ጥበብ የሆነው ክርስቶስ ነው።❤

👉 ከሰው ይልቅ የእግዚአብሔር ሞኝነት ይጠበባልና፥ የእግዚአብሔርም ድካም ከሰው ይልቅ ይበረታልና።
ወንድሞች ሆይ፥ መጠራታችሁን ተመልከቱ፤ እንደ ሰው ጥበብ ጥበበኞች የሆኑ ብዙዎች፥ ኀያላን የሆኑ ብዙዎች፥ ባላባቶች የሆኑ ብዙዎች አልተጠሩም።
ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን እንዲያሳፍር የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ፤ ብርቱንም ነገር እንዲያሳፍር እግዚአብሔር የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ፤
እግዚአብሔርም የሆነውን ነገር እንዲያጠፋ የዓለምን ምናምንቴ ነገር የተናቀውንም ነገር ያልሆነውንም ነገር መረጠ፥
ሥጋን የለበሰ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት እንዳይመካ።
ነገር ግን፦ የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ ተብሎ እንደ ተጻፈው ይሆን ዘንድ፥ ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ጽድቅ ቅድስናም ቤዛነትም በተደረገልን በክርስቶስ ኢየሱስ የሆናችሁ ከእርሱ ነው።
1ቆሮ 1፥18-31
❤❤❤❤❤❤❤✞❤❤❤❤❤❤❤

ይህም ደግሞ በማመን ብቻ እንጂ በመልካም ሥራ ውጤት ወይ ከሆኑ ቡድኖች ወይም ድርጅቶች ጋር በመተባበር አይደለም።

👉 🤔 ክርስቶስ የመስቀሉን መከራ ስቀበል ለእያንዳንዱ የሰው ልጅ ህይወት ነውና።

ስለዚህ ማንም ህይወቱን የሚሻና መዳን የሚፈልግ ሰው ሁሉ የእግዚአብሔር የማዳን ሥራ ንድፈ-ሀሳብን በመቀበልና የእግዚአብሔር ልጅ በመሆን የዘላለም የመንግስቱን ርስት ለማገኘት በኢየሱስ ክርስቶስ ለማመን ወስኖ ያደረገው ብቻ ነው።

የዘላለም ህይወት ዋስትና ኢየሱስ ነውና!!

ትልቁ የወንጌል ተልኮና የክርስቲና ግቡ የእግዚአብሔር ልጆች መሆንና የዘላለሙን መንግስት ወራሽነት ነው።

👉👉👉 እና በእኛ በሰዎች እውቀትና ማስተዋል ብዛት ወይም መልካም ሥራ ሊለካ አይችልም።
ምክንያቱም ሰው ሁሉ ሐጥአተኛ ነው ትክክለኛ መስሎ ታይቶ ልሳሳት፣ የጸንቶ የቆመ መስሎ ልወድቅ የሚችል ፍጡር ነውና በራሳችን ማንነት አንመካ...🤔🤔🤔

በእግዚአብሔር እንመካ እንጂ
depend on Mighty God only
And so Trust in him.
❤❤❤❤❤❤
ለዚህ ነው የእግዚአብሔርን ማዳን ምንነት ያላወቁና ድንቅ ሥራውን ስያጠላሹ፣ በራሳቸው እውቀትና ማስተዋል የሚመኩ ትዕብተኞች የራሳቸውን ከፍታ ለማስከበር የሚጥሩና የእግዚአብሔርን ሥራ የሚቃወሙትን አይሁዳዊያንን የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ተከታይ የሆነው ሐዋሪያው ጴጥሮስ የእግዚአብሔር ማዳን ለማስረዳት በድፍረት ይህንን የተናገረው...👇👇👇

👉 በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ መንፈስ ቅዱስንም ተሞልቶ እንዲህ አላቸው፦ እናንተ የሕዝብ አለቆችና ሽማግሌዎች፥
እኛ ዛሬ ለድውዩ ሰው ስለ ተደረገው መልካም ሥራ ይህ በምን እንደዳነ ብንመረመር፥
እናንተ በሰቀላችሁት እግዚአብሔርም ከሙታን ባስነሣው በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይህ ደኅና ሆኖ በፊታችሁ እንደ ቆመ፥ ለእናንተ ለሁላችሁ ለእስራኤልም ሕዝብ ሁሉ የታወቀ ይሁን።
👉 እናንተ ግንበኞች የናቃችሁት፥ የማዕዘን ራስ የሆነው ይህ ድንጋይ ነው።
❤መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።❤
ጴጥሮስና ዮሐንስም በግልጥ እንደ ተናገሩ ባዩ ጊዜ፥ መጽሐፍን የማያውቁና ያልተማሩ ሰዎች እንደ ሆኑ አስተውለው አደነቁ፥ ከኢየሱስም ጋር እንደ ነበሩ አወቁአቸው፤
ሐዋ 4፥8-13
❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤

ጳውሎስና ሲላስ በፊልጵስዩስ እስር ቤት ውስጥ ነበሩ። እጃቸውና እግራቸው በሰንሰለት ታስሮ፣ ጀርባቸው በግርፋት ቆስሎ፣ በጨለማ ክፍል ውስጥ ተጥለው ነበር(የሐዋርያት ሥራ 16፡16-26)። ሰው...
06/07/2026

ጳውሎስና ሲላስ በፊልጵስዩስ እስር ቤት ውስጥ ነበሩ። እጃቸውና እግራቸው በሰንሰለት ታስሮ፣ ጀርባቸው በግርፋት ቆስሎ፣ በጨለማ ክፍል ውስጥ ተጥለው ነበር(የሐዋርያት ሥራ 16፡16-26)። ሰው ቢሆን በዚህ ሁኔታ ምን ያደርግ ነበር? ያለቅሳል፣ ያማርራል፣ ተስፋ ይቆርጣል። ነገር ግን እነዚህ ሁለት የእምነት ሰዎች የተለየ ነገር አደረጉ።
በእኩለ ሌሊት ዘመሩ። ጸለዩ። አመለኩ።
በሥቃያቸው መካከል፣ በሰንሰለታቸው ውስጥ ሆነው፣ ድምፃቸውን ወደ ሰማይ አሰሙ። እና በዚያች ቅጽበት፣ መሬቱ ተንቀጠቀጠ፣ የእስር ቤቱ ደጆች ተከፈቱ፣ ሰንሰለቶቹም ተፈቱ!
ውድ ወዳጄ፣ ዛሬ በምን አይነት እስር ቤት ውስጥ ነህ? *የበሽታ ሰንሰለት?
*የችግር እና የእዳ ሰንሰለት?
* የተስፋ መቁረጥ ጨለማ?
እግዚአብሔር አሁንም ያ አምላክ ነው! በሌሊትህ ውስጥ ብርሃን ማምጣት ይችላል። በእስርህ ውስጥ ድልን ማምጣት ይችላል። ችግርህ የመጨረሻው ምልክት አይደለም እግዚአብሔር ገና አልጨረሰም!
በጨለማህ ውስጥ ዘምር። በስቃይህ ውስጥ አመስግን። ምክንያቱም ለውጥ ሊመጣ ያለው ብዙ ጊዜ በጣም ጨለማ በሚመስልበት ቅጽበት ነው።አሜን!!!

Address

GfWStag/ወአመሁት
Konso
JESUSISSAVIOR

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gospel for World Saves to All generation ወንጌል ለአለም መዳን ለሁሉም ትውልድ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share