25/06/2026
ሰበር ዜና!!! እንኳን ደስ አላችሁ።
አዲሱ የፌዴራል ሸሪዓ ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ፀደቀ::
"""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""
ላለፉት 25 አመታት አገልግሎት ላይ የነበረው የፌደራል ሸሪዓ ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 188/1992 ሙሉ በሙሉ የሚተካው አዲሱ ረቂቅ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው እለት ፀድቋል::
የዚህ የሕግ ማርቀቅ ሥራው የተከናወነው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ባቀረበው ጥያቄ መሠረት በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት በተዋቀረ ባለ 7 አባላት ያሉት የዳኞችና የባለሙያዎች ኮሚቴ ነው።
ኮሚቴው የውጭ ሀገራት ተሞክሮዎችንና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት የተገኙ ጠቃሚ ግብዓቶችን በማካተት የተዘጋጀ ሲሆን ረቂቁ ለፓርላማው ለህግ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተመርቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል::
ሰባት ክፍሎችን ይዞ በአዲስ መልክ የተዘጋጀው ይህ ረቂቅ አዋጅ የፍርድ ቤቶቹን የዳኝነት ሥልጣን፣ አደረጃጀትና አሠራር፣ የዳኞች አሿሿምና በጀት፣ እንዲሁም የፍርድ ቤቶች አስተዳደር ጉባኤን በአዲስ መልክ ማቋቋምን ጨምሮ ልዩ ልዩ ድንጋጌዎችን በዝርዝር አካቷል።
የህዝበ ሙስሊሙ የመልካም አስተዳደር የረጅም ጊዜ ጥያቄ የነበረው የዚህ ተቋም በአዲስ መልኩ መደራጀት ምላሽ የሚሰጥ ነው::
ይህ አዋጅ እንዲፀቅ ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝደንት ጀምሮ የፌደራል ጠቅይላይ ፍርድ ቤት አመረሮች፣ ረቂቁን ያዘጋጁ የኮሚቴ አባላት ፣ የፓርላማው የህግ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ በማበርከታቸው ላቅ ያለ ምስጋና ይገባቸዋል::
የሸሪዓ ፍርድ ቤቶች ቁመናቸው ተስተካክሎ ለህዝበ ሙስሊሙ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ የተጀመረው የለውጥ ጉዞ ከአዋጁ በተጨማሪ የሁሉንም ህዝበ ሙስሊም ድጋፍ እና እገዛ ያሻዋል::
ይህ ረቂቅ አዋጅ እንዲፀድቅ ኃላፊነታቸውን ለተወጡ ሁሉ በድጋሚ ላቅ ያለ ምስጋናዮን ማቅረብ እወዳለሁ