United Jimma orthodox tewahedo youth የጅማ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ወጣቶች

  • Home
  • Ethiopia
  • Jimma
  • United Jimma orthodox tewahedo youth የጅማ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ወጣቶች

United Jimma orthodox tewahedo youth የጅማ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ወጣቶች የጅማ የክርስቲያን ወጣቶች ማህበር

21/05/2023
https://youtu.be/a40l7vkwlI0የጅማ ደብረ መዊዕ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ላይ ከፍተኛ ከበባ ተደርጎበታል።የጅማ ሀገረ ስብከት መንበረ ጵጵስና የሚገኝበትን ደብረ መዊዕ መድኃ...
10/02/2023

https://youtu.be/a40l7vkwlI0
የጅማ ደብረ መዊዕ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ላይ ከፍተኛ ከበባ ተደርጎበታል።

የጅማ ሀገረ ስብከት መንበረ ጵጵስና የሚገኝበትን ደብረ መዊዕ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያንን ሰብሮ ለመግባት ከፍተኛ የጸጥታ ኃይል የቤተ ክርስቲያኑን ቅጽር ከብቦ መቆሙና በዚህም ውጥረት መንገሡ ተገለጸ።

የኦሮሚያ ፖሊስና ልዩ ኃይል ሀገረ ስብከቱን ለ22 ዓመታት ያህል ያስተዳድሩትን ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስን ከጅማ አየር ማረፊያ እንዲመለሱ ካደረገ በኋላ ሕገ ወጡን ቡድን ለማስገባት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

የጅማ ምእመናን እና ምእመናት ግን ይህንን ሕገ ወጥ ሹመት በመቃወም አድባራቶቻቸውን በመጠበቅ ላይ ናቸው።

ነገር ግን የኦሮሚያ ፖሊስ፣ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ የደብሩ በር ዘግቶ በመቆም ከውጪ ሌሎች ምእመናን እንዲጠጉ እንደማይፈቅዱና በሩቅ እየመለሷቸው እንደሚገኙም መረጃ አድራሾቻችን ጠቁመዋል።

በዚህም ምክንያት ባለፉት ሦስት ቀናት ውስጥ ምንም ዓይነት ምግብ እየገባላቸው እንዳልሆነና ለቀብር የሚመጡ ኦርቶዶክሳውያንን ሳይቀር ደብቀው ምግብ ያስገባሉ በሚል ጥርጣሬ ከፍተኛ ፍተሻ እንደሚደረግባቸውም ነው የተነገረው።

በተጨማሪም ጥቁር ልብስ የለበሱ ምእመናንን ጨምሮ በርካታ ኦርቶዶክሳውያን ካህናት አባቶችን ጭምር እያሠሩ እንደሚገኝ ተጠቅሷል። እስካሁን ድረስም አባ ተክለ ሃይማኖት የሚባሉ የማኅደረ ስብሐት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን አገልጋይን አሥረዋል።

ከዚህም በተጨማሪም የደብረ መዊዕ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ለሆኑት መልአከ መዊዕ አባ አብርሃም ከቤተ ክርስቲያኑ ግቢ እንዲወጡ ከጸጥታ ኃይሉ ደብዳቤ እንደተላከባቸውም ነው የተገለጸው።

እንደ ምንጮቻችን ገለጻ በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ያሉ ምእመናን እንዲወጡ ለማግባባት እየሞከሩ ቢሆንም ብንወጣም ቤት ለቤት ተለቅመን እንታሠራለን እዚሁ ሆነን የሚመጣውን መከራ እንቀበላለን በሚል አቋም ጸንተው እየጠበቁ መሆናቸው ነው የተነገረው።

08/02/2023

ለሁሉም ኦርቶዶክስዊ ይዳርስልን!
ጅማ ደብረ መዊዕ መድኃኔዓለምን በድጋሚ ሰብርው ሊገቡ ነው እንዲሁም ውስጥ ያሉትን ኦርቶዶክስውያን በሙሉ ለመጨፍጭፍ በዝግጅት ላይ ናቸው!
ይሄን 3ቀን ወደ ቤተክርስቲያን ማንም ምእመን አይገባም አይወጣም በርቀት ሆነው ይመልሱ ነበር!
አሁን በደረሰን መረጃ ሙሉ ለሙሉ ሰብርው ሊገቡ በዝግጅት ላይ ናቸው ይሄ መልክት ለሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ይድረስልን!!!!

05/02/2023

ይህን በማሕበራዊ ገፆች በማጋራት በቤተክርስቲያን ላይ እየደረሰ ያለውን የተቀናጀ ጥቃት እንቃወም!

!
!
!
!
!
!
!
!
!
!

04/02/2023

ጅማ ላይ ውንብድና ቀጥሏል

ጅማ ደብረ መዊዕ መድኃኔዓለም ሙሉ ለሙሉ በኦሮሚያ ልዩ ኃይል ተስብሮል ፣ የደብሩ ካህናት ዲያቆናት ወጣቶች ወደ ወረዳ 2 ፖሊስ ጣቢያ ታስርው ሄደዋል

20 ፓትሮል ሲቪል እና ኦሮሚያ ልዩ ኃይል ነው ነበሩ

04/02/2023

ወንድሞች፥-
ነገ ጠዋት ቤተ ክርስቲያን እንሂድ ፥ ፀሎት እናድርግ፡፡የሰንበት ት/ቤቱ ፅ/ቤት እንሂድና "ምን እየሰራችሁ ነው? ምን እናግዝ?" እንበል፡፡የሰበካ ጉባኤ ተወካዮቻችንን እናፈላልግና እንዴት ነው አካሄዳችን? ብለን እንጠይቅ፡፡እስኪጠሩን አንጠብቅ ፥ ራሳችንን ለመታዘዝ ዝግጁ እናድርግ፡፡

ጅማ ተከብበዋል!ከትላንት ምሽት ጀምሮ ጅማ ደብረ መዊዕ መደኃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን በኦሮሚያ ልዩ ኃይል ሙሉ ለሙሉ ተከቧል! ድምጻችን አይናችን ወደ ጅማ ደብረ መዊዕ ደብረ መዊዕ መድኃኔዓለም...
04/02/2023

ጅማ ተከብበዋል!

ከትላንት ምሽት ጀምሮ ጅማ ደብረ መዊዕ መደኃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን በኦሮሚያ ልዩ ኃይል ሙሉ ለሙሉ ተከቧል! ድምጻችን አይናችን ወደ ጅማ ደብረ መዊዕ ደብረ መዊዕ መድኃኔዓለም ቤተክርስትያን እንድርግ! ይሄን መልክት ለሁሉም ለጅማ ኦርቶዶክስዊ ምእመን እናድርስ!

በጅማ ኦርቶዶክሳውያንን ቤት ለቤት በማሰስ ማሰር ቀጥሏል:: አሁንም የአካባቢው ባለሥልጣናት እድል አላቸው:: የታሰሩትን ፍቱ! ወከባውን አቁሙ! ቤተ ክርስቲያን ቀኖናዊት ናት!! የማይነካውን አትንኩ! "ዘመኑ ዘመነ ሰማዕታት ነው!" እኛም የክፉ አድራጊዎችን መረብ በመረጃ አሳልፈን እንሰጣለን::

እፈሩ! እጃችሁን ከቤተ ክርስቲያን ላይ እንሡ!!


Address

Jimma
Jimma

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when United Jimma orthodox tewahedo youth የጅማ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ወጣቶች posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share