Emanuel united church zeway

Emanuel united church zeway Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Emanuel united church zeway, Religious organisation, Jijiga.

15/06/2026

ዘወትር ረቡዕ ተከታታይ ትምህርት ስላለ ሁላችሁም እየመጣቸው እንድትማሩ ይሁን።

09/06/2026

የተወደደው የትምህርት ጊዜያችን ነገ ዕረቡ ምሽት በሰኔ 3 ይቀጥላል፤መጥታችሁ የበረከቱ ተካፋይ ሁኑ!

02/06/2026

የተወደደው የትምህርት ጊዜያችን ነገ ዕረቡ ምሽት በግንቦት 26 ይቀጥላል፤መጥታችሁ የበረከቱ ተካፋይ ሁኑ!

ረቡዕ ምሽት 19/9/2018   በመጋቢ ዶ/ር ጌቱ ፀጋዬርዕስ:-ሚዛናዊ የክርስትና ህይወት ማቲ 6:19-21  ምሳ 23:4 ''ባለጠጋ ለመሆን አትድከም የገዛ ራስህን ማስተዋል ተው። #እነኚህን...
02/06/2026

ረቡዕ ምሽት 19/9/2018
በመጋቢ ዶ/ር ጌቱ ፀጋዬ
ርዕስ:-ሚዛናዊ የክርስትና ህይወት
ማቲ 6:19-21
ምሳ 23:4 ''ባለጠጋ ለመሆን አትድከም የገዛ ራስህን ማስተዋል ተው።
#እነኚህን ቃላት የተጠቀመው ለምንድነው?
የምንሰበስበው ያለ እግዚአብሔር ከሆነ ከንቱ ነው።
#የተባረከ ኑሮ መኖር የሚፈልግ ሰው ልቡ መዝገቡ ላይ ሊሆን ይገባል፤የኛ መዝገብ ደገሞ እራሱ ጌታ ነው።
#በሸክላ ዕቃ ውስጥ የከበረ መዝገብ ያስቀመጠ እግዚአብሔር ይባረክ።
👉ስለዚህ ፦
#1፦ሰማይ የሚያየው ሀብት ሰብስብ
#ሰማይ የሚያየው ሀብት የሚሰበሰበው ለታይታ የምናደርገውን ነገር በማቆም በስውር ለድሀ ወይም ለተቸገረ ሰው ቸርነት ስናደርግ ነው።
#2፦ዛሬ ልብህ ያረፈው ምን ላይ ነው?
#ማቲ 6:24 ላይ ለሁለት ጌቶች መገዛት አይቻልም ይላል፤
ልብህ እግዚአብሔር ላይ ከሆነ ገንዘብ ይቀርብሀል ልብህ ግን ገንዘብ ላይ ብቻ ከሆነ ግን ይርቅሀል።
👉ይቀጥላል...ተባረኩ!

ረቡዕ ምሽት 12/9/2018   በመጋቢ ዶ/ር ጌቱ ፀጋዬርዕስ:-ሚዛናዊ የክርስትና ህይወት  #ማቲ 6:16 #ጾም ለሰዎች ታይታ ሳይሆን ለጌታ ነው። #ጾም ጸሎት ስንገባ እንታጠብ እንቀባ እንጂ...
02/06/2026

ረቡዕ ምሽት 12/9/2018
በመጋቢ ዶ/ር ጌቱ ፀጋዬ
ርዕስ:-ሚዛናዊ የክርስትና ህይወት #ማቲ 6:16
#ጾም ለሰዎች ታይታ ሳይሆን ለጌታ ነው።
#ጾም ጸሎት ስንገባ እንታጠብ እንቀባ እንጂ እጾማለው ብለን መጎሳቆል እና እየጾምኩ ብላችሁ አትናገሩ።
#ስትጾሙ እንደ ግብዞች አትጹሙ።
#ጾም👉1፦በእግዚአብሔር ፊት ብቻ የሚደረግ ነው
2፦ሰው እንዳያውቅብን እየታጠብን እየተቀባን የምናደርገው መሆን አለበት።
3፦የመገዛት ምልክት ነው
#መገዛት ስንል ለእግዚብሔር ብቻ በመገዛት ከአምላካችን ጋር ብቻ ምናሳልፈው ነው።
#ስንጾም የሚሆነው ምንድነው?
#1፦እግዚአብሔር ደስ ይለዋል
#2፦አልነቀል ያለ ነገር የሚነቀለው በጸሎት ነው
#3፦ጤንነታችን ጥሩ ይሆናል
👉ይቀጥላል ...እግዚአብሔር ይባርካችሁ

ዕሁድ ማለትም 09/09/2018 በጣም ደስ የሚልልዩ የባለትዳሮች ፕሮግራም ነበር ስለ ሁሉም ነገር እግዚአብሔር  ይመስገን ።
19/05/2026

ዕሁድ ማለትም 09/09/2018 በጣም ደስ የሚል
ልዩ የባለትዳሮች ፕሮግራም ነበር
ስለ ሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን ።

12/05/2026
29/04/2026

ስለ ተራራው ስብከት የጀመርነው ትምህርት ዛሬ ረቡዕ ሚያዚያ 21 ምሽት ከ 12ሰዓት ጀምሮ ይቀጥላል
የበረከቱ ተካፋይ ትሆኑ ዘንድ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል

28/04/2026
ረቡዕ ምሽት 14/8/2018       ክፍል 16በመጋቢ ዶ/ር ጌቱ ፀጋዬርዕስ:-ሚዛናዊ የክርስቲያን ህይወት “ለሰዎች ትታዩ ዘንድ ምጽዋታችሁን በፊታቸው እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ፤ ያለዚያ በሰማያ...
28/04/2026

ረቡዕ ምሽት 14/8/2018
ክፍል 16
በመጋቢ ዶ/ር ጌቱ ፀጋዬ
ርዕስ:-ሚዛናዊ የክርስቲያን ህይወት
“ለሰዎች ትታዩ ዘንድ ምጽዋታችሁን በፊታቸው እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ፤ ያለዚያ በሰማያት ባለው አባታችሁ ዘንድ ዋጋ የላችሁም።”
— ማቴዎስ 6፥1
👉ዋጋ ሊያሳጡን የሚችሉ ዋና ዋና ነገሮች
#1፦ጤናማ በሆነ ስሜት ምጽዋት መስጠት
#ለቤተ ክርስቲያን ስጦታ አስራት ወይንም ደግሞ በኩራት ስንሰጥ ለታይታ የምንሰጥ ከሆነ ዋጋ ያሳጣናል።
#ለቤተ ክርስቲያንም ይሁን ለግለሰብ ምንም አይነት ስጦታ ስትሰጡ ለታይታ አትስጡ፤መለከት አታስነፉ ፣ቀኛችሁ የሚሰጠዉንም ግራችሁ አይመልከት።
# ቀኝህ የሚሰጠዉን ግራህ አይመልከት ማለት ፦
፦ግራዉ ለመቀነስ አይተባበር
፦ለእግዚአብሔር ከሆነ ልብህ እንዳሰበዉ ስጥ
፦በሙሉ ሀይልህ የሰራኸዉን ስራ በደካማ ሀይል አትቀናንሰዉ ማለትነዉ።
#... የሚሰጥ በልግስና ይስጥ፤ ...
ሮሜ 12፥8
👉ይቀጥላል ...እግዚአብሔር ይባርካችሁ

Address

Jijiga
1234

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Emanuel united church zeway posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share