የሶማሌ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት/Somali Diocese Secretary/

  • Home
  • Ethiopia
  • Jigjiga
  • የሶማሌ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት/Somali Diocese Secretary/

የሶማሌ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት/Somali Diocese Secretary/ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የሶማሌ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት/Somali Diocese Secretary/, Religious organisation, Jigjiga.

በሶማሌ(ጅግጅጋ) ክልል ሀገረ ስብከት የሚከበሩ ቅዱሳት በዓላትን ፥ መንፈሳዊ ስብከቶችና ትምህርቶችን እንዲሁም በሀገረ ስብከቱ የሚሰሩ ልማቶችን የሚዘገብበት ፔጅ ነው!! ፈጣን እና ተአማኒ መረጃ ለማግኘት ላይክ ፎሎው እና ሼር በማድረግ ቤተሰብ እንዲሆኑ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስም ጋብዘናል!!

24/08/2026
  ክርስቲያን መፍረሱ ተገለጸ።▮ነሐሴ ፲፰/፳፻፲፰ ዓ/ም▮አ/አ/ሀገረ ስብከት ሚዲያበሶማሌ ጅግጅጋ ከተማ የመድኃኔዓለም መቃኞ ቤተ ክርስቲያን መፍረሱ ተገለጸ።ቤተ ክርስቲያኑ እንዲሠራ ለሚመለከ...
24/08/2026

ክርስቲያን መፍረሱ ተገለጸ።

▮ነሐሴ ፲፰/፳፻፲፰ ዓ/ም▮አ/አ/ሀገረ ስብከት ሚዲያ

በሶማሌ ጅግጅጋ ከተማ የመድኃኔዓለም መቃኞ ቤተ ክርስቲያን መፍረሱ ተገለጸ።

ቤተ ክርስቲያኑ እንዲሠራ ለሚመለከተው የመንግሥት አካል ጥያቄ በማቅረብ ከትትል ከተጀመረ ለዓመታት የቆየ መሆኑ የተገለጽው ይሄው ቤተ ክርስቲያን በዛሬው ዕለት በግብረ ኃይል መፍረሱን ከሀገረ ስብከቱ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

የቤተ ክርስቲያን የቦታ ጥያቄው በርካታ ጊዜ የቆ ቢሆንም አግባባዊ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ በአቅራቢያው ሌላ ቤተ እምነት ማምለኪያ ሲሠራ መፈቃድ በሚመስል ዝምታ ያለፉ ሲሆን የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን መቃኞኝ ለማፍረስ ግን ለሌሎች ያለሰተጠቁሙት ሕግ ምክንያት በማድረግ በግብረ ኃይል እንዲፈርስ ተደርጓል ነው ተብሏል።

የተሠራውን የመድኃኔዓለም መቃኞ ቤተ ክርስቲያን ከማፍረሳቸው በተጨማሪ ለምን ብለው የተጠየቁትን የቤተ ክርስቲያን ልጆችና የሥራ መሪዎች አሥረዋቸዋል ብለዋል የሀገረ ስብከቱ መረጃ ሰጪ አካል።

ጉዳዩን መፍትሔ እንዲሰጠው ከሀገረ ስብከቱ ብፁዕ ጳጳስ አቡነ ኤልሳዕ ጀምሮ በደረጃው ያሉ አካላት ከሚመለከተው የመንግሥት አካል ጋር እየተነጋገሩ እንደሚገኙ ተገልጿል።

መረጃውን ያደረሰን የሶማሌ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ነው።
@ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ አገልግሎት/Addis Ababa Diocese Media Service

24/08/2026

ሰበር ዜና ‼️ እጅግ አሳዛኝ ክስተት በጅጅጋ ከተማ
የሃይማኖት እኩልነትና ነጻነት በተረጋገጠባት ሀገራችን፤ ዛሬ በጅጅጋ ከተማ ያልተጠበቀና አሳዛኝ ድርጊት ተፈጽሟል።
በከተማው አዲስ የተሠራው የመድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን መቃኞ ቤት መፍረሱ ታውቋል። ይህ ድርጊት በአካባቢው ምዕመናን ዘንድ ከፍተኛ ሀዘንን የፈጠረ ሲሆን፣ የሚመለከታቸው አካላት ስለዚህ ድርጊት አስቸኳይ ህጋዊ ማጣራት እንዲያደርጉ ማህበረሰቡ እየጠየቀ ይገኛል።

24/08/2026

ሼር ሼር አድርጉ

24/08/2026

ናታኒም ዘጅግጅጋ

24/08/2026


የሃይማኖት እኩልነትና ነጻነት ባለባት ሀገር
ዛሬ በጅጅጋ ከተማ አዲስ የተሠራው የመዳኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በዚህ መልኩ አፍርሰውታል!!

Address

Jigjiga

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የሶማሌ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት/Somali Diocese Secretary/ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share