05/12/2025
ገቢ ማሰባሰቢያ ኮንፈረንስ ተካሄደ።
የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የምስራቅ ሸዋና አካባቢው ክልል በአዳማ ከተማ ባሉ 15 አጥቢያዎች ላይ ገቢ የማሰባሰብ እና ቤተ ዕምነቷ የምትገኝበትን አሁናዊ ሁኔታ ገለጻ ተደርጓል።
የቤተ እምነቷ ፕሬዚዳንት የሆኑት መጋቢ ላኮ በዳሶ፣ የክልሉ ፕሬዝዳንት መጋቢ ፍቃዱ አርገኔ ፣ተጋባዥ አገልጋዮች ፣ጥሪ የተደገላቸው እንግዶች ምዕመኑ ተገኝተዋል።
በኮንፈረንሱ ላይ የጸሎትና የአምልኮ ጊዜ የተካሄደ ሲሆን የተለያዩ አገልጋዮች አገልግለዋል።
የቤተ እምነቷ ፕሬዚዳንት የሆኑት መጋቢ ላኮ በዳሶ የጊዜውን የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት አካፍለዋል።
አያይዘውም ቤተ እምነቱ አሁናዊ ያለችበትን ሁኔታ የገለጹ ሲሆን ቤተ እምነቷ ዘርፈ ብዙ መንፈሳዊ ፣ማህበራዊ ፣ልማታዊ ፣ሀገራዊ ስራዎችን በትጋትና በመሰጠት እያከናወነች እንደምትገኝ ተናግረው በቁጥርም በመጨመር የእግዚአብሔርን መንግስት እያሰፋች መሆኑንን አጽንኦት በመስጠት ተናግረዋል።
በተጨማሪም ቤተ እምነቷ እያስገነባችው የሚገኘው ባለ 10 ወለል እና ባለ 2 ቤዝ የጽ/ቤት የህንጻ ግንባታ 9ኛ ወለል ላይ መድረሱን ገልጸው በጋራ የጀመርነውን ስራ በጋራ እንጨርስ ሲሉ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን የእግዚአብሔር ህዝብ እስካሁን ድረስ ላበረከተው በጎና ንቁ ተግባር አመስግነዋል።
ህዝቡም በተካሄደው ኮንፈረንስ በተካፈለው ፀጋ ደስተኛ መሆናቸው ለአዘጋጆችሁ የገለጹ ሲሆን ለዋናው ህንጻ ግንባታ አገልጋዮች፣ መሪዎች ፣ህዝቡ በደስታ የገቢ ማሰባሰቢያ ስጦታ አበርክተዋል።
በኮንፈረንሱ ላይ ብዙዎች በመንፈስ ቅዱስ በመሞላት፣ከአጋንት እስራት በመፈታት፣ከተለያዩ ደዌዎች የተፈወሱ መሆናቸውን እና ጌታ መልካም ጊዜ እንደሰጣቸው የደረሰን መረጃ ያመላክታል።
ለበለጠ መረጃ
በዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/etfullgospel/
ቴሌግራም፡ https://t.me/EFGBC_HO እንዲሁም በሌሎች ፕላትፎርሞቻችን ይከታተሉን።
ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና፥ ዛሬም ለዘልዓለምም ያው ነው። ዕብ 13:8