Hawassa Alamura Full Gospel Church

Hawassa Alamura Full Gospel Church “ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ለዘላለምም ያው ነው።” ዕብራውያን 13፥8

በአላሙራ ሙሉ ወንጌል በወጣቶች ዘርፍ እየተካሄደ ያለዉ summer camp ስልጠና ሁለተኛ ቀን አይቶ መነሳት በሚል ርዕሰ የቀጠለ ስልጠና
25/08/2026

በአላሙራ ሙሉ ወንጌል በወጣቶች ዘርፍ እየተካሄደ ያለዉ summer camp ስልጠና ሁለተኛ ቀን
አይቶ መነሳት በሚል ርዕሰ የቀጠለ ስልጠና

በአላሙራ ሙሉ ወንጌል በወጣቶች ዘርፍ እየተካሄደ ያለዉ summer camp ስልጠና ( Digital purity) በሚል እርዕስ ዛሬ የጀመረ ሲሆን በተለያዩ ርዕሶች ሳምንቱን ይቀጥላል
24/08/2026

በአላሙራ ሙሉ ወንጌል በወጣቶች ዘርፍ እየተካሄደ ያለዉ summer camp ስልጠና
( Digital purity) በሚል እርዕስ ዛሬ የጀመረ ሲሆን በተለያዩ ርዕሶች ሳምንቱን ይቀጥላል

ቀን 17/12/18የእሁድ አምልኮ👉ፀሎት:- በ ወ/ም ገዛኸኝ ጌታቸው 👉አምልኮ:- በቤተክርስቲያኒቱ የአምልኮ መሪዎች👉መዝሙር :- በቤተክርስቲያኒቱ  ርሆቦት መዘምራን 👉የእግዚያብሄር ቃል :- ...
23/08/2026

ቀን 17/12/18
የእሁድ አምልኮ
👉ፀሎት:- በ ወ/ም ገዛኸኝ ጌታቸው
👉አምልኮ:- በቤተክርስቲያኒቱ የአምልኮ መሪዎች
👉መዝሙር :- በቤተክርስቲያኒቱ ርሆቦት መዘምራን
👉የእግዚያብሄር ቃል :- በ ፓስተር ተስፋዬ ኔንቆ
👉የንባብ ክፍል:-ፊልጵስዩስ 4፣1-9
በዚህ ክፍል ውስጥ ሐዋሪያው ጳውሎስ ሊኖረን የሚገባንን የ አምልኮ ዘይቤ በብዙ ቦታ ላይ ይናገራል።
ፊሌጵስዩስ 4፣1 ላይ:- ስለዚህ፥ የምወዳችሁና የምናፍቃችሁ፥ ደስታዬና አክሊሌ የምትሆኑ ወንድሞቼ ሆይ፥ እንዲሁ በጌታ ቁሙ፥ ወዳጆች ሆይ።
👉ስለዚህ ብሎ ይጀምራል ጳውሎስ ስለዚህ ብሎ ሲጀምር ከላይ ቀደም ሲል የተናገረው ነገረ መኖሩን ያሳያል ፊልጵስዩስ 3፣17-23 ላይ በተለይም እኔ ፣እኛ እና እነሱ እያለ ሲናገር እንመለከታለን።
👉 ፊሌጵስዩስ 3፣17 ላይ እኔን የምትመስሉ ሁኑ ሲል እንመለከታለን
👉 ፊሌጵስዩስ3፣18 ላይ እነሱ እንደዚህ ናቸው የሚሉ ነገሮችን በዝርዝር ሲናገር እንሰማለን።
👉 ፊሌጵስዩስ3፣20 ላይ ደግሞ እኛ እያለ ክርስቲያኖች ምን መሆን እንዳለባቸው ያሳየናል።
ታድያ ሊኖረን የሚገባ የአምልኮ ዘይቤ ምንድነው
1️⃣ ፊሌጵስዩስ 4፣1 ላይ በጌታ ቁሙ ይላል ምክኒያቱም በ ጌታ ሳይቆሙ ለጌታ መቆም ስማይችሉ ነው። ይኼ የአምልኮ ሂወት ነው ጌታ ማምለክ የምንችለው በጌታ ስንቆም ነው።
2️⃣ ፊሌጵስዩስ 4፣2 ላይ አንድነታችሁን ጠብቁ ተስማሙ ሲል እንመለከታለን በስም በስም እየጠራ እንዲስማሙ ሲነግራቸው እንመለከታለን በጌታ እንዲስማሙ ሲናገር ነበር። በ ቤተክርስቲያ ውስጥ ሰዎች በተለያዩ ሀሳቦች ሊጋጩ ይችላሉግን ትልቁ ውድቀት ግጭትን አለመፍታት ነው ጳውሎስ በጌታ እንዲስማሙ ግጭትን እንዲፈቱ ሲነግራቸው እንመለከታለን ይህም ጌታን የማገልገል አንዱ ዘይቤ ነው።
3️⃣ ፊሌጵስዩስ 4፣4 ሁል ጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ ሲል እንመለከታለን ከላይ ጀምሮ በጌታ ፣በጌታ ሲል እንመለከታለን ምክኒያቱም ያለ ጌታ የሚሆን ነገር ስለ ሌለ ነው
#ጳውሎስ ይሄን መልዕክት ሲፅፍ እስርቤት ውስጥ ሆኖ ነው የጳውሎስ ደስታ በእስር ቤት ውስጥም ነበር። ይሄም አንዱ የ አምልኮ አይነት ነው።
4️⃣ ፊሌጵስዩስ 4፣5 ላይ ገርነታችሁ ለሰው ሁሉ ይታይ ሲል እንመለከታለን ገርነታችን ገር መሆንም አንዱ የ አምልኮ ክፍል ነው። ከዚያም ጌታ ቅርብ ነው ይላል ጌታ ገርነታችሁን አይቶ ሊሸልመን ገርነታችንን ሊያይ ቅርባችን ይሆናል።
5️⃣ ፊሌጵስዩስ 4፣6 የሚያስጨንቀንን ሁሉ በእርሱ ላይ በመጣል።
# እግዚአብሄር የሚያመልክ ሰው ጭንቀቱን ማን ላይ ማራገፍ ማን ላይ መጣል እንዳለበት ያውቃል። ከዚያም አዕምሮን የሚያልፍ ሰላም ፣ውስጣችንን ይጠብቃል።
6️⃣አስብ ሲል እንመለከታለን 4፣8 በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ፥ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፥ መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ፥ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን አስቡ፤ ላይ እንዲሁ ያስብ አዕምሮዋቸውን እንዲጠቀሙበት የሀሳብ ልዕልና ይኑራችሁ ይላል።
7️⃣ፊሌጵስዩስ 4፣8 የተግባር ሰው መሆን ቁጥር 9 ላይ የተግባር ሰው እንዲሆኑ እና ማድረግ ስላለባቸው ነገር ይዘረዝራል። ስለዚህ እውነተኛ አምልኮዋችንም እንዲሁ በተግባር ይገለፃል።
✳️የአምልኮዋችን ሂወት ልምምድ በዚህ ሲቃኝ ምን ይሆናል?
1 እግዚአብሔር አዕምሮን የሚያልፍ ሰላም ይሰጠናል። የሰላም አምላክ እራሱ ከ እኛ ጋር ይሆናል።
2 የሰላም አምላክ ዲያብሎስን ከ እግራችን በታች አድርጎ ይቀጠቅጠዋል።
# ማጠቃለያ :- ስለዚህ አምልኮዋችንን በዚህ ልምምድ ስር እናድርግ
Facebook https://www.facebook.com/profile.php?id=61567498017093&mibextid=ZbWKwL
Telegram
https://t.me/+AqjPGNRFvlEyMmFk
Youtube
https://youtube.com/?si=fwcZPawNrwOD_thg
Tiktok
https://www.tiktok.com/?is_from_webapp=1&sender_device=pc
Instagram
https://www.instagram.com/hawassaalamurafullgospelchurch/
Follow, Like, Share በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ፡፡

በአላሙራ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን የተዘጋጀ የወጣቶች ሰመር ካምፕ የመጀመርያው ዙር የልጆች ሰልጠና በመካሄድ ላይ ነው። ሚቀጥለው ሳምንት የወጣቶች ሰልጠና ይቀጥላል
21/08/2026

በአላሙራ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን የተዘጋጀ የወጣቶች ሰመር ካምፕ የመጀመርያው ዙር የልጆች ሰልጠና በመካሄድ ላይ ነው። ሚቀጥለው ሳምንት የወጣቶች ሰልጠና ይቀጥላል

10/12/2018የእሁድ አምልኮ ፕሮግራም ፀሎት:- ፖሰተር ተሾመ ሞገሰአምልኮ :-በወንድም እንግዳወርቅ ሰይፉየእግዚአብሔር ቃል:-ፖሰተር መርሻ ገብሬዘወትር በመሠዊያው ላይ እሳት ይነድዳል፤አይ...
16/08/2026

10/12/2018
የእሁድ አምልኮ ፕሮግራም
ፀሎት:- ፖሰተር ተሾመ ሞገሰ
አምልኮ :-በወንድም እንግዳወርቅ ሰይፉ
የእግዚአብሔር ቃል:-ፖሰተር መርሻ ገብሬ
ዘወትር በመሠዊያው ላይ እሳት ይነድዳል፤አይጠፋም ዘሌ 6፡ 8-13
ሉቃ 12፡49 በምድ ላይ እሳት ልጥል መጣሁአሁን የነደደ ከሆነ ዘንድ ም እፈልጋለሁ፡፡
መግቢያ
የዘሌዋውያን መጽሐፍ የሕግ ስብስብ ብቻ ሳይሆን፣ ቅዱሱእግዚአብሔር ከወደቀውና ከኃጢአተኛው ሰው ጋር እንዴትእንደሚገናኝና ሕዝቡም በቅድስና እንዴት ከእርሱ ጋር መኖርእንደሚችሉ የሚያሳይ ነው፡፡
የመጀመሪያውን የመሠዊያ እሳት ያቀጣጠለው እግዚአብሔርነበር (ዘሌ 9:24)።
ለካህናቱ የተሰጠው ዋነኛ ኃላፊነት የነደደው እሳት እንዳይጠፋእንጨት በመጨመር መንከባከብ እና ዘወትር እንዲነድ መጠበቅነው፡፡
«ዘወትር በመሠዊያው ላይ እሳት ይነድዳል፤ አይጠፋም»ትእዛዙ የብሉይ ኪዳን አምልኮ ማዕከል የሆነውን የመሥዋዕትህያውነት ያመለክታል። በመሠዊያው ላይ ያለው እሳትእንዳይጠፋ የካህናቱን ዕለታዊ ትጋትና ንቃት ይጠይቃል፡፡
1. የእግዚአብሔር ህላዌ፤ የምህረት እና ቅድስና መገለጫ
በብሉይ ኪዳን ታሪክ ውስጥ እሳት የእግዚአብሔርን ቅድስናናህላዌ የሚያሳይ ዋነኛ ምልክት ነው (ዘጸአት 3:2)፤
• በመሠዊያው ላይ ዘወትር የሚነደው እሳት እግዚአብሔርበህዝቡ መካከል ዘወትር እንዳለ የሚያሳይ ምስክር ነው።
• መሠዊያው የኃጢአት ማስተስረያና ከእግዚአብሔር ጋርየመታረቂያ ስፍራ ነው።
• እሳቱ ዘወትር መንደድ የእግዚአብሔር የምህረት ደጅ ዘወትርክፍት መሆኑን ነው።
2 . የካህናቱ የትጋትና የኃላፊነት ድርሻ
• እሳቱ እንዳይጠፋ ማድረግ ።
• ማለዳ ማለዳ እንጨት የመጨመር፡
እንጨት ደግሞ ለዕለቱ እሳት መቀጣጠያ የሚሆን አዲስመሥዋዕትና መታዘዝ ነው። ብዙ ጊዜ የመንፈሳዊ ህይወት ቅዝቃዜ ምክንያቱ በትናንት መንፈሳዊ ልምምድ (አመድ) ላይተቀምጠው አዲስ እንጨት (ዕለታዊ የቃልና የጸሎት ሕይወት) ማቅረብ ማቆም ነ
• የመሠዊያውን አመድ ማንሳት
አመድ ትናንት የተቃጠለውና አልፎ የሄደው መሥዋዕትፍሬ ነው። ትናንት የነደደው እሳት ዛሬ አመድ ሆኗል ። አዲስእሳት እንዲነድድ ከተፈለገ አመዱ መወገድ አለበት።
• የመሥዋዕቱን አካል የማዘጋጀት (ዘሌ6:12)። ይህ የሚያሳየውየእግዚአብሔር መንፈሳዊ ስጦታ በሰው በኩል በሚደረግትጋትና እንክብካቤ እንደሚጠበቅ ነው።
እግዚአብሔር በሰው ውስጥ ያስቀመጠው የፀጋ ስጦታእንዳይጠፋ የመንፈስ ቅዱስ እሳት ማቀጣጠል ይገባል፡፡
. በሰው ሰራሽ እሳት አለመተካት፡-
• የነደደው እሳት እንዳይጠፋ መጠበቅ እንጂ ሰው ሰራሽ እሳትማቀጣጠል አልተፈቀደም ፡፡
ያለጥንቃቄ በራሳቸው ተነሳስተው እሳት ያቀጣጠሉ ናዳብናአብድዩ በየራሳቸው ጥናውን ወስደው እሳት አደረጉበት በላዩምእጣን አኖሩበት በእግዚአብሔርም ፊት እርሱ ያላዘዛቸውንሌላእሳት አቀረቡ፡፡ ከእግዚአብሔርም ፊት እሳት ወጥቶ በላቸው በእግዚአብሔርም ፊት ሞቱ / ዘሌ 10፡1-2 ፡፡
ከእግዚአብሔር እንደሆነ በማስመሰል የራስን አሳብ በእግዚአብሔር ስም መናገር ወይንም ማድረግ በእገዚአብሔር ፊት ያስጠይቃል፡፡ ስለሆነም ሁሉን ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡

ሀ. ከብሉይ ኪዳን
• ዘሌዋውያን 9:24 – "እሳትም ከእግዚአብሔር ፊት ወጣች፥በመሠዊያውም ላይ ያለውን የሚቃጠለውን መሥዋዕትናስቡን በላች..."
• ነገሥት 18: 38 – "የእግዚአብሔርም እሳት ወደቀች፥የሚቃጠለውንም መሥዋዕትና እንጨቱን ድንጋዮቹንምአፈርህንም በላች. "
• ኢሳይያስ 6: 6-7 – "ከሰራፌልም አንዱ በመቆንጠጫከመሠዊያው የወሰደውን ፍም በእጁ ይዞ ወደ እኔ በረረ፤አፌንም ዳሰሰበት..
ለ. ከአዲስ ኪዳን ከጥላ ወደ እውነት፡
የብሉይ ኪዳን መሠዊያና እሳት የአዲስ ኪዳን ታላቅ እውነት እና ጥላ ናቸው።
• መሠዊያው፡ በብሉይ ኪዳን ከነሐስ እና የድንጋይ ወይምየቦርድ መሠዊያ ነበረ፤ በአዲስ ኪዳን
ግን የክርስቶስ መስቀልና የአማኙ ልብ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያመሠዊያ ሆኗል 1ቆሮ 3፡ 17 ።
በአዲስ ኪዳን በክርስቶስ ኢየሱስ አምነው የዳኑ ሁሉ ካህናቶች ናቸው 1ጴጥሮስ 2፡9 �መሥዋዕቱ፡ በብሉይ ኪዳን የእንስሳት ደም ነበረ፤ በአዲስ ኪዳንክርስቶስ አንድ ጊዜ ፈጽሞ ራሱን ያቀረበው ፍጹም መሥዋዕትነው / ዕብ 5፡ 7 ።
• እሳቱ፡ በብሉይ ኪዳን በድንኳኑ ውስጥ ይነድድ የነበረውእሳት፤ በአዲስ ኪዳን በበዓለ ጴንጤቆስቴ ወርዶ በቤተክርስቲያንና በአማኞች ልብ ውስጥ የሚነድደው መንፈስቅዱስ ነው።
• የሐዋርያት ሥራ 2:3-4 – "የእሳት ነበልባል የሚመስሉየተከፋፈሉ ልሳኖች ታዩአቸው፤ በእያንዳንዳቸው ላይተቀመጡባቸው። በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው .."
• ሮሜ 12:1፤ 11 – "ሰውነታችሁን ሕያው፥ ቅዱስ፥እግዚአብሔርንም ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት አድርጋችሁታቀርቡ ዘንድ... በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ፤ ለጌታ ተገዙ።"
• 2 ጢሞቴዎስ 1:6 – የእግዚአብሔርን ስጦታ እንድታነሣሣ እንድታቀጣትል አሳስብሃለሁ ይላል ።
• 1 ተሰሎንቄ 5:19 – "መንፈስን አታጥፉ።
ማጠቃለያ
እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠው ትእዛዝ "እሳቱ ዘወትርይነድዳል፤ አይጠፋም" የሚል ከሆነ፣
እሳት እንዳይጠፋ አራት ዋና ዋና ነገሮች ያስፈልጋሉ፡
• አየር (የመንፈስ ቅዱስ ህልውና)፡ ያለ መንፈስ ቅዱስ እርዳታሃይማኖታዊ ሥርዓት ብቻ ይሆናል፡፡
• እንጨት (የእግዚአብሔር ቃልና ጸሎት)፡ በየዕለቱ ቃሉንማብላትና በጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር እሳቱንያቀጣጥለዋል።
• አመዱን ማንሳት (ንሰሐ)፡ ክፉ ምኞት፣ ቂም፣ አድመኝነትን እና አጠቃላይ የኃጢአት ልምምድ ማስወገድ፡፡
• መሥዋዕት ማቅረብ እሳት ያለ መሥዋዕት የሚበላው አጣሁብሎ ይጠፋል። ሕይወታችንን ሙሉ በሙሉ ለጌታ ፈቃድአሳልፈን ስንሰጥ እሳቱ ዘወትር ይነድዳል ሮሜ 12፡1-2፡፡
ተግባራዊ እርምጃዎች
1. መሠዊያችንን ማደስ የፈረሰውን የግልና የቤተሰብ ጸሎትመሠዊያ እንደገና አድሱ ። እሳቱ እንዲነድ መሰዊያውን / ልባችንን/ ማደስ፡፡
2. ከሕይወታችን አመድ የሆነውን ማስወገድ፡- በትናንትስኬት ወይም በትናንት መንፈሳዊ ልምምድ ላይ ብቻ አለመደገፍ ። እንዲሁም በልብ ውስጥ የተቀመጠውንየቂም፣ የኃጢአትና የዓለማዊነት አመድ በንሰሐ ማስወገድ ፡፡
3. በየቀኑ የእግዚአብሔርን ቃል በማንበብ፣ በማሰላሰልናበመታዘዝ አዲስ እንጨት በመሠዊያው ላይ በመጨመር ማቀጣጠል ። እሳቱ እንዳይጠፋ የማድረግ ኃላፊነት የየግላችን ነው።

Facebook https://www.facebook.com/profile.php?id=61567498017093&mibextid=ZbWKwL
Telegram
https://t.me/+AqjPGNRFvlEyMmFk
Youtube
https://youtube.com/?si=fwcZPawNrwOD_thg
Tiktok
https://www.tiktok.com/?is_from_webapp=1&sender_device=pc
Instagram
https://www.instagram.com/hawassaalamurafullgospelchurch/
Follow, Like, Share በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ፡፡

በአላሙራ ሙሉ ወንጌል በወጣቶች አገልግሎት የተዘጋጀ የጥያቄ እና መልስ ዉድድር በቤተክርስቲያን አገልግሎት ዘርፎች መሃከል የተከናወነ የማጠቃለያ ዉድድር በህብረቶች አገልግሎት ዘርፍ የተዘጋጀF...
12/08/2026

በአላሙራ ሙሉ ወንጌል በወጣቶች አገልግሎት የተዘጋጀ የጥያቄ እና መልስ ዉድድር በቤተክርስቲያን አገልግሎት ዘርፎች መሃከል የተከናወነ የማጠቃለያ ዉድድር በህብረቶች አገልግሎት ዘርፍ የተዘጋጀ
Facebook
https://www.facebook.com/profile.php?id=61567498017093&mibextid=ZbWKwL
Telegram
https://t.me/+AqjPGNRFvlEyMmFk
Youtube
https://youtube.com/?si=fwcZPawNrwOD_thg
Tiktok
https://www.tiktok.com/?is_from_webapp=1&sender_device=pc
Instagram
https://www.instagram.com/hawassaalamurafullgospelchurch/

Follow, Like, Share በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ፡፡

ቀን 03/12/18የ እሁድ አምልኮ👉🏿ፀሎት በወንድም ፍቅሩ ፀጋዬ👉🏿አምልኮ:- በቤተክርስቲያኒቱ የአምልኮ መሪዎች👉🏿መዝሙር :-በናዝራዊ መዘምራን 👉🏿የእግዚአብሄር ቃል :-በወንጌላዊ ካሳሁን ገ...
09/08/2026

ቀን 03/12/18
የ እሁድ አምልኮ
👉🏿ፀሎት በወንድም ፍቅሩ ፀጋዬ
👉🏿አምልኮ:- በቤተክርስቲያኒቱ የአምልኮ መሪዎች
👉🏿መዝሙር :-በናዝራዊ መዘምራን
👉🏿የእግዚአብሄር ቃል :-በወንጌላዊ ካሳሁን ገበየው
🔹ርዕስ:-የተቻለንን ሁሉ ለጌታ እናድርግ
🔹የንባብ ክፍል: ማርቆስ 14፣1-9
🔹 ይሄ የመፅሀፍ ቅዱስ ክፍል በ አራቱም ወንጌላት ውስጥ ተፅፎ እናገኘዋለን።
🔹በዚህ ክፍል ውስጥ በተለይም ከ 1-3 እንደምንመለከተው ወደ 3ያህል ዝግጅቶች ያሉበት ነው
#የመጀመሪያው ዝግጅት:- የ አይሁድ የፍሲካ እና የቂጣ በአል ዝግጅት አለ።
# ሁለተኛው ዝግጅት :- የካህናት አለቆችና ፃፍቶት እንዴት አድርገው ጌታን ለመያዝ ፣ለመግደል እንደሚችሉ ሲዘጋጅ ያሳያል።
#ሶስተኛው ዝግጅት:- ጌታ እየሱስ እራሱን ለመጣበት አላማ ለሞት ዝግጅት ላይ ነው።
🔹ከ 3 እስከ 8 ባለው ክፍል ውስጥ ኢየሱስ በስምኦን ቤት እያለ 7 አጋንንት የወጣላት ማርያም መጣች ይህች ሴት እጅግ የከበረውን የከበረውን ብቻ ሳይሆን ሙሉ የናርዶስን ሽቶ ነው ይዛ የመጣችው
ይህች ሴት በ እጇ ያላትን ውድ ነገር ነው ለጌታ ይዛ የመጣችው ሰው ምን ይለኛል ሳትል ፣ይሉኝታ ሳይዛት፣ ብልቃጡን ሰብራ አፈሰሰች
ይህች ሴት ያላትን ውዱን የሞላውን ስጦታ ለጌታ ሰጠች
🔹ይሄን ስታደርግ እንደ ይሁዳ ያሉ ነቅፈዋት ነበር
🔹ጌታም በ ቁጥር ማርቆስ 14፣ 6 ኢየሱስ ግን እንዲህ አለ፡— ተዉአት፤ ስለ ምን ታደክሙአታላችሁ? መልካም ሥራ ሠርታልኛለች።
👉ኢየሱስ የልቧን አምልኮ ስለሚያውቅ ስለ ነበር ተዋት መልካም ሰርታለች አለ።
👉ጌታ ከልባቸው የሚያመልኩትን ያውቃቸዋል።
👉አምልኮ ከመስጠት ሳይሆን ከመሰጠት ይጀምራል።
✳️የተቻለንን ሁሉ ለ ጌታ ስናደርግ ምን ይሆናል።
1 ጌታ አምልኮዋችንን ይቀበለዋል።
2 አምልኮዋችንን ሲቀበል ቁጥር 6 ላይ እንዳለው ይሟገትልናል።
3 የስጦታችንን መልካምነት ከብዙሀን ለይቶ ያየዋል።
# ማጠቃለያ :- ለጌታ የተቻለንን ሁሉ እናድርግ።

Facebook https://www.facebook.com/profile.php?id=61567498017093&mibextid=ZbWKwL
Telegram
https://t.me/+AqjPGNRFvlEyMmFk
Youtube
https://youtube.com/?si=fwcZPawNrwOD_thg
Tiktok
https://www.tiktok.com/?is_from_webapp=1&sender_device=pc
Instagram
https://www.instagram.com/hawassaalamurafullgospelchurch/
Follow, Like, Share በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ፡፡

የእሁድ አምልኮ ቀን:- 26/11/18ዓ.ምፀሎት:- በወንድም ቁምልኝ አለማየሁ አምልኮ:- በቤተክርስቲያኑቱ አምልኮ መሪዎችዝማሬ:- በቤቴል መዘምራንየእግዚአብሔር ቃል:- በፕሮፌሰር ደሴ ሽፈራው...
02/08/2026

የእሁድ አምልኮ
ቀን:- 26/11/18ዓ.ም
ፀሎት:- በወንድም ቁምልኝ አለማየሁ
አምልኮ:- በቤተክርስቲያኑቱ አምልኮ መሪዎች
ዝማሬ:- በቤቴል መዘምራን
የእግዚአብሔር ቃል:- በፕሮፌሰር ደሴ ሽፈራው

ርዕስ:- የህይወት/የኑሮ ቅመም
ምሳሌ 3÷13-18
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³ ጥበብን የሚያገኝ ሰው ምስጉን ነው፥ ማስተዋልንም ገንዘቡ የሚያደርግ፤
¹⁴ በወርቅና በብር ከመነገድ ይልቅ በእርስዋ መነገድ ይሻላልና።
¹⁵ ከቀይ ዕንቍም ትከብራለች፥ የተከበረም ነገር ሁሉ አይተካከላትም።
¹⁶ በቀኝዋ ረጅም ዘመን ነው፥ በግራዋም ባለጠግነትና ክብር።
¹⁷ መንገድዋ የደስታ መንገድ ነው፥ ጎዳናዋም ሁሉ ሰላም ነው።
¹⁸ እርስዋ ለሚይዙአት የሕይወት ዛፍ ናት፥ የተመረኰዘባትም ሁሉ ምስጉን ነው።

▪️ክርስቲያናዊ ህይወትን በጣፈጠ መልኩ ለመምራት የኑሮ ቅመም ያስፈልጋል
ይህ የህይወት ቅመም ጥበብ ይባላል

▪️ጥበብ በአዕምሮ ብልህነት ነገሮችን በብልሀት እና በማስተዋል ማድረግ ነው

▪️ማስተዋል የምናደርገውን ነገር በደምብ መመልከት እና ማጤን ነው።እያንዳንዱን ነገር በማስተዋል ማድረግ አለብን

🔸ፍቅርን በማስተዋል መስጠት
“ለእግዚአብሔርም ክብርና ምስጋና ከኢየሱስ ክርስቶስ የሚገኝ የጽድቅ ፍሬ ሞልቶባችሁ፥ ለክርስቶስ ቀን ተዘጋጅታችሁ ቅኖችና አለ ነውር እንድትሆኑ የሚሻለውን ነገር ፈትናችሁ ትወዱ ዘንድ፥ ፍቅራችሁ በእውቀትና በማስተዋል ሁሉ ከፊት ይልቅ እያደገ እንዲበዛ ይህን እጸልያለሁ።”
— ፊልጵስዩስ 1፥9-11
🔸ኑሮን በማስተዋል መኖር
“እንዲሁም፥ እናንተ ባሎች ሆይ፥ ደካማ ፍጥረት ስለ ሆኑ ከሚስቶቻችሁ ጋር በማስተዋል አብራችሁ ኑሩ፤ ጸሎታችሁ እንዳይከለከል አብረው ደግሞ የሕይወትን ጸጋ እንደሚወርሱ አድርጋችሁ አክብሩአቸው።”
— 1ኛ ጴጥሮስ 3፥7

▪️በዚህ ዘመን ለክርስትና አቅም ማጣት ምክኒያቱ የአማኞች ጥበብ ማጣት ነው።በማስተዋል እና በጥበብ አለመመላለስ ራስንም ባለመግዛት ትልቁ የክርስቲያን ነቀፌታ ነው።

▪️ስሜትን ተቆጣጥሮ እራስን በመግዛት ለመንፈስ ቅዱስ ምሪት አሳልፎ በመሰጠት መመላለስ ያስፈልጋል

▪️በሰዎች መካከል እንደ ጨው መመላለስ ይገባናል በገባንበት ስፍራ ማጣፈጥ መቻል አለብን

✅ይህንን ጥበብ እግዘብሔርን በመፍራት እንዲሁም ጥበብን እንዲሰጠን በመለመን በማግኘት በእለተእለት ኑሮአችን በጥበብ በማስተዋል እና እግዚአብሔርን በመፍራት ልንመላለስ ይገባል።

Facebook https://www.facebook.com/profile.php?id=61567498017093&mibextid=ZbWKwL
Telegram
https://t.me/+AqjPGNRFvlEyMmFk
Youtube
https://youtube.com/?si=fwcZPawNrwOD_thg
Tiktok
https://www.tiktok.com/?is_from_webapp=1&sender_device=pc
Instagram
https://www.instagram.com/hawassaalamurafullgospelchurch/
Follow, Like, Share በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ፡፡

ቀን 21/11/18መደበኛ የወጣቶች አምልኮ በቤቴል መዘምራን የተዘጋጀ እስክትመጣ በሚል ርዕስ የአምልኮ ምሽት ዝማሬ :-በቤቴል መዘምራን ቃል:- ወንድም ባሻዉ በየነ ርዕስ: ትኩረቱ በኢየሱስ ...
29/07/2026

ቀን 21/11/18
መደበኛ የወጣቶች አምልኮ
በቤቴል መዘምራን የተዘጋጀ እስክትመጣ በሚል ርዕስ የአምልኮ ምሽት
ዝማሬ :-በቤቴል መዘምራን
ቃል:- ወንድም ባሻዉ በየነ
ርዕስ: ትኩረቱ በኢየሱስ የተወሰደ ትውልድ!
ሉቃ 9:27-36; ቆላ 3:1-4
ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:1 እንግዲህ ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ፥ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ እሹ
፤2 በላይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም
3 ሞታችኋልና፥ ሕይወታችሁም በእግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ተሰውሮአልና
4 ሕይወታችሁ የሆነ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ፥ በዚያን ጊዜ እናንተ ደግሞ ከእርሱ ጋር በክብር ትገለጣላችሁ።
▪️መግብያ:-ድርጊታችንንና ልምምዳችን የሀሳባችን ውጤት ነው።በምድር ስንኖር ሰፊ ጊዜያችንን የሚወስዱ ነገሮች አንድም ለመኖር ግዴታ ሆነውብን ሌሎቹ ደግሞ ትኩረት ሰጥተን ነው ግዜያችንን የወሰዱት።
▪️በክፍሉ የሚናየው እነ ጴጥሮስ ኢየሱስ ገና በክብሩ ዳግመኛ ሲመጣ የሚኖረውን መልክና ዉበት በጥቂቱ ስያሳያቸው በዚያ መቅረት ሲመኙ እናያለን!
ጻውሎስም የቆላስይስ አማኞችን በላይ ያለውን አስቡ ይላል።
▪️በኢየሱስ ያተኮረ ትውልድ ባህሪያት
1-ኢየሱስን አስበልጦ መኖር
ሙሴ በዘጸ 33:13 እግዚአብሔር ያለ እኔ ሂዱ ትወርሳላችሁ መልአኬም ፊታችሁ ይወጣል ሰለው እንቢ አለ ለምን?
▪️እግዚአብሔር ለሙሴ ትወርሳለህ ከሚለው መልዕክትና ከፊትህ ይወጣል ከተባለው መልአክ እግዚአብሔር ይበልጣል!
እኔ የራሳቸው ነገር ረስተው ባዩት ኢየሱስ ረክተው እዚህ እንሆናለን!
2- ሲመጣ ክብራችንም አብሮ እንደሚመጣ ማወቅ(ቆላ 3:4)
ኢየሱስ በክብር ሲመጣ ለእኛም የክብር ቀን ይመጣል።
መጠቃልያ
▪️ዛሬ ትኩረታችንን የሰጠነው ነገር ነው የሚገዛን!
ኢየሱስን ከመናፈቅ ወደ መሰልቸት ከሄድን ሌላ ትኩረታችንን የወሰደ ነገር አለ ማለት ነው።
ሰይጣን ምናልባት ሃሳባችንን ሰርቆ እንዳይሆን ተማርከን ከሆነ እንመለስ በሃሳብ ትኩረታችንን ኢየሱስ ላይ እናድርግ ሕይወታችን ክብራችንም ነውና።
Facebook
https://www.facebook.com/profile.php?id=61567498017093&mibextid=ZbWKwL
Telegram
https://t.me/+AqjPGNRFvlEyMmFk
Youtube
https://youtube.com/?si=fwcZPawNrwOD_thg
Tiktok
https://www.tiktok.com/?is_from_webapp=1&sender_device=pc
Instagram
https://www.instagram.com/hawassaalamurafullgospelchurch/

Follow, Like, Share በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ፡፡

መንፈሱና ሙሽራይቱም፡— “ና፡” ይላሉ። የሚሰማም፡— “ና፡” ይበል። ራእይ 22:17    እስክትመጣ.....ዛሬ ልዩ አምልኮ ምሽት በሀዋሳ አላሙራ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን  ከ10 ሰዓት ጀም...
28/07/2026

መንፈሱና ሙሽራይቱም፡— “ና፡” ይላሉ። የሚሰማም፡— “ና፡” ይበል። ራእይ 22:17

እስክትመጣ.....
ዛሬ ልዩ አምልኮ ምሽት በሀዋሳ አላሙራ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ከ10 ሰዓት ጀምሮ በቤቴል ኳየር የተዘጋጀ።

Address

Hawassa
Hawassa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hawassa Alamura Full Gospel Church posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share