መራሔ ድኅነት ሰንበት ት.ቤት /Hawassa St. Gebriel Sunday School/

  • Home
  • Ethiopia
  • Hawassa
  • መራሔ ድኅነት ሰንበት ት.ቤት /Hawassa St. Gebriel Sunday School/

መራሔ ድኅነት ሰንበት ት.ቤት /Hawassa St. Gebriel Sunday School/ የደብረ ምህረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም መራኄ ድኅነት ሰንበት ?

እንኳን አደረሳችሁ/ አደረሰን…!
11/09/2026

እንኳን አደረሳችሁ/ አደረሰን…!

''ይህ ልጄ ጠፍቶ ነበር ተገኝቷል'' ሉቃ 15፥24በገዳማችን መራሔ ድኅነት ሰንበት ት/ቤት በ2018 ዓ.ም በነበረው የዕቅበተ ዕምነት አግልግሎት መሠረታዊ የቤተ-ክርስቲያን ትምህርት በማስተማ...
08/09/2026

''ይህ ልጄ ጠፍቶ ነበር ተገኝቷል'' ሉቃ 15፥24

በገዳማችን መራሔ ድኅነት ሰንበት ት/ቤት በ2018 ዓ.ም በነበረው የዕቅበተ ዕምነት አግልግሎት መሠረታዊ የቤተ-ክርስቲያን ትምህርት በማስተማር እና የእግዚአብሔርን ልጅነት እንዲያገኙ በማስተባበር በዚህ ዓመት 14 አዳዲስ አማኞች የጥምቀት ሥርዓት ተፈጽሞላቸው ወደ ቅድስት ተዋህዶ ዕምነታችን የተቀላቀሉ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ደግሞ 13 ወንድሞች እና እህቶች የጥምቀት ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ይገኛሉ፤ ከእነዚህም መካከል 8ቱ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ በመሆናቸው በዚህ ወር ይጠመቃሉ ተብሎ ይጠበቃል። ለዚህም ያበቃን የአባቶቻችን አምላክ ቅዱስ እግዚአብሔር ይመስገን እያልን በዚህ ክንውን ውስጥ መመሪያ በመስጠት በፀሎት በማሰብ እንዲሁም በመምከር የገዳማችን ዋና አስተዳዳሪ መ/ፀ/ቆ/ አባ ኪዳነ ማርያም አንዷለም ትልቁን ድርሻ ሲወስዱ የሰንበት ትምህርት ቤቱ ግንኙነት ክፍል አባላት እህቶች እና ወንድሞች በመማር ማስተማር ሂደቱ በመሳተፍ በማስተባበር እንዲሁም መምህራን በተከታታይነት በማስተማር ላበረከታችሁት ጉልህ ድርሻ በማመስገን አገልግሎታችሁን አምላከ ቅዱሳን ይቀበልላችሁ እያልን በቀጣይም በብርታት እገልግሎታችሁን እንድታስቀጥሉ እንላለን!!!

መራሒ ሚድያ

👉 Telegram

👉 Facebook

👉 Youtube

የሀዋሳ ደብረ ሰላም ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ፈለገ ሰላም ሰንበት ትምህርት ቤት እንኳን ለ46ኛ ዓመት የምሥረታ በዓላችሁ አደረሳችሁ!አገልግሎታችሁን ያስምርልን ረጅም የአገልግሎት ዘመንን ያድል...
02/09/2026

የሀዋሳ ደብረ ሰላም ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ፈለገ ሰላም ሰንበት ትምህርት ቤት እንኳን ለ46ኛ ዓመት የምሥረታ በዓላችሁ አደረሳችሁ!

አገልግሎታችሁን ያስምርልን ረጅም የአገልግሎት ዘመንን ያድልልን !

+ ሀ/ደ/ም/ቅ/ገ/ገ መራሔድኅነት ሰ/ት/ቤት

ፍኖት ዘመራሔ ድኅነት የሰንበት ት/ቤታችን የአንድነት ጉዞጷጕሜ 1 2018 ዓ.ምየጉዞውን ትኬት ለመግዛት ከሥር በተቀመጡ ስልኮች ይጠቀሙ።+ ሀ/ደ/ም/ቅ/ገ/ገ መራሔድኅነት ሰ/ት/ቤት
02/09/2026

ፍኖት ዘመራሔ ድኅነት የሰንበት ት/ቤታችን የአንድነት ጉዞ

ጷጕሜ 1 2018 ዓ.ም

የጉዞውን ትኬት ለመግዛት ከሥር በተቀመጡ ስልኮች ይጠቀሙ።

+ ሀ/ደ/ም/ቅ/ገ/ገ መራሔድኅነት ሰ/ት/ቤት

የሕፃናት ልዩ የበጋ ትምህርት ምዝገባ ተጀምሯል
31/08/2026

የሕፃናት ልዩ የበጋ ትምህርት ምዝገባ ተጀምሯል

‎2019 ዓ.ም ሐዋሳ የሚገኙ አጥቢያ ሰ/ት/ት ቤቶች የልምድ ልውውጥ በሐ/ደ/ም/ቅ/ገብርኤል ገዳም መራሔ ድኅነት ሰ/ት/ቤት አደረጉ።‎በሐ/ደ/ም/ቅ/ገብርኤል ገዳም መራሔ ድኅነት ሰ/ት/ቤት ...
30/08/2026

‎2019 ዓ.ም ሐዋሳ የሚገኙ አጥቢያ ሰ/ት/ት ቤቶች የልምድ ልውውጥ በሐ/ደ/ም/ቅ/ገብርኤል ገዳም መራሔ ድኅነት ሰ/ት/ቤት አደረጉ።

‎በሐ/ደ/ም/ቅ/ገብርኤል ገዳም መራሔ ድኅነት ሰ/ት/ቤት ጠሪነት በሐዋሳ የሚገኙ 6 ሰ/ት/ቤቶች ማለትም

1. የ‎ደብረ ታቦር ቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን ሰ/ት/ቤት
2. የ‎ደብረ ሳሕል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ፍኖተ ቅዱሳን ሰ/ት/ቤት
3. የ‎ቅዱስ ያሬድ ቤተክርስቲያን ውሉደ ያሬድ ሰ/ት/ቤት
4. የ‎ደብረ ቀርሜሎስ ቅዱስ ኤልያስ ሰ/ት/ቤት
5. የቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን ሰ/ት/ቤት
6. የሎቄ ‎ደብረ መድኃኒት መስቀለ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ሰ/ት/ቤት

በአካል በመገኘት በሰ/ት/ቤት ዙሪያ ውይይት እና ልምድ ልውውጥ አድርገዋል።
በውይይቱም ‎በቀጣይ ሊኖሩ ስለሚገባቸው የእርስ በእርስ ግንኙነቶችና መንፈሳዊ አገልግሎቶቻችን ዙሪያ ጠንካራ ትብብር መፍጠር እንደሚገባ አጽንዖት የተሠጠው ሲሆን በተለይም አዳዲስ በቅርብ ጊዜ የተመሰረቱ ሰ/ት/ቤቶች ሰፋ ያለ እገዛ እንደሚያስፈልጋቸውና በሚገባ እንዲደራጁ ደግሞ የጋራ ትብብር መኖር እንዳለበት አጽንዖት ተሰጥቶ ውይይት ተደርጎበታል።

‎በቀጣይም እንዲህ ያሉ ግንኙነቶች በተለያዩ የአገልግሎት መስመሮች በሚገባ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በመስማማት እና የጋራ አቋም በመያዝ ተግባራዊነቱ ላይ በማተኮር እንዲሰራ በማሳሰብ የውይይት መርሐግብሩ ተቋጭቷል።

በመጨረሻም ለልምድ ልውውጡ ከተለያዩ ሰንበት ትምህርት ቤቶች የመጡ አገልጋዮች እና የሥራ አመራር አባላት ከመራሔድኅነት ሰ/ት/ቤት ላገኙት ልምድ እና አጠቃላይ ለተደረገላቸው ትብብር ምስጋና አቅርበው የልምድ ልውውጥ መርሐግብሩ በጸሎት ፍጻሜ አግኝቷል

‎ለዚህም የጋራ የውይይትና የልምድ ልውውጥ መርሐግብር ፈቃዳቸውን በመስጠት ከሩቅም ጭምር የመጡትን የሰ/ት/ቤት ወንድሞች እና እህቶች እንዲሁም የሥራ አመራር አባላት መራሔ ድኅነት ሰ/ት/ቤት ምስጋና ያቀርባል።

+ ሀ/ደ/ም/ ቅ/ገ /ገ መራሔድኅነት ሰ/ት/ቤት

የሐዋሳ ቅዱስ ገብርኤል ትምህርት ቤት በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎችን በሙሉ 100% በማሳለፍ ከፍተኛ ውጤት አስመዘገበ።በ2018 ዓ.ም. የ12ኛ ክፍ...
26/08/2026

የሐዋሳ ቅዱስ ገብርኤል ትምህርት ቤት በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎችን በሙሉ 100% በማሳለፍ ከፍተኛ ውጤት አስመዘገበ።

በ2018 ዓ.ም. የ12ኛ ክፍል ዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና የወሰዱ 69 ተማሪዎች በሙሉ 100% በማለፍ ከፍተኛ ውጤት አስመዝግበዋል።

በዚህም ትምህርት ቤቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ 100% ካሳለፉ 88 ትምህርት ቤቶች መካከል በመሆን እንዲሁም በሲዳማ ክልል ደግሞ ከተመረጡት 2 ትምህርት ቤቶች አንዱ ሆኖ ትልቅ የሚያኮራ ታሪክ ሠርቷል።

ለዚህም የትምህርት ቤቱ አስተዳደር ይህ ውጤት እንዲገኝ የድርሻቸውን ለተወጡ እና ትምህርት ቤቱን ለዚህ ከፍ ላለክብር እንዲበቃ ላደረጉ አካላት ማለትም የገዳሙ አስተዳደር ፣የትምህርት ቤቱ አስተዳደር አካላት ፣መምህራን እና ተማሪዎች እንዲሁም ለተማሪ ወላጆች በሙሉ ምስጋናውን አቅርቧል።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን!

+ መራሔድኅነት ሰ/ት/ቤት

" ሦስቱ ወጣቶች እሳት ውስጥ ሆነው እንደዘመሩ በመከራ ውስጥ ሆኖ ፈጣሪን የሚያመሰግን ሰው የመከራው እሳት ውኃ ይሆንለታል። ለድሆች ምጽዋትን የሚሰጥ ሰው ደግሞ ሠልስቱ ደቂቅን ከእሳት የታደ...
25/08/2026

" ሦስቱ ወጣቶች እሳት ውስጥ ሆነው እንደዘመሩ በመከራ ውስጥ ሆኖ ፈጣሪን የሚያመሰግን ሰው የመከራው እሳት ውኃ ይሆንለታል። ለድሆች ምጽዋትን የሚሰጥ ሰው ደግሞ ሠልስቱ ደቂቅን ከእሳት የታደገውን የእግዚአብሔር መልአክን ይመስለዋል…" /ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ/

+መራሔድኅነት ሰ/ት/ቤት

"…አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነስ አንተና የመቅደስህ ታቦት…"መዝ 131፥8
22/08/2026

"…አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነስ አንተና የመቅደስህ ታቦት…"መዝ 131፥8

Address

Hawassa
Hawassa

Telephone

+251462215117

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when መራሔ ድኅነት ሰንበት ት.ቤት /Hawassa St. Gebriel Sunday School/ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share