Mar-sil DAILY Devotion ማር-ሲል

Mar-sil  DAILY Devotion ማር-ሲል ወደ ሮሜ ሰዎች 10፥11 ... በእርሱ የሚያምን ሁሉ አያፍርም ይላልና፡፡

11/02/2019


ውድ ወገኖቼ ፡- በቅድሚያ ሰላማችሁ የተጠበቀ ፤እንዲሆን መልካም ምኞቴን እገልጣለሁ፡፡
ኢትዮጵያ ሃገራችን በአላትና በነበራት ታሪክ ላይ ሃገር በመውደድና መስዋእትነት በመክፈል የበኩላችሁን አኩሪ አሻራ ያኖራችሁ ፣ አብሮነታችሁ የተደነቀና የታወቀ መሆኑን ከልጅነት እስከ እውቀት በአብሮነት ያሳለፍኩት ህይወቴ ህያው ምስክር ነውና ነቃሽ መጥራት አያስፈልግም፡፡
ይሁንናም አሁን አሁን በአንዳንድ የሃገራችን ክፍሎች እየተስተዋለ ያለው መገፋፋት በእሳቱ ላይ ነዳጅ እንደመጨመር ያለ፣ በመንገዳችን ላይ ጋሬጣ እየነሰነሰ የሚታይ ሁነት ነው፡፡
በዚህ በ21ኛው ክፍለዘመን ላይ ጥቂት የማይባሉ ሃሮች እያለፉበት ያለው አሳዛኝ እጣ ፈንታ በሐገራችን ውስጥ እንዲሆን ፣ ሰው እምነቱን በነጻነት እንዳያራምድና እንዲሸማቀቅ የሚያደርግ ሥራ እየተሰራ መሆኑ ለሁላችንም የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡
ሰው ያመነበትን በግሉም በቡድንም ማምለክ እምነቱንም ማሰራጨት በሃገራችን በኢትዮጵያ ህገመንግስት አንቀጽ 27 ተደንግጎልን እየተዳደርንበት ያለ እውነት ነው ብለን እናምናለን፤ ይንም ሰሞኑን በሃላባ ልዩ ወረዳ በቁሊቶ ከተማ በጠራራ ጸሐይ አብያ ክርስቲናት እንደጧፍ ነድደዋል፤ ንብረታቸው እንደተራ ጉዳይ ተቃጥሏል፤ ተሰባብረዋል፤ ምስባካቸው ተደፍሯል፡፡ ‹‹እስቲ በእኛ ዞን ይለምዳችሁና ሁለተኛ ታመልኩና ፤ ዋ !›› የተባለ ይመስል ክርስቲያኖች እምነት ተኮር ጥቃት ደርሶባቸዋል፡፡
ማንም ወገን ያመነውን ማምለክ መሰረታዊ መብቱ መሆኑን እና የሌሎችም የአምልኮ መብት እንዳይጣስ ስለምናምን መብታችን እንዲከበርልን የምናሳስበው በፍቅር ነው፡፡
እያንዳንዷ የአመጻ በትር ምት፣ በሰማይ ትደመጣለች፤ ተደምጣም ብቻ አትቀርም ዋጋ ታስከፍላለች፤ እያንዳንዷ የቃጠሎ ብናኝ፣ የሚድን ነፍስ ዋጋ ነው ያላት፤ እያንዳንዷ የቤተክርስቲያን ፍርስራሽ የወደቀበት ስፍራና ጢስ በአምላካችን እይታ ውስጥ እንደዘበት ባክኖ አይቀርም፡፡
እስራኤላውያን በባቢሎን የምርኮ ሃገር ተንከራተው በኖሩባቸው 70 ዓመታት ውስጥ ያልጠፋው የእግዚአብሄር ህልውና ገሃድ ሲሆን ሁሉን እንደአዲስ ለመጀመር አልተቸገሩም ፡፡ የእርሱ ጽዋ በሞላ ጊዜም የእርሱ የሆኑትን ሁሉ ወደቀደመ ስፍራቸው ለመመለስ የቻለው አምላክ ዛሬም እንዲህ ለማድረግ ጉልበቱ አልዛለም ፤ አልደከመም፤ ዛሬም ግፍን ዝም ብሎ አይታገስም፡፡
የተበተኑ ልጆችን መሰብሰብ አምላካዊ ባህሪ ነውና ብዙ ደሃ አደግ ልጆችን ሰብስቦ የሚረዳን ድርጅት የፕሮጀክት ጽህፈት ቤትን መሰባበርን ምን አመጣው?...እግዚአብሔርን ለማምለክም ሆነ ሌሎች ስራዎችን ለማስተዋወቅ የሚገለገሉበትን የድምጽ ማጉያ ማቃጠልን ምን ይሉታል? ልጆቻችሁ የሚማሩበትን ትምህርት ቤት መሰባበርን እንዴት አስቻላቸው? ሁሉ በሁሉ የተደረገው ነገር ቀና አሳብና መልካምነት ከጎደለው ልብ እንደሆነ ማጤን አያቅትም ፡፡
ከሰባበሩዋቸው ንብረቶች ይልቅ በጣም ሊሰብሩት ያሰቡት ልባችን ግን አልተሰበረም፤ ዛሬም ቀና ቢያስቡ እንደወትሮው ልንሆን እኛ ጌታችን ባስተማረን ትእግስትና ትህትና በይቅርታ ልብ ቆመናል፡፡

ውድ ወገኖቻችን!
፣ ይህ በስማችሁ የተፈጸመ ጥፋት በሚቆምበት መፍትሔ ላይ አበክራችሁ ትሰሩ ዘንድ ከልቤ ማሳስብ እወዳለሁ፡፡
ትናንት በልጅነት እድሜዬ አብሬያቸው ስማር ፣ አብሬያቸው ስዋኝ፣ አብሬያቸው ስጫወት ፣ አብሬያቸው ስኖር የነበርኳቸው ሙስሊም ወገኖቼ ሰላማዊነት አሁንም በቀደም እለት እንደሆነ ሁሉ ፊቴ ድቅን ይልብኛል፤ ዛሬ ምን ተገኘና ወደማመልክበት ቦታ መጥተው ማምለክ አትችልም፤ ሰፈሬን ልቀቅ ማለት ይሆንላቸዋል? እንደ እኔ እምነት በስማችሁ በመነገድ የቀደመውን አብሮነታችንን እንደ ውሃና ወተት ድብልቅ ሳይሆን እንደ ወተትና ሎሚ እንዲሆን የሚፈልጉ ክፉዎች ስራ ያለ ይመስለኛል፡፡
ኢትዮጵያ ለሁሉም ህዝቦቿ የሚበቃ እህል ፣ ለሁሉም ወገኖቿ የሚሆን መስክ ፤ ለሁሉም እምነቶች መስተናገጃ የሚረዳ ህግም ትውፊትም ያላት ሃገር እንጂ አጥፍተው ለመጥፋት የሚፈልጉ ክፉዎች የሚፈነጩባት ሜዳ ሆና አታውቅም፤ አትሆንምም ፡፡
እኔን የተሰማኝ ህመም እናንተንም ያማችኋል ብዬ አምናለሁ፤ በአምላካቸው ፊት እንባቸውን ከማፍሰስ ያለፈ ነገር የሌላቸው፣ ሰይፍ ላነሳባቸው ሰይፍ የማያነሱ ወገኖቹን ለማስደንበር የሚሞክረው ሃይል እየተፎካከረ ያለውና የሚገዳደረው፣ ‹‹ጦሩን ሲወረውር ሳይሆን ሲወጋ ብቻ ከሚታወቀው አምላክ ›› ጋር መሆኑንም ማወቅ አለበት፡፡
በሌላ በኩል ክርስቲያን ወገኖቻችንም በዚህ ረገድ፣ በወገኖቻሁ ላይ የደረሰውን ሞገድ በከንፈር መጠጣ የምታልፉት ሳይሆን ትናንት ሃላባዎችን ዛሬና ነገ ደግሞ እናንተን ሊሆን ስለሚችል ይህን ተግዳሮት፣ በጸሎት፣ በምልጃና በተባበረ ድምጽ ልትቃወሙትና ለወገኖቻችሁም በተገቢው ጎን ልትደርሱላቸው ይገባል፡፡
፡፡ መናገር ወርቅ ነው ከሚሉት ወገን ነኝ ፤
!!
የፈረሰውን ቅጥር ሊሰራ የሚወድ አብሮ ሊቆም የግድ ነውና ፣ በህብረትና በሰላም እንቁም!!

የማርሲል ቴሌቪዥን ዋና ሥራ አስፈጻሚ

14/08/2018
28/07/2018

THANK YOU ALL FOR 10K LIKES. GOD BLESS YOU!!

ወደ ሮሜ ሰዎች 10፥11 ... በእርሱ የሚያምን ሁሉ አያፍርም ይላልና፡፡

ይህ መልካም ወጣት 2010 ነው!!መልካም ወጣት!!ለ ሀገሩለ ቤተክርስቲያንለ ቤተሰቡ!!መልካም ወጣት 2010 አንደኛ ዙር  ስልጠና እና ቦርፎሪኮን መጽሐፍ
23/07/2018

ይህ መልካም ወጣት 2010 ነው!!
መልካም ወጣት!!
ለ ሀገሩ
ለ ቤተክርስቲያን
ለ ቤተሰቡ!!
መልካም ወጣት 2010 አንደኛ ዙር ስልጠና እና ቦርፎሪኮን መጽሐፍ

11/07/2018
11/07/2018
https://www.facebook.com/permalink.php?story_fbid=2036665839905279&id=1602823613289506
05/06/2018

https://www.facebook.com/permalink.php?story_fbid=2036665839905279&id=1602823613289506

ለመልካም ወጣት ተመዝጋቢዎች በሙሉ
ይህንን ድህረገፅ (http://www.melkamwetat.com/) በመጫን በድህረገፁላይ ያሉትን ሁሉንም ጥያቄዎች በአግባቡ በመመለስና ይመዝገብ የሚለውን በተን በመጫን ይመዝገብ::
በተመዘገብ ጊዜ ወዲያው በተመዘገብበት ስልክ ቁጥር በሚደርሶት መልእክት ወይም ከዚህ በታች በሚያገኙት የባንክ ቁጥር የሚያስፈልገውን ገንዘብ ያስገብ::

http://www.melkamwetat.com/

Address

Hawassa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mar-sil DAILY Devotion ማር-ሲል posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share