14/12/2025
የሰው ሶስትነት
ሰው በእግዚአብሔር የባሕርይ ምሳሌ ተፈጥሯል (ዘፍ1-:-26-27፣ ያዕ3-:-9)፡፡ ለዚህም ማስረጃ ከሚሆኑት መካከል ጥቂቶቹ፡-
ሦስትነቱ (ሥጋ፣ ነፍስና መንፈስ) 1ተሰ5-:-23፣ ዕብ4-:-12
ዘላለማዊነቱ (ከሞት በኋላ ትንሳኤ ያለው መሆኑና ከተፈጠረበት ቀን ጀምሮ የማይጠፋ መሆኑ (ሉቃ23-:-39-43)
የመግዛት ባሕሪው (ዘፍ1-:-28)
የመስራት ችሎታው (ዘፍ2-:-15)
የማስተዋል ችሎታው (ኢዮ32-:-8)
ሰውን ከሌሎች ፍጥረቶች ልዩ ከሚያደርጉ ባሕሪያት አንዱና ዋናው በግዙፍ አካል ውስጥ የእግዚአብሔር እስትንፋስ መቀመጡ ነው(ሥጋ፣ ነፍስና መንፈስ አለውና)1ተሰ5-:-23፡፡
የሰውን ሦስትነት መጽሀፍ ቅዱስ ሥጋ፣ ነፍስና፣ መንፈስ በማለት በሚገባ ያብራራል:: (1ተሰ5-:-23፣ ዕብ4-:-12)፡፡ የሰው ሦስትነት በተናጠል ሲታይም፡-
ሥጋ
ሥጋ በአይን የሚታይና በእጅ ሊዳሰስ የሚችለው የሰው አካል ሲሆን (ሉቃ24-:-36-40) ለማይታዩት ለነፍስና መንፈስ ማደሪያ ነው:: (ማቴ10-:-28፣ ኢዮ19-:-26)፡፡ ከግዙፍ አለም ወይም ፍጥረት ጋር የሚያገናኙትንም አምስቱን የስሜት ሕዋሳት ይዟል:: ሟችና በስባሽም ነው (1ቆሮ15-:-20፣ 1ጴጥ1-:-24፣ ዘፍ3-:-19)፡፡
ስጋችን እንደምርጫችን ለእግዚአብሔር መንፈስ ወይንም ለሰይጣን መንፈስ ማደሪያ ነው:: (ኤፌ1-:-13፣ 1ቆሮ6-:-19፣ 1ዮሐ4-:-13፣ ማር5-:-1-5፣9-:-17-25፣ ሉቃ8-:-27-33፣ ዘፍ3-:-6)፡፡
በአማርኛ ሥጋ የሚለው አንድ ቃል በግሪክ ቋንቋ አራት ትርጉሞች አሉት:: እነሱም:-
ሶማ - በአይናችን የምናየው ሥጋና አጥንት ነው:: (1ተሰ5-:-23)
ሰርኮስ - ለእግዚአብሔር የማይታዘዘው የሰው የማመጽ ባሕርይ (ከአዳም የተወረሰውና የተበላሸው ተፈጥሮአዊ ማንነት) ነው:: (ሮሜ8-:-3-8፣7-:-24)
ቶ ሶማቶስ ሐማርቲያ - የሰርኮስና የሶማ የመተባበር ውጤት የሆነው የተግባር ኃጢአት መገለጫ በመሆን ለእግዚአብሔር የማይጠቅምና የተበላሸ ማንነት ነው::
ሶማቶስ - እግዚአብሔር የሚፈልገውና የተቀደሰው ማንነት ወይም ከክርስቶስ የተቀበልነው ስጋ ማለት ነው::
ስለዚህ መጽሀፍ ቅዱስ ስጋ እርኩስ ነው የሚለው ከአዳም የወረስነውን አለመታዘዝ ባሕርይን (ሰርኮስን) እንጂ በአይናችን የምናየውን ስጋና አጥንትን (ሶማን) አይደለም::
ስለዚህ ጌታ ኢየሱስ ሶማችንን ወስዶ ከውስጡ የአዳምን አለመታዘዝ ባሕርይ (ሶርኮስን) አስወግዶ ነው ሶማቶስ አድርጎ የለወጠው:: በመሆኑም ስጋችን የክርስቶስ ስጋ (ሶማቶስ) ስለሆነ በእግዚአብሔር ዘንድ የከበረ ስጋ ነው::
በቅድስት ማርያም በኩል ሲወለድ ጌታ ኢየሱስ ለብሶት የተገለጠው ስጋ የእኛን ስጋ (ሶማን) ነው፡፡ የአዳምን ዘር ባለመያዙም ሰርኮስ በሕይወቱ አልሰራም (ዘፍ3-:-8-13፣ ዕብ4-:-14-18)፡፡ እኛን ተክቶ በመስቀል ሲሞት ሶማችንን ከወሰደ በኋላም ሰርኮስ እንዳይሰራ ገደለው፤ እንደገና በትንሳኤ ደግሞ ሲነሳ ሶማቶስ በኛ እንዲሰራ በማድረግ ስጋችንን የተቀደሰና የከበረ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ አደረገው:: (ዮሐ14-:-15-17,1ቆሮ6-:-19) ስሙ ለዘለአለም ይክበር፡፡
ነፍስ
እግዚአብሔር የሕይወትን እስትንፋስ በሰው እፍ ባለበት ጊዜ የተፈጠረው የሰው አካል ክፍል ነው (ዘፍ2-:-7)፡፡
በሰው ስጋ ውስጥ የእግዚአብሔር እስትንፋስ ሲቀመጥ ሰው ሕያው ይሆናል:: እስትንፋሱ ሲለይ ደግሞ ይሞታል:: (ዘፍ2-:-7፣ ያዕ2-:-26፣ 1ነገ17-:-20-22፣ መዝ104-:-29፣ ኢዮ34-:-14-15)፡፡ ነፍስ ከሰው ስጋ ቢለይም የማይጠፋና ዘላለማዊ ነው (ማቴ10-:-28)፡፡ የሰ