15/09/2025
ግድያው ዘመን ተሻግሯል
በአማራ ክልል በደቡብ ጎንደር ዞን ዛሬ በ 5/1/2018 ከማህደረ ማሪያም ደብረ ታቦር መንገድ ከማህደረ ማሪያም ወጣ ብሎ ህዝብ የጫነ አባዱላ ሚናባስ ላይ ወደ ህዝብ ተኩስ በመክፈት በምታዩት መልኩ መኪናውን በመምታት ሹፌሩን ደረቱን በጥይት መተው ገድለውታል። አሁን ደብረታቦር ሆስፒታል አስከሬኑ ይገኛል።
በአረመኔነት ሹፌርን የሚያግቱ የሚዘርፉ የሚገድሉ አካላት ሽፋን እየተሰጣቸው ለእኩይ ድርጊታቸው ተከላካይ ያላቸው ዘራፊወች ወደ ህዝብ መኪና ጥይት መተኮስ ጀምረዋል።
በየመንገዱ ሹፌር የሚዘርፉ የሚያግቱ ነፍስ የሚያጠፉ አካላት ሊወገዙ ይህንን ድርጊታቸውን ለማስቆም ለህግ እንዲቀርቡ ለማድረግ ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ ይገባል።
በሹፌር ላይ የሚደረገው ግድያ የግል ሀብት ለማፍራት ሰወች የለፉበትን ነጥቆ ለመብላት አላማ ያደረገ የአረመኔነት የሽፍትነት ተግባር ነው።
ፍትህ በግፍ ለሚገደሉ
ነፍስ ይማርልን