23/08/2026
እሁድ ነሐሴ 17/2018 ዓ.ም
የሉቃስ ወንጌል 7:11-16
••••••••••
¹¹ በነገውም ናይን ወደምትባል ወደ አንዲት ከተማ ሄደ፥ ደቀ መዛሙርቱም ብዙ ሕዝብም ከእርሱ ጋር አብረው ሄዱ።
¹² ወደ ከተማይቱም በር በቀረበ ጊዜ፥ እነሆ፥ የሞተ ሰው ተሸክመው አወጡ፤ እርሱም ለእናቱ አንድ ልጅ ነበረ፥ እርስዋም መበለት ነበረች፥ ብዙም የከተማ ሕዝብ ከእርስዋ ጋር አብረው ነበሩ።
¹³ ጌታም ባያት ጊዜ አዘነላትና። አታልቅሽ አላት።
¹⁴ ቀርቦም ቃሬዛውን ነካ፥ የተሸከሙትም ቆሙ፤ አለውም። አንተ ጐበዝ፥ እልሃለሁ፥ ተነሣ።
¹⁵ የሞተውም ቀና ብሎ ተቀመጠ ሊናገርም ጀመረ፥ ለእናቱም ሰጣት።
¹⁶ ሁሉንም ፍርሃት ያዛቸውና። ታላቅ ነቢይ በእኛ መካከል ተነሥቶአል፥ ደግሞ። እግዚአብሔር ሕዝቡን ጐበኘ እያሉ እግዚአብሔርን አመሰገኑ።
—ወልድ_ያለው_ሕይወት_አለው—
GIMBICHU_KETEMA_KALE_HIWOT_CHURCH
📌ሌሎች የማህበራዊ ሚድያ ገፃችን
የቴሌግራም ገፅ:-
https://t.me/Kalehiwot11
የቲክቶክ ገፅ:-
https://www.tiktok.com/