30/08/2026
የዲማ ቤቴል ፕሪስቤቴሪ አዲስ አመራሮችን መረጠ
# # # # # # # # # # # # # # # # # # # # #
የዲማ ቤቴል ፕሪስቤቴሪ ነሐሴ 22ቀን 2018 ዓ.ም.፣ ዓርብ ዕለት ልዩ ጉባኤ እና ልዪ የካውንስል ስብሰባ አካሂዷል። በዚህ መሠረት ለሚቀጥሉት አራት ዓመታት ፕሪስቤቴሪውን ለማገልገል አዲስ አመራሮችና የመምሪያ አስተባባሪዎች ተመርጠዋል።
ከምርጫው በኋላ አዲስ የተመረጡት አመራሮችና አስተባባሪዎች በሲኖዶሱ ፕረዚዳንት ቄስ ኝጎዎ ኡሞድ እና በሲኖዶሱ ወ.ተ.ቲ. መምሪያ ዳይሬክተር ቄስ አፓይ ኡጁሉ በይፋ የምደባ ሥነ ሥርዓት ተፈፅሟል።
በዚህ መሠረት የተመረጡት አመራሮች፦
ወ/ዊ ጆን ኡቾጊ — ስብሳቢ
መ/ር ፖኦጅዎክ ኡቲየፕ— ምክትል ሰብሳቢ
ወ/ሮ ቻም ኡጆሆ— ዓቃቤ-ንዋይ
ወ/ም ጀቢኮ ኡሞድ — ጸሐፊ
ወ/ም ኡቶው ኡጁሉ— የወንጌል አስተባባሪ
ወ/ም ኡጁሉ ኡሉል — የወጣቶች አስተባባሪ
ወ/ሮ ሀና ኡቶው — የልማት አስተባባሪ
ወ/ሮ ኡኮኝ ኡሞድ — የሴቶች አስተባባሪ
አዲስ ለተመረጡት አመራሮችና የመምሪያ አስተባባሪዎች ሁሉ ልባዊ የደስታ እና የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታችንን እናቀርባለን።
ኃላፊነታቸውን በመረከብ ቤተክርስቲያንንና መላውን ማኅበረሰብ በታማኝነት ሲያገለግሉ፣ እግዚአብሔር ጥበብን፣ ብርታትን፣ አንድነትን፣ ትሕትናን እና ታማኝነትን እንዲሰጣቸው እንጸልያለን።
እግዚአብሔር የዲማ ቤቴል ፕሪስቤቴሪን ይባርክ፣ አዲሱን አመራር ያበርታ እና በሚቀጥሉት አራት ዓመታት የአገልግሎት ጉዞአቸውን ይምራ።
ለአዲስ ለተመረጣችሁ አመራሮች እንኳን ደስ አላችሁ!
እግዚአብሔር በአገልግሎታችሁ ይምራችሁ፣ ይባርካችሁም!
Dimma Bethel Presbytery Elects New Leaders
# # # # # # # # # # # # # # # # # # # # #
Dimma Bethel Presbytery held an Extraordinary Assembly on Friday, 28 August 2026, followed by a council meeting during which new leaders and departmental coordinators were elected to serve the presbytery for the coming four years.
Following the election, the newly elected leaders and coordinators were officially installed by Rev. Gnigwo Omod, President of EGBS, and Rev. Apay Ojulu, EGBS DMT Director.
The following leaders were elected:
Ev. John Ochogi — Chairperson
Pwojwøk Othiep — Deputy Chairperson
Mrs. Cham Ojho — Treasurer
Jibiko Omod — Secretary
Othow Ojulu — Evangelism Coordinator
Ojulu Olul — Youth Coordinator
Anna Othow — Development Coordinator
Okony Omod — Women’s Department Coordinator
We warmly congratulate all the newly elected leaders and departmental coordinators. We pray that God will grant them wisdom, strength, unity, humility, and commitment as they take up their responsibilities and faithfully serve the church and the wider community.
May God bless Dimma Bethel Presbytery, strengthen its new leadership, and guide them throughout the coming four years of ministry and service.
Congratulations to the newly elected leadership! May God lead and bless your service.