Besu mezmur

Besu mezmur Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Besu mezmur, Eastern Orthodox church, https://youtube. com/-of1kf3nw5h?si=537Msv1dut03-RNi, Debre Zeyit.

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ።«ጥብዒኬ እም ወኢትናፍቂ  ንፈጽም ገድለነ ወስምዓነ»‟እናቴ ሆይ! ገድላችን እንፈጽም ዘንድ ጨክኝ በርቺ አትጠራጠሪ  አናንያን፣ አዛርያንና ሚ...
25/07/2025

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ።

«ጥብዒኬ እም ወኢትናፍቂ ንፈጽም ገድለነ ወስምዓነ»
‟እናቴ ሆይ! ገድላችን እንፈጽም ዘንድ ጨክኝ በርቺ አትጠራጠሪ አናንያን፣ አዛርያንና ሚሳኤልን ያዳነ አምላክ ያድነናል”
(ቅዱስ ያሬድ)

እንኳን ለታላቁ መልአክ ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን !!

በዛሬው ዕለት የቅዱስ ገብርኤልና የቅዱስ ቂርቆስ የቅድስት ኢየሉጣ አመታዊ ክብረ በዓል ነው።
በዚህ ቀን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ቅድስት እየሉጣንና ልጇን ቅዱስ ቂርቆስን ከሥጋ መከራ እንደታደጋቸው ከፈላ የብረት ጋን እንዳወጣቸው ታሪክ ይናገራል።

➾ በዘመነ ሰማእታት ከሐድያን ነገሥታትና አላውያን መኳንንት በክርስቲያኖች ላይ መከራ አጽንተውባቸው ነበር። በዚህም ምክንያት ብዙዎች ሰማእትነትን ሲቀበሉ የተቀሩት ሀገር ጥለው ተሰደዱ።
➾ እየሉጣም የሦስት ዓመት ህፃን ልጇን ቅዱስ ቂርቆስን ይዛ ሸሸች በዚያም በሸሸችበት ሀገር የሸሸችውን መኮንን አገኘችው ሰዎችም ነገር ሰሩባት ወደእርሱም አስቀረባት እና ስለ አምልኮ ጣዖት ጠየቃት እርሷም መኮንን ሆይ ዕድሜው ሦስት አመት የሆነው ህፃን አለ አማልክቶችህን ማምለክ መልካም እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ ያስረዳን ዘንድ እሱን ጠይቅ አለችው።
➾ ከዚህ በኋላ ሕፃኑን አስመጥቶ ቢጠይቀው ነቢዩ ዳዊት የተናገረውን ኃይለ ቃል መንፈስ ቅዱስ ገልጾለት፤
‹‹የአሕዛብ ጣዖታት የወርቅና የብር የሰው እጅ ሥራዎች ናቸው አይን አላቸው ግን አያዩም ጆሮ አላቸው ግን አይሰሙም ………የሚታመኑባቸውም ሁሉ እንደ እነርሱ ይሁኑ››
መዝ. ፻፴፬ ÷ ፲፭ (134 ÷ 15)

በማለት ሲዘልፏቸው ሰምቶ ተቆጣና የብረት ጋን አስመጥቶ ውኃ አስሞልቶ ከዕቶን እሳት ላይ አስጥዶ ልዩ ልዩ ማገዶዎች ፣ ጨው፣ ባሩድ፣ ሙጫ ፣ ሰም፣ የዶሮ ማር፣ እርሳስ፣ ብረት፣ ቅንጭብ፣ ቁልቋል ጨምራችሁ አንድዱትና አፍሉት ብሎ ጭፍሮቹን አዘዛቸው።

«ድምጻ ለጽሕርት ከመ ነጎድጓደ ክረምት» ይላል

ነበልባሉ ከመጠን በላይ ሆነ። ድምፁም እንደ ክረምት መብረቅና ነጎድጓድ እስኪያስፈራ ድረስ አስነድዶ ሕፃኑን እና እናቱን ወስዳችሁ ጨምሩአቸው ብሎ አዘዘ።
በዚህ ጊዜ ቅድስት ኢየሉጣ ከድምጹ የተነሳ በጣም ፈራች።
የእግዚአብሔር ኃይልና መንፈስ ግን በሕፃኑ ላይ ስለነበረ ድንቅ ግሩም ረቂቅ በሆነ ተአምር ገና አፉን ያልፈታ የሦስት ዓመት ሕፃን።
«ጥብዒኬ እም ወኢትናፍቂ ንፈጽም ገድለነ ወስምዓነ»
‟እናቴ ሆይ! ገድላችን እንፈጽም ዘንድ ጨክኝ በርቺ አትጠራጠሪ አናንያን፣ አዛርያንና ሚሳኤልን ያዳነ አምላክ ያድነናል ”

እያለ ቢያበረታታትም እናቱ ቅድስት ኢየሉጣ ግን ፍርሃቱ ሊለቃት ባለመቻሉ፣ ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ጸለየ፡፡
‹‹ጌታ ሆይ! የወይኑን ፍሬ ስትሻ ግንዱን ታጠፋለህን? እንደዚህስ ሁሉ እኔን አድነህ እናቴን ታጠፋታለህን?››

ብሎ በጸለየ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ አደረባትና መንግሥተ ሰማያትን በዓይነ ሥጋ እንድታይ አደረጋት።

ከዚህ በኋላ ፍርሃቱ ለቀቃትና ‹‹ልጄ ሆይ! ከዛሬ ጀምሮ መምህሬ፣ አባቴ፣ መካሪዬ እልሃለሁ እንጂ ልጄ አልልህም›› ብላ በጭካኔ ከልጅዋ ጋር ወደ ፈላው የብረት ጋን ገባች።
➾ በዚህ ጊዜ ሕፃኑ ቂርቆስ አናንያን፣ አዛርያንና ሚሳኤልን ያዳነ አምላክ ያድነናል እንዳለው ለወዳጆቹ ቅርብ የሆነና በመከራቸው የሚደርስ ጸሎታቸውን የሚሰማ ከመከራ የሚያድናቸው እግዚአብሔር አምላክ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው።
➾ መልአኩም በትእምርተ መስቀል እሳቱን ቢባርከው እንደ በረዶ ቀዘቀዘላቸው። መልካቸውም እንደ ፀሐይ አበራ።
የለበሱት ልብስ ስንኳን ምንም ሳይሆን አንድም ሳይጎዳቸው በደህና

የስሙ ትርጓሜ ‹አክሊል› የሆነው በሕገ ወንጌል የመጀመሪያ ሊቀ ዲያቆናትና ቀዳማዊ ሰማዕት የተባለ ቅዱስ እስጢፋኖስ ‹‹ሊቀ ዲያቆናት›› ከመባሉ በፊትም በመጀመሪያ ሐዋርያና ካህን ነበር፤ ከዚ...
23/07/2025

የስሙ ትርጓሜ ‹አክሊል› የሆነው በሕገ ወንጌል የመጀመሪያ ሊቀ ዲያቆናትና ቀዳማዊ ሰማዕት የተባለ ቅዱስ እስጢፋኖስ ‹‹ሊቀ ዲያቆናት›› ከመባሉ በፊትም በመጀመሪያ ሐዋርያና ካህን ነበር፤ ከዚያም ዲያቆን ሆኖ ተሾሟል፤ ይህም ጥቅምት ፲፯ ቀን ነው፡፡

በሐዋርያት ሥራ ላይ እንደተጠቀሰው ይህ ቅዱስ በመጀመሪያ ገማልያል በተባለ መምህር ትውፊትን፣ ኦሪትንና ነቢያቱን ተምሯል፡፡ በጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መዋዕለ ስብከት ወቅትም እርሱ በዋለበት እየዋለ ባደረበት እያደረ ወንጌልን ተማረ፤ ደቀ መዝሙሩም ሆነ፤ ጌታችንም ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ አደረገው፤ አጋንንትም ተገዙለት፡፡ (የሐዋ.፭፥፴፬፣፮፥፭-፲)

በበዓለ ሃምሳም መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ ከሰባ ሁለቱ አርድእት መካከል የእርሱን ያህል ልሳን የበዛለት ምሥጢርም የተገለጠለት አልነበረም፡፡ በመንፈስ ቅዱስ መሪነትም ወንግልን ሰብኳል፡፡ በቤተ ክርስቲያንም ፈተና ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ሰባት ዲያቆናት ሲመርጡ አንዱ እርሱ ነበር፡፡ የስድስቱ ዲያቆናት አለቃና የስምንት ሺህ ማኅበር መሪ ሆኗል፡፡ ከዚህም በኋላ ቅዱስ እስጢፋኖስ ከጌታ ዕርገት በኋላ ለአንድ ዓመት ያህል ስምንት ሺህውን ማኅበረ እየመራ ወንጌልን እየሰበከ ቢጋደል ኦሪት እየጠፋች ወንጌል ደግሞ እየሰፋች ሄደች፡፡ (የሐዋ.፮፥፬)

ቅዱስ እስጢፋኖስም የእግዚአብሔር ጸጋና ኃይል ያደረበትና ታላቅ እንዲሁም ድንቅ ታምራትን የሚያደርግ ሰው ስለነበር በዚያን ጊዜ አይሁድ በምቀኝነት ተነሡበት፤ ከእርሱ ጋርም ክርክር ገጠሙ፤ ነገር ግን ሊያሸንፉት አልቻሉም፤ የእግዚአብሔር መንፈስ አድሮበታልና በፈጣሪ ኃይል አሸነፋቸው፡፡

ከዚህም በኋላ በሐሰት ምስክር ‹‹ይህን ሰው በሙሴና በእግዚአብሔር ላይ የስድብን ቃል ሲናገር ሰምተነዋል›› በማለት ወነጀሉት፤ እርሱ ግን ስለ እውነት መሰከረ እንጂ በጀ አላላቸውም፤ ሊቀ ካህናቱም በጠየቁት ጊዜ ስለ እግዚአብሔር አምላኩ መሰከረ፤ በመጨረሻም እንዲህ አላቸው፤ ‹‹እናንተ አንገታችሁ የደነደነ፥ ልባችሁም የተደፈነ፥ ጆሮአችሁም የደነቈረ፥ እንደ አባቶቻችሁ መንፈስ ቅዱስን ዘወትር ትቃወማላችሁ፡፡ አባቶቻችሁ ከነቢያት ያሳደዱት ማን አለ? ዛሬም እናንተ አሳልፋችሁ የሰጣችሁትንና የገደላችሁትን የጻድቁን መምጣት አስቀድመው የተናገሩትን ገደሉአቸው፡፡ በመላእክትም ሥርዐት ኦሪትን ተቀብላችሁ አልጠበቃችሁም፡፡›› በዚህም ተበሳጭተው በድንጋይ ወግረው ገደሉት፡፡ በዚህም ምስክሩን ፈጽሞ የሰማዕታት አክሊልን በጥር ፩ ቀን ተቀዳጅቷል፤ በዚህም ቀዳሜ ሰማዕታት ይባላል፡፡(የሐዋ. ፯፥፶፩-፶፫)

አይሁድ ቅዱስ እስጢፋኖስን ለማጥፋት ቀንተው ሲገድሉት ጠላት ዲያብሎስ ደግሞ ክርስትናን ለማጥፋት እነርሱን ሰበብ አድርጎ ለሞቱም ተጠያቂ እንዲሆኑ አድርጎአቸዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜም ክርስትናን ለማጥፋት ጠላት በሰዎች ላይ እያደረ ክርስቲያኖችን ያስገድላል፤ ያስጨፈጭፋል፤ እንዲሁም ያሳድዳል፡፡ በየጊዜውም በተለያዩ ክፍለ ሀገራት በጅምላ የሚጨፈጨፉት ሕፃናት፣ አረጋዊያን እንዲሁም ወጣቶች ምንም በማያውቁት ምክንያት፣ በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው በመናገራቸው ሳቢያ፣ ቤተ ክርስቲያን ሄደው በዓላትን በማክበራቸውና ባህላቸውን ለማስጠበቅ በመፈለጋው ብቻ ነው፡፡ እነዚህ እርኩስ መንፈስ ያደረባቸው ሰዎች የጠላት ተገዢ ከመሆናቸው ባሻገር ለራሳቸውና ለሌሎች ጥፋት መንሥኤ በመሆናቸው እንደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ሐሰተኞችን በመቃወም ለእውነት መመስከር ይገባናል፡፡ ለዚህም በሃይማኖት ጸንቶ መኖር ይጠበቃልና እንጽና!

የቅዱስ እስጢፋኖስ አማላጅነትና ተረዳኢነት አይለየን፤ አሜን፡፡

Address

Https://youtube. Com/@user-of1kf3nw5h?si=537Msv1dut03-RNi
Debre Zeyit

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Besu mezmur posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share