Remnant Youth & Kids Holistic Nonprofit Corporation

Remnant Youth & Kids Holistic Nonprofit Corporation VISION:-To save a generation from the destruction and bondage of this evil world

28/12/2025
04/12/2025
You can Get at “Amazon” three books.    Let's save the generation by buying the book .     BRIDGING GENERATIONAL    PART...
19/06/2025

You can Get at “Amazon” three books.
Let's save the generation by buying the book .
BRIDGING GENERATIONAL
PART I- Understanding Generation
PART II- Cause of Generational Gap
PART III- Bridging & Solution
BY “Author” Askale Asfaw Weldearegay (PhD)

***ክፍል 29***“የእግዚአብሔር ጥበብ ለወጣቶችና ለልጆች”(ምሳሌ 4፡1-27) †  ወደ መልካም መንገድ የሚመራን ልክ እንደ እግዚአብሔር ውድ ካርታ ነው። †  ጥበብን ከተከተልን ደስታን፣ ...
01/06/2025

***ክፍል 29***
“የእግዚአብሔር ጥበብ ለወጣቶችና ለልጆች”
(ምሳሌ 4፡1-27)
† ወደ መልካም መንገድ የሚመራን ልክ እንደ እግዚአብሔር ውድ ካርታ ነው።
† ጥበብን ከተከተልን ደስታን፣ ሰላምን እና ዓላማን እናገኛለን።
† ዓለም ግራ በሚያጋባበት ጊዜ እንኳን የእግዚአብሔር እውነት መንገዱን ያሳየናል፣ ይመራናል።
1. ከሚወዷችሁ ተማሩ
“እናንተ ልጆች፥ የአባትን ተግሣጽ ስሙ፥ ማስተዋልንም ታውቁ ዘንድ አድምጡ፤” (ምሳሌ 4፡1)
† ልጆቼ ሆይ የአባትን ምክር ስሙ
† ወላጆችህ፣ አስተማሪዎችህ እና መሪዎችህ ከስህተት እንድትርቁ ሊረዱ ይፈልጋሉና ተማሩ።
† በጆሮ ብቻ ሳይሆን ከልብ አዳምጡ። እናንተን ለመርዳት እየሞከሩ ነውና ተማሩ!
2. ጥበብ ከወርቅ ትበልጣለች
“ጥበብ ዓይነተኛ ነገር ናትና ጥበብን አግኝ፤ ከሀብትህም ሁሉ ማስተዋልን አትርፍ።” (ምሳሌ 4፡7)
† ማስተዋልና ጥበብን በብርቱ ፈልጉ
† ብልህ መሆን፥ ሀብታም ከመሆን ይበልጣል፣
† አዋቂ መሆን፥ ታዋቂ ከመሆን ይበልጣል።
3. ከመጥፎ ጎዳና ራቁ
“በኃጥኣን መንገድ አትግባ፥ በክፉ ሰዎችም ጎዳና አትሂድ። ከእርስዋ ራቅ፥ አትሂድባትም፤ ፈቀቅ በል ተዋትም።” (ምሳሌ 4፡14-15)
† የክፉ ሰዎችን መንገድ አትከተሉ።
† አንዳንድ ነገሮች አስደሳች ቢመስሉም ወደ ችግር ያመራሉና ተጠንቀቁ።
† ከሐሜት፣ ከውሸት፣ ከጠብ ወይም ከማንኛውም ነገር ከእግዚአብሔር ከሚያርቁ ነገሮች ራቁ።
4. መልካምና ትክክለኛውን ማድረግን ቀጥሉ።
“የጻድቃን መንገድ ግን እንደ ንጋት ብርሃን ነው፥ ሙሉ ቀን እስኪሆንም ድረስ እየተጨመረ ይበራል።” (ምሳሌ 4፡18)
† የደግ ሰዎች መንገድ እንደ ንጋት ፀሀይ ነው፤ ወደ ትክክለኛ መንገድ ይመራል።
† መልካም ሥራ እየበራ እና እያደገ ይሄዳል።
† ከእግዚአብሔር ጋር ስትኖሩ ነገሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተዋቡ ይሄዳሉ።
† ደግነትን፣ እውነትን፣ እና ፍቅርን ማሳየቱን ቀጥሉ።
5. ልብህን ጠብቅ
“አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ፥ የሕይወት መውጫ ከእርሱ ነውና።” (ምሳሌ 4፡23)
† ከሁሉ በላይ ልብባችሁን ጠብቁ፤ የምታደርጉት ነገር ሁሉ ወደ መልካም ይመራችኋል።
† ወደ ልባችሁ የገባው መልካም ያልሆኑ ነገሮች፥በህይወታችሁ ላይ ተጽእኖ ያሳድራሉና ተጠንቀቁ።
† ራሳችሁን እንዲህ ብላችሁ ጠይቁ??? ወዴት ነኝ?? ከማንና ከምን ጋር ነኝ???
† ልቤ የእግዚአብሔርን መንገድ እየጠበቀ ነው???
6. የምትሄዱበትን መንገድ ተመልከቱ
“የእግርህን መንገድ አቅና፥ አካሄድህም ሁሉ ይጽና። ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል፤ እግርህንም ከክፉ መልስ።” (ምሳሌ 4፡26-27)
† በመልካም መንገድ ላይ ቆዩ።
† ከክፉ መንገድ ተመለሱ።
† ትኩረትን ከሚከፋፍሉ ነገሮች ራቁ።
† ከመልካም መንገድ ሊያወጣችሁ ካለው ተጠበቁ።
† ሌሎችንና ራሳችሁን ለመርዳት ወደ መልካም ግቦች ተመልከቱ።

24/05/2025

***ክፍል 28***
በልጆችና በወላጆች መካከል ያለውን የትውልድ ልዩነት እንዴት ማቃለል ይቻላል?
1. በመግባባትና በመተሳሰብ፡- በወላጆችና በልጆች መካከል ግልጽ እና ታማኝ የሆነ ግንኙነት እንዲኖር ማበረታታት። አንዳችሁ የሌላውን አመለካከት ሳይነቅፉ በአክብሮት ያዳምጡ።
2. ልዩነቶችን በማስወገድ፡- እያንዳንዱ ትውልድ የተለያየ እሴት፣ እምነት እና ልምድ እንዳለው መቀበል። እነዚህን ልዩነቶች ለመረዳት እና ለማክበር ይሞክሩና መፍትሔ መሆን
3. አብራችሁ ጊዜ አሳልፉ፡- የሚወዷቸውን ነገሮች በማድረግ ጥሩ ጊዜ ለማሳለፍ ይሞክሩ። የበለጠ ጠንካራ ግንኙነት እና ግንዛቤ ለመፍጠር ይረዳል።
4. ተሞክሮዎችን ያካፍሉ፡- ልምዶቻችሁን አካፍሉ እና ከልጅዎ ተሞክሮዎች ጋር ያዛምዷቸው። ክፍተቱን ለማጥበብ እና የጋራ ግንዛቤን ለመፍጠር ይረዳል።

17/05/2025

*** ክፍል 27***
"የወንድማማችነት ፍቅር በተግባር"
በወንድማማች መዋደድ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ፤ እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ፤ (ሮሜ 12:10)
ልጆችን ደግነትን፣ ክብርንና ወንድማማችነትን በስሜት ብቻ ሳይሆን በእውነተኛ ተግባራት ላይ የተመሰረተ መዋደድና መከባበርን እንዲረዱና እንዲለማመዱ መርዳት።
1.“በደግነት መዋደድ” ሲባል ምን ማለት ነው?
† በቅርብ ቤተሰብ ውስጥ እንዳለ ፍቅር ለሌሎች ጥልቅ፣ ልባዊ ፍቅርና እንክብካቤ መስጠት
† ያዘኑትን ማጽናናት
† ከሌሎች ምንም ነገር ሳንጠብቅ ሌሎችን መርዳት
† በግጭት ጊዜ ትዕግስትና ጸጋን ማሳየት
2. በእውነተኛ ህይወት ውስጥ "የወንድማማችነት ፍቅር" ምን ይመስላል?
† በእውነተኛ ህይወት ውስጥ ሌሎችን እንደ ቅርብ ወንድምና እህት ወይም የቅርብ ጓደኛ በምትሰጡት የመውደድ አይነት መውደድ፣ አክብሮት እና ታማኝነት መስጠት።
† ሌሎችን የሚያስቀድም ፣ ከራስ ወዳድነት ነፃ የሆነ ፍቅር። በስሜት ብቻ ሳይሆን፣ በመልካም ቃላት፣ አጋዥ ድርጊቶች እና ተከታታይ ድጋፍ መስጠት።
“የወንድማማች መዋደድ ይኑር። እንግዶችን መቀበል አትርሱ፤ በዚህ አንዳንዶች ሳያውቁ መላእክትን እንግድነት ተቀብለዋልና። (ዕብራውያን 13፡1-2)
3. ራሳችንን ላይ ብቻ እንድናተኩር በሚያበረታታ ዓለም ውስጥ ‘ሌሎችን ልንወድ’ የምንችለው እንዴት ነው?
† “ሌሎችን መውደድ” ስሜታቸውን እና ፍላጎታቸውን ከራሳችን በፊት ማስቀደም ።
† “ራስህን አስቀድም” በምትል ዓለም ውስጥ፣እውነተኛ ፍቅር እና ክብርን ማሳየት፣
“በወንድማማች መዋደድ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ፤ እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ፤” (ሮሜ 12:10)

11/05/2025

እጅ ለእጃችን ተያይዘን

04/05/2025

Remnant Youth & Kids Holistic
***ክፍል 26***
የልጆች የመታዘዝ ውጤት
መጽሐፍ ቅዱሳዊ እና ተግባራዊ ጥቅሞች
1. መጽሐፍ ቅዱሳዊ የመታዘዝ ውጤቶች
• የእግዚአብሔር በረከትና ሞገስ፡
“ልጆች ሆይ፥ ለወላጆቻችሁ በጌታ ታዘዙ፥ ይህ የሚገባ ነውና። መልካም እንዲሆንልህ ዕድሜህም በምድር ላይ እንዲረዝም አባትህንና እናትህን አክብር፤ እርስዋም የተስፋ ቃል ያላት ፊተኛይቱ ትእዛዝ ናት። (ኤፌሶን 6:2–3)
• እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት፡ “ልጆች ሆይ፥ ይህ ለጌታ ደስ የሚያሰኝ ነውና በሁሉ ለወላጆቻችሁ ታዘዙ።”
(ቆላስይስ 3:20)
• መንፈሳዊ እድገት እና ጥበቃ፡ የሚታዘዙ ልጆች የእግዚአብሔርን መመሪያ እንዲከተሉና በእሱ ጥበቃ ስር እንዲቆዩ ይመራቸዋል።
2.ተግባራዊ የመታዘዝ ውጤቶች
• አክብሮት እና መተማመን፡- አዋቂዎች ታዛዥ ለሆኑ በበለጠ ኃላፊነት ለመስጠት ያምናሉ።
• ደህንነት እና መመሪያ፡ መመሪያዎችን ማክበር ከአደጋና ጉዳትን ለማስወገድ ይረዳል።
• ጠንካራ ግንኙነት፡ ታዛዥ ልጆች ከወላጆች እና ከሌሎች ጋር የተሻለ ግንኙነት ይፈጥራሉ።
• ራስን መግዛት እና ስኬት፡ ወደ ጥሩ ልምዶች፣ የትምህርት ስኬት እና የግል እድገት ይመራል።

REMNANT YOUTH & KIDS HOLISTIC***ክፍል 25***ለወላጆች እና ለእግዚአብሔር መታዘዝ ብዙ በረከቶችን ያመጣል፡-1. ረጅም እድሜ እና ጤና “ልጆች ሆይ፥ ለወላጆቻችሁ በጌታ ታዘ...
19/04/2025

REMNANT YOUTH & KIDS HOLISTIC
***ክፍል 25***
ለወላጆች እና ለእግዚአብሔር መታዘዝ ብዙ በረከቶችን ያመጣል፡-
1. ረጅም እድሜ እና ጤና
“ልጆች ሆይ፥ ለወላጆቻችሁ በጌታ ታዘዙ፥ ይህ የሚገባ ነውና።መልካም እንዲሆንልህ ዕድሜህም በምድር ላይ እንዲረዝም አባትህንና እናትህን አክብር፤ እርስዋም የተስፋ ቃል ያላት ፊተኛይቱ ትእዛዝ ናት። (ኤፌሶን 6: 1-3)
†እግዚአብሔር ወላጆቻቸውን ለሚያከብሩ እና ለሚታዘዙ ረጅም እና የበለጸገ ሕይወት ይሰጣል።
†ልጆች ባለመታዘዛቸው ምክኛት ህይወታቸውን ሊያሳጥሩ ከሚችሉ አደገኛ እና ጎጂ ሁኔታዎች እንዲርቁ ይረዳል።
2. ሞገስ እና ጥበብ
“ልጄ ሆይ፥ የአባትህን ምክር ስማ፥ የእናንትህንም ሕግ አትተው፤ለራስህ የሞገስ ዘውድ ለአንገትህም ድሪ ይሆንልሃልና።” (ምሳሌ 1:8-9)
†ለወላጆች መታዘዝና ምክርን መስማት፥ ወደ ጥበብ፣ወደ መልካም ህይወት እና ክብር ይመራል።
†የወርቅ ሐብል ዋጋ እንዳለው ሁሉ፥ የወላጆች ምክርም ለልጆች በመልካም ሁኔታ እንዲኖሩ ይረዳቸዋል።
3. ከጉዳት መከላከል
“ልጄ ሆይ፥ የአባትህን ትእዛዝ ጠብቅ፥ የእናትህንም ሕግ አትተው፤ሁልጊዜ በልብህ አኑረው፥ በአንገትህም እሰረው።ስትሄድም ይመራሃል፤ ስትተኛ ይጠብቅሃል፤ ስትነሣ ያነጋግርሃል።” (ምሳሌ 6:20-23)
†ለወላጆች በመታዘዝና የሰጡንን የመመሪያ ሕጎችን መጠበቅ ከአደጋ ያድናል።
†ወላጆችን መታዘዝ፥ ልጆች ከመጥፎ ተጽእኖዎች፣ ጎጂ ምርጫዎች እና አደገኛ ሁኔታዎችን እንዲያስወግዱ ይረዳቸዋል።
4. ከጥበበኞች ጋር መቆጠር
“ምክርን ስማ፥ ተግሣጽንም ተቀበል በፍጻሜህ ጠቢብ ትሆን ዘንድ።” (ምሳሌ 19፡20)
†ምክርን አዳምጥ ተግሣጽንም ተቀበል፥ በመጨረሻውም ከጥበበኞች ጋር ትቈጠራለህ።
†በሥራ ሁሉ ብልሃት፣ በጥበብም፣ በማስተዋልም፣ በእውቀትም የእግዚአብሔር መንፈስ ይሞላብናል።
†ወላጆቻቸውን የሚያዳምጡ ልጆች የበለጠ ፍቅር፣ ድጋፍ እና ደስታ ያገኛሉ።
5. መንፈሳዊ እድገት እና ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት
“ኢየሱስም መለሰ አለውም፦ የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወደዋል ወደ እርሱም እንመጣለን በእርሱም ዘንድ መኖሪያ እናደርጋለን። (የዮሐንስ ወንጌል 14:23)
†ለወላጆች የሚታዘዙ ልጆች እግዚአብሔርን መታዘዝ እንዲማሩ ይረዳቸዋል።
†ስንታዘዝ፣ ለእግዚአብሔር ፍቅር እናሳያለን፣ እርሱ በመገኘቱ፣ በደስታ እና ሰላም ይባርከናል።

12/04/2025

Address

Debre Zeyit

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Remnant Youth & Kids Holistic Nonprofit Corporation posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Remnant Youth & Kids Holistic Nonprofit Corporation:

Share