14/09/2026
እግዚአብሔርን ፈለግሁት መለሰልኝም፥ ከመከራዬም ሁሉ አዳነኝ።”
(መዝሙር 34፥4)
በሕይወታችን ውስጥ የጨለማ ወራት፣ የጭንቀትና የፈተና አውሎ ነፋሶች ሊበዙ ይችላሉ። ነገር ግን በጸሎት ወደ እግዚአብሔር ስንጮኽ የሚሰማ፣ የልባችንን ስብራት የሚያክም፣ ከጭንቀታችንም ሁሉ የሚያወጣ ታማኝ አምላክ አለን!
ዛሬ በምንም ዓይነት መከራና የሕይወት ውጥረት ውስጥ ብትሆን ተስፋ አትቁረጥ። እርሱን በፍጹም ልብህ ፈልገው፤ እርሱ በጊዜው ይ መልስልሃል፣ ከከበበህም መከራ ሁሉ ያወጣሃል።
እግዚአብሔር ጸሎትን የሚሰማ አምላክ ነው።
ለእርሱ የሚሳነው ነገር የለም።
በፍጹም ልብህ የፈለግኸው ዕለት መላሹን ታገኘዋለህ!
የዕለቱ መልእክት፦ ዛሬ ጭንቀትህን፣ ፍርሃትህንና ሸክምህን ሁሉ ወደ እግዚአብሔር አቅርብ። እርሱ አሁንም ይሰማል፤ ዛሬም ይታደጋል!