Meba page

Meba page Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Meba page, Religious organisation, Amhara, Dabra-Berhan.

ማህበረ ቅዱሳን ይለያል!!!******************** #በ44ኛው የሰበካ አጠቃላይ ጉባኤ የማኅበረ ቅዱሳን ሪፖርት‼️👉ማኅበረ ቅዱሳን በዩኒቨርሲቲና በኮሌጆች በሚሰጠው አገልግሎት ከ200...
17/10/2025

ማህበረ ቅዱሳን ይለያል!!!
********************
#በ44ኛው የሰበካ አጠቃላይ ጉባኤ የማኅበረ ቅዱሳን ሪፖርት‼️

👉ማኅበረ ቅዱሳን በዩኒቨርሲቲና በኮሌጆች በሚሰጠው አገልግሎት ከ200ሺ በላይ የግቢ ጉበኤ ተማሪዎችን በሀገር ዉስጥና በውጭ ሀገራት በተለያዩ ቋንቋዎች እያተማረ እንደሚገኝ አስታውቋል።

👉ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ 27,524 ተማሪዎች ደግሞ ባላቸው ሙያ ቤተ ክርስቲያንን እንዲያገለግሉ መሰማራታቸው ተገልጿል።

👉ሪፖርቱ 8,418 የግቢ ጉባኤ ተማሪዎችን የአብነት ትምህርት በማስተማር 146ቱ ሥልጣነ ክህነት አንዲቀበሉ ማድረጉንም ጠቅሷል።

👉ማኅበሩ በሚሰጠው የትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ከ41ሺ በላይ አዳዲስ አማኒያንን ማስጠመቁ የተገለጸ ሲሆን በካህናት እጥረት የተዘጉ 34 አብያተ ክርስቲያናት ካህናት በመቅጠር አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረጉን ተገልጿል።

👉በስበከተ ወንጌልና በሐዋርያዊ አገልግሎት 58,673,518,00 ብር ወጪ በማድረግ 31 መጽሐፍትን በ94,544 ቅጅ በተለያዩ ቋንቋዎች አሳትሞ አሰራጭቷል።

👉በ173 የአብነት ትምህርተ ቤት ለሚገኙ ትምህርተ ቤቶች 239 መምህራንና ለ2,220 ደቀ መዛሙርት 10,713,090,00 ብር ወጪ በማድረግ ወርኃዊ ድጎማ አድርጎዋል።

👉ስለማኅበረ ቅዱሳን አገልግሎት በ44ተኛ የሰባካ አጠቃላይ ጉባኤ ላይ በቀረበው ሪፖርት በአባ ጊዎርጊስ ዘ ጋስጫ በሚሰጠው ነጻ የትምህር እድል 37 ተማሪዎችን በማስተማር 427,945,00 ብር ወጪ በማድረግ ድጎማ ያደረገ ሲሆን በሀገራችን በተከሰተ ወቅታዊ ችግር ምክንያት በትግራይና በሌሎች አካባቢ ለሚገኙ ገዳማትና የአብነት ትምህርት ቤቶች 6,834,100,00 ድጋፍ ተደርጓል ተብሏል።

👉በአብነት ትምህርት ቤት ግንባታ በምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት 8,870,407 ብር፣ በሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት 23,021,025 ብር፣ በምዕራብ ኢትዮጵያ ቡኖ በደሌ ሀገረ ስበከት 16,671,804, ,53 ብር ወጪ በማድረግ የአብት ትምህርት ቤቶችና የገዳማት ገቢ ማስገኛ ሕንጻዎችን ማስገንባቱ በ44ተኛው የሰባካ ሆባኤ ላይ በቀረበው ሪፖርት ተገልጿል።

09/10/2025

እንኳን ለእናታችን ቅድስት አርሴማ አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

08/10/2025
አማኑኤል ማለት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ ማለት ነው። እንኳን አደረሳችሁ ድህረ ገጹን 👉👉follow 👉👉like 👉🖐🖐🖐🖐🖐
07/10/2025

አማኑኤል ማለት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ ማለት ነው። እንኳን አደረሳችሁ ድህረ ገጹን 👉👉follow 👉👉like 👉🖐🖐🖐🖐🖐

ፅጌ ፆም ሰኞ መስከረም 26 ይጀምራልስደቷ የሰው ዘርን ለማዳን ነበር!!!ስደት፣ ልመና፣ ልቅሶ፣ ዝርፊያ፣ ስድብ፣ ርሀብ ፣ ጥም ፣ ባይተዋርነት ............................አ...
06/10/2025

ፅጌ ፆም ሰኞ መስከረም 26 ይጀምራል
ስደቷ የሰው ዘርን ለማዳን ነበር!!!
ስደት፣ ልመና፣ ልቅሶ፣ ዝርፊያ፣ ስድብ፣ ርሀብ ፣ ጥም ፣ ባይተዋርነት ............................
አምላክን ለማዳን ብላ
በማታውቀው የግብጽ በረሀ እግሯን የአሸዋው ግለት እየገረፋት ተሰደደች።
እንባ ጠራጊዋ እመ አምላክ አለቀሰች።
ከህጻነቷ ጀምሮ እስከ እረፍቷ ድረስ ልቅሶ አልተለያትም።
ስጋና ነፍስ መጋቢዋ እመ አምላክ ተራበች፣ ተጠማች።
ሰጭዋ እናት ኮፌዳ ይዛ በየመንደሩ ፍርፋሪ ለመነች።
በእሷ ልጅ ምክንያት ሄሮድስ የገሊላን ህጻናት በጠቅላላ
እንደ ገደለ ስትሰማ በበረሀው ላይ አለቀሰች ።
+ የሚበላ ቁራሽ ለመለመን መንደር ሄደች። ባዶዋን ተመለሰች።
የልጇ የወርቅ ጫማ ተሰርቆ ጠበቃት። ቁራሽ ላላገኝ የልጄን
ጫማ አሰረኩኝ ብላ አለቀሰች።
+ ከእትማን ቤት ስትለምን ኮቲባ ልጇን ቀምታ ምድር ላይ ጣለችባት።
እመ አምላክ አለቀሰች ፣ ልጇም አለቀሰ።
+ በበረሀ ሲከራተቱ ሽፍቶች የልጇን ልብስ ገፈው ዘረፏት።
ይገሉብኛል ብላ # አለቀሰች።..............................
እመ አምላክ ስታለቅ ልጇ ፈጣሪ አልቅሷል፣ ዮሴፍ አልቅሷል። ሰሎሜ አልቅሳለች።
መላእክት ሚካኤል፣ ገብርኤል፣ ዑራኤል..........አዝነዋል።
ያላዘነው ዲያቢሎስ ብቻ ነው። ጥንት በሄሮድስ ልብ አድሮ እመብርሃንን አሰደደ።
አዳምን ለማውጣት ተንከራተተች።
አዳምን ለማዳን በ33 ዓም ልጇ ተሰቀለ። ከመስቀሉ ስር ሆና
አለቀሰች።
በአምላክ እናት ስደት ያልደረሰባት መከራ የለም። ተርባለች፣ ተጠምታለች፣ ተሰድባለች፣
ተንገላታለች፣ በፀሐይ ተቀቅላለች፣ እሾህ ተወግታለች፣ እንቅፉት ተመታለች፣ ተዘርፋለች፣ የሰው ፊት አይታለች፣
ፍርፋሪ ለምናለች፣ ባይተዋር ሆናለች፣ ብርድ ተበርዳለች፣ ቤተሰቧን ናፍቃለች፣
ልጇን እንዳይገሉባት ተሰቃለች፣ አልቅሳለች ፣ በአቀበቱ በቁልቁለቱ ደክማለች፣ ... 3 ዓመት ከመንፈቅ በስደት ፣ 64 ዓመት የመከራ ፀጋ ለብሳለች።
ምንጭ 81ዱ መጽሐፍ ቅዱስ፣ ቅዳሴ ማርያም አንድምታ.....
የድንግል ማርያም ምልጃ በረከት አይለየን
ፆሙን የበረከት ፆም ያድርግልን

06/10/2025

ሰላም ውድ የተዋህዶ ልጆች እንኳን ለወር ፅጌ በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ ወርሀ ፅጌ ማለት የአበባ ወቅት ማለት ሲሆን በዚህ ወቅት እመቤታችን የተሰደደችበት ወቅት ነው ። የእመቤታችን ስደት እንደ ኢትዮጵያ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከመስከረም 26- ህዳር 06 ታከብራለች።ከእመቤታችን ረድኤት በረከት ታውልብን ታሳድርብን ይህንን ፔጅ follow like shear በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ። ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ይሁን። አሜን

Address

Amhara
Dabra-Berhan

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Meba page posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share