Biyya Lallaba Buunnoo Beddellee የቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት

  • Home
  • Ethiopia
  • Bedele
  • Biyya Lallaba Buunnoo Beddellee የቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት

Biyya Lallaba Buunnoo Beddellee የቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት ይህ የቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት የፌስቡክ ገጽ ነው

24/04/2026
🙏  Abbaa keenya Abbaa Efreemii phaaphaasii biyya Lallaba Buunnoo Beddeellee Eebbaf dawwana hojii misoomaa Aanaa Cooraa k...
20/04/2026

🙏 Abbaa keenya Abbaa Efreemii phaaphaasii biyya Lallaba Buunnoo Beddeellee Eebbaf dawwana hojii misoomaa Aanaa Cooraa keessa jiru deemuun mana kiristiyaanaa D B Q Mikaa'elii sirna qulquleessa dursun Uummataa dhufaniif erga bagaa ifa du'a ka'u Gooftaa keenya Iyeesuus Kiristoosin gesan ebba Abbummaanfi kallatti hojii keennanii gara teesso isaaniiti nagaan galaaniru
🙏❤ #ሚያዝያ 12/2018 ዓ.ም ብጹዕ አባታችን አቡነ ኤፍሬም የቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ወደ ጮራ ወረዳ በደ/ብ/ቅ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በመገኘት ሥርዓተ ቅዳሴውን በመምራት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክትና አባታዊ ቡራኬ በመስጠት ለማስቀደስ የወጣውን ምዕመናን አጽናንተዋል
🙏❤ #በዚያውም በመገንባት ላይ ያለውን የጮራ ወረዳ ቤተ ክህነት ሕንፃ ጎብኝተዋል
🙏❤ #ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘውን የጮራ ቅ/ራጉኤል ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ቦታው ድረስ በመሄድ ግንባታው የደረሰበትን ደረጃ አይተው የሥራ አቅጣጫ እና ጸሎት አድርገዋል
🙏❤ #በመጨረሻም የአብደላ ራማ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የተጀመሩትን የልማት ሥራዎችን ጎብኝተው አባታዊ መመሪያ በመስጠት ወደ መንበረ ጵጵስናቸው በሰላም ተመልሰዋል
❤🙏 #የአባታችን ቡራኬ ከሁላችን ጋር ትሁን
#ቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት
❤ #የሀገረ ስብከቱ ሚድያ
❤❤ሚያዝያ 12/2018
❤❤❤በደሌ ኢትዮጵያ

❤ምሳሌ 19: 17: ለድሀ ቸርነትን የሚያደርግ ለእግዚአብሔር ያበድራል፥በጎነቱንም መልሶ ይከፍለዋል።   🙏  hiyyeessaaf garaa laafuakka waan Waaqayyoof liqeess...
13/04/2026

❤ምሳሌ 19: 17: ለድሀ ቸርነትን የሚያደርግ ለእግዚአብሔር ያበድራል፥በጎነቱንም መልሶ ይከፍለዋል።
🙏 hiyyeessaaf garaa laafu
akka waan Waaqayyoof liqeessuu ti;
Waaqayyos gatii isaa isaaf in deebisa;

❤የበደሌ ከተማ ምግባረ ሥናይ ኮሚቴ የተለመደውን በየዓመቱ የሚያደርገውን ከማህበረ ናታኒም በጋራ በማረሚያ ያሉ ወገኖቻችን እና አቅመ ደካሞችን ምግብ የማጋራት ስራ ሰርተዋል
የቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከትም ለዚሁ መልካም ሥራ ሃያ ሺህ ብር ድጋፍ አድርጓል 20,000

 #በስመ አብ ወወልድ  #ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ  #አምላክ አሜን 🙏 #የብጹዕ አቡነ ኤፍሬም  #የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ❤❤?ሉቃስ 24:5:  “ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላ...
11/04/2026

#በስመ አብ ወወልድ #ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ #አምላክ አሜን
🙏 #የብጹዕ አቡነ ኤፍሬም #የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት
❤❤?
ሉቃስ 24:5: “ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ?
የክርስቶስ ትንሣኤ የትንሣኤያችን በኵር ነው:: እርሱ መቃብር ክፈቱልኝ መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል ሞትን ድል አድርጎ እንደተነሣ ሙታንም በትንሣኤ ዘጉባኤ መቃብር ክፈቱልን መግነዝ ፍቱልን ሳይሉ በጸጋ ሞትን ድል አድርገው ይነሣሉ፣ በእርሱ ትንሣኤ ማመናችን ለድኅነታች ለትንሣኤያችን መሠረት ነው::

❤ #ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለባሕርይ አባቱ ለአብ ለእናቱ ለድንግል ማርያም የበኵር ልጅ እንደኾነ ሁሉ ለበጎ ነገርም ሁሉ በኵር ነው፤ የትንሣኤያችንም በኵር እርሱ ነው፡፡ ሉቃ ፪ • ፯ “አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ-ከሙታን ተነሥቷል፤ ሞት በሰው በኩል ስለ መጣ፣ ትንሣኤ ሙታንም በሰው በኩል ሆኗልና፣ ሁሉ እንደሚሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና:: ፩ኛ ቆሮ ፲፭ + ፳
❤🙏 #የፅንሰቱና የልደቱ ምሥጢር ከትንሣኤው ምሥጢር ጋር የተስማማ ነበር ይኸውም በፅንስቱና በልደቱ የእናቱ የቅድስት ድንግል ማርያምን ማኅተመ ድንግልናን ሳይከፍት እንደ ተፀነስና ሳይከፍት እንደተወለደ ሁሉ አሁንም በተዘጋ በተገጠመ መቃብር በድንቅ አምላካዊ ጥበብ ኃያል የሆነው አምላክ ተነሣ፤

❤ #ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ጌታችንን ገንዘው ከቀበሩት በኋላ የካህናት አለቆች ፈሪሳውያን ወደ ጲላጦስ ተመልሰው «ያ ሰው (ክርስቶስ) ገና በሕይወቱ ሳለ ከሦስት ቀን በኋላ እነሣለሁ ስል ሰምተነው ነበር፤ እንግዲህ ደቀመዛሙርቱ በሌሊት ስርቀው ከሙታን ተነሣ እንዳይሉ መቃብሩ እስከ ሦስተኛው ቀን ድረስ እንዲጠበቅ እዘዝ” አሉት::
❤🙏 #እነርሱም ሄደው ድንጋዩን አትመው ለስነው ከጨረሱ በኋላ ይህም አልበቃ ብሎ መቃብሩን በወታደሮች አስጠበቁ። በታላቅ ድንጋይ የተገጠመው መቃብር ድንጋይ እንደታተመ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ ተነሣ።
❤🙏 #በሐዲስ ኪዳን የሚከበረው የፋሲካ በዓል የክርስቶስ ትንሣኤ የታወጀበት፣ እስራኤል ዘነፍስ ከጎጢአት ወደ ጽድቅ፣ ከሐሳር ወደ ክብር ከባርነት ወደ ዘለዓለማዊ ነጻነት፤ ከአሮጌው ኪዳን ወደ አዲሱ ኪዳን፣ ከጐሰቆለ ማንነት ወደ ከበረው ሕይወት አሻገረን
❤🙏 #ስለዚህ የክርስቶስን ትንሣኤ ስናከብር እና ስናስብ በትንሣኤ ልቦና ውስጥ በመሆን አለበት መከራ ስደት ረሀብ የተለያዩ ችግሮች ውስጥ ገብተን ልሆን ይችላል ነገር ግን ዓርብ ሁሌም መከራ አለ ትንሣኤ ደግሞ አርብ ሳይሆን ሰንበት ነው የደስታ ጊዜ የሳቅ ጊዜ ይመጣል እንዳዘንን አንቀርም ትንሣኤ አለንና
❤❤❤🙏 #በዓሉን ስናከብር የሌላቸውን በማሰብ ካለን ላይም በማካፈል መሆን አለበት
ለሀገር ሰላም ሁል ጊዜ መጸለይ መዘንጋት የለብንም
#ብጹዕ አቡነ #ኤፍሬም የቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት #ሊቀ ጳጳስ እና #የቅዱስ ሲኖዶስ አባል
🙏 #መልካም ❤ #የትንሣኤ #በዓል ይሁንልን ።
የብጹዕ አባታችን ቡራኬ በሁላችን ላይ ይደር
#ሚያዝያ 03/2018
❤ #ቡኖ #በደሌ #ሀገረ #ስብከት
❤ #ኢትዮጵያ #በደሌ

 #ከእራት ተነሣ ልብሱንም አኖረ፥ ማበሻም ጨርቅ ወስዶ ታጠቀ፤"ሐዋርያቲሁ ከበበ እግረ አርዳኢሁ ሐጸበ…ኮኖሙ አበ ወእመ ወመሐሮሙ ጥበበ……/    #ሐዋርያቱን ሾመ የደቀመዛሙርቱንም እግር አጠ...
09/04/2026

#ከእራት ተነሣ ልብሱንም አኖረ፥ ማበሻም ጨርቅ ወስዶ ታጠቀ፤
"ሐዋርያቲሁ ከበበ እግረ አርዳኢሁ ሐጸበ…
ኮኖሙ አበ ወእመ ወመሐሮሙ ጥበበ……/

#ሐዋርያቱን ሾመ የደቀመዛሙርቱንም እግር አጠበ…
አባትም እናትም ሆናቸው…ጥበብንም (ትህትናን/ራስን ዝቅ ማድረግን) አስተማራቸው

(ዮሐንስ 13:1_20)


Eebbifamoo Abune Efreem Phaaphaasi Biyya Lallaba Buunnoo Beddeellee Bakka Argamanitti Kaatediraala Fayyisaa addunyaa Beddeelleetii
Torbee Dhukkubbii Guyyaa Kamisaa — ‘Guyyaa Dhiqannaa, Guyyaa Iccitii fi Guyyaa Kadhannaa’

 #እድለኞች የእጣ ትኬታችሁን በማቅረብ ሽልማቱን ከሀገረ ስብከት ጽ/ቤት መረከብ ትችላላችሁ        carraa kan taatan gara waajjiira Biyya Lallabaa keenya ...
06/04/2026

#እድለኞች የእጣ ትኬታችሁን በማቅረብ ሽልማቱን ከሀገረ ስብከት ጽ/ቤት መረከብ ትችላላችሁ
carraa kan taatan gara waajjiira Biyya Lallabaa keenya dhuftanii warqaa Abbaa carrumma keessan qabachuun akka dhiihaatan erga keenya siinf dabarsinaa
1ffa 11 847 #ፊሪጅ
2ffa 01 195 #ቲቪ
3ffa 10 436 #ሞባይል ቀፎ

  fannifamu jalqabaa(ጥንተ ስቅለት) Gooftaa Keenya Iyeesuus kiristos fi Ayyaana Hoosa'inaa Biyya lallaba Buunnoo Beddeellee D...
06/04/2026

fannifamu jalqabaa(ጥንተ ስቅለት) Gooftaa Keenya Iyeesuus kiristos fi Ayyaana Hoosa'inaa Biyya lallaba Buunnoo Beddeellee D/S/D/Maadani'alamitti Bakka Eebbifamoo Abbaa Efreemii Biyya Lallaba Buunnoo Beddeellee Akkasumaas miseensa Sinoodoosii Qulqulluu,Hojii Gaggeessa Biyya lallaba soraa kaakuu dura Luba Saahile Mariyaamii Argamanitti Haala Hoo'a ta'een kabajama Jira.

 #ሮሜ  2:10: ክብር ወስብሐት ወሰላም ለኵሉ ዘሠናይ ምግባሩ በጎ ሥራ ለሚያደርጉ ሁሉ ምስጋናና ክብር ሰላምም ይሆንላቸዋል፥     🙏🙏 #እንኳን ለሆሳዕና በዓል እና ለአባታችን ለቸሩ መድ...
05/04/2026

#ሮሜ 2:10: ክብር ወስብሐት ወሰላም ለኵሉ ዘሠናይ ምግባሩ
በጎ ሥራ ለሚያደርጉ ሁሉ ምስጋናና ክብር ሰላምም ይሆንላቸዋል፥

🙏🙏 #እንኳን ለሆሳዕና በዓል እና ለአባታችን ለቸሩ መድኃኔዓለም ጥንተ ስቅለት በሰለም አደረሳችሁ እያልን የቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት በዛሬው ዕለት መጋቢት 27/2018 ዓ.ም በበደሌ ደ/ሣ መድኃኔዓለም ካቴድራል ብጹዕ አባታችን አቡነ ኤፍሬም የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት ዕድለኛ የሚያደርገውን የሎተሪ ዕጣ ወጣ
#በተጨማሪም በጥር 24/2018 ዓ.ም በሀገረ ስብከቱ የተዘጋጀውን ታላቅና ታሪካዊ ጉባኤን በአቢይ ኮሚቴነት ስሠሩ ሲያስተባብሩ የነበሩትን አገልጋዮችን የከባቢ ምዕመናን እና በዓሉን ለማክበር በመጡት ሕዝበ ክርስቲያን ሁሉ ፍት የምስጋና ሠሪተፍኬት እና ስጦታ በብጹዕ አባታችን አቡነ ኤፍሬም እንዲሁም በሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራአስኪያጅ በኩል ተበርክቶላቸዋል።

 #በቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት በዲዴሣ ወረዳ ቤተ ክህነት አዲስ የሚገነባው የደንቢ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ለማጠናቀቅ የሚቀሩት     #1ኛ የቤተልሔም ሥራ አልተጀመረም       #2ኛ...
04/04/2026

#በቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት በዲዴሣ ወረዳ ቤተ ክህነት አዲስ የሚገነባው የደንቢ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ለማጠናቀቅ የሚቀሩት
#1ኛ የቤተልሔም ሥራ አልተጀመረም
#2ኛ የቅዱሣት ሥዕሎች ሥራ አልተጀመረም
#3ኛ የመብራት አፑል ስኬቶች ማብሪያ ማጥፊያ ብሬከሬች ሥራ አልተጀመረም
#4ኛ ጊቢ የማስዋብ ሥራ አልተጀመረም
#5ኛ መገልገያ ንዋየ ቅዱሳት በሙሉ
#6ኛ መንበር
#7ኛ 3የቤተ መቅደስ በሮች 8 መስኮት እና የመስኮት መስታውት
#8ኛ 940 ካሬ ወለል ሚንጣፍ
🙏🙏🙏 #እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩትን አስፈላጊ የሆኑት በአከባቢው ምዕመናን ልሟሉ ያልተቻሉት ናቸው በቦታው የምዕመናን ቁጥር አናሣ በመሆኑ የዚህ ቤተክርስቲያን ሥራ ከተጀመረ ከ10 ዓመት በላይ ሁኖታል ለማጠናቀቅም የሁሉም የኦርቶዶክሳውያን እርብርብ አስፈልጓቸዋል በሀገር ውስጥም ከሀገር ውጭም ያላችው የቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች በዚህ መንፈሳዊ ሥራ ላይ እንዲት ረባረቡ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን::
🙏🙏🙏 #ለበለጠ መረጃ 09 13 15 75 16 🙏🙏0917 35 5923
#የሕንፃ ሥራ #አካውንት 10000 999 32981
10000 6436 3167 0132 2995 0054900

🙏🙏 #ብጹዕ አባታችን አቡነ ኤፍሬም የቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የሀገረ ስብከቱን የልማት ጎበኙየቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት የልማት እንቅስቃሴ በጥሩ ሁነታ ቀጥሏ...
04/04/2026

🙏🙏 #ብጹዕ አባታችን አቡነ ኤፍሬም የቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የሀገረ ስብከቱን የልማት ጎበኙ
የቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት የልማት እንቅስቃሴ በጥሩ ሁነታ ቀጥሏል የሁለቱም የሰውም የሕንፃ ግንባታ እኩል በማስኬድ የተዘጉትን አቢያተ ክርስቲያናትን በማስከፈት ከገጠር እስከ ከተማ የአገልግሎት መስመር ተዘርግቷል::
Abbaa keenya Abbaa Efreem phaaphaasii biyya Lallabaa Buunnoo Beddeellee hojii misoomaa Biyya lallabichaa yeroo dawwatan
Hojiin amma hojjetama jiran hordooftoota ammanitichaa jajjaabesuu manneen kiristiyaanaa cuufaman bansiisuu hojii misoomaa jalqabamaan xumuursisu dha.

🙏🙏🙏 #የብጹዕ አባታችን አቡነ ኤፍሬም የዕለት  ቅዱስ ገብርኤል ሐዋርያዊ ጉዞ      Abbaa Eefreem Hangafa Phaphaasii biyya lallaba Buunnoo Beddellee ...
28/03/2026

🙏🙏🙏 #የብጹዕ አባታችን አቡነ ኤፍሬም የዕለት ቅዱስ ገብርኤል ሐዋርያዊ ጉዞ
Abbaa Eefreem Hangafa Phaphaasii biyya lallaba Buunnoo Beddellee fi Miseensa qulqulluu Siinoodoosii akkasumas Hoji geggeessaa Olaanaa Biyya lallaba Buunnoo Beddellee
🙏🙏 Kakuu Moofaa Saahile Maariyaam Hibruu Mana Lubummaa Aanaa Gachii Bataskaana Tulluu Ifaa Qulqulluu Gebri'eelii Gachiitti Argamuun Sirna qulqulleessaa Raawwatanii, Amantoota Ebbisuun jajjabeessanii jiru.
Wangeelaas Karaa Sooraa Kakuu Moofaa SaahileMaariyaamiin kennamee jira.

# #ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም የቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እንዲሁም የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ መጋቤ ብሉይ ሣህለ ማርየም ሕብሩ በገቺ ወረዳ ቤተክህነት በምትገኘው በገቺ ደ/ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በመገኘት ቅዳሴ በመቀደስ ፣ ምዕመናኑን ባርከው ቃለምዕዳን ሰጥተዋል።
#ትምህርተ ወንጌልም በመጋቤ ብሉይ ሣህለ ማርያም ተሰጥቷል።

የቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት ሚዲያ
መጋቢት 19/2018ዓ.ም
ከገቺ ወረዳ

Address

Bedele

Telephone

+251953957812

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Biyya Lallaba Buunnoo Beddellee የቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share