Amhara Region Islamic Affairs Higher Council/የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Bahir Dar
  • Amhara Region Islamic Affairs Higher Council/የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት

Amhara Region Islamic Affairs Higher Council/የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ለክልሉ ሙስሊም ማህበረሰብ ትክክለኛ መረጃ እንሰጣለን‼️

እንኳን ደህና መጡልን......ረውዷና የሁጃጆች መስተንግዶ በደማቅ አሻራ የተመዘገበ ልፋትና በስኬት የተቋጨ አማና!بسم الله الرحمن الرحيم​የዘንድሮው የሐጅ ጉዞ የብዙዎችን ልብ በ...
15/06/2026

እንኳን ደህና መጡልን......
ረውዷና የሁጃጆች መስተንግዶ በደማቅ አሻራ የተመዘገበ ልፋትና በስኬት የተቋጨ አማና!
بسم الله الرحمن الرحيم

​የዘንድሮው የሐጅ ጉዞ የብዙዎችን ልብ በደስታና በእርካታ የሞላ ታላቅ ስኬት ሆኖ ተጠናቋል። ለዚህ ደግሞ ሌት ተቀን የደከሙ፣ አማናን በተግባር ያሳዩ መሪዎች ሚና የላቀ ነበር።

​ከእነዚህ የላቁ መሪዎች መካከል የሃጅ ቡሽራ የነሸይኽ ገትዮች የልጅ ልጅ የሆኑት፣ የሃርቡው እንቁ፣ የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የዳዕዋ፣ ትምህርት፣ ማህበራዊ፣ ፈታዋና ብቃት ማረጋገጫ ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት ተወዳጁሸይኽ አወል አብደላህ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ናቸው። በእሳቸው የተመራውና የተስተባበረው ስራ ታሪክ የማይረሳው ትልቅ ስኬትን አስመዝግቧል!

​ የረውዷ ጉብኝት ስነ-ስርዓትን በማስተባበር በኩል
​ገና ከሐጁ ስነ-ስርዓት አስቀድሞ፣ እያንዳንዱ ሙስሊም በጉጉት በሚጠብቀው የረውዷ ጉብኝት ላይ የታየው ዝግጅት እጅግ አስደናቂ ነበር። ሸኽ አወል አብደላህ መዲናንና ሐረምን ብሎም ከመዲና በፊት የእስልምና ታሪክ ያላትን ሃበሻን በሚመጥን መልኩ፣ ታይቶ በማይታወቅ ስነስርዓት የኢትዮጵያውያንን ሁጃጆች በክብርና በደስታ ከውዱ ነቢያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ጋር አገናኝተዋል።
የሁጃጆቻችን ፊት ላይ የነበረው የእርካታ ፈገግታ የእሳቸውና የቡድናቸው ልፋት ውጤት የሚያሳይ ነበር።

​መልፋትና መትጋት ወትሮውንም መለያቸው የሆኑት እኚህ ታላቅ ሸኽ፣ የረውዷን ኃላፊነት ስላጠናቀቁ ብቻ እጃቸውን አላጣጠፉም። ይልቁኑ መስተንግዶና እገዛ በአስፈለገበት ቦታ ሁሉ እጃቸው ቀዳሚ ነበር።

• ​ሚና ኢስቲቅባሉ ላይ የተሰራው ልፋት ፣ የአረፋ ተራራም በተመሳሳይ እንቅልፍ የታጣባት በልፋት ላብ የተደከመበት ፍሬ የመጣበት ሁነት ሆኖ አልፏል ... ያ አስቸጋሪ በረሃ አፍ አውጥቶ ቢናገር ኖሮ፣ ለሁጃጆች የዋሉትን ውለታና ያሳዩትን ተቆርቋሪነት በምስክርነት በነገረን ነበር!

እንደ ውዷ ሃገራችን ኢትዮጲያ የዘንድሮው የ1447ኛው የሐጅ ስኬት የላቀና ጉልህ ድርሻ ለእሳቸውና ለቡድናቸው የሚሰጥ ነው የተገኘውም ሽልማት ለሃጅና ዑምራ ዘርፉ የሚገባ ነው።

ሁጃጆች ሽኝት ላይ የካርጎና መሰል ስራዎችን በተመለከተ አዳዲስ ለውጦች ታይተዋል የሃጅን የመስተንግዶ ችግር ለመቅረፍና ለማዘመን ብቻ ሳይሆን ለኺድማ የተመደቡት ሰዎች ሸይኽ አወልን ጨምሮ ለአላህ ብለው በየቂን የለፉት ልፋት ለዛሬው የሃጅና ዑምራ ሽልማት ትልቁን ድርሻ ይይዛል።

​አማናን እንደ ክብር መቁጠር!

​ለሸኽ አወል አብደላህም ሆነ አሁን ላለው ለአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አመራሮች ስራ ማለት 'አማና' (አደራ) ነው። አደራን በታማኝነት መወጣትና ለህዝብ መልፋትን እንደ ትልቅ ክብርና ጸጋ ነው የሚቆጥሩት።

​ አላህ ኸይር ስራቸውን ይቀበላቸው! ለዲናቸውና ለህዝባቸው ያበረከቱትን መልካም አሻራ በዱንያም በአኺራም የደስታ ምንጭ ያድርግላቸው። 🤲

8/10/28
Dhuʻl-Hijjah 29, 1447 AH

Amhara Region Islamic Affairs Higher Council/የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council

ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!!ጀግናው ታጋዩ ና አይነ አማው ወንድማችን ሸኽ አብዱል ሃፊዝ ኢብራሂም ወደ አኼራ ሄዱ ።የሰሜን ሸዋ ዞን እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት የመስጂድና አውቃፍ ዘር...
14/06/2026

ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!!
ጀግናው ታጋዩ ና አይነ አማው ወንድማችን ሸኽ አብዱል ሃፊዝ ኢብራሂም ወደ አኼራ ሄዱ ።

የሰሜን ሸዋ ዞን እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት የመስጂድና አውቃፍ ዘርፍ ሃላፊ ሆነው እያገለገሉ የነበሩት ሸህ አብዱል ሃፊዝ በጠና ከታመሙበት ህመም ሳይድኑ ዛሬ ወደ አኼራ ሂደዋል።

የሪፎርሙን መጅሊስ በምክትል ሰብሳቢ የመሩ
ሁሌም ለትግል ከፊት እንጂ ያልታዩት ሸይኽ
አይናቸው አለማየቱ ሳይበግራቸው በጀግንነት ወደር ሳይገኝላቸው ህዝባቸውን ታግለው ያታገሉት ወንድማችን ዛሬ የምድር ቆይታቸውን ጨርሰው ወደ አምላካቸው ወደ አላህ ሂደዋል።

ዑለማን በዛ ላይ ጀግናን ማጣት ለዑማው ከባድ ነው ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብ እና ለቤተሰቦቻቸው አላህ ሶብሩን ይስጥ።
የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት።

7/112018
Dhuʻl-Hijjah 28, 1447 AH

Amhara Region Islamic Affairs Higher Council/የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council

ለክቡር ፕሬዝዳንታችን ሸኽ ኑረዲን ቃሲም በወሎ ኮምቦልቻ ኤርፖርት አቀባበል ተደረገላቸው። 🕋بسم الله الرحمن الرحيم​የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ...
10/06/2026

ለክቡር ፕሬዝዳንታችን ሸኽ ኑረዲን ቃሲም በወሎ ኮምቦልቻ ኤርፖርት አቀባበል ተደረገላቸው። 🕋
بسم الله الرحمن الرحيم

​የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸኽ ኑረዲን ቃሲም የዘንድሮውን የ1447ኛው የሐጅ ስርዓት ክንውን በዳዕዋ እና በፈተዋ በኩል ሁጃጆችን በንቃት ሲያግዙና ሲያገለግሉ ቆይተው፣ ዛሬ አመሻሹን በኮምቦልቻ ኤርፖርት ሲገቡ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

​ሸኽ ኑረዲን ቃሲም የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝዳንትነቱን መንበር ከተረከቡበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ ስራዎችና እንቅስቃሴዎችን እያከናወኑ እንደሚገኙ ይታወቃል።

​በዘንድሮው የሐጅ ወቅት ለሁጃጆች ከተደረገው ሁለንተናዊ መስተንግዶ እኩል፣ ታላቁን የሐጅ ስርዓት እንዴት በትክክለኛው መንገድ ማከናወን እንዳለባቸው ማስተማር፣ በዳዕዋና በፈተዋ ማገዝ ትልቁንና ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛል።
ምክንያቱም ምንዳው ትልቅ የሆነውን ሃጅ ሰው በደምብ ተረድቶ ና አውቆት ማከናወንና በምላሹም የሄደበትን አላማ አሳክቶ ከእናቱ እንደተወለደ ህፃን ወንጀሉ ፀድቶ መምጣት ስላለበት ነው ትምህርቱ የሚያስፈልገው ያ ካልሆነ ግን ትርፉ ልፋት ነው የሚሆነው።

​ክቡር ፕሬዝዳንታችን ሸኽ ኑረዲን ቃሲም ከአያታቸው ከሸኽ አሊ (ውጅግራው) የተረከቡትን የኢልም (የዕውቀት) አደራ እና አስተምሮት በተግባር በማዋል ላይ በዘንድሮው የሐጅ ስርዓት ላይ
​በቅድስት መካ እና
​በተለያዩ ከ19 በላይ በሚሆኑ ቦታዎች ላይ
​ሰፊ የዳዕዋና የፈተዋ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ የዘንድሮውን የሐጅ ጉዞ በዳዕዋው ዘርፍ በስኬት አጠናቀው ተመልሰዋል።

​የአላህ ጥበቃና እገዛ አይለዮት! አላህ ይጠብቆት። 🤲

ሰኔ 3 ቀን 2018
Dhuʻl-Hijjah 24, 1447 AH

Amhara Region Islamic Affairs Higher Council/የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council

በሀጅ አገልግሎት እና መስተንግዶ ዘረፍ ለተገኘው ውጤት ድርሻ ለነበራቸው አካላት እውቅና ተሰጥቷል። የእውቅና መርሃ ግብሩን ያዘጋጁት የክልል እና የከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ...
03/06/2026

በሀጅ አገልግሎት እና መስተንግዶ ዘረፍ ለተገኘው ውጤት ድርሻ ለነበራቸው አካላት እውቅና ተሰጥቷል። የእውቅና መርሃ ግብሩን ያዘጋጁት የክልል እና የከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አመራሮች፣ የኡለማ ጉባኤ አባላት፣ የመካ ኮሚኒቲ አባላት እና የሀጅ ልዑክ አባላት ናቸው።

መርሃ ግብሩ የተዘጋጀው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ሀጅና ዑምራ ዘርፍ ከሳዑዲ አረቢያ ሀጅና ዑምራ ሚኒስቴር ያገኘውን የዲያመንድ (Diamond) ሽልማት መነሻ በማድረግ ነው።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ በምክትል ፕሬዝደንት ማዕረግ የሀጅና ዑምራ ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር ሙሀመድ ሷሊህ

"ዘርፉ ለዚህ ታላቅ ሽልማት የበቃው የሳዑዲ ሀጅ ሚኒስቴር ያስቀመጣቸውን መስፈርቶች በማሟላቱ እና መመሪያዎችን በማክበሩ ነው።" ሲሉ ገልፀዋል።

ግንቦት 25 / 2018
Amhara Region Islamic Affairs Higher Council/የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council

የተከበራችሁ የአማራ ክልል ሙስሊሞች፣ እንዲሁም በመላው ኢትዮጵያ ብሎም በዓለም ዙሪያ የምትገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች፤ እንኳን ለ1447ኛው ዓመተ ሂጅራ ታላቁ የዒድ አል-አድሐ (ዐረፋ)...
26/05/2026

የተከበራችሁ የአማራ ክልል ሙስሊሞች፣ እንዲሁም በመላው ኢትዮጵያ ብሎም በዓለም ዙሪያ የምትገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች፤ እንኳን ለ1447ኛው ዓመተ ሂጅራ ታላቁ የዒድ አል-አድሐ (ዐረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ። አልሐምዱሊላህ፤ ኩሉ ዓም ወአንቱም ቢአልፊ ኸይር! ።

Amhara Region Islamic Affairs Higher Council/የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት

በክልላችን ባሉ ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች የተጀመረውን ድጋፍና ክትትል በደሴ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ቢሮ በመገኘት ድጋፍና ክትትሉን አከናውኗልየክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክ...
23/05/2026

በክልላችን ባሉ ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች የተጀመረውን ድጋፍና ክትትል በደሴ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ቢሮ በመገኘት ድጋፍና ክትትሉን አከናውኗል

የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤቱ የ9ወር የስራ አፈፃፀም ክትትል ሲያደርግ ተቋሙን ለማዘመን እና ወጥ የሆነ የስራ ሂደት እንዲኖር ለማድረግ ታስቦ እየተደረገ ያለው የስራ ክትትልና ድጋፍ በሌሎች ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች አጠናክሮ ይቀጥላል::

የቸክሊስት ክትትልና ድጋፉ በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር እና በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ቀጥሏል ።የ9ወር የስራ አፈፃፀምን አስመልክቶ የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ...
20/05/2026

የቸክሊስት ክትትልና ድጋፉ በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር እና በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ቀጥሏል ።

የ9ወር የስራ አፈፃፀምን አስመልክቶ የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የጀመረውን ክትትልና ድጋፍን አጠናክሮ ቀጥሏል ።
በወሎ ክላስተር ስር የሚገኙትን የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤትን እንዲሁም የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤትን በቦታው ተገኝቶ በቸክሊስቱ መሰረት ክትትልና ድጋፉን አድርጓል።
በሌሎች በቀሩ ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮም ተጠናክሮ ይቀጥላል።

የቸክ ሊስት ድጋፍና ክትትሉ  ቀጥሏል...بسم الله الرحمن الرحيم የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት  በዞንና በከተማ አስተዳደር መዋቅሮች ላይ የጀመረውን ተቋማዊ ...
18/05/2026

የቸክ ሊስት ድጋፍና ክትትሉ ቀጥሏል...
بسم الله الرحمن الرحيم

የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በዞንና በከተማ አስተዳደር መዋቅሮች ላይ የጀመረውን ተቋማዊ የድጋፍና ክትትል ስራ አጠናክሮ ቀጥሏል።

​ምክር ቤቱ ባዘጋጀው የተቀናጀ የክትትል መርሃ-ግብር መሰረት፥ በደቡብ ወሎ ዞን እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ድጋፍ እና ክትትሉን አከናውኗል።

​ይህ የድጋፍና ክትትል ስራ አስቀድሞ በተዘጋጀው እና በተላከው ዝርዝር የዳሰሳ ቅፅ (Checklist) ላይ ተመስርቶ የተከናወነ ሲሆን፥ በዞኑ ምክር ቤት ያሉ ጠንካራ ጎኖችን ለማስቀጠልና የታዩ ክፍተቶችን በጋራ ለመፍታት ታስቦ የተደረገ መሆኑ ተገልጿል።

​የክልሉ ከፍተኛ ምክር ቤት በዞንና ከተማ አስተዳደር ከተሞች የሚያደርገው ይህ ተከታታይ የድጋፍና ክትትል ስራ ፥ ተቋማዊ አሰራርን ለማዘመንና ህዝበ ሙስሊሙን ይበልጥ ውጤታማ በሆነ መልኩ ለማገልገል ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዲኖረው ያደርጋል።

Dhuʻl-Hijjah 1, 1447 AH
10/9/2018

Amhara Region Islamic Affairs Higher Council/የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council

የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በአዊ ብሄረሰብ ዞን የሥራ አፈጻጸም  ድጋፍ እና ክትትል አደረገ::بسم الله الرحمن الرحيم​ የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍ...
08/05/2026

የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በአዊ ብሄረሰብ ዞን የሥራ አፈጻጸም ድጋፍ እና ክትትል አደረገ::
بسم الله الرحمن الرحيم
​ የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የጀመረውን ተቋማዊ የክትትልና ድጋፍ የ9 ወራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ በአዊ ብሄረሰብ ዞን አከናውኗል።

​በቻግኒ ከተማ በተካሄደው በዚህ ክትትልና ድጋፍ የምክር ቤቱ አመራሮች ቀደም ሲል በላኩት (Checklist) መሠረት የዞኑን እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት የ9 ወራት የሥራ ክንውን ተመልክቷል።

በክትትሉ እና ድጋፉ ወቅት የተከናወኑ ሥራዎችን የለየ ሲሆን፣ በቀጣይ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡና መስተካከል ያለባቸውን ጉዳዮች ላይም አቅጣጫ አስቀምጧል።

​በቦታው ተገኝተው ድጋፍና ክትትሉን የመሩት የከፍተኛ ምክር ቤቱ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የሕዝብ ግንኙነት የሥራ ኃላፊዎች የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች ገልጸዋል፦
ተጠያቂነትን ማረጋገጥ፦
ሕዝብ የመረጣቸው መሪዎች ለሕዝብ የሚጠበቅባቸውን አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ እንዲህ ዓይነቱ የቅርብ ክትትል እና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑ ተገልጿል።

አመራርን ማብቃት፦
የቀረበው የድጋፍና ክትትትል (Checklist) አመራሮች ብቁና ውጤታማ እንዲሆኑ፣ እንዲሁም አሠራራቸውን እንዲፈትሹ የሚያስችል መሆኑ ተጠቁሟል።

ተከታታይነት፦
ይህ በዞኖችና በከተማ አስተዳደሮች የሚደረገው ድጋፍ እና ክትትል ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ዓላማውም ተቋማዊ መዋቅርን በማጠናከር ለሕዝቡ የተሻለ አገልግሎት መስጠት እንደሆነ ተመላክቷል።

​በአጠቃላይ ክትትሉና የድጋፉ ሂደት የዞኑ ምክር ቤት ያሉበትን ክፍተቶች በድጋፍ እንዲያርምና የተጀመሩ መልካም እንቅስቃሴዎችን ይበልጥ እንዲያጠናክር መነቃቃትን የሚፈጥር መሆኑ ተገልጿል።

Dhuʻl-Qiʻdah 21, 1447 AH
30/8/2018

Amhara Region Islamic Affairs Higher Council/የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council

የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የ9 ወር የሥራ አፈጻጸም ግምገማ በባሕር ዳር ከተማ ጀመረ።بسم الله الرحمن الرحيم​የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር...
05/05/2026

የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የ9 ወር የሥራ አፈጻጸም ግምገማ በባሕር ዳር ከተማ ጀመረ።
بسم الله الرحمن الرحيم
​የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የዞንና የከተማ አስተዳደር ምክር ቤቶችን የ9 ወር የሥራ አፈጻጸም በክልሉ ርዕሰ መዲና በባሕር ዳር ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ተገኝቶ ለሁለተኛ ዙር በቸክ ሊስት የተደገፈ ድጋፍና ክትትል ማድረጉን በይፋ ጀምሯል።

​ምክር ቤቱ ቀደም ብሎ ለሁሉም ዞኖችና የከተማ አስተዳደሮች በተላከው የድጋፍና ክትትል (Checklist) መሠረት፣ የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤትን የሥራ ክንውን ገምግሟል።

በድጋፍና ክትትሉ ወቅትም በዕቅድ የተያዙ ተግባራት ምን ያህል ውጤታማ እንደነበሩና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን የመለየት ሥራ ተከናውኗል።

በ​ድጋፍና ክትትሉ ላይ የተሳተፉት የከፍተኛ ምክር ቤቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ፣ ዋና ፀሃፊና እንዲሁም ህዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፉ እንደገለፁት ፦
​ይህ የክትትልና የድጋፍ መርሐ-ግብር በባሕር ዳር የተጀመረው በሁሉም የክልሉ ዞኖችና የከተማ አስተዳደሮች ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።

​የግምገማው ዋነኛ ዓላማ የመሪዎችን የሥራ አፈጻጸም ለመመዘንና የምክር ቤቱን የሥራ ሂደት ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ ነው።

​በተጨማሪም ተቋማዊ አሠራርን በማዘመንና ጠንካራ መዋቅር በመፍጠር፣ ለኅብረተሰቡ የሚሰጠውን አገልግሎት ለማሻሻል ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል።

​ይህ የክትትልና ድጋፍ ሥራ ተቋሙ ያሉትን ጥንካሬዎች እንዲያስቀጥልና ድክመቶች በወቅቱ ታርመው ለቀጣይ የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ተገልጿል።

27/8/2018
Dhuʻl-Qiʻdah 18, 1447 AH

Amhara Region Islamic Affairs Higher Council/የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council

Address

Bahir Dar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara Region Islamic Affairs Higher Council/የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share