Orthodox tewahido church

Orthodox tewahido church ORTHODOX TEWAHIDO----------the right road

 #አቡነ ሐራ ድንግል ወር በገባ በ11 የአባታችን የአቡነ ሐራን  ድንግል ወርሐዊ መታሰቢያቸው ነው፡፡አባታችን አቡነ ሐራ ድንግል ያደረጉት ተአምር ይህ ነው፡፡ ጸሎቱና በረከቱ ከሁላችን ከሕዝ...
21/10/2025

#አቡነ ሐራ ድንግል

ወር በገባ በ11 የአባታችን የአቡነ ሐራን ድንግል ወርሐዊ መታሰቢያቸው ነው፡፡አባታችን አቡነ ሐራ ድንግል ያደረጉት ተአምር ይህ ነው፡፡ ጸሎቱና በረከቱ ከሁላችን ከሕዝበ ክርስቲያን ጋር ይኑር ለዘለዓለሙ አሜን፡፡

#አምስት መነኮሳያት ከአባታች ሐራ ድንግል ገዳም ወደ ዳውንት ወደ ሚባል ሀገር ሄዱ አነርሱም ለምግባቸውና ለልብሳቸው የሚሆናቸውን ገንዘብ ከሀገሩ ሰዎች ይለምኑ ዘንድ ወደ ዳውንት ደረሱ፡፡
☞ወደዚያም በደረሱ ጊዜ በድንገተኛ በሽታ የታመመ አንድ ሰውና በከብት በሽታ የታመመ አንድ በሬ አገኙ የሀገሩ ሰዎችም እነዚያን መነኮሳያት በሀገራችን ሁለት በሽተኞች አሉ አንዱ ሰው ነው አንዱም በሬ ነው ለእነዚህ መድኃኒት የሚሆናቸው ምንድነው አሏቸው፡፡
☞መነኮሳያቱም ለጠየቋቸው ሰዎች የአባታችን ሐራ ድንግል ከሚሉት ከጻድቁ አባታችን መቃብር ያመጣነው አፈር አለ ሁለቱንም እንቀባቸዋለን አሏቸው፡፡
☞የሀገሩ ሰዎችም እናንተ እንዳችሁ ይሁን አሏቸው ወዲያውም ሰውየውንም በሬውንም ቀቧቸው ሁለቱም በአባታችን ሐራ ድንግል የረድኤት ኃይል ከደዌያቸው ተፈወሱ፡፡
☞የጻድቁ አባታችን የአቡነ ሐራ ድንግል የጸሎታቸው በረከቱ ከሁላችን ሕዝበ ክርስቲያኑ ጋር ይሁን፡፡
☞(ገድለ አቡነ ሐራ ድንግል )

🎤ነብይ ነኝ..😭ራስህን "ነቢይ ነኝ " ብለህ ከመሾምህ በፊት ነቢዩ ኢሳይያስ እኛ አሁን እየታነፅንበት ላለው ወንጌል  በመጋዝ ሁለት ቦታ ተሰንጥቆ መሞቱን ታውቃለህ?ራስህን "ነቢይ ነኝ" ብለ...
16/07/2023

🎤ነብይ ነኝ..😭
ራስህን "ነቢይ ነኝ " ብለህ ከመሾምህ በፊት ነቢዩ ኢሳይያስ እኛ አሁን እየታነፅንበት ላለው ወንጌል በመጋዝ ሁለት ቦታ ተሰንጥቆ መሞቱን ታውቃለህ?

ራስህን "ነቢይ ነኝ" ብለህ ከመሾምህ በፊት ለዚህ የወንጌል እውነት ሐዋርያው ዮሐንስ በሚፈላ ዘይት በርሜል ውስጥ ተዘፍዝፎ መሞቱን ፡ እንዲሁም ሐዋርያው ጴጥሮስ"እንደ ጌታዬ በቁሜ አልሰቀልም" ብሎ ወደታች ተዘቅዝቆ በመስቀል መሞቱን ታውቃለህን!?

የጥንቱ ሐዋርያት ዘመናዊ ውድ መኪና የመንዳት፡ዘመናዊ ቪላ የመስራት ፡የቱርክ ሱፍና የፈረንሳይ ሽቶ የመቀባት አባዜና ጥማት አልነበረባቸውም።

የጥንቱ ሐዋርያው በጥቁር ገበያ በተጭበረበረ ዶላር ዩሮና ፓውንድ ፡ ከድሆች መቀነት በተዘረፈ ብር ቢሊይነር የመሆን ሕልም አልነበራቸውም።

የጥንቱ ሐዋርያት ዘይት ውኃ ጨርቅ ሶፍት ጨርቃ ጨርቅ ሸጠው ባለጠጋ የመሆን ህልም አልነበራቸውም። ትልልቅ የተንጣለለ አዳራሸ አልገነቡም ፡የተሸቃቀጠ ወንጌል ሰብከው ዝናን አላካበቱም። ሐሰትን ከእውነት ቀላቅለው እንደ ሸቀጥ ለገበያ አላቃረቡም!!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን..📖✝️✝️✝️

"ኤጲስ ቆጶሳትን መሾም የጎደለውን ለመሙላት  እንጂ  የጎደላቸውን ለመሙላት  አለመሆኑ ሊሠመርበት ይገባል"።ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ
16/07/2023

"ኤጲስ ቆጶሳትን መሾም የጎደለውን ለመሙላት እንጂ የጎደላቸውን ለመሙላት አለመሆኑ ሊሠመርበት ይገባል"።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ

16/07/2023
የሲኖዶስ መግለጫ ትዕዛዙን በሚገባ እንቀበል
11/02/2023

የሲኖዶስ መግለጫ
ትዕዛዙን በሚገባ እንቀበል

•••"እኔ ግን እላለሁ! እምዬ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አንቺ እናትዓለም፤ የእነ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ፣ የእነ ቅዱስ አትናቴዎስ እና ቅዱስ ቄርሎስ የእነ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ የእነ ቅድስት አርሴማ፣ የእነ...
02/02/2023

•••
"እኔ ግን እላለሁ! እምዬ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አንቺ እናትዓለም፤ የእነ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ፣ የእነ ቅዱስ አትናቴዎስ እና ቅዱስ ቄርሎስ የእነ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ የእነ ቅድስት አርሴማ፣ የእነ አቡነ ተክለሃይማኖት፣ የእነ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ፣ የአባ ሳሙኤል ዘዋልድባ፣ የቅድስት ክርስቶስ ሠምራና የአቡነ አረጋዊ ሃይማኖታቸው የሆንሽ ንጽህት፣ ቅድስት፣ ርትዕት ተዋሕዶ ሃይማኖቴ ሆይ! ብረሳሽና ብከዳሽ ቀኜ ትርሳኝ። ትክዳኝም። ባላስብሽና ባልሟገትልሽ ባልሞትልሽም ምላሴ ከጉሮሮዬ ይጣበቅ። ሳለጎበድድና ሳለከዳሽ እንድኖርም አምላክሽ ይርዳኝ። ይህን ባላደርግና ሳልጮህልሽ ዝም ብዬ ብሞት ስሜ ከህይወት መጽሐፍ ይደምሰስ።

"ድንግል ሆይ እናቴ ! አዛኝቱ ዛሬም እንደትናንቱ ቅደሚ ከፊት ከኋላችን''
ከዘመድኩን በቀለ👌🙏

29/01/2023
ታህሳስ ፩፱(19) እንኳን ለአብሳሪው  መላክ  ቅዱስ ገብርኤል  አመታዊ ክብረ በአል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ !!  የአብሳሪው መላአክ  ጥበቃው እና አማላጅነቱ ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን...
28/12/2022

ታህሳስ ፩፱(19) እንኳን ለአብሳሪው መላክ ቅዱስ ገብርኤል አመታዊ ክብረ በአል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ !! የአብሳሪው መላአክ ጥበቃው እና አማላጅነቱ ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን!!

   Abew  gubaye
10/12/2022


Abew
gubaye

በዚህ ዮቱቭ ቻናል መንፈሣዊ ስብከት:መዝሙር እና ሌሎች መንፈሳዊ ትምህርቶችን ያገኛሉ
08/12/2022

በዚህ ዮቱቭ ቻናል መንፈሣዊ ስብከት:መዝሙር እና ሌሎች መንፈሳዊ ትምህርቶችን ያገኛሉ

በዚህ ዮቱቭ ቻናል መንፈሣዊ ስብከት:መዝሙር እና ሌሎች መንፈሳዊ ትምህርቶችን ያገኛሉ

Address

Bahir Dar
6040

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Orthodox tewahido church posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Orthodox tewahido church:

Share