Hawassa Mehal Kale Heyewt Youth - ሐዋሳ መሐል እናት ቃለ-ሕይወት ወጣቶች

  • Home
  • Ethiopia
  • Awassa
  • Hawassa Mehal Kale Heyewt Youth - ሐዋሳ መሐል እናት ቃለ-ሕይወት ወጣቶች

Hawassa Mehal Kale Heyewt Youth - ሐዋሳ መሐል እናት ቃለ-ሕይወት ወጣቶች DAG - Hawassa Mehal Kale Heywet Church Youth and Teens Ministry. Acts 2:42

21/09/2024

 እህታችን የሺ ( ከንፍታሌም የጸሎት ህብረት) ጸሎት በመምራት አገልግላለች። ከ ግሎሪ የአምልኮ ህብረት ጋር ደግሞ በዝማሬ እግዚአብሔርን አምልከናል። ወንድማችን ይስሃቅ አብርሃም የእንግድነት...
21/09/2024



እህታችን የሺ ( ከንፍታሌም የጸሎት ህብረት) ጸሎት በመምራት አገልግላለች። ከ ግሎሪ የአምልኮ ህብረት ጋር ደግሞ በዝማሬ እግዚአብሔርን አምልከናል። ወንድማችን ይስሃቅ አብርሃም የእንግድነት ህይወት በሚል ርዕስ ከ 2ኛ ጴጥሮስ 2፡4-12 የእግዚአብሔርን ቃል አካፍሎናል። በመልዕክቱም ቅዱሳን በምድር ላይ የሚኖረን ቆይታ የእንግድነት ስለሆነ፤ እንዴት መመላለስ እንዳለብን ከክፍሉ አሳይቶናል።

እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት የሚቻለው የልጁን በመምሰል በሚኖር ህይወት ነው።

ቅዱሳን በምድር ላይ ሲኖሩ እንግዳ እንደመሆናቸው ፤ ከስጋዊ ምኞትና ከምድራዊነት በመራቅና ኢየሱስን በመቅረብ፤ ሰማያዊ ቤታቸውን መጠባበቅ አለባቸው።

የቅዱሳን የእንግድነት ህይወት ምን መምሰል አለበት?

1, በኢየሱስ ህያዋን ድንጋይ በመሆን

1ኛ ጴጥሮስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴ በሰውም ወደ ተጣለ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ወደ ተመረጠና ክቡር ወደ ሆነው ወደ ሕያው ድንጋይ ወደ እርሱ እየቀረባችሁ፥
⁵ እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።

ይህም ቅዱሳን ኢየሱስን የመምሰል ህይወት ሊኖራቸው እንደሚገባ የሚያሳይ ነው።

2, በኢየሱስ መንፈሳዊ መሥዋዕትና መንፈሳዊ ቤት በመሆን

“እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።”
— 1ኛ ጴጥሮስ 2፥5

ይህም ደግሞ ቅድሳን ለእግዚአብሔር የተሰጠና የተለየ ህይወት ሊኖረን እንደሚገባ የሚያሳይ ነው።

3, ከስጋዊ ምኞት በመራቅ

“ወዳጆች ሆይ፥ ነፍስን ከሚዋጋ ሥጋዊ ምኞት ትርቁ ዘንድ እንግዶችና መጻተኞች እንደ መሆናችሁ እለምናችኋለሁ፤”
— 1ኛ ጴጥሮስ 2፥11

4, በአህዛብ መካከል ያለነቀፍና በመልካም ህይወት በመመላለስ

“ስለሚመለከቱት ስለ መልካም ሥራችሁ፥ ክፉ እንደምታደርጉ በዚያ እናንተን በሚያሙበት ነገር፥ በሚጎበኝበት ቀን እግዚአብሔርን ያከብሩት ዘንድ በአሕዛብ መካከል ኑሮአችሁ መልካም ይሁን።”
— 1ኛ ጴጥሮስ 2፥12

በአጠቃላይ እኛ ቅዱሳን ሰማያዊ ቤት ያለን እንደመሆናችን መጠን በምድር ላይ እንግዳና መጻተኛ መሆናችንን ተረድተን፤ ኢየሱስን በመምሰልና ስጋዊ ምኞትን በማስወገድ መንፈሳዊ መሥዋዕትና መንፈሳዊ ቤት ለመሆን መሰራት አለብን።

የአገልግሎት ትምህርት ሲማሩ ለቆዩ ልጆች ሰርተፍኬት ተሰቷቸዋል።

በጥቂቱ የነበረን ፕሮግራም ይህን ይመስላል። በፕሮግራሙ የተሳተፍችሁ ሁሉ እግዚአብሔር ይባርካችሁ። ዘወትር ቅዳሜ ከአመሻሽ 11፡30 ጀምሮ በሐዋሳ መሐል ከተማ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን በመገኘት አብረውን የጌታን ጸጋ ይካፈሉ።

የሐ/መ/ከ/ቃ/ሕ/ቤ/ክ የሚዲያ አግልግሎት ክፍል ።
መስከረም 11 2017 ዓ.ም

📸HMKHC MEDIA CREW

ዛሬ ከ 11፡30 ጀምሮ
14/09/2024

ዛሬ ከ 11፡30 ጀምሮ

🌻🌻🌻እንኳን ለ2017 አዲስ ዘመን ጌታ በምህረቱና በቸርነቱ ጠብቆ አደረሳችሁ።🌻🌻🌻🌻🌻🌻ልዩ የአዲስ አመት ፕሮግራም 🌻🌻🌻🌻 ረቡዕ መስከረም 1 ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ልዩ የበአል ፕሮግራም 🌻 ...
10/09/2024

🌻🌻🌻እንኳን ለ2017 አዲስ ዘመን ጌታ በምህረቱና በቸርነቱ ጠብቆ አደረሳችሁ።🌻🌻🌻
🌻🌻🌻ልዩ የአዲስ አመት ፕሮግራም 🌻🌻🌻

🌻 ረቡዕ መስከረም 1 ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ልዩ የበአል ፕሮግራም
🌻 ረቡዕ መስከረም 1 ከ10 ሰዓት ጀምሮ በ22 ማዞሪያ የወንጌል ስርጭት
🌻 ሐሙስ መስከረም 2 ከ10፡30 ጀምሮ ልዩ የወጣቶች የበአል ፕሮግራም

አገልጋዮች

🌻 መጋቢ ዳንኤል
🌻 መጋቢ ምንተስኖት
🌻 ዘማሪ ኢዩ
🌻 ዘማሪ ደረጀ
🌻 ዘማሪ አማኑኤል
🌻 ይሳኮር የአምልኮ ህብረት
🌻 ናዛሪን የአምልኮ ህብረት
🌻 ግሎሪ የአምልኮ ህብረት
🌻 ይዲድያ የመዘምራን ህብረት
🌻 ፊሊሎጎስ የመዘምራን ህብረት

ሁላችሁም ተጋብዛቹኀል

#አዲስአመት #እንቁጣጣሽ #በአል #በዓል

“ዳሩ ግን፦ እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ ተብሎ ስለ ተጻፈ የጠራችሁ ቅዱስ እንደ ሆነ እናንተ ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ።”  — 1ኛ ጴጥሮስ 1፥15-16                  ...
26/08/2024

“ዳሩ ግን፦ እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ ተብሎ ስለ ተጻፈ የጠራችሁ ቅዱስ እንደ ሆነ እናንተ ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ።”
— 1ኛ ጴጥሮስ 1፥15-16

Address

Mehal Ketema Subcity
Awassa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hawassa Mehal Kale Heyewt Youth - ሐዋሳ መሐል እናት ቃለ-ሕይወት ወጣቶች posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share