The Crown of Righteousness International Church

The Crown of Righteousness International Church Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from The Crown of Righteousness International Church, Religious organisation, Around old bus station, Awassa.

የእሁድ አምልኮ ፕሮግራም  አቅራቢ ፦ ፓስተር ሀብታሙ ለገሰ ( ፒና ) ቀን ፦  05 - 10 - 2014ርዕስ፦ ሰዋልኝ።የቃል ክፍል፦ ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 22እግዚአብሔር አብርሃምን አንድ ...
15/06/2022

የእሁድ አምልኮ ፕሮግራም

አቅራቢ ፦ ፓስተር ሀብታሙ ለገሰ ( ፒና )

ቀን ፦ 05 - 10 - 2014

ርዕስ፦ ሰዋልኝ።

የቃል ክፍል፦ ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 22

እግዚአብሔር አብርሃምን አንድ ጊዜ ተናገረዉ እርሱም ሰምቶ ታዘዘ ፤ ከአባት ቤት ዉጣ ካለዉ ጊዜ አንስቶ እስከ ህይወት ፍፃሜዉ አብርሃም አምላኩን እግዚአብሔርን ልጁን ለመሰዋት እስከመፍቀድ ታዟል።

በዚህ የቃል ክፍል የሚከተሉትን መልካም የህይወት መርሆዎች ከእምነት አባታችን ከአብርሃም እንማራለን።

1ኛ፦ አብርሃም የተዘጋጀ ማንነት ነበረዉ

(ኦሪት ዘፍጥረት 22:1)

" ከእነዚህም ነገሮች በኋላ እግዚአብሔር አብርሃምን ፈተነው፥ እንዲህም አለው። አብርሃም ሆይ። አብርሃምም። እነሆ፥ አለሁ አለ።"

አብርሃም እነሆ አለሁ ሲል አምላኩ እግዚአብሔርን ለምትለኝ ነገር ለመታዘዝ ዝግጁ ነኝ ማለቱ ነዉ።

ለእግዚአብሔር ቤት መሪዎች እና ለእግዚአብሔር ቃል መታዘዝ በህይወታችን የስኬት መሰረት ነዉ ፤ ስለዚህ መንፈስ ቅዱስን ከእኛ ምን እንደሚፈልግ ልንጠይቀው ይገባል።

2ኛ፦ አብርሃም የእምነት ህይወት ያለዉ ሰዉ ነበር።

(ኦሪት ዘፍጥረት 22:5)

" አብርሃምም ሎሌዎቹን አላቸው። አህያውን ይዛችሁ ከዚህ ቆዩ፤ እኔና ልጄ ወደዚያ ሄደን እንሰግዳለን፥ ወደ እናንተም እንመለሳለን።"

(ኦሪት ዘፍጥረት 22:8)

" አብርሃምም። ልጄ ሆይ፥ የመሥዋዕቱን በግ እግዚአብሔር ያዘጋጃል አለው፤ ሁለቱም አብረው ሄዱ። "

አብርሃም ምንም እንኳን ልጁን ለመሰዋት እየሄደ ቢሆንም እግዚአብሔር ልጁን መልሶ እንደሚሰጠዉ ያምን ነበር።

3ኛ፦ አብርሃም እግዚአብሔርን ይፈራ ነበር

እግዚአብሔርን መፍራት ማለት ለእርሱ እዉቅና መስጠት ፤ በየትኛውም ስፍራ እና ሁኔታ እርሱን ሰምተን መታዘዝ ነዉ።

የእግዚአብሔር ቃል ስለ እየሱስ ሲናገር እግዚአብሔርን በመፍራቱ ፀሎቱ ተሰማለት ይላል።

እግዚአብሔርን የመፍራት ህይወት እንዲኖረን እራሳችንን ማለማመድ አለብን።

4ኛ፦ አብርሃም የመታዘዝ ህይወት ነበረዉ

(ኦሪት ዘፍጥረት 22:12)

" እርሱም። እነሆኝ አለ። እርሱም። በብላቴናው ላይ እጅህን አትዘርጋ፥ አንዳችም አታድርግበት፤ አንድ ልጅህን ለእኔ አልከለከልህምና እግዚአብሔርን የምትፈራ እንደ ሆንህ አሁን አውቄአለሁ አለ።"

በዚህ ክፍል " አንድ ልጅህን ለእኔ አልከለከልህምና " የሚለዉ አብርሃም ለአምላኩ ለእግዚአብሔር ቃል ልጁን እስከመስጠት እንደታዘዘ ያሳያል ፤ የአብርሃም የመታዘዝ ህይወት የሚጀምረዉ የአባቱን ቤት ትቶ እግዚአብሔር ወደ አሳየዉ ምድር በመሄድ ነዉ።

እግዚአብሔር በሚታዘዝ ማንነት ዉስጥ በረከቱን ይለቃል

" እሺ ብትሉ ለእኔም ብትታዘዙ፥ የምድርን በረከት ትበላላችሁ፤ "
(ትንቢተ ኢሳይያስ 1:19)

የእግዚአብሔር መንግስት አንደኛ! መልካም ሳምንት

ለበለጠ መረጃ፦ 0916 - 82 23 55
0911 - 43 53 16

የእሁድ አምልኮ ፕሮግራም  አቅራቢ ፦ ወንድም ደረጀ ወልደዮሐንስ ቀን ፦  28 - 09 - 2014ርዕስ፦ አትምሰሉ።የቃል ክፍል፦ ወደ ሮሜ ሰዋች 12 ፥ 1-2(ወደ ሮሜ ሰዎች ምዕራፍ 12)--...
10/06/2022

የእሁድ አምልኮ ፕሮግራም

አቅራቢ ፦ ወንድም ደረጀ ወልደዮሐንስ

ቀን ፦ 28 - 09 - 2014

ርዕስ፦ አትምሰሉ።

የቃል ክፍል፦ ወደ ሮሜ ሰዋች 12 ፥ 1-2

(ወደ ሮሜ ሰዎች ምዕራፍ 12)
----------
1፤ እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፥ እርሱም ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው።

2፤ የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።

1. መስዋዕት

በክፍሉ የሚናገረው መስዋዕት የሚለዉ ለደህንነት ስለሚደረግ መስዋዕት አይደለም ነገር ግን ወደ ዕብራውያን 10:12 " እርሱ ግን ስለ ኃጢአት አንድን መሥዋዕት ለዘላለም አቅርቦ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ፥" ስለሚል የደህንነት ስራ በክርስቶስ ያለቀ ነዉ።
ስለዚህ የእኛ መስዋዕት ከልብ ፍቃድ የሆነ አምልኮ ነዉ።

መስዋዕታችን እግዚአብሔርን ደስ ሊያሰኝ ይገባል።

(ወደ ዕብራውያን ምዕራፍ 13)
----------
15፤ እንግዲህ ዘወትር ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት፥ ማለት ለስሙ የሚመሰክሩ የከንፈሮችን ፍሬ፥ በእርሱ እናቅርብለት።

16፤ ነገር ግን መልካም ማድረግን ለሌሎችም ማካፈልን አትርሱ፤ እንዲህ ያለው መሥዋዕት እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋልና።

" ነገር ግን ሁሉ አለኝ ይበዛልኝማል፤ የመዓዛ ሽታና የተወደደ መሥዋዕት የሚሆነውን ለእግዚአብሔርም ደስ የሚያሰኘውን ስጦታችሁን ከአፍሮዲጡ ተቀብዬ ተሞልቼአለሁ።"
(ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4:18)

የተወደደ መስዋዕት የተቀደሰ መስዋዕት ነዉ።

(ወደ ሮሜ ሰዎች 15:15-16)

" ነገር ግን አሕዛብ በመንፈስ ቅዱስ ተቀድሰው የተወደደ መሥዋዕት ሊሆኑ፥ ለእግዚአብሔር ወንጌል እንደ ካህን እያገለገልሁ፥ ለአሕዛብ የክርስቶስ ኢየሱስ አገልጋይ እሆን ዘንድ ከእግዚአብሔር በተሰጠኝ ጸጋ ምክንያት ተመልሼ ላሳስባችሁ ብዬ በአንዳንድ ቦታ በድፍረት ጻፍሁላችሁ።"

2. የእግዚአብሔር ፈቃድ

ፈቃድ ማለት እግዚአብሔር በእኛ ህይወት እንዲገለጥ የሚፈልገዉ ህይወት ነዉ።

3. ደስ የሚያሰኝ

የሚገለጠዉ ህይወታችን ፈቃዱ ሲሆን እርሱን ደስ የሚያሰኝ ይሆናል።

4.ፍፁም

የእግዚአብሔር ፍቃድ መሻሻል የማይፈልግ ቅዱስ እና ንፁህ ነዉ

5. ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ

የእርሱ የሆነዉን ፍቃድ በቃሉ ፈትነን መረዳት አለብን።

(ወደ ቆላስይስ ሰዎች ምዕራፍ 1)
----------
9፤ ስለዚሁ እኛ ደግሞ ይህን ከሰማንበት ቀን ጀምረን የፈቃዱ እውቀት መንፈሳዊ ጥበብንና አእምሮን ሁሉ እንዲሞላባችሁ እየለመንን፥ ስለ እናንተ ጸሎትን አልተውንም።

10-11፤ በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ በእግዚአብሔርም እውቀት እያደጋችሁ፥

12፤ ከደስታም ጋር በሁሉ ለመጽናትና ለመታገሥ እንደ ክብሩ ጉልበት መጠን በኃይል ሁሉ እየበረታችሁ፥ በቅዱሳንም ርስት በብርሃን እንድንካፈል ያበቃንን አብን እያመሰገናችሁ፥ በነገር ሁሉ ደስ ልታሰኙ ለጌታ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እንለምናለን።

(ወደ ዕብራውያን 4:12)

" የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል፤"

6. በአዕምሮ መታደስ ተለወጡ

በእግዚአብሔር ቃል ዕዉቀት በማደግ መለወጥ ማለት ነዉ።

(ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:10)

" የፈጠረውንም ምሳሌ እንዲመስል እውቀትን ለማግኘት የሚታደሰውን አዲሱን ሰው ለብሳችሁታል።"

7. ይህን ዓለም አትምሰሉ

ዓለም ማለት ምን ማለት ነዉ?

(1ኛ የዮሐንስ መልእክት 2:15-16)

" ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ፤ በዓለም ያለው ሁሉ እርሱም የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮት ስለ ገንዘብም መመካት ከዓለም ስለ ሆነ እንጂ ከአባት ስላልሆነ፥ ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም።"

(ወደ ገላትያ ሰዎች ምዕራፍ 5)
----------
19፤ የሥጋ ሥራም የተገለጠ ነው እርሱም ዝሙት፥ ርኵሰት፥

20፤ መዳራት፥ ጣዖትን ማምለክ፥ ምዋርት፥ ጥል፥ ክርክር፥ ቅንዓት፥ ቁጣ፥ አድመኛነት፥

21፤ መለያየት፥ መናፍቅነት፥ ምቀኝነት፥ መግደል፥ ስካር፥ ዘፋኝነት፥ ይህንም የሚመስል ነው። አስቀድሜም እንዳልሁ፥ እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።

ስለ ገንዘብ መመካት ማለት ምን ማለት ነዉ?

(የማቴዎስ ወንጌል 6:24)

" ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።"

(የያዕቆብ መልእክት 4:4)

" አመንዝሮች ሆይ፥ ዓለምን መውደድ ለእግዚአብሔር ጥል እንዲሆን አታውቁምን? እንግዲህ የዓለም ወዳጅ ሊሆን የሚፈቅድ ሁሉ የእግዚአብሔር ጠላት ሆኖአል።"

ስለዚህ ምን እናድርግ ?

መፍትሄው ወደ ፀጋዉ ዙፋን ስር መዉደቅ ነዉ።

(ወደ ቲቶ ምዕራፍ 2)
----------
11፤ ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤

12-13፤ ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤

(የዮሐንስ ወንጌል 1:16)

" እኛ ሁላችን ከሙላቱ ተቀብለን በጸጋ ላይ ጸጋ ተሰጥቶናልና ሕግ በሙሴ ተሰጥቶ ነበርና፤"

የእግዚአብሔር መንግስት አንደኛ! መልካም ሳምንት

ለበለጠ መረጃ፦ 0916 - 82 23 55
0911 - 43 53 16

የእሁድ አምልኮ ፕሮግራም  አቅራቢ ፦ ዶ/ር ዳዊት ሀዬሶቀን ፦  21 - 09 - 2014ርዕስ፦ እግዚአብሔር መልካም ነዉ።የቃል ክፍል፦ ትንቢተ ናሆም 1:7(ትንቢተ ናሆም 1:7)" እግዚአብሔር...
31/05/2022

የእሁድ አምልኮ ፕሮግራም

አቅራቢ ፦ ዶ/ር ዳዊት ሀዬሶ

ቀን ፦ 21 - 09 - 2014

ርዕስ፦ እግዚአብሔር መልካም ነዉ።

የቃል ክፍል፦ ትንቢተ ናሆም 1:7

(ትንቢተ ናሆም 1:7)

" እግዚአብሔር መልካም ነው፥ በመከራ ቀንም መሸሸጊያ ነው፤ በእርሱ የሚታመኑትንም ያውቃል። "

፡ አምላካችን እግዚአብሔር በተራራም ሆነ በሸለቆ ፤ በከፍታም ሆነ በዝቅታ በደስታም ሆነ በሀዘን መልካም አምላክ ነዉ።

፡ እግዚአብሔር በሉአላዊ አሰራሩ ሲሰጥም ሆነ ሲከለክል መልካምነቱን በዛ አንለካዉም ፤ እንካስ እኛ በምናልፍበት መንገድ የሚረባንን እንኳን የማናዉቅ ስለሆንን እግዚአብሔር በራሱ መንገድ የሚረባንን እንዲመርጥልን ፈቃዳችንን ልንሰጠዉ ያስፈልጋል።

፡ እግዚአብሔር የመልካም ነገር ሁሉ ምንጭ ስለሆነ በህይወታችን እርሱን ፈልገን ስናገኝ ( ፈቃዱን ስንረዳ ) ከህይወት ምንጭ ጋር እንጣበቃለን ፤ በኑሮ አዙሪት ዉስጥ የምንፈልገው እና የምናገኘው ነገር ለህይወታችን መልስ አይሰጠንም ነገር ግን እግዚአብሔርን ማግኘት ከመልካምነቱ ሁሉ የመጥገቢያ መንገድ ነዉ።

፡ እኛ በክርስቶስ የዳንን አዲስ ፍጡራን ከእግዚአብሔር የተካፈልነዉ መልካምነት በዉስጥ ማንነታችን ( በመንፈሳችን) ሲሆን እርሱም በመንፈስ ቅዱስ በኩል የተካፈልነዉ የእግዚአብሔር ባህሪ ነዉ።

፡ ሰይጣን ሁል ጊዜ ከህይወታችን ሊያወጣ የሚፈልገዉ አንድ ትልቅ ሀሳብ አለ እርሱም እግዚአብሔር መልካም ነዉ የሚለዉ ነዉ ፤ የሰዉንም ልጅ ማሳት የጀመረው በዚሁ ሀሳብ ነዉ በዘፍጥረት መፅሐፍ እንደምናየዉ እግዚአብሔር ስድስቱንም ቀን መልካም ነዉ ያለዉን ስራ ፤ ለሄዋን መልካም እንዳልሆነ እና የሚቀር አንድ ነገር እንዳለ እርሱም የአይን መከፈት እንደሚባል በሀሰት ሰበካት ደግሞም አሳታት።

፡ በዚህ አለም ላይ የእግዚአብሔርን መልካምነት ጥያቄ ዉስጥ የሚያስገባ አንዳች መከራ ወይም ችግር የለም ሊኖርም አይችልም ፤ ነገር ግር የእግዚአብሔር ቃል በዘመን መጨረሻ ቀኖቹ አስጨናቂ እንደሚሆን እንድናዉቅ ያስረዳናል (ማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 24) ፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል በሌላ ስፍራ " በእኔ ሳላችሁ ሰላም እንዲሆንላችሁ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ ስለሚል ከአሸናፊዉ ጌታ ጋር ይህን አለም እናሸንፋለን።

የእግዚአብሔር መንግስት አንደኛ! መልካም ሳምንት

ለበለጠ መረጃ፦ 0916 - 82 23 55
0911 - 43 53 16

የእሁድ አምልኮ ፕሮግራም  አቅራቢ ፦ ፓስተር ሊሬ ቴካሶቀን ፦  14 - 09 - 2014ርዕስ፦ የእግዚአብሔር ቀን ቀርቧል።የቃል ክፍል፦ ትንቢተ ኢዮኤል ምዕራፍ 21ኛ ፦ የእግዚአብሔር ቀን የ...
22/05/2022

የእሁድ አምልኮ ፕሮግራም

አቅራቢ ፦ ፓስተር ሊሬ ቴካሶ

ቀን ፦ 14 - 09 - 2014

ርዕስ፦ የእግዚአብሔር ቀን ቀርቧል።

የቃል ክፍል፦ ትንቢተ ኢዮኤል ምዕራፍ 2

1ኛ ፦ የእግዚአብሔር ቀን የፍርድ ቀን ነዉ።

ትንቢተ ኢዮኤል 2:3

" እሳት በፊታቸው ትባላለች፥ በኋላቸውም ነበልባል ታቃጥላለች፤ ምድሪቱ በፊታቸው እንደ ዔድን ገነት፥ በኋላቸውም የምድረ በዳ በረሃ ናት፤ ከእነርሱም የሚያመልጥ የለም። "
(ትንቢተ ኢዮኤል 2:3)

እግዚአብሔር መንገድህን ያዉቃል አካሄድህንም ይለካል ( ይመዝናል ) ፤ በሃጢአት እና በበደል ስንመላለል ዝም የሚለን እና ፍርዱ የሚዘገየዉ በንስሐ እንድንመለስ ነዉ።

በዘረኝነት ፣ በዝሙት እንዲሁም በተለያየ አመፅ ስንሄድ እግዚአብሔር ይፈርዳል እንደዚህ በሚያደርጉት ላይ የእግዚአብሔር ፍርድ ከቤቱ ይጀምራል።

ደግሞም እግዚአብሔር ለተገፉት እና ፍርድ ለተጓደለባቸዉ ለእነርሱ ይፈርድላቸዋል ፤ እግዚአብሔር ችግርህ ፣ መከራህ እና ጉስቁልናህ ላይ ይፈርድበት እና ከህይወትህ ያስወግደዋል።

2ኛ፦ የእግዚአብሔር ቀን የመመለስ ቀን ነዉ።

(ትንቢተ ኢዮኤል ምዕራፍ 2)

16፤ ሕዝቡንም አከማቹ፥ ማኅበሩንም ቀድሱ፥ ሽማግሌዎቹንም ሰብስቡ፥ ሕፃናቱንና ጡት የሚጠቡትን አከማቹ፤ ሙሽራው ከእልፍኙ፥ ሙሽራይቱም ከጫጉላዋ ይውጡ።

17፤ የእግዚአብሔርም አገልጋዬች ካህናት ከወለሉና ከመሠዊያው መካከል እያለቀሱ። አቤቱ፥ ለሕዝብህ ራራ፥ አሕዛብም እንዳይነቅፉአቸው ርስትህን ለማላገጫ አሳልፈህ አትስጥ፤ ከአሕዛብ መካከል። አምላካቸው ወዴት ነው? ስለ ምን ይላሉ? ይበሉ።

18፤ እግዚአብሔርም ስለ ምድሩ ቀና፥ ለሕዝቡም ራራለት።

19፤ እግዚአብሔርም መልሶ ሕዝቡን። እነሆ፥ እህልንና ወይንን ዘይትንም እሰድድላችኋለሁ፥ እናንተም በእርሱ ትጠግባላችሁ፤ ከእንግዲህም ወዲያ በአሕዛብ መካከል መሰደቢያ አላደርጋችሁም።

እግዚአብሔር እየሄድን ማለትም እያመፅን ካለንበት መንገድ እንድንመለስ በዚህ ክፍል ይናገረናል። በፆምና በፀሎት እንዲሁም በእንባ ወደ እርሱ መመለስ ይሁንልን። ወደ እርሱ ሀሳብ እና መንገድ ስንመለስ እርሱም ወደ እኛ ይመለሳል ደግሞም ይራራልናል። ወደ ፆም ፣ ወደ ፀሎት ፣ ወደ እንባ ፣ ወደ ትህትና ተመለሱ።

3ኛ፦ የእግዚአብሔር ቀን የጉብኝት ቀን ነዉ

(ትንቢተ ኢዮኤል ምዕራፍ 2)

24፤ አውድማዎችም እህልን ይሞላሉ፥ መጥመቂያዎችም የወይን ጠጅንና ዘይትን አትረፍርፈው ያፈስሳሉ።

25፤ የሰደድሁባችሁ ታላቁ ሠራዊቴ አንበጣና ደጎብያ ኩብኩባና ተምች የበላቸውን ዓመታት እመልስላችኋለሁ።

26፤ ብዙ መብል ትበላላችሁ፥ ትጠግቡማላችሁ፤ ከእናንተም ጋር ተአምራትን የሠራውን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ስም ታመሰግናላችሁ፤ ሕዝቤም ለዘላለም አያፍርም።

ሀ. እግዚአብሔር በኢኮኖሚ በረከት ይባርካል

እግዚአብሔር በጉብኝቱ ቀን የቤታችሁን ጉስቁልና ይሽራል። ባለመታዘዝ ያለፋችሁን በረከት ቆጥሮ ስትመለሱ ይመልስላችኋል። እግዚአብሔር በመመለስ ዉስጥ ጉብኝት አለዉ።

ለ. እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ እና በፀጋ በረከት ይባርካችኋል።

(ትንቢተ ኢዮኤል ምዕራፍ 2)

28፤ ከዚህም በኋላ እንዲህ ይሆናል፤ መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈስሳለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ፥ ሽማግሌዎቻችሁም ሕልምን ያልማሉ፥ ጐበዞቻችሁም ራእይ ያያሉ፤

29፤ ደግሞም በዚያ ወራት በወንዶችና በሴቶች ባሪያዎች ላይ መንፈሴን አፈስሳለሁ፤

30፤ በላይ በሰማይ ድንቆችን አሳያለሁ፥ በታች በምድርም ደምና እሳት የጢስም ጭጋግ።

በስጋ ለባሽ ሁሉ ላይ መንፈሴን አፈሳለሁ የሚለዉ ጌታን በተቀበሉ ሁሉ ላይ እግዚአብሔር ከመንፈሱ ለማካፈል ፈቃዱ እንደሆነ ነገር ግን እኛ በመመለስ ዉስጥ ልንሆን እንደሚገባን ይናገራል።

ወደ እርሱ ስንመለስ እግዚአብሔር ከፀጋ ስጦታ አያጎድለንም ፤ በተለይ የክርስቶስን መምጣት የምትጠባበቅ ቤተክርስቲያን ከፀጋ ስጦታ አትጎድልም።

የእግዚአብሔር መንግስት አንደኛ! መልካም ሳምንት

ለበለጠ መረጃ፦ 0916 - 82 23 55
0911 - 43 53 16

በእግዚአብሔር መገኘት ይረስርሱ
14/05/2022

በእግዚአብሔር መገኘት ይረስርሱ

(መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 113)----------4፤ እግዚአብሔር በአሕዛብ ሁሉ ላይ ከፍተኛ ነው፥ ክብሩም ከሰማያት በላይ ነው። 5፤ እንደ አምላካችን እንደ እግዚአብሔር ማን ነው? በላይ የሚኖ...
12/05/2022

(መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 113)
----------
4፤ እግዚአብሔር በአሕዛብ ሁሉ ላይ ከፍተኛ ነው፥ ክብሩም ከሰማያት በላይ ነው።

5፤ እንደ አምላካችን እንደ እግዚአብሔር ማን ነው? በላይ የሚኖር፤

6፤ በሰማይና በምድር የተዋረዱትን የሚያይ፤

7-8 ከአለቆች ጋር ከሕዝቡም አለቆች ጋር ያኖረው ዘንድ ችግረኛን ከመሬት የሚያነሣ፥ ምስኪኑንም ከፋንድያ ከፍ ከፍ የሚያደርግ፤

9፤ መካኒቱን በቤት የሚያኖራት፥ ደስ የተሰኘችም የልጆች እናት የሚያደርጋት። ሃሌ ሉያ።

" ኢየሱስም። ሰው በእግዚአብሔር ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል ብሎ መለሰለት።"(የሉቃስ ወንጌል 4:4)
12/05/2022

" ኢየሱስም። ሰው በእግዚአብሔር ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል ብሎ መለሰለት።"
(የሉቃስ ወንጌል 4:4)

10/05/2022
" ታዳጊህ፥ የእስራኤል ቅዱስ፥ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ። እኔ የሚረባህን ነገር የማስተምርህ በምትሄድባትም መንገድ የምመራህ አምላክህ እግዚአብሔር ነኝ። "(ትንቢተ ኢሳይያስ 48:17)
07/05/2022

" ታዳጊህ፥ የእስራኤል ቅዱስ፥ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ። እኔ የሚረባህን ነገር የማስተምርህ በምትሄድባትም መንገድ የምመራህ አምላክህ እግዚአብሔር ነኝ። "
(ትንቢተ ኢሳይያስ 48:17)

06/04/2022

(ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች ምዕራፍ 2)
----------
7፤ ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥

8፤ በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ።

9፤ በዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው፥ ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው፤

10፤ ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥

11፤ መላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው።

12፤ ስለዚህ፥ ወዳጆቼ ሆይ፥ ሁልጊዜ እንደ ታዘዛችሁ፥ በእናንተ ዘንድ በመኖሬ ብቻ ሳይሆን ይልቁን አሁን ስርቅ፥ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፤

13፤ ስለ በጎ ፈቃዱ መፈለግንም ማድረግንም በእናንተ የሚሠራ እግዚአብሔር ነውና።

የእሁድ አምልኮ ፕሮግራም  አቅራቢ ፦ ፓስተር ደመቀቀን ፦  25 - 07 - 2014ርዕስ፦ እግዚአብሔር ከገመገም ፣ ከገደል ፣ ከጥግ ያወጣል።የቃል ክፍል፦ (መጽሐፈ ኢዮብ ምዕራፍ 39)----...
03/04/2022

የእሁድ አምልኮ ፕሮግራም

አቅራቢ ፦ ፓስተር ደመቀ

ቀን ፦ 25 - 07 - 2014

ርዕስ፦ እግዚአብሔር ከገመገም ፣ ከገደል ፣ ከጥግ ያወጣል።

የቃል ክፍል፦

(መጽሐፈ ኢዮብ ምዕራፍ 39)
----------
27፤ በአፍህ ትእዛዝ ንስር ከፍ ከፍ ይላልን?

ቤቱንስ በአርያም ላይ ያደርጋልን?
. .
28፤ በገደል ላይ ይኖራል፤

በገደሉ ገመገምና በጥጉ ያድራል።
. .
29፤ በዚያም ሆኖ የሚነጥቀውን ይጐበኛል፤

ዓይኑም በሩቅ ትመለከታለች። . .
30፤ ጫጩቶቹም ደም ይጠጣሉ፤

በድን ባለባትም ስፍራ እርሱ በዚያ አለ።

በቃሉ ክፍሉ ገመገም ማለት በአንድ ተራራ ላይ ያለ ስፍራ ሲሆን ፤ ከገደል በላይ ከተራራዉ በታች ያለ ስፍራ ሲሆን ንስን እንቁላሎችዋን የምትጥልበት ቦታ ነዉ ፤ ይህ ስፍራ ወደ ታች ሸለቆ ወይም ገደል ሲሆን ወደ ላይ ደግሞ ቀጥ ያለ ተራራ ነዉ ፤ ንስር እንቁላሎችዋን ከመጣል ባለፈ ጫጩቶችዋን የምትፈለፍለዉ እንዲሁም መብርረር እስኪጀምሩ በዚህ ስፍራ ታቆያቸዋለች። ይህ ስፍራ ገደሉም ሆነ ተራራዉ የሚያስፈራ ቢሆንም ለየትኛዉም የጠላት ጥቃት የሚያጋልጥ አይደለም።

እዮብ በመፅሃፉ እስከ ምዕራፍ 37 ድረስ ከደረሰበት ነገር የተነሣ በዚህ የገመገም ስፍራ ሆኖ የስንፍናን ቃል ይናገራል ፤ እግዚአብሔር ግን በዚህ የስንፍና ቃል አልተደሰተም።

ዛሬም እኛ በምን አይነት ገመገም ዉስጥ ነዉ የምንገኘው ? የስንፍናስ ቃል በአፋችን አለ?

(መጽሐፈ ኢዮብ ምዕራፍ 39)
----------
27፤ በአፍህ ትእዛዝ ንስር ከፍ ከፍ ይላልን?

ቤቱንስ በአርያም ላይ ያደርጋልን?

በዚህ ስፍራ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ንስርን ከገመገም አዉጥቼ ወደ አርያም ( ሰማይ ) ከፍ ከፍ እንዲል የማደርግ ፤ ቤቱንም በዚያ የማደርግ ፤ ዳግመኛም ወደዚያ ገመገም እንዳይመለስ የማደርግ እኔ ነኝ ይላል።

በጌታ ወንድምች እና እህቶች የሆናችሁ ባላችሁበት የገመገም ስፍራ ሆናችሁ እግዚአብሔር አትሞግቱ እግዚአብሔር ሁሉን ያደርግ ዘንድ ቻይ ነዉ ሀሳቡም ከቶ ሊከለከል አይችልም እና ከገባችሁበት ገመገም ፣ ገደል ወይም ጥግ በጌታ በእየሱስ ስም ያወጣችኋል።

የእግዚአብሔር መንግስት አንደኛ! መልካም ሳምንት

ለበለጠ መረጃ፦ 0916 - 82 23 55
0911 - 43 53 16

02/04/2022

የእሁድ አምልኮ ፕሮግራም

አቅራቢ ፦ መጋቢ ዮሴፍ

ቀን ፦ 18 - 07 - 2014

ርዕስ፦ ክፉ ቀን

የቃል ክፍል፦

(ወደ ኤፌሶን ሰዎች ምዕራፍ 6)
----------
10፤ በቀረውስ በጌታና በኃይሉ ችሎት የበረታችሁ ሁኑ።

11፤ የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ።

12፤ መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።

13፤ ስለዚህ በክፉው ቀን ለመቃወም፥ ሁሉንም ፈጽማችሁ ለመቆም እንድትችሉ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ አንሡ።

በቀረውስ ከዚህ በኋላ ባላችሁ ቀናት በጌታና በሀይሉ ችሎት የበረታችሁ ሁኑ ፤ የጌታ ሀይል ከሁሉ የሚበልጥ ሀይል ሁሉን የፈጠረ ሀይል ሲሆን ይህ በዉስጣችሁ መንፈስ ቅዱስ ባስቀመጠዉ ሀይል በርቱ።

ቁጥር 13 ፦ ስለዚህ በክፉው ቀን ለመቃወም፥ ሁሉንም ፈጽማችሁ ለመቆም እንድትችሉ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ አንሡ።

በክፉ ቀን ለመቋቋም ፣ ለመቃወም እንድንችል የጦር ዕቃን ሁሉ እንድንለብስ ታዟል።

በመፅሀፍ ቅዱሳችን ክፉ ቀን ካጋጠማቸዉ እና ክፉዉን ቀን ከጌታ ጋር ያሸነፉ የእግዚአብሔር ሰዎችን እንመልከት።

ዳንኤል ፦ በአንበሳ ጉድጓድ ውስጥ ከመጣሉ በፊት ፤ ጠላቶቹ እርሱ ላይ ስለቀኑ ሰበብ ይፈልጉበት ነበር ፤ እርሱ ግን ታማኝ ነበር።

የታመነ ፦ ስህተት እና በደል አልተገኘበትም እና ከአምላክ ህግ በቀር በዳንኤል ላይ ሌላ ሰበብ እና በደል ያገኙበት አልቻሉም።

ዳንኤል፦ በአንበሳ ጉድጓድ ሊጣል የለበሰዉ ልብስ (ቅንነት) ነበር። ይህ ለእርሱ የጦር ዕቃዉ ነበር ከአንበሶች አፍ ወይም ከክፉ ቀን እንድናመልጥ የእግዚአብሔርን የጦር ዕቃ ልናነሳ ያስፈልጋል ዳንኤልን ከአንበሳ አፍ ያዳነዉ የተገኘበት ቅንነት ነበር ።

(ትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ 6)
----------
21፤ ዳንኤልም ንጉሡን። ንጉሥ ሆይ፥ ሺህ ዓመት ንገሥ።

22፤ በፊቱ ቅንነት ተገኝቶብኛልና፥ በአንተም ፊት ደግሞ፥ ንጉሥ ሆይ፥ አልበደልሁምና አምላኬ መልአኩን ልኮ የአንበሶችን አፍ ዘጋ፥ እነርሱም አልጐዱኝም አለው።

የእግዚአብሔር መንግስት አንደኛ! መልካም ሳምንት

ለበለጠ መረጃ፦ 0916 - 82 23 55
0911 - 43 53 16

Address

Around Old Bus Station
Awassa

Telephone

+251916822355

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when The Crown of Righteousness International Church posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share