Apostolic church firex man

Apostolic church firex man Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Apostolic church firex man, Religious organisation, Hawassa worancha አጥብያ, Awassa.

30/12/2021

ሚስት አጣሁ
"""""""""""""""
አንድ ወጣት ሚስት ማግባት ፈለገ። በዙሪያውም ብዙ ቆነጃጂት ሞልተዋል።ወጣቱ ግን ለአይኑ እምትሞላ ፣ ለትዳሩ የምትበጅ ፣ ሙሉ የሆነች ቆንጆ ና ውብ ሴት የሚላት የትኛዋ እንደሆነች መምረጥ ተቸገረ።ሴት በሞላበት አገር ሚስት ፍለጋ ቢናውዝም ይችን ላግባ ብሎ መምረጥ እና መወሰን ተሳነው።ብቻ ቢፈልግም ቢያስፈልግም ሚስት አጣ።
ከዕለታት አንድ ቀን ምን ይሻላ ብሎ ሰው ሲያማክር እራቅ ወዳለ አገር አንድ ጠቢብ ሰው ስላሉ እሳቸው ጋር ቢሄድ አንዳች መፍትሄ እንደሚያገኝ ነገሩትና እርሱም ወደዛ አሉ ወደተባሉ ጠቢብ ሽማግሌ ዘንድ ይሄዳል።ጠቢቡ ዘንድም ደርሶ የበቆሎ ማሳ ቁጭ ብለው ሲጠብቁ አገኛቸው።ሚስት ያጣው ወጣትም ከማሳው ዳር ካለው የእርሻው ዲብ ላይ ጺማቸውን አንጀርግገው በግርማ ሞገስ ቁጭ ብለው የበቆሎ ማሳ ወደሚጠብቁት ጥበበኛ ሽማግሌ ጠጋ አለና እንደምን ዋሉ አባቴ አላቸው።እርሳቸውም እግዚያብሄር ይመስገን እንደምን ዋልክ ልጀ አሉት። ጥበበኛ ነወት ተብየ መምጣቴ ነው አላቸው።እርሳቸውም በእርጋታ ትኩር ብለው እያዩት " ምን እንድረዳህ ፈልገህ ነው የመጣኸው? " ብለው ጠየቁት።እርሱም "ሚስት አጣሁ !..."ብሎ የመጣበትን ጉዳይ አንድ በአንድ አስረዳቸው።
እርሳቸውም " አይይ ልጀ !! በል ና ተከተለኝ " ብለው ከበቆሎው ማሳ ዳር ቆሙና " የመጣህበትን እንድነግርህ ከዚህ ከምታየው የበቆሎ ማሳ ከዚህ ከቆምንበት ጀምርና እስከ ዳር ድረስ ውስጥ ለውስጥ ገብተህ ከዚህ ሁሉ የበቆሎ እሸት በመጠኑ ከፍ ያለ እና አሪፍ እምትለውን አንድ ብቻ የበቆሎ እሸት ዘንጥለህ አምጣልኝ ። ነገር ግን ማሳሰቢ ልስጥህ ።
1ኛ ከዚህ ከቆምክበ ከፊትህ ካለው እሸት ወደ ውስጥ ብገባም ከዚህ የበለጠ እሸት አላገኝም ብለህ ካመንክ እዚሁ ዘንጥለህ ልትሰጠኝ ትችላለህ።
2ኛው ማሳሰቢያ ከዚህ ጀምረህ እስከ ማሳው ዳር ድረስ ወደፊት እየተራመድክ መምረጥ ትችላለህ ነገር ግን ልብ በል አንዴ ያለፍከውን እሸት እንደገና ወደ ቡሀላ ተመልሰህ መቁረጥ አትችልም ወደፊት ብቻ።
3ኛው ማሳሰቢያ አጥቻለሁ ብለህ ባዶ እጅህን መምጣት አትችልም።
4ኛው እና የመጨረሻው ደግሞ ከዚህ ሰፊ የበቆሎ ማሳ አንድ የበቆሎ እሸት ብቻ ነው ቆርጠህ እምታመጣልኝ። መጀመር ትችላለህ " አሉትና ተመልሰው ቁጭ አሉ ወጣቱም ወደ በቆሎው ገባና የተሻለ የሚለውን በቆሎ መፈለግ ጀመረ። ሁሉም እሸት አማረው አይን አዋጅ ሆነበት ትንሽ ገባ እንዳለ በጣም የሚያማልል እሸት አየና ሊቆርጥ አሰበና " ወደፊት ከዚህ ከሚታየኝ የበለጠ ትልልቅ እና እሚያማምር ቢኖርስ ? ብሄድ ይሻላል"። ብሎ ፍለጋውን ቀጠለ።ነገር ግን ወደ ፊት በሄደ ቁጥር እንደ ቅድሙ የሚያምር ሳይሆን ጥራቱ እየቀነሰ ሄደ። አሁንም ወደ ፊት ጥሩ እሸት አገኛለሁ እያለ መዳከር ያዘ።ነገር ግን ጭራሽ ከቅድሙ የባሰ በመጠኑ ያነሰ፣ ገና ለጋ የሆነ እና ትል የበላው እየሆነ መጣ።ወጣቱም ወደ ኋላ መመለስ አትችልም ስለተባለ ምናለ ቅድም ዳር ላይ ቆርጨ በነበር እያለ እየተፀፀተ አሁንም ተስፋ ሳይቆርጥ ወደፊት ልክ ቅድም ስገባ እንዳየሁት እሚያማምር እሸት አገኝ ይሆናል እያለ በተስፋ ወደ ፊት ፍለጋውን ቀጠለ።እሚያሳዝነው የተባለውን እሸት ሳይቆርጥ በገባበት ተቃራኒ የእርሻው ዳርቻ ሊወጣ ሲዳረስ እንዳለ ግማሹን ወፍ የጠረጠረው እየሆነ መጣ።" እስኪ እንደ ቅድሙ ዳር ላይ ጥሩ በቀሎ ባገኝ ብሎ የእርሻው ጫፍ ላይ ብቅ አለ ነገር ግን እሚገርመው ጭራሹንም ወፍ እልም አድርጎ የጨረሰውና ቆረቆንዳ ብቻ ሁኖ አገኘው።ወደ ቡሃላ እንዳይመለስ ወደ ኋላ መመለስ አትችልም ተብሏል።ባዶ እጁን እንዳይመለስ ምንም ቢሆን ባዶ እጅህን እንዳትመለስ ተብሏል።ስለዚህ አማራጭ ስላጣ ወፍ የበላውን የበቆሎ ቆረቆንዳ አንዱን ዘንጥሎ ወደ ጠቢቡ ተመለሰ እና ከፊታቸው ቆመ።
እርሳቸም "እስኪ ያመጣኸውን አሳየኝ "አሉት።እርሱም አንድም በላዩ ላይ ጥሬ የለለውን ቆረቆንዳ ሰጣቸውና በሀፍረት ፀጥ ብሎ ቆመ።"ይህንን ነው የተሻለ ያገኘኸው?" ብለው ቢጠይቁት እርሱም በሀፍረት አባቴ ያው የተሻለ አገኛለሁ ብየ ስፈልግ ሳላስበው ወፍ ከበላው ደረስኩ " አለ እየተንተፋተፈ። ቁጭ በል እስኪ አሉና "አየህ የኔ ልጅ ሚስት እያማረጡ አንዷን ከአንዷ እያመረጡ መኖርም ልክ እንደዚህ ነው።አብዝቶ መምረጥ መጨረሻ ከምራጭ ይጥላልና ሚስት ከእግዚያብሔር ስለሆነች በአንተ ምርጫ አይሆንም።ከፊትህ ያለችውን ሚስት አድርግ "አሉት
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ምን ተማራችሁ? ሸር ሸር አድርጉት

03/10/2021
Wara yenafekew b***a          Amen 🙏
20/03/2021

Wara yenafekew b***a
Amen 🙏

ሀዋሳ 01 እናት አጥብያ       ያስጀመሬው እግ/ር ነውናያስጀመሬው አምላካችን እስከ        ፍንሽንግ ድሬስ እንድያበቃፀልዩልን
26/12/2020

ሀዋሳ 01 እናት አጥብያ
ያስጀመሬው እግ/ር ነውና
ያስጀመሬው አምላካችን እስከ
ፍንሽንግ ድሬስ እንድያበቃ
ፀልዩልን

+ Me all Apositolicልዩ ነን የምል ሁሉ አሜን ይበል
31/10/2020

+ Me all Apositolic
ልዩ ነን የምል ሁሉ አሜን ይበል

አንድ ጌታ+ አንድ ሀይማኖት+ አንድት ጥምቀት+ = የምትስል ነች እውነተኛ የሱስ መንገድ•               Add me all apositolic #
27/10/2020

አንድ ጌታ+ አንድ ሀይማኖት+ አንድት ጥምቀት+ = የምትስል ነች እውነተኛ የሱስ መንገድ•
Add me all apositolic #

Amen ፔጁን ላይክ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
02/09/2020

Amen
ፔጁን ላይክ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ

Address

Hawassa Worancha አጥብያ
Awassa
112233

Telephone

+251937306177

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Apostolic church firex man posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share