Gobezu Assefa Negiya /አጠቃላይ የሕትመትና የማስታወቂያ ሥራ ሀዋሳ

  • Home
  • Ethiopia
  • Awassa
  • Gobezu Assefa Negiya /አጠቃላይ የሕትመትና የማስታወቂያ ሥራ ሀዋሳ

Gobezu Assefa Negiya /አጠቃላይ የሕትመትና የማስታወቂያ ሥራ ሀዋሳ https://t.me/https://whatsapp.com/dl/ “Ye are the light of the world. A city that is set on an hill cannot be hid.”
— Matthew 5:14 (KJV)
የወንጌል አገልጋይ ነኝ!

''የአርቲስት ሰማኸኝ በለው አሟሟት ይመርመር ይጣራልን ማብራሪያ እንጠብቃለን!'' ይህንን ነገር በቸልታ የምናየው አይሆንም፣ ለሞት ያበቃው የጤና ችግር ይብራራልን?'' ወዳጆቹ እና አድናቂዎቹ...
16/06/2026

''የአርቲስት ሰማኸኝ በለው አሟሟት ይመርመር ይጣራልን ማብራሪያ እንጠብቃለን!'' ይህንን ነገር በቸልታ የምናየው አይሆንም፣ ለሞት ያበቃው የጤና ችግር ይብራራልን?'' ወዳጆቹ እና አድናቂዎቹ......

አርቲስት ሰማኸኝ በለው ባለፉት ጥቂት ወራት Glow Ethio-Turkiye ወደሚባል ድርጅት ሄጄ የክብደት መቀነስ ህክምና በመከታተል ላይ ነኝ ብሎን በየጊዜው ያስመዘገበውን የክብደት ለውጥ(weight loss progress) እያሳየን በርታ በሉኝ እያለ ድርጅቱንም በ Social Media ላይ promote ሲያደርግ ሲያስተዋውቅ የምናውቀው ሰውዬ ከእለታት በአንዱ ጠዋት ከመኝንታ ስንነሳ ህልፈተ ህይወቱን ሰማን።

እንዴት ሊሆን ይችላል?

አርቲስት ሰማኸኝ በለው ለክብደት መቀነስ የተጠቀመው መድሃኒት ሳይረዳው ቀርቶ ነው ወይንስ መድሃኒቱ ራሱ ጎድቶት ነው?

ነው ወይንስ በህመም ምክንያት እየተከሰተ የነበረውን የክብደት መቀነስ ነው ልክ በህክምና ክትትል የተገኘ achievement አስመስለው መስታወቂያ ሲሰሩበት ሌሎችንም ሊያጠምዱበት ሲሯሯጡ የከረሙት ?

ይህንን ነገር በቸልታ የምናየው አይሆንም፣ ለሞት ያበቃው የጤና ችግር ይብራራልን!!

ዝም ብሎ በደፈናው ብቻ "ባደረበት ህመም በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ" የምትለው Generic ዜና ዕረፍት sense አትሰጥም።

ይህ አይነቱ የሞት ዜና በብዙ አርቲስቶች ላይ በጣም ተደጋገመ ህዝቡም ለምን ብሎ መጠየቅ አልቻለም ለምን?

ማብራሪያ እንጠብቃለን?
ወዳጆቹ!

እህቶች ከእኛ ላይ ዱላችሁን መልሱ!
15/06/2026

እህቶች ከእኛ ላይ ዱላችሁን መልሱ!

የሞት ቅጣት በኢትዮጵያ የወንጀል ህግሀገራችን ኢትዮጵያ የሞት ቅጣትን በወንጀል ህጓ ዉስጥ እዉቅና በመስጠት ተግባራዊ እያደረገች ያለች ሀገር ናት፡፡ በወንጀል ህጋችን ዉስጥ የሞት ቅጣት በተለ...
04/06/2026

የሞት ቅጣት በኢትዮጵያ የወንጀል ህግ

ሀገራችን ኢትዮጵያ የሞት ቅጣትን በወንጀል ህጓ ዉስጥ እዉቅና በመስጠት ተግባራዊ እያደረገች ያለች ሀገር ናት፡፡ በወንጀል ህጋችን ዉስጥ የሞት ቅጣት በተለዬ ሁኔታ ከባድ ተብለው ለሚገመቱ ወንጀሎች የሚደነገግ የቅጣት ዓይነት ነው፡፡

በወንጀል ህጉ አንቀጽ 117(1) መሰረት የሞት ቅጣት በአጥፊዎች/ጥፋተኛ በተባሉ ሰዎች ላይ የሚፈረደው የሚከተሉት ዋና ዋና ነጥቦች ከግምት ውስጥ ገብተው ነው፡፡ እነኚህም፡-
1. የወንጀል ድርጊቱ በሞት የሚያስቀጣ ስለመሆኑ ወንጀሉን በሚያቋቋመው የህጉ ልዩ ክፍል በግልጽ ተደንግጎ ሲገኝ፣
2. ወንጀሉ ፍፃሜ ያገኘ ማለትም በሙከራ ደረጃ ላይ ያልተገታ ሲሆን፣
3. ቅጣቱን የሚያቀልለት ምንም አይነት ማቅለያ ምክንያት የሌለ እንደሆነ፣
4. የተፈፀመው ወንጀል እጅግ በጣም ከባድና ወንጀለኛው በተለይ አደገኛ ሲሆን እና
5. አጥፊው የቅጣት ፍርድ በሚሰጥበት ጊዜ እድሜው 18 የሞላዉ ከሆነ ነዉ፡፡

ከላይ ከተጠቀሱት መስፈርቶች በተጨማሪ የተላለፈዉ የሞት ቅጣት ለመጽናትና ተፈጻሚ ለመሆን የአገሪቱን ርዕሰብሔር ፈቃድ አስፈላጊ ነዉ፡፡ በዚህ ረገድ ምንም እንኳን በህግ የሞት ቅጣት ያለ ቢሆንም በርዕሰብሄሩ መፅናት የሚገባው በመሆኑ እና በሌሌች እንደ ይቅርታና ምህረት ምክንያቶች በአገራችን ተፈፃሚነቱ ዝቅተኛ ነዉ፡፡

በሌላ በኩል አፈጻጸሙን ስንመለከት የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው ሰዎች ፍርዱ በህዝብ ፊት በአደባባይ፣ በስቅላት ወይም በማንኛውም ኢ-ሰብዓዊ መንገድ ሊፈጸምባቸው እንደማይገባ በአንቀጽ 117(3) ስር በግልጽ ተደንግጓል፡፡ ቅጣቱ የሚፈጸመዉ የሚመለከተዉ ማረሚያ ቤት አስተዳደር የበላይ ሃላፊ በሚወስነዉ የአፈጻጸም ዘዴ/ሁኔታ በማረሚ ቤቱ ቅጥር ጊቢ ዉስጥ ይሆናል፡፡ የሞት ቅጣቱ ከመፈጸሙ በፊት በተቀጪዉ ላይ ምንም አይነት የበቀል እረምጃ፣ የአካል ጉዳትና ስቃይ ማድረስ በፍጹም የተከለከለ ነዉ፡፡

👉የሞት ቅጣት ታግዶ የሚቆይበት ሁኔታ (አንቀጽ 119)

ነብሰ ጡር ሴቶች እና ኢ-ሀላፊ እና ከፊል የወንጀል ሀላፊነት ላይ የሚገኙ እና የታመሙ ሰዎች ምንም እንኳን የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው ቢሆንም ከዚሁ ሁኔታ ውስጥ ወጥተው እስኪገኙ ድረስ የሞት ፍርዱ ሳይፈጸም ተንጠልጥሎ ይቆያል፡፡ ነብሰ ጡሯ ፍርደኛ በሰላም ከተገላገለች እና ህጻኑን ማሳደግ እንዳለባት ፍ/ቤቱ ሲያምን የሞት ቅጣቱን ወደ እድሜ ልክ እስራት ሊለውጥላት ይችላል፡፡
ከዚህ ሌላ ይህ አይነቱ ቅጣት በምህረት ወይም በይቅርታ ሊለወጥ ወይም ቀሪ ሊሆን እንሚችል የወንጀል ህጉ በአንቀጽ 120 (1 እና 2) ስር በግልጽ ይደነግጋል፡፡

👉 የሞት ቅጣት የተፈረደበት ሰዉ ቅጣቱ እስኪፈጸም የሚቆይበት ሁኔታ

የሞት ቅጣት የተፈረደበት ሰዉ ቅጣቱ እስኪጸናና እስኪፈጸም ድረስ ጽኑ እስራት የተፈረደበት እስረኛ እስራቱን በሚፈጽምበት ሁኔታ የማረሚያ ቤት አስተዳደር አስፈላጊዉን የደህንነት ጥበቃ እያደረገለት ታስሮ የሚቆይ ይሆናል፡፡

❤️🤍🏆 𝐀𝐑𝐒𝐄𝐍𝐀𝐋 𝐋𝐈𝐅𝐓 𝐏𝐑𝐄𝐌𝐈𝐄𝐑 𝐋𝐄𝐀𝐆𝐔𝐄 𝐓𝐑𝐎𝐏𝐇𝐘 𝐅𝐎𝐑 𝐓𝐇𝐄 𝐅𝐈𝐑𝐒𝐓 𝐓𝐈𝐌𝐄 𝐀𝐅𝐓𝐄𝐑 𝟐𝟐 𝐋𝐎𝐍𝐆 𝐘𝐄𝐀𝐑𝐒! 😁
24/05/2026

❤️🤍🏆 𝐀𝐑𝐒𝐄𝐍𝐀𝐋 𝐋𝐈𝐅𝐓 𝐏𝐑𝐄𝐌𝐈𝐄𝐑 𝐋𝐄𝐀𝐆𝐔𝐄 𝐓𝐑𝐎𝐏𝐇𝐘 𝐅𝐎𝐑 𝐓𝐇𝐄 𝐅𝐈𝐑𝐒𝐓 𝐓𝐈𝐌𝐄 𝐀𝐅𝐓𝐄𝐑 𝟐𝟐 𝐋𝐎𝐍𝐆 𝐘𝐄𝐀𝐑𝐒! 😁

Arsenal ዋንጫ ከበላ መብላት ያለበት እነዚህ 3 ሰዎች በሊጉ ውስጥ እያሉ መሆን አለበት፡፡ 1.  #ፔፕ የዓለም ምርጡ አሰልጣኝ ነው፣ ነገር ግን ቡድን ሰርቶ አያውቅም (የከበርቴዎች አሰል...
22/03/2026

Arsenal ዋንጫ ከበላ መብላት ያለበት እነዚህ 3 ሰዎች በሊጉ ውስጥ እያሉ መሆን አለበት፡፡

1. #ፔፕ የዓለም ምርጡ አሰልጣኝ ነው፣ ነገር ግን ቡድን ሰርቶ አያውቅም (የከበርቴዎች አሰልጣኝ ስለሆነ)፣ በዚህ እረገድ አርቴታ ከዜሮ ተነስቶ፣ ቡድን ገንብቶ በዓለም ላይ ምርጡን አሰልጣኝ ማሸነፍ ከቻለ ትልቅ ትርጉም ያለው ዋንጫ ይሆናል። ለዚህም ፔፕ ሲቲን ሳይለቅ፣ በዙፋኑ ላይ እያለ ዋንጫውን ማሳካት አለብን፡፡

2. #ሮድሪ የተባለ በግርግር ባሎንዶር የወሰደ የአንድ ሲዝን ተጫዋች ደግሞ ስለ አርሰናል የማሸነፍ ሜንታሊቲ ብዙ ሲበጠረ*ቅ ነበር። ቅሉ አሁን የእራሱ የማሸነፍ ወኔ ጠፍቶ ሽንፈቱን ዳኛ ላይ የሚደፈድፍ (በዚህም ቅጣት የቀመሰ)፣ ገፍ አወጣሽ ተጫወች በሊጉ ውስጥ እያለ ብቻ ሳይሆን ከእሱ ጋር ተፎካክረን ዋንጫውን መውሰድ በትንሹም ቢሆን ለእንዲህ አይነት እርባና ቢስ ሰዎች ጥሩ ሌሰን የምንሰጥበት ስለሚሆን ትርጉም ይኖረዋል።

3. #ሲልቫ ስለተባለ ጡጦ እንደተቀማ ህፃን እዬዬ የማይሰለቸው አልቃ*ሻ ተጫዋች እያዬ ባሸንፍ ደስ ይለኛል።

የሚገርመው ይኸን ለማሳካት የሚቀረን ጥቅት ሰዓታት ብቻ መሆኑ ነው፡፡

ዛሬ ግዴታ ማሸነፍ አለብን
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

ተወዳጁ አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ***************** ተወዳጁ የኪነ-ጥበብ ባለሙያ ነጻነት ወርቅነህ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።በፊልም እና ቲያትር ተዋናይነት፣...
16/01/2026

ተወዳጁ አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
*****************

ተወዳጁ የኪነ-ጥበብ ባለሙያ ነጻነት ወርቅነህ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

በፊልም እና ቲያትር ተዋናይነት፣ በቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢነት እና በሌሎች የጥበብ ስራዎች ውስጥ ስመጥር እና ተወዳጅ ከሆኑ የጥበብ ሰዎች አንዱ የሆነው ነጻነት ወርቅነህ ባደረበት ህመም በድንገት ህይወቱ ማለፉ ነው የተገለፀው።

ለበርካታ ዓመታት በኢቢኤስ ቴሌቪዥን የሚተላለፈው የቤተሰብ ጨዋታ ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ የሆነው ነጻነት ወርቅነህ ባለትዳርና የ3 ልጆች አባት እንደነበር ከኢቢስ ቴሌቪዥን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በአሁኑ ወቅት ማስተር አብነት ከበደ በሀገራችን በሚገኝ አንድ ትልቅ ሆስፒታል ህክምናውን እየተከታተለ ይገኛል። በፈጣሪ እርዳታ አሁን ያለበት ሁኔታ ጥሩ የሚባል ነው። የሀኪሞችን ውሳኔ ተከትሎ...
19/12/2025

በአሁኑ ወቅት ማስተር አብነት ከበደ በሀገራችን በሚገኝ አንድ ትልቅ ሆስፒታል ህክምናውን እየተከታተለ ይገኛል። በፈጣሪ እርዳታ አሁን ያለበት ሁኔታ ጥሩ የሚባል ነው። የሀኪሞችን ውሳኔ ተከትሎ በቀጣይ ከሀገር ውጪ አልያም በሀገር ውስጥ ህክምናውን ተከታትሎ በቅርቡ ወደ በጎ ስራው ይመለሳል ብለን ተስፋ እናደርጋለን። የሚኖረውን አዲስ ነገር የምናሳውቃቹ ይሆናል። አሁንም በፀሎት አስቡት። እናመሰግናለን።

NB:- በማስተር አብነት እውቅና ለመላው ኢትዮጽያውያን የተላለፈ መልዕክት።

Address

South
Awassa
TABOR

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gobezu Assefa Negiya /አጠቃላይ የሕትመትና የማስታወቂያ ሥራ ሀዋሳ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Gobezu Assefa Negiya /አጠቃላይ የሕትመትና የማስታወቂያ ሥራ ሀዋሳ:

Shortcuts

Share