Amanuel

Amanuel አማኑኤል

18/05/2025

"Dear children, let us not love with words or speech but with actions and in truth." —1 John 3:18

16/10/2024

?
ሀ. ዘፈን የአጋንንት ሥራ ስለሆነ፡፡ አጋንንት ይዘፍናሉና፡፡
የወደቁ መላእክት መዘመር ስለማይችሉ ይዘፍናሉ፤
➭ መጽሐፍ ቅዱስ ‹‹በዚያም አጋንንት ይዘፍናሉ›› በማለት ስለ አጋንንት ዘፋኝነት ይናገራል፡፡ ኢሳ 13 ፥ 21። አትዝፈኑ ማለት የአጋንንትን ሥራ አትሥሩ ማለት መሆኑን መረዳት ተገብ ነው።
እኛ ክርስቲያኖች የራሳችን የሆነ ተግባር በእግዚአብሔር ቃል ስለተሰጠን የአጋንትን ባንተገብር መልካምና መረዳትም ነው!!

ለ. ዘፋኝነት ‹‹የስጋ ስራ›› በመሆኑ ፡፡ ገላ 5 ፥ 21
" የሥጋ ሥራም የተገለጠ ነው፡፡ እርሱም ዝሙት .. ስካር፣ ዘፋኝነት እንደነዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግስት አይወርሱም"ገላ 5 ፥21
‹‹በመንፈስ ተመላለሱ፤ የስጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ›› ገላ 5 ፥ 16።
እኛ ክርስቲያኖች መንፈሳዊያን ስለሆንን የስጋ ሥራ አይመለከተንም፤

ሐ. ዘፈን በአዲስ ኪዳን ስለተወገዘ፤ ዘፋኝነትም ስለተከለከለ፡፡
‹‹በስካር እና በዘፈን የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃል፡፡›› ይለናል 1ኛ ጴጥ 4 ፥ 3
‹‹በቀን እንደምንሆን በአግባቡ እንመላለስ፡፡ በዘፈንና በስካር አይሁን›› ፡፡ ሮሜ 13 ፥ 13
እኛ ክርስቲያኖች በአዲስ ኪዳን የታደስን ነንና ያለፈውን ማንነት አንመኝም

መ. ዘፈን ርኩሰትን የምጋብዝ በመሆኑ፤
‹‹በቀን ሲዘፍኑ እንደ ተድላ ይቆጥሩታል፡፡ ነውረኞችና ርኩሳን ሆነው ከእናንተ ጋር ሲጋበዙ በፍቅር ግብዣ ይዘፍናሉ፡፡›› በማለት ዘፋኝነትን የርኩሳንና የነውረኞች ተግባር አድርጎታል፡፡ 2ኛ ጴጥ 2 ፥ 13-15።
ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ እነዚህን የዘፈን ሰዎች በሌላ ማንነታቸው ሲገልጻቸው ደግሞ ‹‹ምንዝር የሞላባቸው ኃጢአትን የማይተዉ ዓይኖች አሏቸው፡፡ የማይፀኑትንም ነፍሳት ያታልላሉ፡፡ ለመኘት የተለመደ ልብ አላቸው፡፡ የተረገሙ ናቸው፡፡›› ይላል 2ጴጥ 2 ፥ 13-15።
እኛ ክርስቲያኖች የተጠራነው ለቅድስና ስለሆነ

ማጠቃለያ ፡-
ይህ ከብዙ በጥቂቱ ሲሆን ክርስትያኖች ክርስቶስን ለመምሰል ከማይጋብዙ ከከንቱ ተግባር ተለይተን የተጠራንበት ልዩ ጥሪ በማሰብ ለክርስቶስ የሚሆን ሕይወት መኖር እንድንችል እግዚአብሔር ይርዳን አሜን ።
ይህንን እንዳዘጋጅ በጽሑፉ ያነሳሱ ወዳጆቼን አመሰግናለሁ!

ያስን የኛ (ወ/ዊ) Yasin Yegna
የወላይታ ቃ/ሕ ቤተክርስቲያን ምክትል ዋና ጸሐፊ

https://youtu.be/IrQZZsgrKrA?si=p0pApe-gdvF0dh8b

16/10/2024
11/10/2024

ዶክተር ለአለም
በአዲስ አልበም
ዶክተር ለአለም ጥላሁን ከረዥም አመታት በኋላ በአዲስ የዝማሬ አልበም እየመጣ ነው። አልበሙ ከፈረንጆች አዲስ አመት በኋላ ይለቀቃል።
ከዶክተር ለአለም የቀድሞ ዝማሬዎች የቱን ታስታውሳላችሁ...?

Address

Piassa
Awassa
BENSA

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amanuel posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share