Salvation Day in Christ International Church /የመዳን ቀን በክርስቶስ ቤተክርስቲያን

  • Home
  • Ethiopia
  • Awassa
  • Salvation Day in Christ International Church /የመዳን ቀን በክርስቶስ ቤተክርስቲያን

Salvation Day in Christ International Church /የመዳን ቀን በክርስቶስ ቤተክርስቲያን Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Salvation Day in Christ International Church /የመዳን ቀን በክርስቶስ ቤተክርስቲያን, Religious organisation, Piazza, Awassa.

The main purpose of the Salvation Day in Christ's International Church is to ensure that the day of salvation is saved by practicing what is written now so that God will not deceive mankind on earth without believing in Christ.

28/08/2021

እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም

04/04/2021
ወንጌል ለአለም ሁሉእንዲህም አላቸዉ፤ ወደ አለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ ማርቆስ 16፡15በዚህ አስቸጋር ዘመን ለሰዉ ልጅ በተለያዩ ጊዜያት ለሚመጡ ችግሮች የሚደርስለትን ሰዉ...
29/03/2021

ወንጌል ለአለም ሁሉ
እንዲህም አላቸዉ፤ ወደ አለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ ማርቆስ 16፡15

በዚህ አስቸጋር ዘመን ለሰዉ ልጅ በተለያዩ ጊዜያት ለሚመጡ ችግሮች የሚደርስለትን ሰዉ ማግኘት እጅግ አዳጋች እየሆነ መጥቷል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ እንደተፃፈዉ ነገር ግን በመጨረሻዉ ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ ይህን እወቅ፡፡(ወደ ጥሞቶዎስ 3፡1)፡፡ እንግዲህ ወደ ሞት የሚሄዴትን ታደግ፤ ሊታረዱ የተወሰኑትን አድን፡፡ እነሆ ይህንን አላዉቅም ብትል፤ ልቦችን የሚመረምር እርሱ አያስተዉልምን? ነብስህንም የሚመለከት እርሱ አያዉቅምን? ለሰዉስ ሁሉ እንደ ሥራዉ አይመልስምን? (ምሳሌ 24፡11-12)፡፡ እንግዲህ እኛ ራሳችንን አድነን እንዲንኖር ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም መትረፍ እንዲንችል ደግሞም ከኃጥአትና ከሚያስከትለዉ ሞት ያልዳኑትን እንዲንታደግ ዛሬ እግዚአብሔር ይጠይቀናል፡፡ ስለሆነም ይህንን መልዕክት ካነበባችሁ በኃላ ‹‹የመዳን ቀንህ/ቀንሽ አሁን ነወ፡፡›› የሚል ጽሑፍ ከፕሮፋይል ፎቷችሁ ጋር ቢታስቀምጡ በአንድ ሣምንት ዉስጥ ቢንያንስ 14,000 ሰዎች መልዕክቱን ሊያነቡት ይችላሉ፡፡ካነበቡት ዉስጥ ቢያን 2 ሰዎች በዚህ ወንጌል ብድኑና አንተም መልዕክቱን ለ7 ሰዎች ብታጋራ ወይም ሼር ቢታደርግ 14 ወደ ሞት የሚሄዱትን ሰዎች ታደካቸዉ ማለት ነዉ፡፡ ደግሞም መልክቱን 100,000 ሰዎች ሼር በማድረግ ብቀባበሉት በአጠቃላይ በአንድ ሣምንት ብቻ 1,400,000 ሰዎች ከጨለማ ወደ ምደነቅ ብርሃን እንዲመጡ አደረግን ማለት ነዉ፡፡ በተለይ የዘወትር ፀሎትህ አንድ ቀን በአደባባይ ወንጌልን እሰብካለዉ፡፡ ለእኔ ያ ነዉ ትልቅ ምስክርነት ለሚትሉ ሁሉ ዛሬ የሚሥራች ልንገራችሁ ለብዙ ሰዎች መድረስ ትችሉ ዘንድ ዛሬም ደግሞ የእናንተም ቀን ነዉና ይህንን መልዕክት በእርግጥ ሼር በማድርግ ወንጌልን ለፍጥረት ሁሉ ስበክ፡፡
‹‹በተወደደ ሠዓት ሰማሁህ በመዳንም ቀን ረዳሁህ ይላልና፤እነሆ የተወደደዉ ሠዓት አሁን ነዉ፤እነሆ የመዳን ቀን አሁን ነዉ፡፡ 2ኛ ቆሮ 6፡2

ማቴዎስ 5:1-16¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ደስ ልለን የሚገባን ጊዜ መች ነው?በእግዚአብሔር ስም ሰዎች ብጠሏችሁ ደስ ይበላችሁ።¹ ሕዝቡንም አይቶ ወደ ተራራ ወጣ፤ በተቀመጠም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እ...
26/02/2021

ማቴዎስ 5:1-16
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
ደስ ልለን የሚገባን ጊዜ መች ነው?
በእግዚአብሔር ስም ሰዎች ብጠሏችሁ ደስ ይበላችሁ።
¹ ሕዝቡንም አይቶ ወደ ተራራ ወጣ፤ በተቀመጠም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ ቀረቡ፤
² አፉንም ከፍቶ አስተማራቸው እንዲህም አለ፦
³ በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።
⁴ የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፥ መፅናናትን ያገኛሉና።
⁵ የዋሆች ብፁዓን ናቸው፥ ምድርን ይወርሳሉና።
⁶ ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው፥ ይጠግባሉና።
⁷ የሚምሩ ብፁዓን ናቸው፥ ይማራሉና።
⁸ ልበ ንጹሖች ብፁዓን ናቸው፥ እግዚአብሔርን ያዩታልና።
⁹ የሚያስተራርቁ ብፁዓን ናቸው፥ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና።
¹⁰ ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።
¹¹ ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ።
¹² ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ፥ ሐሴትም አድርጉ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳድደዋቸዋልና።
¹³ እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፤ ጨው አልጫ ቢሆን ግን በምን ይጣፍጣል? ወደ ውጭ ተጥሎ በሰው ከመረገጥ በቀር ወደ ፊት ለምንም አይጠቅምም።
¹⁴ እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም።
¹⁵ መብራትንም አብርተው ከዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል።
¹⁶ መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።
ካነበባችሁ በኃላ ሼር ብቻ ብታደርጉ ዋጋችሁ እጅግ ታላቅ ነው።

ቃሉን በእምነት ለሚቀበል ሁሉ ይህ ቃል መልካም ያድርግለታል።
26/02/2021

ቃሉን በእምነት ለሚቀበል ሁሉ ይህ ቃል መልካም ያድርግለታል።

ለእነ ነው የሚል ብቻ አሜን አሜን አሜን ይበል።
24/02/2021

ለእነ ነው የሚል ብቻ አሜን አሜን አሜን ይበል።

24/02/2021

ሮሜ 1:1-17
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
የሮመ መልዕክት ትምህርት
¹-² ሐዋርያ ሊሆን የተጠራ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ጳውሎስ በነቢያቱ አፍ በቅዱሳን መጻሕፍት አስቀድሞ ተስፋ ለሰጠው ለእግዚአብሔር ወንጌል ተለየ።
³-⁴ ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
⁵ በእርሱም ስለ ስሙ በአሕዛብ ሁሉ መካከል ከእምነት የሚነሣ መታዘዝ እንዲገኝ ጸጋንና ሐዋርያነትን ተቀበልን፤
⁶ በእነርሱም መካከል የኢየሱስ ክርስቶስ ልትሆኑ የተጠራችሁ እናንተ ደግሞ ናችሁ።
⁷ በእግዚአብሔር ለተወደዳችሁና ቅዱሳን ልትሆኑ ለተጠራችሁ በሮሜ ላላችሁት ሁሉ፥ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።
⁸ እምነታችሁ በዓለም ሁሉ ስለ ተሰማች አስቀድሜ ስለ ሁላችሁ አምላኬን በኢየሱስ ክርስቶስ አመሰግናለሁ።
⁹-¹⁰ በልጁ ወንጌል በመንፈሴ የማገለግለው እግዚአብሔር ምስክሬ ነውና፤ ምናልባት ብዙ ቆይቼ ወደ እናንተ አሁን እንድመጣ በእግዚአብሔር ፈቃድ መንገዴን እንዲያቀናልኝ እየለመንሁ ሁልጊዜ ስጸልይ ስለ እናንተ ሳላቋርጥ አሳስባለሁ።
¹¹ ትጸኑ ዘንድ መንፈሳዊ ስጦታ እንዳካፍላችሁ ላያችሁ እናፍቃለሁና፤
¹² ይህንም ማለቴ በመካከላችን ባለች በእናንተና በእኔ እምነት አብረን በእናንተ እንድንጽናና ነው።
¹³ ወንድሞች ሆይ፥ በሌሎቹ አሕዛብ ደግሞ እንደ ሆነ በእናንተም ፍሬ አገኝ ዘንድ ብዙ ጊዜ ወደ እናንተ ልመጣ እንዳሰብሁ እስከ አሁን ግን እንደ ተከለከልሁ ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ።
¹⁴ ለግሪክ ሰዎችና ላልተማሩም፥ ለጥበበኞችና ለማያስተውሉም ዕዳ አለብኝ፤
¹⁵ ስለዚህም በሚቻለኝ መጠን በሮሜ ላላችሁ ለእናንተ ደግሞ ወንጌልን ልሰብክ ተዘጋጅቼአለሁ።
¹⁶ በወንጌል አላፍርምና፤ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው፥ ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን ነውና።
¹⁷ ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎ እንደ ተጻፈ የእግዚአብሔር ጽድቅ ከእምነት ወደ እምነት በእርሱ ይገለጣልና።

ይህንን መልዕክት አይተህ እንዳታልፍ። ምክንያቱም የእግዚአብሔር መንፈስ አሁን ያገኝሃልና።
23/02/2021

ይህንን መልዕክት አይተህ እንዳታልፍ። ምክንያቱም የእግዚአብሔር መንፈስ አሁን ያገኝሃልና።

23/02/2021

ዛሬ መልካም ይሆናል።

Address

Piazza
Awassa
94342

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Salvation Day in Christ International Church /የመዳን ቀን በክርስቶስ ቤተክርስቲያን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share