16/08/2026
የወንድም ከቤና አቤ ውይይት ይቀጥላል....
=========================
ጌታ የሱስ ስለ ሰንበት ምን አለ?
መልስ፡- ጌታ የመጣው አስርቱን ትኢዛዘት ኢንደገና ለመከለስ ወይም ለመሻር አይደለም። ጌታ ስለ ሰንበት በተግባር‚ በቀጥታና በተዘዋዋር አስተምሯል። ሀ. ሕግን ለመሻር አልመጣሁም ሲል ሰንበት ከሕጎቹ አራተኛው ሕግ መሆኑን መዘንጋት የለብንም(ማቴ 5፡17) ፡(ዘፀ. 20፡8) ። ለ. ሽሽታችሁ በክረምት ወይም በሰንበት ኢዳይሆን ጸልዩ ብሏል(ማቴ 24፡20)በክረምት ብርቱ ብርድ፡ ዶፍ ዝናብና የበረዶ ቁልል የምበዛበት አስጨናቂ ግዘ ስሆን ሰንበት ግን ለአምልኮ የተቀደሰ ጉባኤ የምሆንበት ቀን እንጅ ረጅም ጉዞ የምደረግበት ስላልሆነ ነው። ጌታ እንደ ልማዱ በሰምበት ቀን ምኩራብ ይገባ ነበር (ሉቃ. 4፡16) ። ሐ. የየሱስ ተከታይ የሆነው ሐዋርያው ጳውሎስ በሰንበት ቀን ጌታን ማምለክ ልማዱ ነበር (ሐዋ‚ 17፡2 ፡24፡ 14፤ 16፡13) ። መ. ሐዋርያትም የአህዛብ ልማድም በሰንበት ቀን ጌታን ማምለክ ነበር(ሓዋ. 16፡3 ፤18፡4፤3፡4)።