Assosa holy saviour catholic church

Assosa holy saviour  catholic church connecting catholic in the worlds

09/11/2019
Yemediya fera
09/11/2019

Yemediya fera

20/02/2019

ወንድምህ ወዴት ነው?

እግዚአብሔር ስለወንድሞቻችን ምቾት የሚነሱንን ጥያቄዎች ይጠይቀናል፡፡ ‹‹ወንድምህ ወዴት ነው ?›› ስለ ታመሙ፣ ስለታሰሩና ስለተራቡ ወንድሞቻችን በልባችን እያንዳንዳችንን ይህን ጥያቄ ይጠይቀናል፡፡

እኛ ሰዎች ስለ ባለንጀሮቻችን እግዚአብሔር የሚጠየቀንን ምቾት የሚያሳጣ ጥያቄ ልክ እንደ ቃየል ለመመለስ እንሞክራለን፡፡ ‹‹አላውቅም፣ የወንድሜ ጠባቂ እኔ ነኝን?›› ብዬ እጄን ከበደል ነጻ ለማድረግ እሞክራለሁ፡፡ ወንድሙን የገደለው ቃየል ከእግዚአብሔር ፊት ለመሸሽ ሞከረ፡፡

ምቾት የሚነሱ ጥያቄዎች

ኢየሱስ ብዙን ጊዜ ምቾት የሚነሱን ጥያቄዎች ይጠይቀናል፡፡ ጴጥሮስን ሦስት ጊዜ ይወደው እንደሆነ ጠየቀው፡፡ ስዎች ስለ እኔ ምን ይላሉ? እናንተስ? ብሎ ደቀመዛሙርቱን ጠየቃቸው፡፡ ዛሬም ጌታችን ጥያቄ ይጠይቀናል፣ ‹‹ያ የራበው ወንድምህ ወዴት ነው? ›› ይለናል፡፡ ‹‹እርሱማ በቁምስና የእርዳታ ብር ምሳ እያበላ ነው›› ብለን እንመልሳለን፡፡ ‹‹የታመመው ወንድምህ ወዴት ነው?›› ተብለን ስንጠየቅ ‹‹እርሱማ ሆስፒታል ገብቶ የለ እንዴ?›› ‹‹ሆስፒታል ሞልቶአል አይደል?›› ‹‹መድኃኒትስ አገኘኽለት?›› ‹‹እርሱማ አያገባኝም፣ በሌላው ሰው ሕይወት ውስጥ ምን ጣልቃ አስገባኝ? ደግሞም መድኃኒት የሚሰጠው ዘመድ አያጣም›› እያልኩኝ ራሴን ነጻ አደርጋለሁ፡፡

‹‹የታሰረው ወንድምህ ወዴት ነው?›› ‹‹አይ እርሱን ተወው፣ እንኳን ታሰረ ይገበዋል›› ‹‹ከስንቱ ወንጀለኛ ጋር መንገድ እየተጋፋን እንኖራለን!››፡፡ እንዲህ ዓይነቶቹን መልሶች ግን ከጌታ አትሰሙም፡፡ ጌታ ‹‹ህግወጥ ሰራተኛ ነው የምትለው፣ በዓመት ዘጠኝ ወር እየሰራ፣ ያለ ዋስትና ያለእረፍት እየሰራ፣ ያ የበዘበዝከው ወንድምህ ወዴት አለ?›› ይለናል፡፡

የወንድም ፊት ስም አለው

በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 25 የተጠቀሱትን፤- የታመሙ፣ የተራቡ፣ የተጠሙ፣ የታረዙ፣ ትምህርት ቤት መሄድ የማይችሉ ህጻናት፣ በሱስ የተያዙትን፣ የታሰሩትን በስም መጥራት አለብን፡፡ ወዴት ነው ያሉት?

ደግመን ደጋግመን የምንጠየቀው ጥያቄ ‹‹ወንድምህ በልብህ ውስጥ ወዴት ነው?››የሚል ነው፡፡ በልቤ ውስጥ ለነዚህ ሰዎች ቦታ አለኝ ወይ፣ ወይስ ትንሽ ሳንትም ተመጸውቼ የሚረብሸኝን ህሊናዬን ጸጥ እሰኛለሁ?

ችግርን ላለመመልከት፣ ችግርን ላለመንካት፣ ከችግር ለመሸሸግ የተድበሰበሰ ምላሽ መስጠቱን ተላምደነዋል፡፡ በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 25 የተዘረዙትን በምናውቃቸው ስሞች ተክተን ካልጠራናቸው፣ በሩ ፊት የቆመው ኃጢአት ወደ ውስጥ ገብቶ ለማጥፋት የተዘጋጀውን የጨለማ ሕይወት በዙሪያችን እንገነባለን፡፡

እግዚአብሔር በዘፍጥረት ውስጥ አዳምን ‹‹አዳም ሆይ፣ ወዴት ነህ?›› ብሎ ጠየቀው፡፡ አዳም ስላፈረ ራሱን ሸሸገ፡፡

ምናልባት በዙሪያችን ያለን ይህን ጉዳይ፣ ይህን መከራ፣ ይህን ስቃይ ልብ ብለን ላንመለከት እንችል ይሆናል፡፡ ክርስቲያኖች ራሳችንን ከእውነታ መሸሸግ የለብንም ፣ ይልቅስ በተከፈተ ልቦና፣ በታማኝነትና በደስታ ጌታችን ስለወንድሞቻችን ለሚጠይቀን ጥያቄ መልስ እንስጠው፡፡

12/02/2019
06/02/2019

ር. ሊ. ጳ ፍራንቸስኮስ “የክርስቲያን መሣሪያ እምነት እና ፍቅር ብቻ ናቸው”።

ቅዱሳን ተብለው የተጠሩበት ምክንያት በሕዝቦች መካከል እውቅናን ስላተረፉ ወይም ሃብትን ስለሰበሰቡ ወይም በሥራቸው ዕውቅናን ስላገኙ ሊመስለን ይችላል።ነገር ግን ለኢየሱስ ክርስቶስ የተቀደሱት የሚላቸው ድሆችን፣ የተረገጡትን፣ የተሰቃዩትን እና የተጨቆኑትን ነው::

ምንጭ ራዲዮ ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ካለፈው እሑድ ጥር 26 እስከ ጥር 28 ቀን 2011 ዓ.ም. ድረስ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ያደረጉትን ሐዋርያዊ ጉብኝት ባጠቃለሉበት ዕለት በአገሩ ከሚኖሩት ካቶሊካዊያን መዕመናን ጋር ባሳረጉት የመስዋዕተ ቅዳሴ ስነስርዓት ላይ እንደገለጹት የክርስቲያን መሣሪያ እምነት እና ፍቅርብቻ መሆናቸውን አስታውቀዋል።ርዕሠ ሊቃነጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በአቡዳቢ ከተማ ውስጥ በሚገኘው በዛይድ ስተዲዬም ያሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ታሪካዊ ነው ተብሏል። አንድ የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ርዕሠ ሊቃነጳጳሳት ወደ አረብ አገሮች
ባሕረሰላጤ ሲጓዙ ርዕሠ ሊቃነጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የመጀመሪያው እንደሆኑ መግለጻችን ይታወሳል።
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ መስዋዕተ ቅዳሴውን ለተካፈሉ መእምመናን በሙሉ ባሰሙት ስብከታቸው ለብጹዓን ምስጋና ይግባቸውና እናንተ የሰላም ምሳሌ ናችሁ በማለት በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ውስጥ በተለያዩ የሥራ ዘርፍ ተሰማርተው የሚገኙ ምዕመናንን አመስግነዋቸዋል።በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የሚገኙ ካቶሊካዊያን መዕመናን ቀላል የሕይወት ምስክርነቶችን እየሰጡ፣ቅዱስ ፍራንቸስኮስ ለመንፈሳዊ ወንድሞቹ ይናገር እንደነበረ ኢየሱስ ክርስቶስን እየተከተሉ የፍቅር ሥራዎችን ለወንድሞች እና እህቶች ማበርከት እነደሚያስፈልግ አሳስበዋል።
ርዕሠ ሊቃነጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ወደ አረብ ባሕረሰላጤ አገሮች ባደረጉት የመጀመሪያ ጉብኝታቸው፣ እንደዚሁም የመጀመሪያቸው በሆነው የመስዋዕተ ቅዳሴ ስነስርዓት ላይ ለምዕመናን በሙሉ ያላቸውን ፍቅር ገልጸዋል። መስዋዕተ ቅዳሴውን ለተካፈሉት 180,000 ምዕመናን ዕለቱየጋራ ጸሎት የቀረበበት የደስታ ዕለት ሆኖ ዉሏል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ከማቴዎስ ወንጌል ተወስዶ በተነበበው መልዕክት ላይ በመመርኮዝ ባቀረቡት አስተንትኖ ከኢየሱስ ጋር ከሆናችሁ፣ እንደ ደቀመዛሙርቱ ቃሉንም የምታደምጡ ከሆነ፣በቃሉም የምትመሩ ከሆነ ብጹዓን ናችሁ ብለዋል። ይህም በክርስትና ሕይወት ውስጥ ማወቅ የቻልነው የመጀመሪያው እውነት ነው ብለዋል።የክርስትና ሕይወት ከሁሉም በላይ የኢየሱስ ክርስቶስ ልጆች መሆናችንን ማወቅ ነው ብለዋል።ይህ ደግሞ ማንም በዚህ ዓለም ላይ ከሕይወታችን ሊነጥቅብን የማይችለው የደስታችን ምክንያት ነው። ውድ ወንድሞቼ እና
እህቶቼ፣እናንተን ሳገኛችሁ ልነግራችሁ የፈለኩት ቃል ይህ ነው፣ የተባረካችሁ የሚል ነው ብለዋል። ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን የተባረካችሁ ናችሁ ሲላቸው፣ እያንዳንዱ ቅዱሳን፣ቅዱሳን ተብለው የተጠሩበት ምክንያት ለምንድነው ብለን ራሳችንን እንጠይቃለን።ቅዱሳን ተብለው የተጠሩበት ምክንያት በሕዝቦች መካከል
እውቅናን ስላተረፉ ወይም ሃብትን ስለሰበሰቡ ወይም በሥራቸው ዕውቅናን ስላገኙ ሊመስለንይ ችላል።ነገር ግን ለኢየሱስ ክርስቶስ የተቀደሱት ድሆች፣ የተረገጡት፣ የተሰቃዩት እና የተጨቆኑት ናቸው።ይህን በሚገባ ለመረዳት ኢየሱስ ክርስቶስ እንዴት እንደኖረ መመልከት ያስፈልጋል። ለአንዳንድ ነገሮች ክብርን ለመስጠት ድሃ ነበር፣ነገር ግን ፍቅርን በማሳየት ሀብታም ነበር።
ብዙ የታመሙ ሰዎችን በማዳን እና በመፈወስ ይታወቅ ነበር ነገር ግን የራሱን ሕይወት ከሞት ሊያተርፍ አልቻለም። ሊያገለግል እንጂ ሊገለገል አልመጣም። ትልቅነት የሚገኘው ከመስጠት እንጂ ከመቀበል አይደለም። ፍጹም ትክክል እና ትሑት ሆኖ ሳለ ራሱን ለሕገወጥ ፍርድ አቀረበ።በዚህ መንገድ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔርን ፍቅር ወደ ዓለም አምጥቷል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ኢየሱስ ክርስቶስን በሙሉ ልብ እንድንከተል የሚያደርገንን የመንፈስ ቅዱስ እገዛን በጸሎት እንጠይቅ በማለት መእምናኑን አሳስበዋል።

05/02/2019

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ 27ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማድረግ ወደ አቡ ዳቢ አቀኑ
“ሰብዓዊ ወንድማማችነት” በሚል መሪ ቃል በተባበሩት የአረብ ኤምሬትስ አገር በሆነችው በአቡ ዳቢ በሚካሄደው ከተለያዩ የሐይማኖት ተቋማት የተውጣጡ የሐይማኖት መሪዎች ስብሰባ ላይ ለመገኘት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በጥር 26/2011 ዓ.ም ወደ እዚያው በማቅናት 27ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝታቸውን መጀመራቸው ከደርሰን ዘገባ ለመረዳት ተችሉዋል።
የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ተጨማሪ ለማንበብ
ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በክርስትና እና በእስልምና እምነት መካከል የወንድማማችነት ድልድይ ይገነባሉ!
01/02/2019
ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በክርስትና እና በእስልምና እምነት መካከል የወንድማማችነት ድልድይ ይገነባሉ!
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በዚህ በተባበሩ የአረብ ኤምሬትስ አገር በሆነችው በአቡ ዳቢ እያደረጉት የሚገኘው 27ኛው ሐዋርያዊ ጉብኝት “የሰላም መሳርያ አድርገኝ” የሚል መሪ ቃል ያነገበ ሐዋርያዊ ጉብኝት እንደ ሆነ ከደርሰን ዘገባ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን እ.አ.አ በ13ኛው ክፍለ ዘመን የዛሬ 8 ምዕተ አመታት በፊት ቅዱስ ፍራንቸስኮስ እና በወቅቱ የገብፅ ሱልጣን የነበሩት ማሊክ አል ካሚል ጋር በጣሊያን በተገናኙበት ወቅት የተጠቀሙበት መሪ ቃል በድጋሚ ለማስታወስ እና አሁንም ቢሆን ከ8 ምዕተ አመታት በኋላም ቢሆን እንኳን ዓለማችን በከፍተኛ ግጭቶች ውስጥ ስለምትገኝ በዚህ በግጭቶች እና በጦርነቶች እየተናጠች በምትገኘው ዓለማችን ሰላም ይሰፍን ዘንድ ሁሉም ባለድርሻ አካላት እና መንግሥታት የራሳቸውን አዎንታዊ አስተዋጾ እንዲያበረክቱ ለማሳሰብ የተመረጠ መሪ ቃል እንደ ሆነ ከደረሰን ዘገባ ለመረዳት ተችሉዋል።

Address

Around Hospital
Asosa

Telephone

+251926421990

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Assosa holy saviour catholic church posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Assosa holy saviour catholic church:

Share