18/08/2022
እኔን የለወጠ ጥቅስ ዮሐ 15 ነዉ አንብቡት
እስከዛሬ ተናግሬው የማላውቀውን ገጠመኜን ላውራችሁ
ሚስጥር ነበር
እንዲህ ከገጠመኝ ላካፍላችሁ
አንዴ ምን ሆንኩላችሁ መሰላችሁ ጠዋት ላይ ነው ከቤቴ ልወጣ ተዘጋጅቼ ጨርሼ ከዛም ስልኬን ብፈልገው አጣሁት ያልፈለኩበት የለም የት እንዳረኩት ጠፍቶኝ ግራ ገባኝ ለካ እያወራሁበት ነበር በራሴ ተገርሜ ቀልቤ ለካ ወሬው ላይ ሆኖ ነው ጉድ ያደረገኝ። ስልኬን ያጣሁትና ስፈልገው የቆየሁት ስልኬ ከእኔ ሩቅ ሆኖ ሳይሆን ጆሮዬ ላይ መሆኑን ዘንግቼው ነው።
አሁንም እግዚአብሔር ሩቅ የመሰለንና ሌላ ቦታ(ሰው) ጋር ፍለጋ የምንዞረው በውስጣችን መሆኑን ዘንግተነው ነው እንጂ እርሱ የቅርብ ነው።
" እኔ የቅርብ አምላክ ነኝ እንጂ የሩቅ አምላክ አይደለሁም። "
(ትንቢተ ኤርምያስ 23:23)
እግዚአብሔር ከእኛ አልራቀም እኛ ነን ከእርሱ የራቅነው በዚህ ክፍል እንደሚያወራው የቅርብ እንጂ የሩቅ አይደለሁም ይለናል
ታድያ እርሱ የቅርብ ነኝ ካለ ማን ነው የራቀው?
እንኳን እግዚአብሔር በቅርብ ያለ ጓደኛ እንኳን ይሰማል። በተለይ ደግሞ ለኛ ለአዲሱ ኪዳን አማኞች እግዚአብሔር የቅርባችን ብቻ ሳይሆን መኖሪያው ነው ያደረገን።
" ወይስ ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን? በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ።
"
(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6:19-20)
----------
5፤ እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል።
6፤ በእኔ የማይኖር ቢሆን እንደ ቅርንጫፍ ወደ ውጭ ይጣላል ይደርቅማል፤ እነርሱንም ሰብስበው ወደ እሳት ይጥሉአቸዋል፥ ያቃጥሉአቸውማል።
7፤ በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል።
(የዮሐንስ ወንጌል ምዕ. 15)
እንግዲህ እርሱ በእኛ የሚኖር ከሆነ ደግሞ ከእስትንፋሳችንም ቅርብ ከሆነ መስማት ያቃተን እኛ እንጂ ሳይሰማን ቀርቶ አያውቅም።
ለነገሩ ሰው በክርስቶስ ኢየሱስ ማን እንደተደረገ ስላላወቀ እግዚአብሔር የሚሰማው አይመስለውም ስለዚህም የሚሰማለት ፃድቅ(ለእግዚአብሔር ቅርብ) የሆነን ሰው ፍለጋ ሳይታክተው ይዞራል ይልቅ ዙረታችንን አቁመን በውስጣችን ያደረውን(ያልራቀውን) ጌታ እንቅረበውና ጥያቄ ይዘን ሳይሆን ምስጋና ተሞልተን ለማመስገንና ምስክር ለመሆን እንቀሳቀስ።
ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለናል።
ቃሉ የሚለንን ልክ እንደዝያው ነን። ቃሉ ምን እንደምለን ደግሞ ከፍተን ማንበብ ይኖርብናል።
ድሮ ድሮ ትዝ ይለኛል እናቶቻችን ብራቸውን መፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያስቀምጡ ነበር እናም እዝያው ያገኙት ነበር ምክንያቱም ማንም አይከፍተውማ።
ማንም ለህመሙ ዋ መድሃኒት ይዤአለሁ ቢለው አይተወውም መፍትሄው መድኃኒቱን መዋጥ ነው።
መፅሐፍ ቅዱስ በተለያየ ቋንቋ እቤታችን ቢኖረን ካላነበብነው
(ቃሉን ካልዋጥነው) መፍትሔ የለም። ቃሉ ውስጥ ሁሉም አለ።
(መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 34)
----------
1፤ እግዚአብሔርን ሁልጊዜ እባርከዋለሁ፥ ምስጋናውንም ዘወትር በአፌ ነው።
2፤ ነፍሴ በእግዚአብሔር ትከብራለች፥ ገሮችም ሰምተው ደስ ይላቸዋል።
3፤ እግዚአብሔርን ከእኔ ጋር ታላቅ አድርጉት፥ በአንድነትም ስሙን ከፍ ከፍ እናድርግ።
4፤ እግዚአብሔርን ፈለግሁት መለሰልኝም፥ ከመከራዬም ሁሉ አዳነኝ።
5፤ ወደ እርሱ ቅረቡ ያበራላችሁማል፥ ፊታችሁም አያፍርም።
6፤ ይህ ችግረኛ ጮኸ፥ እግዚአብሔርም ሰማው፥ ከመከራውም ሁሉ አዳነው።
ከእግዚአብሔር ጋር ሩቅ አይደለንም በደሙ ኃይል ቀርበናል።
" አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል።"
(ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2:13)
በጌታ ወንድማችሁ ፓስተር ሶፎንያስ ሞላልኝ ነኝ።
ከወደዱት ሼር ያድርጉት