Al-Hidaya Islamic University

Al-Hidaya Islamic University አልሂዳያ ኢስላማዊ ዩንቨርሲቲ በጉራጌ ዞን ጉመር እየተገነባ የሚገኝ ተቋም ሲሆን በምዕራፍ 1 ያስገነባው መስጅድና መድረሳው ተመርቆ ስራ ጀምሯል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከ/ም/ቤት ፕሬዚዳንት ኢማም ሐጅ ዐብዱልሃዲ አህመድ ቡርሃን፣ ም/ፕሬዚዳንቱ ሸኽ በህጃ ዐ/ጀሊል፣ የዑምራ እና ሐጅ ተጠሪ ሸኽ ሳዲቅ ወጌቦ፣ የጉራ...
15/09/2026

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከ/ም/ቤት ፕሬዚዳንት ኢማም ሐጅ ዐብዱልሃዲ አህመድ ቡርሃን፣ ም/ፕሬዚዳንቱ ሸኽ በህጃ ዐ/ጀሊል፣ የዑምራ እና ሐጅ ተጠሪ ሸኽ ሳዲቅ ወጌቦ፣ የጉራጌ ዞን እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት ሰብሳቢ ሸኽ አባስ ያሲን የቁርአን ሂፍዝ ተመራቂዎቻችን ካስመረቁ በኋላ የአልሂዳያ ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲ ፕሮጀክት ያለበት ሁኔታ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

ፕሬዚዳንቱ ኢማም ሐጅ ዐብዱልሃዲ በክልል እስልምና ጉዳዮች ከ/ም/ቤት ስም 300 ሺህ ብር ለአልሂዳያ ዩኒቨርሲቲ ፕሮጀክት የነየቱ ሲሆን በግላቸው 50 ሺህ ብር እዚያው ገቢ አድርገዋል። በሌላ በኩል የአልሂዳያ ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲ የማስፋፊያ ቦታ ጥያቄ ከክልሉ እና ከዞኑ መንግስት ጋር በመነጋገር እንዲፈታ እንደሚያደርጉ በመድረኩ ገልፀዋል።

ጀዛኩሙሏህ ኸይር መሪዎቻችን!

15/09/2026

አጭር ቁጥሩ ሙሉ ለሙሉ ተዘግቷል‼

አልሂዳያ ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲ ሲጠቀምበት የነበረው የአቢሲኒያ አካውንት አጭር ኮድ 131313 የተለያዩ ሰዎች በስህተት ገንዘብ ገቢ እያደረጉ እኛም እየመለስን በመቸገራችን አጭር ቁጥሩ እንዲዘጋ ለባንኩ አመልክተን ከተዘጋ በኋላ ከሌላ ቅርንጫፍ ለሌላ ድርጅት እንዲጠቀምበት አጭር ቁጥሩን በመስጠታቸው የአልሂዳያ ቤተሰቦች አጭር ቁጥሩን ተጠቅማችሁ ገቢ እንዳታደርጉ ማሳሰባችን ይታወሳል። አጭሩ ቁጥር ለረዥም ጊዜ ስንጠቀምበት የቆየንና ያስተዋወቅነው በመሆኑ የአልሂዳያ ቤተሰቦች ለአልሂዳያ የነየቱት ገንዘብ ወደ አጭሩ ቁጥር ሊልኩ ስለሚችሉ ባንኩ አጭሩን ቁጥር እንዲዘጋልን አቤቱታ አቅርበን ዘግተውልናል። ስለሆነም ባለፈው መረጃው ባጋራንበት ወቅት "አልሂዳያ ሲጠቀምበት የቆየ ኮድ እንዴት ለሌላ ድርጅት ይሰጣል?" የሚል ጥያቄ የፈጠረባችሁ ወንድም እህቶች እኛም ለባንኩ በደብዳቤ አቤቱታ አቅርበን ኮዱ በመዘጋቱ ቅሬታው መፈታቱን ለመግለፅ እንወዳለን።

የአልሂዳያ የአቢሲኒያ አካውንት ረዥሙ ቁጥር 137596644 አሁንም ክፍት ነው። ንያዎቻችሁን መላክ ትችላላችሁ።

የአልሂዳያ ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲ ፋይናንስ መምሪያ

ቁርአን የሐፈዙ እና የተወሰኑ ኪታቦችን የቀሩ 32 አዳሪ ተማሪዎችን መስከረም 3/2019 አስመርቀናል! አልሐምዱሊላህ።  ለተማሪዎች ለሁለት አመት ቆይታ የምግብ፣ የኡስታዞችና የሌሎች ሰራተኞች...
14/09/2026

ቁርአን የሐፈዙ እና የተወሰኑ ኪታቦችን የቀሩ 32 አዳሪ ተማሪዎችን መስከረም 3/2019 አስመርቀናል! አልሐምዱሊላህ። ለተማሪዎች ለሁለት አመት ቆይታ የምግብ፣ የኡስታዞችና የሌሎች ሰራተኞች ደሞዝ ጨምሮ አጠቃላይ 8.5 ሚሊየን ብር ወጪ ተደርጓል።

ይህንን ወጪ ለ1፣ለ2፣ ለ3 ተማሪ እያላችሁ እና በተለያየ መልኩ ወጪውን በመሸፈን ለዚህ ስኬት ወሳኝ ሚና የተጫወታችሁ እህት ወንድሞች ሁሉ የሁለት ዓለም ስንቅ በሆነው ቁርአን ወጪ አድርጋችሁ ፍሬውን ስላያችሁ እንኳን ደስ ያላችሁ‼

2019 ለአልሂዳያ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሽግግር አመት እንዲሆን በመወሰን በ2020 ለዩኒቨርሲቲው የመጀመሪያ የሆኑ የዲግሪ ተማሪዎች ለመቀበል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ በመድረኩ ይፋ ሆኗል። በግንባታ ላይ የሚገኙት 3 ህንፃዎች በያዝነው አመት ማጠናቀቅ የዝግጅቱ አካል መሆኑን የተገለፀ ሲሆን በሽግግሩ ወቅት የቁርአን ሂፍዝ ፕሮግራም በማቋረጥ ዱዓቶችን/ኡስታዞችን ለማፍራት ተወስኖ የተማሪዎች ምዝገባ ላይ እንደሚገኝ ተብራርቷል።

የቀደመ ድጋፋችሁ ለዛሬ ስኬት አብቅቶናል። ቀጣይ ድጋፋችሁ ዩኒቨርሲቲውን እውን ያደርጋል ኢንሻላህ!
***
በወር 200 ብር በማዋጣት አሻራዎን ለማሳረፍ በሚከተሉት በቴሌብር ወይም በጎግል ፎርም ሊንክ በመግባት በአባልነት ይመዝገቡ!

👉 የቴሌብር ተጠቃሚ ከሆኑ የአልሂዳያ ቴሌብር ሊንክ https://bit.ly/Al-hidaya_Islamic_University ተጭነው በመግባት 👉"Donate"👉200 ብር በመምረጥ👉 "Subscribe" 👉 ፓስወርድ ያስገቡ።

👉 ቴሌብር የማይጠቀሙ ከሆነ በዚህ :https://forms.gle/tixRPtbsVyRf6CX57 ቅፅ ይመዝገቡና በየወሩ በሚሴጅ እያስታወስንዎ ገቢ ያደርጋሉ።

14/09/2026
13/09/2026
10/09/2026

አስቸኳይ ‼

የአልሂዳያ ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲ አቢሲኒያ አካውንት አጭሩ ቁጥር 131313 ስለተዘጋ ረዥሙን ቁጥር 137596644 ብቻ እንድትጠቀሙ እናሳስባለን። አጭሩ ቁጥር ሌላ ድርጅት እየተጠቀመበት ስለሆነ ማንም ወደ 131313 እንዳይልክ።

የአልሂዳያ ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲ የቁርአን ሐፊዞች ምርቃት 4 ቀን ቀረው‼የሁለት ዓለም ስንቅ የሆነውን ቁርአን ከፍ ለምናደርግበት የምረቃ ፕሮግራም ሁላችሁም ተጋብዛችኋል‼
08/09/2026

የአልሂዳያ ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲ የቁርአን ሐፊዞች ምርቃት 4 ቀን ቀረው‼

የሁለት ዓለም ስንቅ የሆነውን ቁርአን ከፍ ለምናደርግበት የምረቃ ፕሮግራም ሁላችሁም ተጋብዛችኋል‼

የኡማችን አይንና ጆሮ የሆነውን ሀሩን ሚዲያን እናመሰግናለን!መስራቹ ወንድም ዐብዱረሂም እና የሚዲያው የአዲስ አበባ ስቱዲዮ ስራ አስኪያጅ ወንድም ባህሩ ስለጎበኛችሁን እናመሰግናለን። ጀዛኩሙሏ...
06/09/2026

የኡማችን አይንና ጆሮ የሆነውን ሀሩን ሚዲያን እናመሰግናለን!

መስራቹ ወንድም ዐብዱረሂም እና የሚዲያው የአዲስ አበባ ስቱዲዮ ስራ አስኪያጅ ወንድም ባህሩ ስለጎበኛችሁን እናመሰግናለን። ጀዛኩሙሏህ ኸይር!

ማስታወቂያ ‼ነፃ የት/ት እድል ከአልሂዳያ!!አልሂዳያ ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲ 2019 የሽግግር አመቱ በመሆኑ ከቁርአን ሒፍዝ ይልቅ ተማሪዎችን ተቀብሎ በዳዒነት ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቅቋል። ...
03/09/2026

ማስታወቂያ ‼

ነፃ የት/ት እድል ከአልሂዳያ!!

አልሂዳያ ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲ 2019 የሽግግር አመቱ በመሆኑ ከቁርአን ሒፍዝ ይልቅ ተማሪዎችን ተቀብሎ በዳዒነት ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቅቋል። በቀጣይ አመት በ2020 ዓ ል የመጀመሪያ የዩንቨርሲቲው የዲግሪ ተማሪዎች ለመቀበል አቅዶ እየሰራ የሚገኘው የዩንቨርሲቲው ቦርድ 2019 የሽግግር እንደመሆኑ ተማሪዎችን ተቀብሎ በዚህ በሽግግር ወቅት በዳዒነት በማስተማር ለዩንቨርሲቲው ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነው። ስለሆነም ለ2 አመታት በአዳሪነት በነፃ መማር የምትፈልጉ መስፈርቱን የምታሟሉ በስልኮቻችን ከጁሙዓ እና ከእሁድ ውጭ ባሉ የስራ ቀናት ደውላችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን

ስልክ: 0989637373፣ 0911267224

01/09/2026

አሰላሙ ዓለይኩም ወራህመቱላህ ወበረካቱህ‼
ውድ የአልሂዳያ ቤተሰቦች! በድጋሚ እንኳን ደስ ያላችሁ እያልን መስከረም 3/2019 ለሚመረቁ ለቁርአን ሐፊዞቻችን ምረቃ ፕሮግራም ስፖንሰር መሆን ለምትፈልጉ ወይም ሰደቃ ስለሆነ በአቅማችሁ መሳተፍ ለምትፈልጉ በሩ ክፍት መሆኑን እየገለፅን በሚከተሉት ሁለት መደቦች ለፈለጋችሁት መነየት ትችላላችሁ:
1ኛ: በምግብ ነክ:
ለበሬ፣
ለውሃ፣
ለእንጀራ፣
ለዳቦ፣
ለቂቤ፣
ወዘተ መነየት ይቻላል።

2ኛ: ለተመራቂ ተማሪዎች
ለጀለቢያ፣
ለጥምጣም፣
ለሪቫን፣
ለባይንደር፣
ለደረጃ ተማሪዎች ሽልማት፣
ወዘተ መነየት ይቻላል።

ንያችሁን በሚከተሉት የአልሂዳያ አካውንቶች ገቢ ማድረግ ትችላላችሁ።

የአልሂዳያ ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲ አካውንቶች:
CBE: 1000536412518
Dashen: 7927695238011
Zamzam: 0019202020101
Hijra: 1003080600002
Awash: 014101625578300
Abyssinia: 137596644
Rammis Bank:1030060606301

Address

Dember-Gumer Mazoria, Addis Ababa To Hosana Road
Arek'it

Telephone

+251911267224

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Al-Hidaya Islamic University posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Al-Hidaya Islamic University:

Shortcuts

Share