30/08/2026
ቀን24/12/2018 ዓ.ም
የጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት ዓመታዊ የንግሥ በዓል በሰላም ተከብሮ ዋለ!
በጋሞና አካባቢው ዞኖች ሀገረ ስብከት፣ በዳራማሎ ወረዳ ቤተክህነት ስር በሚገኘው በዶምኣ ቀበሌ አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ዓመታዊው የንግሥ በዓል በመንፈሳዊ ድምቀት ተከብሮ ውሏል።
በዕለቱ በተካሄደው የጻድቁ አባታችን መታሰቢያ ሥነ-ሥርዓት ላይ የአከባቢው ካህናት፣ ዲያቆናትና በርካታ ቁጥር ያላቸው ምዕመናን ተገኝተዋል። የበዓሉ ታዳሚዎች በያሬዳዊ ወረብ፣ በማኅሌትና በእልልታ በዓሉን በታላቅ መንፈሳዊ ተመስጦ አሳልፈውታል።
የጻድቁ አባታችን የአቡነ ተክለሃይማኖት ረድኤት፣ በረከትና ምልጃ ከሁላችን ጋር ይሁን!
አሜን።
በጋሞና አካባቢው ዞኖች ሀገረ ስብከት የዳራማሎ ወረዳ ቤተ ክህነት ሚዲያ