ታምራት ሰይፉ /Tamirat Seifu/

ታምራት ሰይፉ /Tamirat Seifu/ ለአንቺም የማይገዛ ሕዝብና መንግሥት ይጠፋል፥ እነዚያ አሕዛብም ፈጽመው ይጠፋሉ። ትንቢተ ኢሳይያስ 60 : 12 ስሜ ታምራት ረይፉ ሲሆን ኢትዮጵያዊ ነኝ መኖሪያዬ ጋሞ ዞን አርባምንጭ ነው።

30/05/2026
17/05/2026
17/04/2026

"ወንጌል ለሰላም፣ ሰላም ለሀገር" በሚል መሪ ቃል ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ በኮንሶ ዞን ወረዳዎች ቤተ ክህነት በካራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ይካሄዳል።
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ሚያዚያ ፱ ቀን ፳፻፲፰ ዓ/ም የጋሞና አካባቢው ዞኖች ሀገረ ስብከት ሚዲያ- አርባ ምን

የጋሞና አካባቢው ዞኖች ሀገረ ስብከት ሥብከተ ወንጌል ጥምር ኮሚቴ እና የኮንሶ ዞን ወረዳዎች ቤተ ክህነት በጋራ በመሆን ያዘጋጁት ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ “ወንጌል ለሰላም ወሰላም ለሀገር” በሚል መሪ ቃል በካራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ከሚያዚያ ፲፮ እስከ ፲፱ ቀን ፳፻፲፰ ዓ/ም ለተከታታይ አራት ቀናት ይካሄዳል ።

በዚህ ታላቅ ጉባኤ ላይ ቡራኬና ትምህርት ለመስጠት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የሚገኙ ሲሆን፤ ከእነዚህም መካከል፦ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ የጋሞና አካባቢው፣ ጎፋና ባስኬቶ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በአሜሪካ የቴክሳስ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ መሆናቸው ተረጋግጧል።

ከአዲስ አበባ የሚመጡት ታዋቂው ሰባኬ ወንጌል ሊቀ ሊቃውንት ዮሴፍ ደስአለኝ የሊቃውንት ጉባኤ አባልን ጨምሮ ሌሎች ዘማሪያን በጉባኤው ላይ ተገኝተው ያገለግላሉ።

የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ኅሩያን ገሪማ ጌታነህ ፣ ዋና ጸሐፊ መጋቤ ሰናያት ያዕቆብ ደስታ እንዲሁም የየክፍል ኃላፊዎች፣ በሀገረ ስብከቱ ሥር የሚገኙ የ፲፭ቱም ወረዳ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጆች፣የከተማ፣ የወረዳና የዞን ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ እንዲሁም አገልጋዮችና ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ ማህበረ ምዕመናን ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የኮንሶ ዞን ወረዳዎች ቤተ ክህነት ባስተላለፈው መልእክቱ፤ ይህ ጉባኤ ወንጌልን በማስፋፋት ለሀገር ሰላምና አንድነት ያለውን ፋይዳ በመገንዘብ፣ ምዕመናን ከየአቅጣጫው በመምጣት በረከቱን እንዲካፈሉ ጥሪውን አቅርቧል።

ይህንን ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ የሀገረ ስብከቱ ሚዲያ በቦታው በመገኘት አጠቃላይ የጉባኤውን ሂደትና መርሃ ግብሮች በቀጥታ ስርጭት (Live) በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ ኦርቶዶክሳዊያን ምዕመናን የሚያስተላልፍ መሆኑን ከወዲሁ እንገልጻለን።

ወንጌል ለሰላም ወሰላም ለሀገር!

ነቅዐ ጽድቅ የጋሞና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሚዲያ
▶️ፌስ ቡክ
https://www.facebook.com/profile.php?id=1

▶️ዩቱብ
https://www.youtube.com/

▶️ኢንታግራም
https://www.instagram.com/gamoha

▶️ቲክ ቶክ
tiktok.com/

04/04/2026

!!

የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ዓመታዊ ጥንተ ስቅለት እና የሆሳዕና በዓል በአርባ ምንጭ!

"እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ ስለ በደላችንም ደቀቀ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን"። ት.ኢ ፶፫፥፷

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በጋሞና አካባቢው ዞኖች ሀገረ ስብከት በአርባ ምንጭ ደብረ መድኃኒት መድኃኔ ዓለም ካቴድራል የሚከበረውን ታላቅ ዓመታዊ የንግስ በዓል ምክንያት በማድረግ መንፈሳዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

መጋቢት ፳፯ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም. የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጥንተ ስቅለቱ የሚታሰብበት እና የዐብይ ጾም ፰ኛው ሳምንት ሆሳዕና በዓል ነው። ሁለቱ ታላላቅ በዓላት በአንድ ዕለት የሚከበሩበት ልዩ መንፈሳዊ አጋጣሚ ሲሆን

በእለቱ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ (የጋሞና አካባቢው፣ የጎፋና ባስኬቶ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል) በመካከላችን በመገኘት በዓሉን ይባርካሉ።

በዚህ ታላቅ መንፈሳዊ ሥነ-ሥርዓት ላይ ተገኝታችሁ የበረከቱ ተካፋይ እንድትሆኑ በታላቅ አክብሮት ተጋብዛችኋል።

የአርባ ምንጭ ደብረ መድኃኒት መድኃኔ ዓለም ካቴድራል ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ

Address

Arba Mintch

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ታምራት ሰይፉ /Tamirat Seifu/ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to ታምራት ሰይፉ /Tamirat Seifu/:

Share