Zefano seventh Day Adventist church:

Zefano seventh Day Adventist church: Zefan Seventh Day Adventist Church is founded in 1992 in Ethiopian calendar and was tempted in many ways.

By the help Almighty God currently it has 20 members and these members decided to built new..

  ፡ ለፍትህና ለቤተክርስቲያን መብት መከበር!"ርስትህን አትልቀቅ"በሀዋሳ ሐይቅ ዳርቻ የሚገኘውና ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ጀምሮ በሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን ይዞታነት የሚታወ...
10/02/2026


፡ ለፍትህና ለቤተክርስቲያን መብት መከበር!

"ርስትህን አትልቀቅ"

በሀዋሳ ሐይቅ ዳርቻ የሚገኘውና ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ጀምሮ በሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን ይዞታነት የሚታወቀው ታሪካዊው ቦታችን፤ ዛሬ ከፍተኛ በደልና ግፍ እየተፈጸመበት ይገኛል። ይህ ለበርካታ አስርት ዓመታት ለወንጌል አገልግሎትና ለቅዱሳን ስብስብ ሲያገለግል የቆየ ቅዱስ ስፍራ፣ ዛሬ በማዘጋጃ ቤት አማካኝነት ለግለሰቦች ተላልፎ በመሰጠት የጥፋት ግንባታ እየተካሄደበት ነው።

የሰበካው መሪዎች ጉዳዩ ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት በተደጋጋሚ አቤቱታ ቢያቀርቡም፣ እስካሁን ሰሚ በማጣት በደሉ እየቀጠለ ይገኛል።
በየካቲት 1 ቀን 2018 ዓ.ም የሰበካው ተወካዮች ግንባታውን በአካል ተገኝተው ለማስቆም ቢሞክሩም፣ አንዳንድ የመንግስት ባለስልጣናት በስተጀርባ ሆነው ህገ-ወጥ ድርጊቱን እያበረታቱ መሆኑን ደርሰንበታል።

ይህ ድርጊት በሀዋሳ የሚገኙ ምዕመናንን ብቻ ሳይሆን በመላው ዓለም የሚገኙ የአድቬንቲስት ማህበረሰብን ታሪክና እሴት የናቀ ፍጹም ህገ-ወጥ ድርጊት ነው።

ለዓለም አቀፍ ምዕመናን፦ ይህ መልዕክት የደረሳችሁ ሁሉ ለሌሎች አባላት በማዳረስ (Share በማድረግ) የበኩላችሁን እንድትወጡና በጽሁፍም ሆነ በማህበራዊ ሚዲያ ድምጽ በመሆን ከጎናችን እንድትቆሙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

መንግስት ይህንን በግልጽ እየታየ ያለውን የመብት ጥሰት በአስቸኳይ እንዲያስቆምና የቤተክርስቲያኗን ይዞታ እንዲያስከብር በጥብቅ እንጠይቃለን!

"እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው!"

Address

Near Zefine 10km Far
Arba Minch'

Telephone

+251926691329

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Zefano seventh Day Adventist church: posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share