Gamo Zone Evangelical Church Fellowship Office

Gamo Zone Evangelical Church Fellowship Office Unites churches for gospel ministry and community transformation.

21/07/2026
16/06/2026
16/06/2026

የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ኅብረት 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ ክብረ በዓል ፕሮግራም አስመልክቶ ዛሬ ሰኔ 9 /2018 የወርቅ ኢዮቤልዩ አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሠጠ።

የኢትዮጵያ ወንጌላውያ አብያተክርስቲያናት ፕሬዚዳንት ፓስተር ደረጄ ታፈሰ እንኳን ለ 50 ኛ አመት አደረሳችሁ በማለት መልዕክታቸውን የጀመሩ ሲሆን ኅብረቱ የተጀመረው መስከረም 4, 1968 በናዝሬት አካዳሚ እንደነበር ተገልጿል። ፕሬዚዳንት አያይዘውም ይህን አስመልክቶ ከሐምሌ 6-9 የተዘጋጀ መርሐግብር እንዳለ ገልጸዋ።

ፓስተር ሰንበቶ ባሼ አያይዘውም 50 ኛ ዓመትን ማክበር በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተሰጠ መመሪያ መሆኑን የተናገሩ ሲሆን፣ በዕለቱም የተለያዩ መርሐግብሮች እንዳሉትን ተገልጿል። በዚያውም ለአባቶች እውቅና የመስጠት ፕሮግራም አለ ብለዋል።

የኅብረቱ የአዲስ አበባ ጸሐፊ ፓስተር ሙላት ኤርምያስ በበከላቸው በፕሮግራሙ ዕለቶች የእንግዶችን ለመቀበልና ለማስተናገድ ሙሉ ዝግጅቶች ተጠናቀዋል ብለዋል። በተለያዩ ቅዱሳን ቤት እንግዶችን ለመቀበል ጭምር ቦታ መዘጋጀቱን ተገልጾል።

ኅብረቱ ሲመሰረት የነበሩት አቶ መኮንን ደሳለኝ በበከሉላቸው ኅብረቱ ያኔ ሲመሰረት በዘጠኝ ቤተ እምነቶች እንደነበርና የተለያዩ ተግሮቶችን አልፎ እዚህ ደርሷል። የተለያዩ ቤተ እምነቶችን አቀራርቧል፣ ለወንጌል አላማ ምድሪቷ ላይ ለተሰራው ስራ ኅብረቱን እግዚአብሔር ተጠቅሞበታል ብለዋል።

የሚሽንና ቲዮሎጂ መምሪያ ሐላፊ ወንድም የኔነህ ታደሰ በበከላቸው ዝግጅቱን በተመለከተ የመጋቢዎችና የመሪዎች ኮንፈረንስን አስመልክቶ ምዝገባዎች ይኖራሉ፣ ያለ ምዝገባ ማንም ሰው መገኘት አይችልም ያሉ ሲሆን፤ ኅብረቱ ሲመሰረት የነበሩት መተዳደሪያ ደንቦች እና የተለያዩ ዶክመንቶች ለህዝብ ይፋ ይሆናሉ። ምዝገባውን ከዚህ በታች ባሉት ስልክ ቁጥሮች በመደወልና ቢሮ በመምጣት መመዝገብ እንደሚችሉ ተናግረዋል። ይህን 50 ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ሙሉውን ዓመት የተለያዩ ኮንፈረንስ ማድረጉንና ብዙዎች ጌታን እንዳገኙና ወንጌል እንደተሰበከ ገልጸዋል።

በመግለጫው የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ኅብረት ለወንጌል የማይመቹ የፖለቲካ እሳቤዎችን ተጋፍጦ የቆመ ነው። ለሰላም የሰራ ተቋም ነው። የተለያዩ አደጋዎች ሲያጋጥሙ አብሮ በመገኘት የተለያዩ ድጋፍ አድርጓል።

ፕሮግራሙ በአራዳ ፓርክ ከሐምሌ 6-9 ድረስ እንደሚከናወን ተነግሯል!!

30/05/2026

"ካውንስሉ ቤተክርስቲያን አይደለም" ዶ/ር ስምዖን ሄሊሶ ‼️

ካውንስል በተመለከተ ካውንስሉ ምንድነው? ስልጣኑስ የት ድረስ ነው? ለሚለው ጥያቄ ቃለ ህይወት በመሪዎቿ በኩል አቋሟን ግልፅ አድርጋለች።

ዶ/ር ስምዖን የሚከተለውን ብለዋል:-
1, ካውንስሉ የኔትወርክ ድርጅት ነው!
2, ካውንስሉ ቤተክርስቲያን አይደለም!
3, ካውንስሉ ቤተክርስቲያናት ከሌሉ ህልውና የለውም!
4, ካውንስሉ ባይኖርም አብያተክርስቲያናት ግን ይኖራሉ!
5, ካውንስሉ የቤተክርስቲያንን ስራ መስራት የለበትም
6, እስከ አሁን የተሰሩ ስህተቶች (ካውንስሉን በተመለከተ) ይታረማሉ!
7, በመግባባት የማይፈታ ከሆነ (ከካውንስሉ ጋር ያለው ግንኙነት) በህግ የቃለ ህይወትን መብት እናስጠብቃለን!

©️ዶ/ር ስምዖን ሄሊሶ

የጋሞ ዞን እና አርባ ምንጭ ከተማ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት፣ካውንስል እና የዊን ሶልስ ፎር ጋድ ኤቫንጄሊካል ሚኒስትሪ ከግንቦት 14-16/2018  የተዘጋጀው መንፈሳዊ ኮንፍራ...
27/05/2026

የጋሞ ዞን እና አርባ ምንጭ ከተማ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት፣ካውንስል እና የዊን ሶልስ ፎር ጋድ ኤቫንጄሊካል ሚኒስትሪ ከግንቦት 14-16/2018 የተዘጋጀው መንፈሳዊ ኮንፍራንስ በድል ተጠናቀቀ።

18/05/2026
17/05/2026

32K likes, 1.5K comments. "Track3// ህክምናዬ//Hekemenaye//Addisalem Assefa // አዲስአለም አሠፋ// New album 2025"

Address

Gamo Zone
Arba Minch'
23

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gamo Zone Evangelical Church Fellowship Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share