የጽዮን ልጆች

የጽዮን ልጆች እስራኤል ሆይ ስማ አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው።

16/03/2026

NO MORE TRINITY!!

ገና ነው ገና ነው ታምራቱገና ነው ገና ነው ድንቅ ይሰራል
16/03/2026

ገና ነው ገና ነው ታምራቱ
ገና ነው ገና ነው ድንቅ ይሰራል

12/03/2026

ዋራ የአዲሲቷ ኢየሩሳሌም ምሳሌ
ከነገድ ከቋንቋ የአንድዬ ልጆች
የሚሰበሰቡባት

WARA BETHEL CONFERENCE 2026 35ኛው ዋራ ቤቴል አለም አቀፍ ኮንፍራንስ ከመጋቢት 3-6/2018 ዓ.ም ይካሄዳል። እንኳን ጌታ ኢየሱስ በሰላም በጤና አደረሰን !!! ስንቶቻችሁ ...
10/02/2026

WARA BETHEL CONFERENCE 2026

35ኛው ዋራ ቤቴል አለም አቀፍ ኮንፍራንስ ከመጋቢት 3-6/2018 ዓ.ም ይካሄዳል።
እንኳን ጌታ ኢየሱስ በሰላም በጤና አደረሰን !!!
ስንቶቻችሁ ለመሄድ ተዘጋጅታችኋል?

 በኢትዮጵያ ሐ/ቤ/ያን ስዳማ ሰበካ አለታ ቅ/ሰበካ አመታዊ ኮንፍረንስ ከጥር 29 እስከ የካቲት 01 /2018 ዓ/ም ድረስ በአለታ ወንዶ እናት አጥብያ ሐ/ቤ/ያን ግቢ ውስጥ ይካሄዳል። #ሁላ...
28/01/2026


በኢትዮጵያ ሐ/ቤ/ያን ስዳማ ሰበካ አለታ ቅ/ሰበካ አመታዊ ኮንፍረንስ ከጥር 29 እስከ የካቲት 01 /2018 ዓ/ም ድረስ በአለታ ወንዶ እናት አጥብያ ሐ/ቤ/ያን ግቢ ውስጥ ይካሄዳል።

#ሁላችሁም ወደዚህ የበረከት ጉባኤ በክርስቶስ ኢየሱስ ፍቅር ተጋብዛችኋል!

11/11/2025

ሥላሴ አማኞች እባካችሁ እስካሁን 3 ብቻ?
ትንቢተ ሕዝቅኤል 1:5 አንብቡና የሆነ ለውጥ አድርጉ እንጂ .....

 #የኢትዮጵያ ሐዋሪያዊት ቤተክርስቲያን እስካሁን ከተከናወኑ ፕሮጀክቶች መካከል በአይነቱ ልዩ እና ትልቅ የተባለውን ስራ ለማከናወን በሰበታ አጥቢያ የሚገነባው የኮንፍራንስ ማዕከል ፕሮጀክት ለ...
06/11/2025

#የኢትዮጵያ ሐዋሪያዊት ቤተክርስቲያን እስካሁን ከተከናወኑ ፕሮጀክቶች መካከል በአይነቱ ልዩ እና ትልቅ የተባለውን ስራ ለማከናወን በሰበታ አጥቢያ የሚገነባው የኮንፍራንስ ማዕከል ፕሮጀክት ለማስጀመር ትላንት ጥቅምት 25 ቀን 2018 ዓ.ም የቤተክርስቲያኗ ዋና አስተዳዳሪ ቢሾፕ ደጉ ከበደ፣ የስራ አስፈፃሚ ቦርድ አባላት፣ ስራውን የሚያከናውኑ ኢንጂነሮች፣ አርክቴክቶች፣ እናቶች፣ አባቶች እና ወጣቶች በተገኙበት የመሰረት ድንጋይ የማስቀመጥ ሰነ ስርዓት ተካሂዷል።

እግዚአብሔር ይመስገን፣ ይህ ፕሮጀክት ሲያልቅ በአንድ ጊዜ ከ15,000 እስከ 20,000 ተሳታፊዎችን የመያዝ አቅም ያለው የኮንፍራንስ ማዕከል ይሆናል።

#እግዚአብሔር ይባርክ።

ከሰማይም፡— ከእንግዲህ ወዲህ በጌታ የሚሞቱ ሙታን ብፁዓን ናቸው። መንፈስ፡— አዎን፥ ከድካማቸው ያርፉ ዘንድ፥ ሥራቸውም ይከተላቸዋል ይላል ብለህ ጻፍ የሚል ድምፅ ሰማሁ። ራዕይ 14:13መልካ...
24/08/2025

ከሰማይም፡— ከእንግዲህ ወዲህ በጌታ የሚሞቱ ሙታን ብፁዓን ናቸው። መንፈስ፡— አዎን፥ ከድካማቸው ያርፉ ዘንድ፥ ሥራቸውም ይከተላቸዋል ይላል ብለህ ጻፍ የሚል ድምፅ ሰማሁ። ራዕይ 14:13

መልካም ዕረፍት አባታችን❤😍

Share it!!
23/08/2025

Share it!!

አድን/2*/ በምድረበዳ በጥልቁ ያሉትንየሱስ ጽድቅ የተራቡ የተጠሙትን
17/08/2025

አድን/2*/ በምድረበዳ በጥልቁ ያሉትን
የሱስ ጽድቅ የተራቡ የተጠሙትን

14/08/2025

ያውቅበታል ውብ ማድረግን ሁሉን በጊዜው/4*
የአመታት እንባ በእሱ ይታበሳል
የዘመናት ጩኸት ለካ ይመለሳል

በታማኙ ኢየሱስ ይመለሳል
ከታማኙ ጌታ መልስ ይመጣል/2*

በምህረቱ ባለጠጋአቤቱ እኔ ማን ነኝ ቤቴስ ምንድነውበእኔ ላይ የምህረትህ የደግነትህ ባለጠግነት የተገለጠውምህረት እየበዛልኝጥበቃህ ሳይለየኝበፍቅር የተቀበልከኝጌታ ሆይ እኔ ማን ነኝ1. አንዳች...
10/08/2025

በምህረቱ ባለጠጋ

አቤቱ እኔ ማን ነኝ ቤቴስ ምንድነው
በእኔ ላይ የምህረትህ የደግነትህ ባለጠግነት የተገለጠው
ምህረት እየበዛልኝ
ጥበቃህ ሳይለየኝ
በፍቅር የተቀበልከኝ
ጌታ ሆይ እኔ ማን ነኝ

1. አንዳች ታሪክ የለኝ በኩራት የምናገረው
ከምህረትህ በቀር ዛሬን አቆመኝ ምለው
ካንተ ፀጋ በቀር አሻገረኝ የምለው
እንደ ብርቱ ቆሜ ዛሬ የምዘምረው
በእኔ ብርታት ሳይሆን የሱስ በምህረትህ ነው
እኔ ችዬ ሳይሆን አንተ አግዘኸኝ ነው

አላልፈውም ያልኩትን ምህረትህ አሳለፈኝ
አልችለውም ያልኩትን በፀጋህ ተሻገርኩኝ
ይህ ከባድ ነው ያልኩትን ደግፈህ አሻገርከኝ

ምህረትህ ከለለኝ (እየሱሴ)*4
ፀጋህ አሻገረኝ (አባዬ)

2. ያ የማይታለፍ የመሰለው ለሊት
ባንተ በቸርነትህ ብርሃን የወጣበት
ያ እንዳይነጋ የረዘመው ለሊት
ባንተ በምህረትህ ብዛት ነጋበት

በምህረትህ ባለፀጋ*2 እየሱስ
በቸርነትህ ባለፀጋ*2 እየሱስ

እንደ አበደ ሰው የሚያደርገኝ
ክብሬን አስጥሎ ሚያዘምረኝ
ብዙ ምህረት በህይወቴ አለ
ያኔ በመስቀል የተከፈለ

ያየሁ ነኝ ብዙ ምህረት ያየሁ ነኝ
ያየሁ ነኝ ብዙ ደግነት ያየሁ ነኝ
ያየሁ ነኝ ብዙ ቸርነት ያየሁ ነኝ
ያየሁ ነኝ ብዙ በጎነት ያየሁ ነኝ
ሲረዳኝ አይቻለሁ
ሲያግዘኝ አይቻለሁ
ደግፎኝ አይቻለሁ
ምህረቱን እዘምራለሁ
አይቻለሁ የሱን ምህረት አይቻለሁ
አይቻለሁ ብዙ ደግነት አይቻለሁ
አይቻለሁ የሱን ቸርነት አይቻለሁ
አይቻለሁ ብዙ በጎነት አይቻለሁ

ዛሬ ላለሁበት መሠረቴ
የመቆሜ ምክንያት ለኔ ብርታቴ
ታሪኬን ለውጦት ነው እንዲህ ያማረብኝ
ከቶ የማልዘነጋው ውለታ አለብኝ

እንዴት ልርሳው ከየት እንዳነሳኝ
አልዘነጋም ማን እንደነበርኩኝ
አመዴን/ትቢያዬን ከላዬ አራግፎልኝ
ለዚህ ክብር እኔን እንዳበቃኝ

ልርሳው ብል እንኳን ችዬ እንዳልረሳው /የማልረሳው/
በህይወቴ ሞልቷል /በዝቷል/ የእርሱ ውለታው
ያሳለፈኝን ያንን ዘመን
እኔስ አልረሳም ደግነቱን /ውለታውን/

አልረሳም ያን ዘመን
>> ያለፍኩትን
አልረሳም ምህረቱን
>> ደግነቱን
>> ያለፍኩትን
>> ውለታውን
አንደበቴ ከሚናገረው በላይ
ከንፈሮቼ ከሚያወሩልህ በላይ
ሰዎች እኔን ሲያዩ ምህረትህን ያያሉ
ሰዎች እኔን ሲያዩ ቸርነትህን ያያሉ
ሰዎች እኔን ሲያዩ ያሳለፍከኝን ያያሉ
ሰዎች እኔን ሲያዩ በአንተ ይፅናናሉ
ሰዎች እኔን ሲያዩ ደግነትህን ያያሉ
ሰዎች እኔን ሲያዩ ታምራትህን ያያሉ
ሰዎች እኔን ሲያዩ አንተን ያመሰግናሉ
ሰዎች እኔን ሲያዩ ለክብርህ ይዘምራሉ
አንተ እንደረዳኸኝ ያያሉ
አባት እንደሆንከኝ ያያሉ
እንደ ደጋገፍከኝ ያያሉ
ዛሬን እንዳቆምከኝ ያያሉ
ምስጋናህ ይዘመርልኝ
ማዳንህ ይነገርልኝ
አንተ እንደረዳኸኝ
እኔ ምስክር ነኝ ።

Address

Apostolic Church Of Ethiopia
Aleta

Telephone

+251941008089

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የጽዮን ልጆች posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share