Ethiopian Orthodox Tewahdo Youth page_የኢኦተቤክ ወጣቶች ፔጅ

  • Home
  • Ethiopia
  • Alamat'a
  • Ethiopian Orthodox Tewahdo Youth page_የኢኦተቤክ ወጣቶች ፔጅ

Ethiopian Orthodox Tewahdo Youth page_የኢኦተቤክ ወጣቶች ፔጅ «ነዋ ወንጌለ መንግሥቱ ለወልደ እግዚአብሔር 📖»

«አውደ ዓመት ለባርኮ ባርኮ ዓውደ ዓመትንዒ ማርያም ለምሕረት ወሣህል።»         እንኳን አደረሳችሁ ፳፻፲፱ዓ.ም የምሕረት ዘመን ያድርግልን🙏
10/09/2026

«አውደ ዓመት ለባርኮ ባርኮ ዓውደ ዓመት
ንዒ ማርያም ለምሕረት ወሣህል።»
እንኳን አደረሳችሁ
፳፻፲፱ዓ.ም የምሕረት ዘመን ያድርግልን🙏

አምላከ ተክለሃይማኖት በዕድሜ በጤና ይጠብቅልን🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏መሪነት አስተዳደራዊ ውሳኔዎችን ከመስጠትና ያለፈ ጥልቅ ማኅበራዊና መንፈሳዊ መስተጋብርን የሚጠይቅ ትልቅ ኃላፊነት ነው። እ...
30/08/2026

አምላከ ተክለሃይማኖት በዕድሜ በጤና ይጠብቅልን🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
መሪነት አስተዳደራዊ ውሳኔዎችን ከመስጠትና ያለፈ ጥልቅ ማኅበራዊና መንፈሳዊ መስተጋብርን የሚጠይቅ ትልቅ ኃላፊነት ነው። እውነተኛና ስኬታማ መሪነት የሚለካው ከሚመሩት ሕዝብ ጋር በሚፈጠር ቅርበት፣ የሕዝብን ሕሊናና እምነት በማክበር፣ እንዲሁም ደስታንም ሆነ ፈተናን አብሮ በመካፈል ነው። በዛሬው ዕለት የወላይታ ሶዶ ከተማ ከንቲባ ክብርት እታገኝ ኃይለማርያም በወላይታ ሶዶ ደብረ መንክራት አቡነ ተክለሃይማኖት ካቴድራል በተከበረው የታላቁ አባታችን ብርሀን ዘኢትዮጵያ የአቡነ ተክለሃይማኖት የእረፍት መታሰቢያ በዓል ላይ የተገኙበት አጋጣሚ ይህንኑ እውነተኛ የመሪነት ባህሪ በግልጽ የሚያሳይ ሁነት ነበር።

Hailemariam

🌿🌿🌿🌿🌿የመልአኩ ጥበቃ ያልተለያችሁ መስክሩ ለዓለም ስሙን ገልጣችሁ ገብርኤል ገብርኤል ገብርኤል ስለውፈጥኖ የታደገኝ አማላጄ እሱ ነው።          🌿🌿🌿🍃🌿በሕይወታችሁ መልአኩ ቅዱስ ገብር...
26/07/2026

🌿🌿🌿🌿🌿
የመልአኩ ጥበቃ ያልተለያችሁ
መስክሩ ለዓለም ስሙን ገልጣችሁ
ገብርኤል ገብርኤል ገብርኤል ስለው
ፈጥኖ የታደገኝ አማላጄ እሱ ነው።
🌿🌿🌿🍃🌿
በሕይወታችሁ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል የረዳችሁ
ድምጻችሁ ይሰማ አለን አለን እያላችሁ ❤





🔥«ጥብዒኬ እምዬ»🔥፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨(እናቴ ሆይ አትፍሪ)፦ በአንድ ወቅት በክርስቶስ ባመኑና በታመኑ እናትና ልጅ የተደረገ የመጽናናት ንግግር ነው።ህጻኑ ቂርቆስ ...
25/07/2026

🔥«ጥብዒኬ እምዬ»🔥
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
(እናቴ ሆይ አትፍሪ)፦ በአንድ ወቅት በክርስቶስ ባመኑና በታመኑ እናትና ልጅ የተደረገ የመጽናናት ንግግር ነው።ህጻኑ ቂርቆስ ይባላል፤አባቱም ቆዝሞስ እናቱ ደግሞ ኢየሉጣ ትባላለች።በሮም ግዛት አንጌበን በሚባል ሥፍራ የሚኖሩ ሰማዕታተ ክርስቶስ ናቸው።

🔥.በ፫፻፫ ዓ.ም በአባ ባጋግዮስ ምክንያት ዲዮቅልጥያኖስ ንጉሠ ሮም «አብያተክርስቲያናት ይትዐጸዋ አብያተ ጣዖታት ይትራኀዋ» ብሎ አወጀ።በዚህ ጊዜ ክርስቲያኖች ወደ ተለያዩ ሥፍራዎች መሰደድ ጀመሩ፤ቅድስት ኢየሉጣ ግን በ3ዓመት ልጇ ምክንያት ርቃ መሰደድ አልቻለችም።ኢቆንዮን ወደምትባል ከተማ ገብታ ተቀመጠች። መከራን ሸሽታ ሀገሯን ጥላ ብትሰደድም መከራው ግን አላለፋትም።የዚያች ሀገር መስፍን እለእስክንድሮስ ይባላል ክርስቶስን የካደ ለጣዖት የሚሰግድ መስፍን ነው። በዚህ ጊዜ ኢየሉጣን አስጠርቶ «ክርስቶስን ካጂ ለጣዖትም ስገጂ» አላት።
ቅድስት ኢየሉጣም ዓይን እያለው ለማያይ፣ጆሮም እያለው ለማይሰማ፣እጅም እያለው ለማይዳስስ ፍጥረት አልሰግድም አለችው። መስፍኑም አይሆንም ካልሽማ በሰይፍ ትቀጫለሽ በማለት አስፈራራት። «ኢየሉጣም አንተ ላቆምከው ምስል አልሰግድም፤ይህንን ሕጻን እንኳ ብትጠይቀው የሚመልስልህ መልስ እኔ የተናገርኩትን ነው።» መስፍኑም በማባበል «አንተ ሕጻን ወርቅ የምሰጥህ ነኝና ለዚህ ጣዖት ስገድ» ቢለው የሚያጸና መንፈስ ቅዱስ አድሮበታልና «አንሰ ኢይሰግድ ለአማልክቲከ ርኩሳን ዘኢይክሉ አድኅኖ ርእሶሙ፤ ራሳቸውን እንኳ ማዳን ለማይችሉ ለረከሱ አማልክቶችህ ፈጽሞ አልሰግድም »አለው።

🔥.በዚህ ጊዜ መስፍኑ እለእስክንድሮስ እጅግ ተበሳጨና የብረት ጋን አስመጥቶ ወኃ በመሙላት እሳት እንዲያነዱበት በዚያ እንዲጨምሯቸው አዘዘ። የእሳቱ ድምጽ 42 ምዕራፍ ድረስ ይሰማ ነበር። ቅዱስ ያሬድም የእሳቱ ፍላት ሲገልጽ «ድምጻ ለጽህርት ከመ ነጎድጓደ ክረምት»በማለት ይገልጸዋል። ወደ ሚፈላው ውኋ ሊጨምሯቸው ሲወስዷቸው ኢየሉጣ ልቧ ታወከ ።በዚህ ጊዜ ነበር ሕጻኑ ቂርቆስ ወደ አምላኩ እየጸለየ «ጥብዒኬ እምዬ» እያለ ያጽናናው። እናቴ ሆይ አትፍሪ ገድላችንን እንፈጽም ከአሁን በኋላ ሞት የሚያገኘን አይደለም ፤በዚያውስ ላይ አናንያን አዛርያንና ሚሳኤልን ያዳነ አምላክ እኛን ያድነን ዘንድ የሚቻለው አይደለምን? እያለ በሚጣፍጥ የሕጻን አንደበቱ እናቱን ያጽናናበት ቃል ነው።

🔥.በዚህ ጊዜም እምዬ ኦርቶዶክስንና ኢትዮጵያ ሀገራችንን ሕጻኑ ቅዱስ ቂርቆስ የመሰሉ ልጆች ያስፈልጓታል።በመከራ ውስጥ እንኳ ብትሆን በአምላኳ ዘንድ ተስፋ እንዳትቆርጥ እጇን ይዞ እሳቱን የሚያሻግራት በእምነቱ የጸና የሚያጸና ልጅ ትሻለች።

🔥.ከሁሉም መጥፎ ነገር በፈጣሪ አዳኝነት ጨርሶ ተስፋ መቁረጥ ነውና ኦርቶዶክሳውያን እያሳለፍነው ያለው የመከራ ስቃይ ምንም እንኳ ሀገራችንን ጥለን ባያሰድደንም በምንወደው አምላክ ተስፋ ከማድረግ እና ከደጁ ፈጽመን እንዳንርቅ «ጥብዑኬ» አይዟችሁ አትፍሩ የሚለው የቅዱስ ቂርቆስ ቃልና «ንቁም በበህላዌነ» የሚለውን የመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል የመጽናኛ ቃላት ያስፈልጉናል።

🔥.የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል አማላጅነት፤ የቅዱሳኑ ቂርቆስ ወኢየሉጣ በረከት ከሁላችንም ጋራ ይደር አሜን/፫/
ጥብዒኬ ኢትዮጵያ



ስምሽ ጉልበት አለው ጨካኙን ያራራል ስለ እመአምላክ ብሎ ድኃው ጠግቦ ያድራል።             🎶🎶🎶🎶ትዝ አለኝ በላዔ ሰብእ ሰምቼ ታምርሽን ድንግል እሰጣለሁ ለጠራ ስምሽን። ❤ስለ እመአም...
22/07/2026

ስምሽ ጉልበት አለው ጨካኙን ያራራል
ስለ እመአምላክ ብሎ ድኃው ጠግቦ ያድራል።
🎶🎶🎶🎶
ትዝ አለኝ በላዔ ሰብእ ሰምቼ ታምርሽን
ድንግል እሰጣለሁ ለጠራ ስምሽን።
❤ስለ እመአምላክ ስለ አዛኝቷ❤
#ሰኔጎልጎታ #ኪዳነምሕረት
#ማርያም #ቤተክርስቲያን

💚💛❤️ለጠፋው ኢትዮጵያዊ እሴት መድኃኒቱ እንደዚህ ያለ በጎ መተሳሰብ ነው።💚💛❤       💕💕💕💕💕💕💕💕በአሁኑ ወቅት በማኅበራዊ ሚዲያ (በተለይም በቲክቶክ) ገጹ “moya” በሚል ስም የሚታወ...
17/07/2026

💚💛❤️ለጠፋው ኢትዮጵያዊ እሴት መድኃኒቱ እንደዚህ ያለ በጎ መተሳሰብ ነው።💚💛❤
💕💕💕💕💕💕💕💕
በአሁኑ ወቅት በማኅበራዊ ሚዲያ (በተለይም በቲክቶክ) ገጹ “moya” በሚል ስም የሚታወቀው አንድ ሙስሊም ወጣት፣ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ለሚያገኛቸው እንግዶችና መንገደኞች ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት የመስጠት (Free Lift) በጎ ተግባር በመጀመር የብዙዎችን ትኩረት ስቧል። በቅርቡ ባጋራውና በከፍተኛ ሁኔታ በቫይራል በሆነው አዲስ ቪዲዮው ላይ፣ በአካል ያገኘውን አንድ የኦርቶዶክስ እምነት አባት (ቄስ) መኪናው ውስጥ በመጋበዝ ያደረጉት እጅግ ትሁት እና ልብ የሚነካ ውይይት የብዙዎችን ቀልብ መግዛት ችሏል።

ወጣቱ እኚህን የሃይማኖት አባትን መንገድ ላይ ተመልክቶ “ልሸኝዎት” በማለት ወደ መኪናው ካስገባቸው በኋላ፣ ጉዟቸውን ሲጀምሩ “ለወትሮው እናቶችን ነበር የምሸኘው፤ እርስዎን ስመለከት ግን ወላሂ አልፌዎት መሄድ አልቻልኩም” ሲል የልብ ስሜቱን በታላቅ አክብሮትና በፈገግታ ይገልጽላቸዋል። አባም በወጣቱ በጎነትና ትህትና እጅግ ተደንቀው፣ “እንዲህ ያለህ ማር የሆንክ ልጅ ከየት ተገኘህ?” በማለት በደስታ የታጀበ ምርቃታቸውን ሲያጎርፉለት፣ እሱም በደስታ ፈገግ እያለ “አልሃምዱሊላህ፤ ይሄን የማደርገው በደስታ ነው፣ የሚሄዱበት ቦታ ድረስ በነፃ አደርስዎታለሁ” በማለት ምላሽ ይሰጣቸዋል።

ይህ በልዩ ፍቅርና በጎነት የታጀበው ጉዞ ከጀሞ ሚካኤል ተነስቶ ገላን አካባቢ ሲደርስ፣ አባ ከተሽከርካሪው ከመውረዳቸው በፊት “እደውልልሃለሁ ልጄ፤ ሁሌም እጸልይልሃለሁ” በማለት የስልኩን አድራሻ ተቀብለውታል። ወጣቱም በታላቅ አክብሮት “እሺ አባቴ፤ እኔም እዘይሮታለሁ” በማለት ቃል ገብቶላቸዋል።

ይህ በሙስሊሙ ወጣት እና በኦርቶዶክስ እምነት አባት መካከል የታየው ጥልቅ መከባበርና መዋደድ “ይቺ ናት እውነተኛዋ ኢትዮጵያ!” የሚያሰኝ ሲሆን፣ በወጣቶቻችን ላይ ያለንን ተስፋ ይበልጥ ያለመለመና በበጎነት እርስ በርስ መደጋገፍ ያለውን ውበት በተግባር ያሳየ ታላቅ ትምህርት ነው።

 👩‍🎓የቀን ሰራተኛዋ የዋንጫ ባለቤት ተቋሙ መድረክ ላይ የቅጥር ደብዳቤ ቢሰጣትም  በደስታዋ ቀን ወላጆቿ ግን አልተገኙም - ተማሪ ማስተዋል ካሳዉ በደቡብ ጎንደር ዞን ደብረታቦር ከተማ አካባ...
12/07/2026

👩‍🎓
የቀን ሰራተኛዋ የዋንጫ ባለቤት ተቋሙ መድረክ ላይ የቅጥር ደብዳቤ ቢሰጣትም በደስታዋ ቀን ወላጆቿ ግን አልተገኙም

- ተማሪ ማስተዋል ካሳዉ በደቡብ ጎንደር ዞን ደብረታቦር ከተማ አካባቢ ተወልዳ እንዳደገች ትናገራለች።
- የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷንም ደብረታቦር አካባቢ እንደተማረች መረጃዎችን ያጋራችን ሲሆን በትምህርቷ ወቅትም ቤተሰቦቿ አቅም የሌላቸዉ በመሆኑ በርካታ ዉጣ ዉረዶችን ፣ፈተናዎችን ለማሳለፍ ተገዳለች።

- የ 12ኛ ክፍል ከአጠናቀቀች በኋላ የሪሚዲያል ትምህርቷን ተመከታተል ወደ ጅጅጋ ዩነቨርሲቲ ብታመራም ዉጤቷ 49.5% በመሆኑ በ 0.5% ዉጤት ሳይመጣላት ቀርቷል።

- ዉጤት በመቅረቱ ተስፋ ያልቆረጠችዉ ተማሪ ማስተዋል ካሳዉ ወደ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ በማቅናት በለስ ፓራዳይዝ ኮሌጅ በዲፕሎማ መርሃግብር በፋርማሲ ትምህርት ክፍል በግል ለመማር ትመዘገባለች።

- ወደ በረሃ ገነቷ ግልገል በለስ ከተማ ለትምህርት ከሄደች በኋላም ቤተሰቦቿ የፋይናንስ አቅም የሌላቸዉ በመሆኑ ህይዎት ዉጣ ዉረድ እንደሆነባት ትገልፃለች።

- ትምህርቷን ለማጠናቀቅ የትምህርት፣የዶርም እንዲሁም የእለት ጉርስ ለማግኜት ከትምህርቷ ጎን ለጎን የቀን ስራ በመስራት ራሷን እያስተዳደረች ትምህርቷን በከፍተኛ ዉጤት ለማጠናቀቅ በቅታለች።

- ተማሪ ማስተዋል ካሳሁን የቀን ሰራተኛ በመሆን ለተከታታይ ዓመታት ጊዜዋን እየገፋች የነበረ ሲሆን ዛሬ ሀምሌ 4/2018 (26 A+ እና 16 A ) 4.00 በማምጣት የ2 ሜዳልያና የዋንጫ ተሸላሚ ለመሆን በቅታለች።

- የዋንጫና የሜዳልያ ባለቤቷ ተማሪ ማስተዋል ካሳሁን ቤተሰቦቿ አቅም የሌላቸዉ በመሆኑ እሷን ለማስመረቅ የመጣ አንድም ቤተሰብ ግን የሌለ በመሆኑ በጣም እንደከፋትም ትናገራለች።

- የበረሃ ሰዉ እጅግ ደግ በመሆኑ አከራዮቿና ጎረቤቶቿ ደስታዋን ለመካፈል በምረቃ ፕሮግራሙ የተገኙ መሆኑን ለመታዘብ ችለናል።

- በመጨረሻም በለስ ፓራዳይዝ ኮሌጅ ግልገል በለስ ካምፓስ የቀን ሰራተኛዋ ብርቱና ጀግናዋን ባለ ዋንጫና ሜዳልያ ባለቤቷን ተማሪ ማስተዋል ካሳሁንን በቋሚ ቅጥር እንደፈፀመላት የሚያሳይ የቅጥር ደብዳቤ ዋንጫዉን ስታነሳ በኮሌጁ አካዳሚክ ኮሚሽን በኩል በይፋ የቅጥር ደብዳቤዉ ተሰጥቷታል።

እንኳን ደስ አለሽ እያልን ዉድ ቤተሰቦቻችን በፍፁም ተስፋ አትቁረጡ !

ምንጭ ምሳሌ ሚዲያ ግልገል በለስ ,ኢትዮጵያ
ሀምሌ 04/2018 ዓ.ም

«ለወንጌል አገልግሎት ተፋጥነው ለሞትም የፈጠኑ ሐዋርያነ አበው ጴጥሮስ ወጳውሎስ በዓለ ዕረፍት እንኳን አደረሳችሁ» 🙏
12/07/2026

«ለወንጌል አገልግሎት ተፋጥነው ለሞትም የፈጠኑ ሐዋርያነ አበው ጴጥሮስ ወጳውሎስ በዓለ ዕረፍት እንኳን አደረሳችሁ» 🙏

Address

Main Road
Alamat'a

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Orthodox Tewahdo Youth page_የኢኦተቤክ ወጣቶች ፔጅ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Ethiopian Orthodox Tewahdo Youth page_የኢኦተቤክ ወጣቶች ፔጅ:

Shortcuts

Share