Abundant Grace የተትረፈረፈ ፀጋ

Abundant Grace የተትረፈረፈ ፀጋ This is a platform to discuss for a better knowledge and understanding of the word of God

ከእግዚአብሔር አፍ የሚወጣ ነገር!
21/07/2025

ከእግዚአብሔር አፍ የሚወጣ ነገር!

43 likes, 9 comments. “ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ”

16/06/2025

ፀጋው !!!

“እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ።” ዕብራውያን 4፥16

ምሕረት ማለት ይቅርታ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ርህራሄ ማሳየት ማለት ነው ። ምሕረት ማለት የጸጋ አንዱ ገጽታ ሲሆን ምሕረትን ፍለጋ ወደ ፀጋው ፊት ስንቀርብ የሚሆነው ይቅርታን መቀበል ብቻ ሳይሆን ፀጋው ይበዛልናል

* ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር የተሰቀለው ወንበዴ ምሕረትን ሲጠይቅ ምህረትን አገኘ ነገር ግን ምሕረትን ብቻ አግኝቶ አልቀረም ወደ ጸጋው ዙፋን ስለቀረበ ወደ ገነት መግባት ሆነለት

* ምሕረት በክፉ የዘራነውን ከማጨድ ታደገን ፀጋ ግን ክርስቶስ የዘራውን አሳጨደን!

* ከአባቱ ሸሽቶ አባክኖ ምህረትን ፍለጋ ወደ አባቱ ዘንድ ሲመለስ ምሕረትን ብቻ አላገኘም ይልቁንም ፀጋው ጋር ስለ ቀረበ ድግስ ተደገሰለት ክብር ተጨመረለት

* ምሕረት ከግብጽ ምድር ያወጣል ጸጋ ግን ወደ ተስፋይቱ ምድር ያስገባል

* በምሕረት እዳችን ተሰረዘልን ፀጋው ግን ከክርስቶስ ጋር ሁሉን ወራሽ አደረገን!

ጸጋው እንደዚህ ነው!

God is the reason of our existence !!!
22/01/2025

God is the reason of our existence !!!

TikTok | Make Your Day

21/01/2025

ወንድሞች ሆይ፥ የሰበክሁላችሁን ደግሞም የተቀበላችሁትን በእርሱም ደግሞ የቆማችሁበትን በእርሱም ደግሞ የምትድኑበትን ወንጌል አሳስባችኋለሁ፤
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:1

እንደ ክርስቲያን ለደቂቃም ቢሆን ችላ ልንለው የማይገባ እውነት ወንጌላችን ነው!
ለሌሎች እናበስረዋለን እኛም ደግሞ በእርሱ ድነናል፣ ቆመንበታል፣ ዘወትር ልንመላለስበት ይገባል!!!

በእግዚአብሔር ተወደናል!

29/06/2024

የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።”
ዕብራውያን 12:2

እኛ ክርስቲያኖች ፀንተን እንድንቆም፣ እንድንቀጥል፣ እንድናድግ፣ እንድናገለግል የሚያስችለን ኢየሱስ ነው!
ዓይናችንን ከኢየሱስ ላይ አንስተን ወደ ግራ ወይም ወደ ቀኝ ወደ ውስጥ ወይም ወደ ውጪ ማየት አይገባንም!

Let us fix our eyes on Jesus!

18/06/2024

1ኛ ዮሐንስ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁶ እርሱ ስለ እኛ ነፍሱን አሳልፎ ሰጥቶአልና በዚህ ፍቅርን አውቀናል፤ እኛም ስለ ወንድሞቻችን ነፍሳችንን አሳልፈን እንድንሰጥ ይገባናል።
¹⁷ ነገር ግን የዚህ ዓለም ገንዘብ ያለው፥ ወንድሙም የሚያስፈልገው ሲያጣ አይቶ ያልራራለት ማንም ቢሆን፥ የእግዚአብሔር ፍቅር በእርሱ እንዴት ይኖራል?

የክርስትናችን መሰረቱ ፍቅር ነዉ! ምንም ቢኖረን ፍቅር ግን ከሌለን ከንቱ ነው! ይላል የእግዚአብሔር ቃል (1ኛ ቆሮ 13፥1-3) ፍቅራችንን የምንገልፅበት ሜዳ ደግሞ በዙሪያችን ያሉ እህትና ወንድሞቻችን ናቸው! LET US WALK IN LOVE!

02/03/2024

“እርሱ ስለ እኛ ነፍሱን አሳልፎ ሰጥቶአልና በዚህ ፍቅርን አውቀናል፤ እኛም ስለ ወንድሞቻችን ነፍሳችንን አሳልፈን እንድንሰጥ ይገባናል::
1ኛ ዮሐንስ 3:16

ኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወቱን ስለ እኛ አሳልፎ ሰጥቶ አድኖናል ኢየሱስ ፍቅር ነው! በዚህም ምክንያት የተቀበልነው ሕይወት ተመልሶ ለወደደን ሕይወቱን ሰጥቶ ላዳነን የሚኖር ነዉ ቤተሰባችንን ብቻ ሳይሆን ጊዜያችንን ብቻ ሳይሆን ገንዘባችንን ብቻ ሳይሆን እውቀታችንን ብቻ ሳይሆን
እርሱ ሕይወቱን አሳልፎ ሰጥቶ እንዳዳነን የክርስትና ሕይወት ማለት ምንም ሳናስቀር ሙሉ ሕይወታችንን ሰጥተን የምንኖረው ነዉ!
እርሱ አድኖናልና!

22/02/2023

ተከበናል!!!

የእግ/ር ቃል በዕብራውያን መፅሐፍ ምዕራፍ 12:1 ላይ ማመን ቀላል ባልነበረበት መንፈስ ቅዱስ ምድር ላይ ወርዶ ባለነበረበት በብሉይ ኪዳን ዘመን በእምነታቸው ድል የነሱ አባቶችን እየጠቀሰ እንደ ደመና ከበውናል እያል እዚያው ቁጥር ላይ ሸክም የሚሆንብንና ቶሎ የሚከበንን ሐጢያት ብሎ ሌላ ከበባም እንዳለ ይጠቁመናል ነገር ግን በዚያ ነገሮች በድንግዝግዝ በሚታዩበት ዘመን ክርስቶስን በርቀት አይተው ያመኑትን የእምነት አባቶችን ተመልክተን እንዲሁም ደግሞ ከእነርሱ የሚልቀውን የእምነታችን ራስና ፈፃሚ የሆነውን ኢየሱስን ተመልክተን ቶሎ የሚከበንን ሸክምና ሃጢያት ወግድ ብለን ክርስቶስ በፊቱ ስላለው ደስታ ነውርን ንቆ ሩጫውን በትህግስት እንደሮጠ እኛም ክርስቶስን እያየን ሩጫችንን በትህግስት እንዳንሮጥ የሚያደርጉንን ሸክሞች አስወግደን የተሰጠንን እሩጫ በትዕግስት እንሩጥ! ይለናል....
የዳንበትንና የምንድንበትን ደግሞም የቆምንበትን ኢየሱስን ዕለት ዕለት እየተመለከትን ሊከበን የሚያስበውን የትኛውንም ከበባ ሰብረን በድል በሕይወት እንጓዝ!

Let us fix our eyes on JESUS!

14/06/2022

በዚህች ሕይወት ብቻ?!

1ኛ ቆሮ 15፥19 ላይ ጳውሎስ “በዚህች ሕይወት ብቻ ክርስቶስን ተስፋ ያደረግን ነን? ብሎ በአግራሞት ይጠይቅና ከሆነ ከሰው ሁሉ ይልቅ ምስኪኖች ነን ይላል። ጳውሎስ በዚህ ምዕራፍ ውስጥ እዉነትን እየገለጠ የሚያስተምራቸው በቆሮንቶስ ከሚገኙ ቅዱሳን መካከል ትንሳኤ ሙታን የለም የሚሉ ስለነበሩ ምዕራፉን ሲጀምር የሰበክንላችሁን እናንተም አምናችሁ የተቀበላችሁትን የቆማችሁበትን ደግሞም የዳናችሁበትን ወንጌል ላሳስባችሁ ይላል፤ ይህም ወንጌል መፅሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ሃጢያታችን ሞተ ተቀበረ መፅሐፍም እንደሚል በ3ኛው ቀን ተነሳ ይህን እኔም ሌሎችም የወንጌል አርበኞት ሰበክንላችሁ እናንተም አመናችሁ፤ እንግዲህ ክርስቶስ ከሙታን እንደተነሳ የሰበክን እንደሆነ ከእናንተ መካከል አንዳዶች እንዴት ትንሳኤ ሙታን የለም ይላሉ? 1ኛ ቆሮ 15፥12 ጳውሎስ አግራሞቱን ይቀጥልና እስቲ ንገሩኝ እያለ ይጠይቃል
1ኛ ቆሮ 15፥ 30-32

​ * እኛስ በሚያስፈራ ኑሮ ( ወንጌል በምንሰብክበት ቦታ ሁሉ ልንገደል በምንችልበት ሁኔታ ውስጥ) ወንጌልን እየሰበክን የምንኖረው?
​* እንደ ሰው በኤፌሶን ከአውሬ ጋር ከታገልኩኝ (በዚያ ዘመን የሮም መንግስት እስረኞችን አውሬዎች ጋር በመጣል የእስፖርት ትህይንት ያደርግ ነበረ ) በወንጌል ታስሬ እንዲህ ያለ ነገር በእኔ ላይ ቢደርስስ? በዚህ አይነት ቁርጠኝነት ወንጌልን የምንሰብከው በዚህች ህይወት ብቻ ክርስቶስን ተስፋ አድርገን ነውን? አይደለም !!! እንደዚያማ ቢሆን ወንጌልን ከምንሰብክ ይልቅ ነገ እንሞታለንና እንብላ እንጠጣ ባልን ነበር ይላል።
በመጨረሻም ጳውሎስ ምዕ 15ን ሲዘጋው ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ ይላል እንኳን እኛ እናንተም ከተማራችሁት እውነት የተነሳ ድካማችሁ በጌታ ከንቱ እንዳይሆን አወቃችዋልና በዚህ እውነት የምትደላደሉ ከዳናችሁበት ወንጌል ውጪ በትምህርት ነፋስ ፣ ስለ ወንጌልም በሚመጣ መከራ የማትነቃነቁ ይልቁንም የጌታ ስራ ሁል ጊዜ የሚበዛለች ሁኑ!

የምትደላደሉ፥ የማትነቃነቁም፥ የጌታም ሥራ ሁልጊዜ የሚበዛላችሁ ሁኑ!!!
1ኛ ቆሮንቶስ 15:58

Address

Addis Ababa

Telephone

+27815069242

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Abundant Grace የተትረፈረፈ ፀጋ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Abundant Grace የተትረፈረፈ ፀጋ:

Share