Temu ዘሚካኤል

Temu ዘሚካኤል "እነሆ ከዋነኞቹ አለቃዎች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ።" (ትንቢተ ዳንኤል ፲÷፲፫)

15/05/2026

❝ በሥላሴ ገመድ ፍጹም ታስረናል ፤ ከልባችን በማይነቀል በቅንዋተ ፍቅሩ ተቸንክረናል ፣ እርሱ ወዶናል አይጠላንም። እኛም በእምነት ይዘነዋል አንተወውም። ❞

[ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ]

‹‹አርሴማ›› ማለት፦ በወርቅ ልብሶች የተጎናጸፋችና የተሽለመች መልከ መልካም ውብ ማለት ነው።ከአባቷ ከቅዱስ ቴዎድሮስና ከእናቷ ቅድስት አትናሲያ በስዕለት ተወለደች፡፡ቅድስት አርሴማ በዓለም ...
14/05/2026

‹‹አርሴማ›› ማለት፦ በወርቅ ልብሶች የተጎናጸፋችና የተሽለመች መልከ መልካም ውብ ማለት ነው።

ከአባቷ ከቅዱስ ቴዎድሮስና ከእናቷ ቅድስት አትናሲያ በስዕለት ተወለደች፡፡

ቅድስት አርሴማ በዓለም ላይ ተወልዳ ዓለሙን ንቃ ለሰማያዊው መንግሥት የተጋች ታላቅ ሰማዕት ናት።

እናታችን ቅድስት አርሴማ ደም ግባቷ ያማረ ግን የናቀችው ሐብትና የዚህ ዓለም ብልጭልጭነት ያላታለላት ናት።

በአንገቷ የሐብል ጌጥ ሳይሆን የሰይፍ ስለት ያለፈ የክርስቶስ ሙሽራ ነች።

ቅድስት አርሴማ በውበቷ ምክንያት አላዊያን ነገሥታት ልባቸው ቀለጠ፤ እናታችን ደግሞ ልቧ በክርስቶስ ፍቅር ቀልጦ ነበርና ከክርስቶስ ፍቅር የሚለያትን የናቀች ናት፡፡

በመጨረሻም በመስከረም ፳፱ ቀን እምነቷን ጠብቃ ሰማዕትነትን ተቀበለች።

የሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ምልጃና በረከት ይደርብን🙏



09/05/2026

✨አንድ ሆና ተወልዳ አንዱን ቃል ብትወልደው “ማርያም “መዓዛዋ ዓለምን አወድው🤍✨

✨እንኳን ለልደታ ማርያም አደረሳችሁ✨

08/05/2026

ድንግል ሆይ የመዳኛችን ምክንያት የሆነው የልደትሽ ቀን ልደታችን ነው

✨እንኳን አደረሳችሁ ልደታ ማርያም የልባችሁን መልካም መሻት ሁሉ ትፈጽምላችሁ✨

08/05/2026

✨ልደታ ለማርያም አንኳን አደረሳችሁ✨

ልደታ ለማርያም✨ዮም ፍስሀ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያምእውነተኛውን ፀሐይ የወለደሽ ፀሐይ ሆይ እንኳን ተወለድሽ✨
08/05/2026

ልደታ ለማርያም

✨ዮም ፍስሀ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም

እውነተኛውን ፀሐይ የወለደሽ ፀሐይ ሆይ እንኳን ተወለድሽ✨

08/05/2026

✨በጉጉት ጠበቅን የልደትሽን ቀን
ካንቺ ስለወጣ የዓለሙ መድህን✨

ልደታ ለማርያም🤍

07/05/2026

“ሰው የሚናፍቀው ሞት
ሞትም የሚናፍቀው ሰው”

መሆኑ ሁሌም ይገርመኛል።

✨መድኃኔዓለም ሆይ ከከንቱ ሞት አድነኝ። ሁሉ ከንቱ ነው። የዚህ ዓለም ንብረት የከንቱ ከንቱ ነው። ሁሉም ኃላፊ ጠፊ ነውና።ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ ሃይማኖት እንኳ ቢኖረኝ በጎ ምግባር የሌለኝ ...
05/05/2026

✨መድኃኔዓለም ሆይ ከከንቱ ሞት አድነኝ። ሁሉ ከንቱ ነው። የዚህ ዓለም ንብረት የከንቱ ከንቱ ነው። ሁሉም ኃላፊ ጠፊ ነውና።ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ ሃይማኖት
እንኳ ቢኖረኝ በጎ ምግባር የሌለኝ
አነስተኛው አገልጋይ ማደርያ ቤት መኖሪያ ቦታዬ ከቅዱሳኖችህ ጋር ይሆን ዘንድ
ፈቃድህ ይሁን ።አቤቱ በፍጥረቱ ሁሉ አንደበት የምትመሰገን ለአንተ ለመድኃኔዓለም ክርስቶስ ክብር ምስጋና ይገባል። አቤቱ ለተራቆቱት ልብስ የምትሆናቸው ለአንተ ለኢየሱስ ክርስቶስ ክብር ምስጋና ይገባል።”❤️‍🩹✨



ማድረግ እንዳይረሳ🙏

ቤተክርስትያን የእናትነት በሃሪ ነው ያላት። ቤተክርስቲያን በሩን ለማንም አትዘጋም፤ ሁሉንም እንደ እግዚአብሔር ፍጥረት በፍቅር ትቀበላለች።ቤተክርስቲያን ማንንም ቢሆን "ተስፋ የሌለው ኃጢአተኛ...
04/05/2026

ቤተክርስትያን የእናትነት በሃሪ ነው ያላት።
ቤተክርስቲያን በሩን ለማንም አትዘጋም፤ ሁሉንም እንደ እግዚአብሔር ፍጥረት በፍቅር ትቀበላለች።
ቤተክርስቲያን ማንንም ቢሆን "ተስፋ የሌለው ኃጢአተኛ" ብላ አትፈርጅም። ይልቁንም "ኃጢአተኛው ከኃጢአቱ ተመልሶ በሕይወት ይኖር ዘንድ እንጂ መሞቱን አልፈቅድም" የሚለውን መለኮታዊ ቃል መሠረት በማድረግ፣ ለሁሉም የንስሐ በር ክፍት መሆኑን ታስተምራለች።

​​ቤተክርስቲያን የጻድቃን መሰብሰቢያ ብቻ ሳትሆን፣ የቆሰሉና በኃጢአት የታመሙ ሰዎች የሚፈወሱባት "መንፈሳዊ ሆስፒታል" ናት። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደተናገረው፦ "ቤተክርስቲያን የኃጢአተኞች እንጂ የጻድቃን መሰብሰቢያ አይደለችም።" ማንም ሰው ፍጹም ሆኖ ሳይሆን፣ ፍጹም ለመሆንና ከኃጢአቱ ለመፈወስ ነው ወደ ቤተክርስቲያን የሚመጣው።
​በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደ መግደላዊት ማርያም ያሉ ሴቶች በሰዎች ዘንድ "ኃጢአተኛ" ተብለው ቢናቁም፣ በጌታ ፊት ግን በንስሐ ታጥበው ትልቅ የቅድስና ደረጃ ላይ ደርሰዋል። "ኃጢአተኛ ናት" በሚል ምክንያት አንድን ሰው ከአገልግሎት ማግለል፣ የንስሐን ኃይልና የእግዚአብሔርን መሐሪነት መጠራጠር ይሆናል።
​እንዲህ ዓይነት ንግግሮች ሰዎችን ከቤተክርስቲያን ከማራቅ ባለፈ የሚያመጡት መንፈሳዊ ጥቅም የለም። ይልቁንም ሰውን ከኃጢአቱ ነጥሎ መጥላትና ግለሰቡ ግን ወደ በጎነት እንዲመለስ መርዳት የክርስትና መመሪያ ነው።



ማድረግ እንዳይረሳ🙏

አንጀት እሚበላ ፎቶይህ ሰው  በጀርባው ለያዘው ህፃን ወተት መግዣበየ መንገዱና በየታክሲው እየለመነ ነው።እሚያቁት ምንም የሌለው ምስኪን እንደሆነ ተናግረዋልወንድ ልጅ የጤና እክል ከሌለበት ከ...
03/05/2026

አንጀት እሚበላ ፎቶ
ይህ ሰው በጀርባው ለያዘው ህፃን ወተት መግዣበየ መንገዱና በየታክሲው እየለመነ ነው።
እሚያቁት ምንም የሌለው ምስኪን እንደሆነ ተናግረዋል

ወንድ ልጅ የጤና እክል ከሌለበት ከመስራት ይልቅ ልመናን መርጦ ልጅን በጀርባው አዝሎ የሰው ፊት ለማየት ጎዳና አይወጣም
ሰውየውን በቅርብ እምታውቁት ሚዲያላይ መርዳት ለሚችሉ ለሚያስተባብሩ ሰዎች ሼር ብታደርጉት መልካም ነው።



Address

Nifassilk
Addis Ababa
1000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Temu ዘሚካኤል posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share