SDARM Ethiopia - የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ተሐድሶ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • SDARM Ethiopia - የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ተሐድሶ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ

SDARM Ethiopia - የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ተሐድሶ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from SDARM Ethiopia - የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ተሐድሶ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ, Religious organisation, Ayat Meri Loke, Addis Ababa.

ክፍል 3ጦርነት፣ ቸነፈር፣ ረሐብና የምድር መንቀጥቀጥ (መናወጥ)  የሱስ ደቀመዛሙርቱን እንዲህ ሲል አስጠንቅቋቸዋል፡- “ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠ...
06/03/2026

ክፍል 3
ጦርነት፣ ቸነፈር፣ ረሐብና የምድር መንቀጥቀጥ (መናወጥ)

የሱስ ደቀመዛሙርቱን እንዲህ ሲል አስጠንቅቋቸዋል፡- “ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ፥ አትደንግጡ፤ ዳሩ ግን መጨረሻው ገና ነው። ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና ፤ ራብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል፡፡” (ማቴዎስ 24:6, 7)፡፡
ከቅርብ ጊዜ ውስጥ ህዝቦች የኖሩባቸውን ኹከትና ብጥብጥ ተመልከተናል፡፡ እያንዳንዱ ሰው ሰላምን ሲያንጋጥጥ፣ በተቃራኒው ጦርነት እየፈነዳ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት እየቀጠፈ ይገኛል፡፡ በብዙ ሀገራት በብሺ የሚቆጠሩ ስደተኞች ያለቀያቸውና አገራቸው እንዲሰደዱ እያደረጉ የሚገኙት ጦርነቶችና የፖለቲካ ነውጦች ረሃብ፣ ስቃይና ረሃብ እያደረሱባቸው ይገኛል፡፡ ምንም እንኳ እነዚህ ዘግናኝ ውድመቶች ቢደርሱም፣ ጦርነቱን ለማስቀጠል የጦር መሳሪያዎችንና ተተኳሽ ጥይቶችን ለመግዛት ቢሊዮን ዶላሮች እየፈሰሱ ናቸው፡፡
ከዚህ በተቃራኒው፣ በአንዳንድ ሀገራት ምግብ ተትረፍርፎ ብዙ ህዝቦችም በሚመገቧቸው ፈጥነው በሚበስሉ (fast food) ወይም ግብስብስ ምግቦች (junk food) ምክንያት በበሽታ እየተጠቁ እና በብዙ ሺህ ቶን የሚመዘን ምግብም ተመጋቢ አጥቶ በየቀኑ በቆሻሻ መጣያ እየተደፋ ቢሆንም፣ በአንፃሩ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ህዝቦች በረሃብ የተነሳ በሞት እየተቀጠፉባቸው ያሉ ሀገራትም ይገኛሉ፡፡ ቴክኖሎጂ እንዲህ በዘመነበት፣ ቁሳቁሶችን በቀላሉ የሚጓጓዙበት ትራንስፖርት እንዲህ በቀለለበት በዚህ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ይህን መቀበል በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡ በተጨማሪም ንፁህ ውኃ ባለመጠጣት ወይም የሚቀመስ ምግብ በማጣት በሚደርስባቸው ድካም የተነሳ የሰው ህይወት የሚቀጠፍባቸው ሀገራትም አሉ፡፡ በቅርብ አስርት ዓመታት ውስጥ እየደረሱ ያሉት የተፈጥሮ አደጋዎችም (መቅሰፍቶችም) የሱስ ከጠቀሳቸው ምልክቶች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡ በምንኖርባት ምድር አንዳንድ ሀገራት ህይወትን ሙሉ በሙሉ እያወደሙ ያለው ድርቅ እንዳለ ሆኖ፣ ያለመጠን ከተፈጥሮው በላይ በሚዘንበው ዝናብ ምክንያት እየተከሰተ ያለው ጎርፍ፣ ማዕበል ወይም አውዳሚ አውሎነፋስ ብዙ የሰው ህይወትንና የንብረት ውድመትን አስከትለው ያልፋሉ፡፡ በቅርብ ዓመታት ውስጥ፣ በብዙ ቦታዎች እየተከሰተ ያለው የምድር መናወጥ (መንቀጥቀጥ) የኃይሉ መጨመር ብቻ ሳይሆን እያደሰ ያለው ጉዳትም ይህ ነው ተብሎ አይገለጽም፡፡
“የመሬት መናወጥና ማዕበል፣ የውኃ ሙላትና የእሳት አደጋዎች፣ በንብረትና በሰው ሕይወት ላይ የሚያደርሱትን ውድመት የምንሰማው ምን ያህል ነው! እነዚህ ጥፋቶች ከሰው ቁጥጥር ውጭ መሆናቸው ግልጥ ነው፡፡ ነገር ግን በሁሉም የእግዚአብሔር እቅድ አለበት፡፡ ከቁጥጥር ውጭ በሆኑ የተፈጥሮ ኃይላት ፍንዳታ፣ ሙሉ በሙሉ ከሰው ቁጥጥር ውጭ በሆኑ ነገሮች የሚፈጠሩ መሆናቸው እርግጥ ነው ፤ ይሁን እንጂ በእነዚህ ሁሉ ነገሮች የእግዚአብሔር ዓላማ መነበብ ይችላል፡፡ ሰዎች ሊደርስባቸው የሚችለውን አደጋ እንዲገነዘቡ ለማድረግ ከሚጠቀምባቸው ወኪሎች መካከል ናቸው፡፡”
ተመራማሪዎች እና ፈላስፋዎች፣ እያንዳንዱ አደጋ የአየር ንብረት በተፈጥሮ ላይ በሚያስከትለው ለውጥ የተነሳ የሚመጣ ውጤት ነው ብለው ማብራሪያ ለማግኘትና ክስተቶቹንም (አደጋዎቹንም) ማስወገድ የሚችሉበትን መፍትሔ ፍለጋ በመጣጣር ላይ ናቸው፡፡ አሁንም በድጋሜ ሰብዓዊ ጽንሰ-ሐሳቦች (ፍልስፍናዎች) ለእነዚህ ክስተቶች ሊኖር ከሚገባው ከእውነተኛው ምክንያት የሰዎችን ጀሮ በማጣመም ላይ ናቸው፡፡ ተፈጥሮ በሰብዓዊ ክፉ ተግባር የተነሳ መሰቃየቷ እና መመሰቃቀሏ እውነት ነው ፤ ይሁን እንጂ ክርስቶስ የዘረዘራቸው ምልክቶች እነዚሁ መሆናቸውንም መርሳት የለብንም፡፡እንዲሁም ምድርን ያወደሙ ሰዎች ባደረሱት ውድመት የተነሳ እነርሱም መሰቃየት የግድ እንደሚላቸውም ጭምር ልንረሳ አይገባም፡፡
“አሕዛብም ተቈጡ፥ ቍጣህም መጣ፥ በሙታንም ትፈርድ ዘንድ ዘመን መጣ፥ ለባሪያዎችህም ለነቢያትና ለቅዱሳን ስምህንም ለሚፈሩት ለታናናሾችና ለታላላቆችም ዋጋቸውን ትሰጥ ዘንድ፥ ምድርንም የሚያጠፉትን ታጠፋ ዘንድ ዘመን መጣ ” (ራዕይ 11:18)፡፡
ታላቁ የመፍጠር ሥራ ውጤቶች በመውደም ላይ ናቸው ፤ ለውድመቱ ኃላፊነቱን የሚወስዱትም ይቀጣሉ፡፡ ክርስቶስ ጊዜውን እንዴት አድርገው ለይተው ያውቁ ዘንድ ለደቀመዛሙርቱ የገለፀላቸው እነዚህ ክስተቶች (ሁነቶች)፣ የመገለጡ ምልክቶች ሊሆኑ ይችላሉ? አወ ፤ ናቸው፡፡ ደቀመዛሙርቱ የዘመኑ መጨረሻ መቼ ነው ? ብለው እንደጠየቁት ፤ እኛም ቀናትን መወሰን አንችልም ፤ ምልክቶችን ብቻ ልንተረጉማቸው እና ለዓለማችንና ለነዋሪዎቿ ከዚህ በላይ ብዙ ጊዜ እንደማይኖር ልናስተውል እንችላለን፡፡ “ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ግን ከአባት ብቻ በቀር የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ፣ ሰውም ቢሆን የሚያውቅ የለም፡፡” (ማቴዎስ 24:36)፡፡

ታሪክ ራሱን ይደግማል

የመጨረሻው ዘመን በምድር ላይ ከወረደው ጎርፉ በፊት ከነበረው ሁናቴ ጋር ተመሳሳይ እንደሚሆን የሱስ አስቀድሞ አመላክቷል፡፡ “ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ግን ከአባት ብቻ በቀር የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ሰውም ቢሆን የሚያውቅ የለም። የኖኅ ዘመን እንደነበረ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናልና።
በዚያች ወራት ከጥፋት ውኃ በፊት፥ ኖኅ ወደ መርከብ እስከገባበት ቀን ድረስ፥ ሲበሉና ሲጠጡ ሲያገቡና ሲጋቡም እንደ ነበሩ፣ የጥፋት ውኃም መጥቶ ሁሉን እስከ ወሰደ ድረስ እንዳላወቁ፥ የሰው ልጅ መምጣት ደግሞ እንዲሁ ይሆናል።” (ማቴዎስ 24:37–39)፡፡
መብላት፣ መጠጣት ወይም መጋባት የኃጢአት ተግባራት አይደሉም፡፡ እነዚህ ነገሮች ለእግዚአብሔር አስፀያፊ እንዲሆኑ ያደረጋቸው ነገር ቢኖር ሰው ያለገደብ እየፈፀማቸው መሆኑ ነው፡፡ በዛሬው ጊዜ በጣም የታወቁ በሽታዎች የተንሰራፉበት ምክንያት በአብዛኛው በመጥፎ አመጋገብ ወይም አጠጣጥ፣ አካላዊ እንቅስቃሴ በሌለው የህይወት አኗኗር፣ እንዲሁም ለጤና ጎጂ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን በመጠቀምና አካልን ከመበዝበዝ የተነሳ የተከሰቱ ናቸው፡፡ መርዛማ ንጥረ ነገሮችን ማለትም በታላላቅ ከተሞች ወደ ትንፋሽ እየገባ ያለው አየር ወይም ትንባሆንና ሱስ አምጭ ንጥረ ነገሮችን (ጎጂ መድሃኒቶችን) በመጠቀም ለረዥም ጊዜ ተጋላጭ መሆን፣ ለብዙ በሽታዎች መንስኤ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን፣ ነገር ግን ሥነ-ባህርያዊ (የሥነ-ትውልድ) መለዋወጥን ሞራለ ቢስ ልሽቀት ወይም በሽታ ተከላካይ ህዋሳትን (ሴሎችን) አጥቂ በሽታ እንዲፈጠር አድርጎታል፡፡ በሰዶምና በጎሞራ የተፈፀመው ታሪክ፣ እንዲሁም ከተስፋዋ ምድር ፊት ለፊት በሰጢም ሸለቆ የእስራኤል ልጆች ያለፉበት የውድቀት ተሞክሮ፣ ሴሰኝነት እና መሻትን ያለመግዛት ልቅ ፍላጎት፣ ከምናስበው በላይ፣ እጅግ አፀያፊ ኃጢአት በእግዚአብሔር ፊት እንዲፈጽሙ ሰዎችን የሚመሩ መሆናቸውን እኛን ለማስተማር የተመዘገቡ ማስጠንቀቂያዎች ናቸው፡፡
“ በስሜት እርካታ ቋጥኝ ላይ ተንኮታኩተው ሆጭ እንዳሉ የተተው፣ የተበታተኑ፣ በዘመናት ዓመታት ሁሉ የባህርይ ስብርባሪዎች ሞልተዋል፡፡ ወደምድር ታሪክ መዝጊያ እየተቃረብን ስንመጣና የእግዚአብሔር ህዝቦች ሰማያዊውን ከንዓን መግቢያ ደንበር ላይ ሲደርሱ፣ ሰይጣን ጥንት ካደረገው ኃይሉን በእጥፍ አሰባስቦ ወደ አምላካዊው መልካም ምድር እንዳይገቡ ይከላከላቸዋል፡፡ በእያንዳንዱ ሰው መንገድ ላይ ወጥመዱን ይዘረጋል፡፡ ከፈተናዎቹ መከለል (መጠበቅ) ያለባቸው ያልተማሩትና እውቀት የሌላቸው ብቻ አይደሉም ፤ ይልቁንም በኃላፊነት ከፍተኛ ቦታ ላይ አልፎም በተቀደሰው መንፈሳዊ ስፍራ እያገለገሉ ለሚገኙት ሁሉ ፈተናዎቹን አቀነባብሮ ያቀርብላቸዋል፡፡ እነዚህን ሰዎች በማሳት ነፍሳቸውን መበከል ከቻለ በእነርሱ አማካኝነት ብዙዎችን ማጥፋት ይቻለዋል፡፡ ለዚህም ሰይጣን ከሶስት ሺህ ዓመታት በፊት የተጠቀመውን ያንውን ወኪል (ዘዴ) አሁንም ጥቅም ላይ ያውለዋል፡፡ ዓለማዊ ጓደኞችን፣ ውበትና ቁንጅናን፣ ደስታና ፈንጠዝያን፣ ሳቅና ጨዋታን፣ ግብዣና የወይን ጠጅን ተጠቅሞ ሰዎች ሰባተኛውን ሕግ እንዲጥሱ ይፈትናቸዋል፡፡”

ክፍል ሁለት እርገቱና ዳግም መመለሱከትንሳኤው አርባ ቀናት በኋላ፣ የሱስ ችላ ወደተባለበትና እንዲሞት ወደተፈረደበት ከየሩሳሌም ከተማ ፊት ለፊት፣ ወደ ቢታንያ ቀርብ ብሎ ወደሚገኘው ወደ ወይራ...
04/03/2026

ክፍል ሁለት
እርገቱና ዳግም መመለሱ

ከትንሳኤው አርባ ቀናት በኋላ፣ የሱስ ችላ ወደተባለበትና እንዲሞት ወደተፈረደበት ከየሩሳሌም ከተማ ፊት ለፊት፣ ወደ ቢታንያ ቀርብ ብሎ ወደሚገኘው ወደ ወይራ ዛፎች ተራራ (የደብረዘይት ተራራ) ደቀመዛሙርቱን እየመራ ወሰዳቸው፡፡ ያ ጊዜም ጠፍቶ የተገኘውን በግ (በጎች) ወክለው ለቆሙት ለእነዚህ ወንዶችና ሴቶች ስብስብ የመሰነባበቻ እና የመጨረሻውን መመሪያ የማስተላለፊያ መልካም አጋጣሚ ነበር፡፡ የየሱስ ቃላት ለእነርሱ ያለውን ጥልቅ አሳቢነትና ርህራሔ እንጂ ላሳዩት ስህተትና ውደድቀት የተሰጠ ተግሳጽ አልነበረም፡፡
“ ሊባርካቸውና እንደሚጠነቀቅላቸው በሚገልጽ ሁኔታ እጆቹን እንደዘረጋ ከማንኛውም ምድራዊ ስበት በበለጠ ኃይል ወደ ሰማይ በመሳብ በቀስታ ከመካከላቸው ተነስቶ ወደላይ አረገ፡፡ እርሱ ወደላይ እየወጣ ሳል የክብር ዳመና ከዓይናቸው ሰወረው፡፡ መላእክት የዳመና ሰረገላ መስለው በተቀበሉት ጊዜ ደቀመዛሙርቱ ‘እነሆ እኔ እስከ ዓለም መጨረሻ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ’ ሲል ጌታ የሰጣቸውን ተስፋ አስታወሱ፡፡ በዚሁ ጊዜ በጣም ጣፋጭ እና አስደሳች የሆነ የመላዕክትን መዘምራን መዝሙር ሰሙ፡፡”
በዚያኑ ጊዜ ሁለት ኃያላን መላዕክት በሰዎች ቅርጽ ተገልፀው፣ ወደ ሰማይ አንጋጥጠው ይመለከቱ ለነበሩት ደቀመዛሙርት ባላቸው ርህራሔና ፍቅር ተነሳስተው ወደ እነርሱ ቀርበው እንዲህ ሲሉ ጠየቋቸው፡- “ደግሞም እናንት የገሊላ ሰዎች ሆይ፥ ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ ስለ ምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው የሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት፥ እንዲሁ ይመጣል አሉአቸው።” (የሐዋ ሥራ 1:11)፡፡ ይህም የሱስ ከብዙ ጊዜ በፊት ለደቀመዛሙርቱ እንዲህ ሲል ከሰጣቸው መልእክት ጋር አንድ ነበር፡፡ “የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላእክቱ ሁሉ፥ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል” (ማቴ 25:31)፡፡ ይህም “እነሆ፥ ከደመና ጋር ይመጣል፤ ዓይንም ሁሉ የወጉትም ያዩታል፥ የምድርም ወገኖች ሁሉ ስለ እርሱ ዋይ ዋይ ይላሉ። አዎን፥ አሜን።” (ራዕይ 1:7) ሲል በፍጥሞ ደሴት ለዮሐንስ ከተገለጠለት ራዕይ ጋር አንድ ነበር፡፡ ወደሰማይ ሲያርግ ያዩት ይኸው የሱስ ልክ ወደሰማይ ባረገበት ሁኔታ ተመልሶ እንደሚመጣ መላዕክት አረጋገጡላቸው፡፡ በእርግጥም፣ እርሱ በዳመናት ይመጣል ፤ አይንም ሁሉ ያየዋል፡፡

የመምጣቱ (የመገለጡ) ምልክቶች

የመጨረሻውን ጊዜ ማወቅ የደቀመዛሙርቱን ትኩረት እጅግ የመሰጠ ጉዳይ ነበር—የእኛንም ትኩረት መሳብ ይገባዋል፡፡ ለብቻቸው ወደየሱስ በመምጣት፡- “ንገረን፥ ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው? አሉት” (ማቴዎስ 24:3)፡፡ ቴክኖሎጂ በተራቀቀበት ቦታዎች እንዲሁም የመንገድ ጉዞ በዘመናዊ የትራንስፖርት መሳሪያዎች በሚከናወንበት በአሁኑ ጊዜ፣ አቅጣጫ መሪ ሳተላይቶች ወይም ጂፒኤስ (GPS) ወደ ምንሄድበት ቦታ ምን ያህል ጉዞ ወይም እርቀት እንደቀረን ለሚሰጡን አቅጣጫ ጠቋሚ ምልክቶች ልዩ ትኩረት እንሰጣለን፡፡ በመንገድ ዳር የቆሙ ምልክቶችም እንዲሁ ያግዙናል፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢታትም ልክ እንደ ጂፒኤስ (GPS) ከጊዜ አንፃር ምን ላይ እንደቆምን በመንገር እንድንዘጋጅ እና ወደ መዳረሻችን በሰላም እንድንደርስ ያመላክቱናል፡፡

ማሳሳቻ (ሽንገላ)

“የሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው። ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ፡፡ ብዙዎች። እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና ፤ ብዙዎችንም ያስታሉ፡፡ ” (ማቴዎስ 24፡-4፣5)፡፡
ለምንድን ነው ክርስቶስ ይህን ከመጨረሻው በፊት የመጀመሪያ ምልክት አድርጎ ያቀረበው ? መልሱ በሐዋሪያው ጴጥሮስ ተሰጥቷል፡- “በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና (1ኛ ጴጥ 5፡-8)፡፡
ውድ ወንድሞችና እህቶች፣ ሰይጣን ራሱ የመጽሐፍ ቅዱስን ትንቢታት እና የክርስቶስ መምጣት የእርሱን የሽብር ግዛት የሚቋጭበት መሆኑን ጠንቅቆ ያውቀዋል፡፡ ለዚያም ነው በታላቅ አታላይ ብልጠትና የሴራ ስለላ ልክ አንበሳ ግዳዩን ከማደኑ በፊት በቀስታ አድብቶ አፈፍ እንደሚያደርግ ሁሉ እርሱም አማኞችን በወጥመዱ ለመጣል፣ ከተወሰኑ የእውነት ክፍሎች ጋር ተቀላቅሎ የተዘጋጀውን የውሸት አስተምህሮዎቹን የሚያቀርበው፡፡ የእስልምና፣ የቡድሂዝም፣ እንዲሁም ከዚህ በኋላ ህይወትም አምላክም የለም የሚል የአጎኒስቲዝም ምንፍቅና እንዲሁም ሌሎች የፍልስፍና ማዕበላት መስፋፋት፣ የሰማይና የምድር ፈጣሪ ስለሆነው ስለ እውነተኛውና ብቸኛው እግዚአብሔር ባህርይ የሰዎችን አስተሳሰብ በማዛባት ብቸኛው የእውነት ምንጭ ከሆነው ከመጽሐፍ ቅዱስ እንዲርቁ አድርጓቸዋል፡፡
ብቸኛ ደህንነታችን በብዙ ፀሎትና ራስን መስጠት ቅዱስ መጽሐፍትን በማጥናት ላይ የተማከለ ነው፡፡ ከስህተት ሊጠብቀን የሚችለው ብቸኛው ዋስትና ይህ ብቻ ነው፡፡ ይህን ካደረግን፣ “ወደ ሕግና ወደ ምስክር ሂዱ! እንዲህም ያለውን ቃል ባይናገሩ ንጋት አይበራላቸውም [“ወደ ሕግና ወደ ምስክር ሂዱ! እንዲህም ያለውን ቃል አለመናገራቸው ምክንያቱ ብርሐን ስለሌላቸው ነው]” (ኢሳይያስ 8፡-20) የሚለውን ማረጋገጥ እንችላለን፡፡ ቅዱሳት መጽሐፍትን ደጋግመን ማጥናት “ተጽፎአል” [“It is written”] ብለን በእርግጠኛነት እንድናገር የሚያስችለንን ብቸኛ መዝገብ በአዕምሯችን ግምጃ ከዝነን እንድናከማች ያስችለናል፡፡ ነገር ግን በተቃራኒው የማስጠንቀቂያ አደጋም አለ፡- ቴክኖሎጂው እየተራቀቀ ሲሄድ፣ (ብዙ ክርስቲያናት) በሁሉም ዘንድ ተቀባይነት ያገኘውን ከወረቀት የተዘጋጀውን መጽሐፍ ቅዱስ ማንበባቸውን (ማጥናታቸውን) እርግፍ አድርገው መተዋቸው የታወቀ እየሆነ መጥቷል፡፡ በሌላ ሁኔታ፣ የሰንበት ትምህርቶች፣ የውዳሴ መዝሙሮች ወዘተ አካቶ የያዘውን የተሟላ የመጽኃፍት መደብር የሚይዙ የኤሌክትሪኒክስ መሳሪያዎችን (ሞባይልና ሌሎችም) ሁልጊዜም በእጃችን መያዝ ቀላል አድርጎልናል፡፡ ዳሩ ግን በተቃራኒው፣ በእነዚህ ኤሌክትሪኒክስ በሚደርሰን አንዲት የመልዕክት (የሜሴጅ) ምልክት፣ ወይም ኃሳብን በሚበትን በሆነ ቅጽበታዊ ትዕይንት መጽሀፍ ቅዱሳትን ማንበባችንን እንተውና በፍጥነት ወደ ሌሎች በመዞር አዕምሯችን ሌሎች ነገሮች ላይ ማውጠንጠን ይጀምራል፡፡ ውስብስብነት በሌለው በዚህ ቀላል መንገድ፣ ሰይጣን ብዙ ጊዜ፣ እውነትን ከማጥነት አማኞችን ዘወር ማድረጉን በሚገባ ቀልሎታል፡፡

የየሱስ ክርስቶስ መገለጥ (መምጣት) “የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚ...
26/02/2026

የየሱስ ክርስቶስ መገለጥ (መምጣት)

“የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል” (ቲቶ 2:13)፡፡“እጅግ ክቡር ብሎም እጅግ አንፀባራቂ ከሆኑ፣ ከተገለፁ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች መካከል አንዱ፣ ታላቁን የመቤዠት ሥራ ለማጠናቀቅ የሚመጣበት የክርስቶስ ዳግም ምፅዓት ነው።“በሞት አገር ጥላ”[(ማቴ 4÷16)] ይቀመጡ ዘንድ ለረጅም ዘመን ለተተውት የእግዚአብሔር የእምነት መንገደኛ ሕዝቦች “ትንሳኤና ሕይወት” [(ዮሐ 11÷25)] የሆነው “ያሳደደውን ወደ ቤቱ ይመልስ ዘንድ” [(2ኛ ሳሙ 14÷13)] ውድና ደስታን የሚያፋፍመው የመገለጡ ተስፋ ተሰጥቶአል፡፡ የዳግም ምፅዓቱ አስተምህሮ የተቀደሱት መጻሕፍት አንኳር ጭብጥ ነው።”
ለመጀመሪያ ጊዜ የቤተክርስቲያንን ጉባኤ ከቤተሰቤ ጋር ስካፈል ገና 11 ዓመቴ ነበር፡፡ በዚያም ለመጀመሪያ ጊዜ የክርስቶስን ዳግም ወደምድር ተመልሶ የመምጣቱን አስደናቂውን ብስራት ላዳምጥ ቻልኩኝ ፤ በትንቢታት የተገለፁት ታላላቅ ክስተቶች (ኹነቶች) እቅጩንና በተተነበየላቸው ጊዜ መፈጸማቸው ያን [የክርስቶስን ዳግም ምፃት] በአጭር ጊዜ ማየት እንደምንችል የማይዋሽ ማስረጃ ነው፡፡

የጌታ ተስፋ

ለመጨረሻ ጊዜ ወደጌተሰማኔ ለፀሎት ከማቅናቱ ጥቂት ቀደም ብሎ የሱስ ለደቀመዛሙርቱ ምድራዊ ተልዕኮው ወደመጠናቀቁ የደረሰ በመሆኑ፣ ተለይቷቸው እንደሚሄድ እና እነርሱ አሁን መሄድ ወደማይችሉበት ቦታ ሊመለስ መሆኑን ነግሯቸው ነበር፡፡ የደቀመዛሙርቱን መከፋትና ብቸኝነት በመመልከት የሱስ እንዲህ አላቸው:- “ልባችሁ አይታወክ” (ዮሐ 14:-1)፡፡ እነዚህ ቃላት ተስፋን ሰጧቸው፤ እንዲሁም እንደእነርሱም እርሱ እያንዳንዱን የሕይወት ውጣ ውረድ ሙሉ በሙሉ ጠንቅቆ እንደሚያውቅና ነፍስ በሰላም ታርፍ ዘንድ ማንኛውም ነገር ያለው መሆኑን እንዲያውቁ የሱስ ለእያንዳንዱ አማኝ መታመንን ሊሰጣቸው ይመኛል፡፡ ከዚያም እንዲህ አላቸው:- “በአባቴ ቤት ብዙ እልፍኝ (መኖሪያ) አለ ፤ እንዲያስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር ፤ ሥፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና” (ዮሐ 14:2)፡፡
እልፍኝ (mansions) የተባሉት ማረፊያ ቤቶች ናቸው ፤ ቤት ደግሞ እንደ አጠቃላይ ሲታይ ዋስትና፣ ሰላምና ደስታ የምናገኝበት ቦታ ነው፡፡ ያ ተስፋ ለእያንዳንዳችን እጅግ ታላቅ መነሳሳት ነው ፤ እኛ የምንደርስበት ቤት “ተኩላና ጠቦት በአንድ ላይ ይሰማራሉ (ይግጣሉ) ፤ አንበሳም እንደ በሬ ገለባ ይበላል” (ኢሳይያስ 65:25) የተባለበት ነው፡፡ ያ ቤት፣ ዛሬ በምድር ላይ በሐዘንና በሰላም ማጣት እንድንሰቃይ ከሚያደርገን የትኛውም ችግር ሰማይ ከምድር የሚርቀውን ያህል የራቀ ነው ፤ ምክንያቱም “እግዚአብሔር እንባን ሁሉ ከአይኖቻቸው ያብሳል ፤ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም ፤ ሐዘንም ቢሆን ወይም ጩኸት ወይም ስቃይ ከእግዲህ ወዲህ አይሆንም” (ራዕይ 21:4)፡፡ ዳሩ ግን ቀጣዩ ተስፋ ልክ እንደመጀመሪያው ታላቅ ነው፡- “ሂጄም ሥፍራ ባዘጋጅላችሁ እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ፤ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ” (ዮሐንስ 14:3)፡፡
“እንደገና እምጣለሁ” የሚለው ቃል ደቀመዛሙርቱ በዚያን ጊዜ አብልጠው የሚሹት ፈዋሽ መድኃኒት ነው፡፡ ወደፊት ምን ዓይነት ፈተና እንደሚጠብቃቸው በዚያን ጊዜ የሚያውቁት ነገር አልነበረም ፤ ሆኖም ግን ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ስለ እርሱ መመለስ ለመስበክ (ለማወጅ) ይዘምቱ ዘንድ ይህ የተስፋ ቃል የትኩረታቸውና የወኔያቸው ማዕከል ሆነላቸው ፤ እንዲሁም የሱስ ክርስቶስን ለእያንዳንዱ ህዝብ፣ ወገን፣ ልሳናትና ህዝቦች ለማስተዋወቅ ታገሉ፡፡
እርገቱና ዳግም መመለሱ ከትንሳኤው አርባ ቀናት በኋላ፣ የሱስ ችላ ወደተባለበትና እንዲሞት ወደተፈረደበት ከየሩሳሌም ከተማ ፊት ለፊት፣ ወደ ቢታንያ ቀርብ ብሎ ወደሚገኘው ወደ ወይራ ዛፎች ተራራ (የደብረዘይት ተራራ) ደቀመዛሙርቱን እየመራ ወሰዳቸው፡፡ ያ ጊዜም ጠፍቶ የተገኘውን በግ (በጎች) ወክለው ለቆሙት ለእነዚህ ወንዶችና ሴቶች ስብስብ የመሰነባበቻ እና የመጨረሻውን መመሪያ የማስተላለፊያ መልካም አጋጣሚ ነበር፡፡ የየሱስ ቃላት ለእነርሱ ያለውን ጥልቅ አሳቢነትና ርህራሔ እንጂ ላሳዩት ስህተትና ውደድቀት የተሰጠ ተግሳጽ አልነበረም፡፡
“ ሊባርካቸውና እንደሚጠነቀቅላቸው በሚገልጽ ሁኔታ እጆቹን እንደዘረጋ ከማንኛውም ምድራዊ ስበት በበለጠ ኃይል ወደ ሰማይ በመሳብ በቀስታ ከመካከላቸው ተነስቶ ወደላይ አረገ፡፡ እርሱ ወደላይ እየወጣ ሳል የክብር ዳመና ከዓይናቸው ሰወረው፡፡ መላእክት የዳመና ሰረገላ መስለው በተቀበሉት ጊዜ ደቀመዛሙርቱ ‘እነሆ እኔ እስከ ዓለም መጨረሻ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ’ ሲል ጌታ የሰጣቸውን ተስፋ አስታወሱ፡፡ በዚሁ ጊዜ በጣም ጣፋጭ እና አስደሳች የሆነ የመላዕክትን መዘምራን መዝሙር ሰሙ፡፡”
በዚያኑ ጊዜ ሁለት ኃያላን መላዕክት በሰዎች ቅርጽ ተገልፀው፣ ወደ ሰማይ አንጋጥጠው ይመለከቱ ለነበሩት ደቀመዛሙርት ባላቸው ርህራሔና ፍቅር ተነሳስተው ወደ እነርሱ ቀርበው እንዲህ ሲሉ ጠየቋቸው፡- “ደግሞም እናንት የገሊላ ሰዎች ሆይ፥ ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ ስለ ምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው የሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት፥ እንዲሁ ይመጣል አሉአቸው።” (የሐዋ ሥራ 1:11)፡፡ ይህም የሱስ ከብዙ ጊዜ በፊት ለደቀመዛሙርቱ እንዲህ ሲል ከሰጣቸው መልእክት ጋር አንድ ነበር፡፡ “የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላእክቱ ሁሉ፥ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል” (ማቴ 25:31)፡፡ ይህም “እነሆ፥ ከደመና ጋር ይመጣል፤ ዓይንም ሁሉ የወጉትም ያዩታል፥ የምድርም ወገኖች ሁሉ ስለ እርሱ ዋይ ዋይ ይላሉ። አዎን፥ አሜን።” (ራዕይ 1:7) ሲል በፍጥሞ ደሴት ለዮሐንስ ከተገለጠለት ራዕይ ጋር አንድ ነበር፡፡ ወደሰማይ ሲያርግ ያዩት ይኸው የሱስ ልክ ወደሰማይ ባረገበት ሁኔታ ተመልሶ እንደሚመጣ መላዕክት አረጋገጡላቸው፡፡ በእርግጥም፣ እርሱ በዳመናት ይመጣል ፤ አይንም ሁሉ ያየዋል፡፡

ይቀጥላል . . .

15/02/2026

ና አንተ የበረከት ምንጭ 🤲🤲

Happy Sabbath!!
13/02/2026

Happy Sabbath!!

እግዚአብሔርን ለማወቅበነቢዩ ኤርምያስ በኩል፣ እግዚአብሔር እዚህና አሁን ለማወቅ የሚያስፈልጉንን ቅድመ ሁኔታዎችን ይሰጠናል፡- “በፍጹም ልባችሁም በፈለጋችሁት ጊዜ ታገኙኛላችሁ፥” (ኤር.29፡...
13/02/2026

እግዚአብሔርን ለማወቅ

በነቢዩ ኤርምያስ በኩል፣ እግዚአብሔር እዚህና አሁን ለማወቅ የሚያስፈልጉንን ቅድመ ሁኔታዎችን ይሰጠናል፡- “በፍጹም ልባችሁም በፈለጋችሁት ጊዜ ታገኙኛላችሁ፥” (ኤር.29፡13)።
እግዚአብሔርን ፍለጋ በንድፈ ሀሳብ ብቻ የተገደበ መሆን የለበትም። በየቀኑ እርሱን በንቃት መፈለግ አለብን። እግዚአብሔር በምሕረቱ ወደ እርሱ የምንቀርብበትን እና እርሱን በቅርበት የምናውቅበትን መንገድ አዘጋጅቶልናል።

1. መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብ

ከዚህ በፊት ሰምተህ የማታውቀው ሰው በንግግር ውስጥ ከተጠቀሰ እና የማወቅ ጉጉትህ ከተነሳሳ ስለ ሰውዬው የበለጠ ለማወቅ የተወሰነ ጊዜ ወስደህ ምርምር ማድረግ ትችላለህ። በሰማኸው አጭር ጥቅስ ብቻ ስላልረካህ ምናልባት ሌሎች ስለእርሱ የተናገሩትን ወይም ስለራሳቸው የተናገሩትን ለማንበብ ጎግል ታደርጋቸው (በበይነ መረብ ትፈልግ) ይሆናል። በዙሪያህ ያሉትን፣ የሰሙትን ወይም ምን እንደሚያስቡ ትጠይቃለህ።
ስለ እርሱ የበለጠ ለማወቅ ለሚፈልጉ እግዚአብሔር የመረጃ ቡፌ አዘጋጅቷል። በላይ ላዩ እውቀት ብቻ መርካት የለብንም። ክርስቶስ “ቅዱሳት መጻሕፍትን እንድንመረምር” ነግሮናል (ዮሐንስ 5፡39)። እርሱን በግል እንድናውቀው ይፈልጋል፤ ስለዚህም መጽሐፍ ቅዱስን ለራሱ መግለጫ እንዲሆን አቅርቧል።
ስለ ታላቁ የድነት እቅድ እውቀት ይሰጠናል እንዲሁም እያንዳንዱ ግለሰብ እንዴት የዘላለም ሕይወትን ሊያገኝ እንደሚችል ያሳየናል። የመጽሐፉ ጸሐፊ ማን ነው?—የሱስ ክርስቶስ ነዉ። እርሱ እውነተኛ ምሥክር ነው፣ ለራሱም እንዲህ ይላል፡- ‘እኔ የዘላለም ሕይወትን እሰጣቸዋለሁ። ለዘላለምም አይጠፉም፥ ከእጄም ማንም አይነጥቃቸውም።” መጽሐፍ ቅዱስ ወደ ክርስቶስ የሚወስደውን መንገድ ያሳየናል በክርስቶስም የዘላለም ሕይወት ተገልጧል።
መጽሐፍ ቅዱስን ስንከፍት አመለካከታችንና ዓላማችን ከገጾቹ ምን እንደምንሰበስብ ይወስናል። የእግዚአብሄር ቃል በተከፈተ ልብ ካጠናነው እሱን በቅርበት እንድናውቀው ይመራናል። መንፈስ ቅዱስ በቅዱሳት መጻሕፍት ንጹሕ እውነቶች እንዲማረክን ከፈቀድን እግዚአብሔርን በቅርበት ልናውቀው እንችላለን።
“አይሁዶች ስለ ክርስቶስ የሚመሰክሩ ቅዱሳት መጻሕፍት ነበራቸው፣ ነገር ግን ክርስቶስን በቅዱሳት መጻሕፍት ሊያውቁት አልቻሉም። የብሉይ ኪዳን እውነቶች ከሰው አስተያየቶች ጋር ስለተቀላቀሉ ትምህርቶቹ ሚስጥራዊ ስለሆኑባቸዉ፣ የእግዚአብሔር ፈቃድ ከሰው ፊት ተሸፈኑ። የክርስቶስ በተራራ ላይ የተናገረው ስብከት ራሳቸውን ጻድቃን ከሆኑት ጸሐፍትና ፈሪሳውያን አስተምህሮ ጋር የሚጋጭ ነበር። እግዚአብሔርን በጣም በስህተት ተርጉመዉ ነበር፤ ስለዚህም እርሱ እንደ ርኅራኄ፣ ምሕረት ወይም ፍቅር እንደሌለው እንደጽኑ ፈራጅ ይታይ ነበር። ለሥልጣናቸው ሲሉ ‘ጌታ እንዲህ ይላል’ የሚል ትዕዛዝ ያልነበራቸውን ማለቂያ የሌላቸውን ንግግሮችና ወጎች ለሕዝቡ አቀረቡ። ምንም እንኳን እውነተኛውንና ሕያው እግዚአብሔርን እንደሚያውቁ እና እንደሚያመልኩ ቢናገሩም፣ በልጁ እንደተገለጠው እሱንና ባህሪውን ሙሉ በሙሉ አዛብተውታል። ሰዎች በእግዚአብሔር ፍቅር ላይ ያላቸው እምነት ተመልሶ እንዲመጣ ክርስቶስ እነዚያን የተሳሳቱ መገለጫዎች ለማጥፋት ያለማቋረጥ ደክሟል። የሰው ልጅ ከሁሉ በላይ የሆነውን መሪ ‘አባታችን’ በሚለው አዲስ ስም እንዲጠሩ አስተምሯል። ይህ ስም ከእርሱ ጋር ያለንን እውነተኛ ግንኙነት ይወክላል፣ እንዲሁ በሰው ከንፈሮች በቅንነት ሲነገሩ፣ ለእግዚአብሔር ጆሮ እንደ ሙዚቃ ያለ ነው። ክርስቶስ በአዲስና በሕያው መንገድ ወደ እግዚአብሔር ዙፋን መራን።
መጽሐፍ ቅዱስህን በክፍት ልብ ለማንበብና ለማጥናት፣ ለመማርና ለመለወጥ ፈቃደኛ ነህን? ያን ጊዜ እግዚአብሔርን ታውቀዋለህ እንዲሁም ኃይሉን ከመቼውም ጊዜ በላይ በህይወትህ ታየዋለህ። በራስህና በአካባቢህ ያሉ ለውጦችን ታያለህ።

2. ጸሎት

በጎግል ላይ ስትፈልገዉ የነበረው ሰው በመጠኑም ቢሆን ታዋቂ ከሆነ፣ በኢሜል ወይም በስልክ ልታገኛቸው አትችልም። ምናልባት ለቢሮአቸው ቁጥር ሊኖር ይችላል፣ ግን በግል ልታገኛቸው አትችልም።
እኛ ግን አንገታችንን ደፍተን እጆቻችንን በማጠፍ ወደ እግዚአብሔር መድረስ እንችላለን። ጸሎት ወደ እግዚአብሔር የሚያደርስ ቀጥተኛ መንገድ ነው። ከእርሱ ጋር ያለንን ግንኙነት ያጠናክራል፣ እንዲሁም ስለ ሰማያዊ አባታችን የበለጠ ግንዛቤ እናገኛለን። ጸሎት የእግዚአብሔርን በሕይወታችን ውስጥ መኖሩን እንድናውቅ ይረዳናል እንዲሁም ከእርሱ ጋር ያለንን ግንኙነት ያጠናክራል።
በጸሎት፣ ምስጋናን መግለጽ፣ የእግዚአብሔርን መመሪያ መፈለግ፣ ኃጢአቶችን መናዘዝና ይቅርታ መጠየቅ እንችላለን። ጸሎት የመንፈስ ቅዱስን ድምጽ እንድንሰማ የሚያስችለን፣ የራሳችንን ፍላጎትና የእግዚአብሔርን ሊባርከንና የማሸነፍ ሀይልን ሊሰጠን ያለውን ፍላጎት እንድንረዳ በጸጥታ ለማሰላሰል እድል ይሰጣል።
“እግዚአብሔር ትእዛዙን ለመፈጸም በተጠንቀቅ ላይ በሚገኙ ቁጥራቸው እልፍ አእላፍ በሆነ ቅዱሳን ፍጡሮች ተከብቦ ከፍ ባለና በተቀደሰ ቦታ ያለ እንጂ ያለምንም ሥራ በጸጥታና በገለልተኝነት የሚኖር አለመሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል። እርሱ እኛ ልናስተውለው በማንችለው መንገድ ከእያንዳንዱ የግዛቱ ክፍል ጋር የማያቋርጥ ግንኙነት አለው። ሆኖም የእርሱና የመላው ሰማያዊ ሠራዊት ዓይን ያረፈው በዚች ኢምንት ዓለም ላይ በሚኖሩ እነርሱን ለማዳን ሲል አንድ ልጁን በሰጠላቸው ነፍሳት ላይ ነው። እግዚአብሔር የጭቁኖችን ጩኸት ለመስማት ከዙፋኑ ላይ እንዳለ ጐንበስ ይላል። ለእያንዳንዱ እውነተኛ ጸሎት መልሱ አለሁልህ የሚል ነው። ያዘኑትንና የተናቁትን ያነሳል” በሚደርስብን ስቃይ ሁሉ አብሮ ይሰቃያል። የእርሱ መልአክ ከሚደርስብን ፈተናና ችግር ሁሉ ሊያድነን በአጠገባችን ይገኛል።”
የአንዲት ድንቢጥ ወፍ በመሬት ላይ መውደቅ ከጌታ የተሰወረ አይደለም። ሰይጣን እግዚአብሔርን በመጥላቱ ምክንያት አጻኛችን የሚጠነቀቅላቸውንም ሁሉ እንዲጠላ ሆኖአል። የእግዚአብሔርን ፍጥረት ለመበከል ይመኛል፣ መናገር የማይችሉ እንስሳትን ማጥፋትም ያስደስተዋል። ወፎች በሕይወት ተርፈው በመዝሙራቸው ሊያስደስቱን የበቁት በእግዚአብሔር ጥበቃ ምክንያት ነው። እግዚአብሔር ትንሽዋን ድንቢጥ ወፍ እንኳ አይረሳትም። «እንግዲህ እናንተ አትፍሩ ምክንያቱም ከብዙ ድንቢጦች ትበልጣላችሁ።”
“የየዕለት ጸሎት ለጸጋ እድገት፣ እና ለመንፈሳዊ ህይወትም ሆነ፣ ጊዜያዊ ምግብ ለሥጋዊ ደህንነት አስፈላጊ ነው። በጸሎት ብዙ ጊዜ ሃሳቦችን ወደ እግዚአብሔር ማንሳት እራሳችንን ማለማመድ አለብን። አእምሮ በማይሆን ቦታ የሚንከራተት ከሆነ መልሰን ወደ አምላክ ማምጣት አለብን፤ በጽኑ ጥረት፣ መለማመድ በመጨረሻ ቀላል እንድሆንልን ያደርገዋል፡፡ እራሳችንን ለአንድ አፍታ ከክርስቶስ በመለየት ደህና መሆን አንችልም። በእያንዳንዱ እርምጃ እኛን ለመከታተል የሱ መገኘት ሊኖረን ይችላል ነገር ግን እሱ ራሱ ያስቀመጠውን ሁኔታ በመመልከት ብቻ ነው።
“ለምኑ ይሰጣችሁማል። ፈልጉ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል” (ማቴዎስ 7፡7)
“ወሰን በሌለው ፍቅር የተሞላው የእግዚአብሔር ልብ፣ ከጠየቁት ወይም ከሚያስቡት ሁሉ በላይ ሊባርካቸው እጅግ ጓጉቶ ሳለ፣ በትንሹ ብቻ ስለሚጸልዩትና እምነታቸውም ደካማ ስለሆነው ለፈተና ስለተጋለጡት፣ ምስኪንና ረዳተቢስ የሰው ልጆች መላእክት ምን ያስቡ ይሆን? መላእክት በእግዚአብሔር ፊት መስገድ ይወዳሉ ወደ እርሱም መጠጋት ደስታቸው ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት ማድረግን እንደ ትልቅ ባርኮት ነው የሚቆጥሩት፤ እግዚአብሔር ብቻ የሚሰጠው እርዳታ በጣም የሚያስፈልጋቸው ምድራዊ ልጆች ግን ያለ የእግዚአብሔር መንፈስ ብርሃንና፣ ያለ ጌታ አጀብ መንገዳቸውን በማድረግ የረኩ ይመስላሉ፡።
“የልባችን በር ዘወትር የተከፈተና የሱስም እንደ ሰማያዊ እንግዳ ሆኖ በነፍሳችን እንዲኖር ያለማቋረጥ ልናድመው ይገባል።
“ምንም እንኳን ኃጢአት በበከለው ከባቢ አየር ውስጥ የምንኖር ብንሆንም ቆሻሻውን መተንፈስ ግን አያስፈልገንም፡፡ በሰማያዊው ከባቢ አየር ውስጥ መኖር እንችላለን፡፡ ልባዊ በሆነ ጸሎት ወደ እግዚአብሔር ሀልዎት (መገኘት) ራሳችንን ከፍ በማድረግ ወደ ምናባችን የሚመጡትን ርኩስ ነገሮችና በኃጢአት የተበከሉ አስተሳሰቦችን እንዳይገቡ በር መዝጋት እንችላለን፡፡ የእግዚአብሔርን እገዛና በረከት ለመቀበል የሚፈቅዱሁሉ፣ በቅድስና ከባቢ አየር ውስጥ ይመላለሳሉ፤ ከሰማይም ጋር ቋሚ ግንኙነት ይኖራቸዋል።
“ከየሱስ ጋር መነጋገር እንችላለን። ሄኖክ ከእግዚአብሔር ጋር እንደተነጋገረው እኛም ከየሱስ ጋር መነጋገር እንችላለን። ስለ ፈተናዎቹ ሁሉ ለአምላኩ መንገር ችሏል። ሄኖክ አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ያደረገው በዚህ መንገድ ነበር፣ ብርሃኑም በመንገዱ ላይ ሲበራ፣ ‘ለምን፣ ጓደኞቼና ዘመዶቼ ይህን መንገድ ብከተል ምን ይሉኛል?’ ሊል አልጠበቀም። ነገር ግን፣ ውጤቱ ምንም ይሁን ምን ትክክል የሆነውን አደረገ።
“አሁን ሄኖክ ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት ለመፍጠር ፈለገ፣ እና ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት የሌላቸው ከመልካም ነገር ሁሉ ለመለየት ከሚመራቸው ከሌላ ሰው ጋር ግንኙነት ይኖራቸዋል። ሁላችንም የምንቀረፅበት ባህሪ አለን። ሄኖክ ጻድቅ ባህሪን አዳበረ ውጤቱም ሞትን ሳያይ ወደ ሰማይ መወሰድ ነበር። ጌታ ለሁለተኛ ጊዜ በሚመጣበት ጊዜ ሞትን ሳያዩ የሚለወጡ ይኖራሉ፣ እኛም በዚያ ቁጥር መካከል እንደምንሆን ማወቅ እንፈልጋለን። እኛ ሙሉ በሙሉ የመለኮታዊ ተፈጥሮ ተካፋዮችና ከጌታ ጎን መሆናችንን ማወቅ እንፈልጋለን— ይህ የሚሆነዉ ግን በአለም ካለው ብልሽት ፍትወት ለማምለጥ፣—ፈተና ወይም ችግር የሌለብን ለእግራችን ጥርት ያለ መንገድን ለመስራት በመሞከር አይደለም። ነገር ግን ራሳችንን ከእግዚአብሔር ጋር ለመገናኘት ትክክለኛ በሆነ የግንኙነት መስመር ላይ በማድረግና ውጤቱን እንዲቀበል በመፍቀድ ነው።8
ከዚህ በኋላ የበለጠ ትጸልያለህን?

ይቀጥላል . . .

12/02/2026

ክፍል 2

እግዚአብሔር በቃሉ ይናገረናል፡ የሱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው (ዮሐ. 1፡1)። ዛሬም እግዚአብሔር በግልና በኃይል የሚናገረን አንዱ መንገድ ይህ ነው። በቃሉ በኩል ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት እንዲኖረን ብቻ ሳይሆን አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ሁሉ ለሌሎች መልስ ለመስጠት በየዋህነትና በፍርሃት (1ኛ ጴጥ. 3፡15) ዝግጁ መሆን አለብን። ዲያብሎስ የሱስን በምድረ በዳ ሲፈትነው፣ ጌታ ከእግዚአብሔር ቃል እውነትን በመጥቀስ ለዲያብሎስ ፈተናዎች ምላሽ ሰጠ። (ማቴዎስ 4: 1–11) የነፍሳችንን ጠላት የምናሸንፍበት የመንፈስ ሰይፍ የሆነውን በእግዚአብሔር ቃል የሚገኘውን እውነት መማር አለብን። የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ስንለብስ የዲያብሎስን ሽንገላ መቃወም እንችላለን (ኤፌሶን 6፡11)። የእግዚአብሔርን ቃል ማክበርና መታዘዝ የእግዚአብሔርን ድምጽ ለመስማት ቁልፍ ነው። ( ዮሐንስ 14:21, 23 ተመልከት።)
እግዚአብሔር በዝምታ ዉስጥ ይናገራል፡ ነቢዩ ኤልያስ ተስፋ በቆረጠ ጊዜ እና በጭንቀት በተሞላ ጊዜ እግዚአብሔር ባልጠበቀው መንገድ ተናገረው። አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር በነፋስ፣ በመሬት መንቀጥቀጥ ወይም በእሳት ይናገራል ነገር ግን ብዙ ጊዜ የሚናገረው በዝምታ (በለሆሳስ) ነው፣ ስለዚህ በትኩረት መከታተል አለብን። (1 ነገሥት 19:11–13 ተመልከት።)
እግዚአብሔር በልጁ በየሱስ ተናግሯል፡ እግዚአብሔር ራሱን ሙሉ በሙሉ በልጁ ማንነት፣ ባሕርይ፣ ቃልና ሥራ ገልጧል። የሱስ እግዚአብሔርን ለሰው የገለጠው በሙሉ ማንነቱ ነው። ህዝቡን በምሳሌ፣ በተረት፣ በተጨባጭ ትምህርት እና በተለይም በራሱ ምሳሌ እንዴት አምላካዊ ህይወት መኖር እንዳለበት አስተምሯል። (ዕብራውያን 1:1፣ 2፤ ማርቆስ 4:34፤ ማቴዎስ 7:3–5፤ ዮሐንስ 13:3–7)
እግዚአብሔር የሚናገረው በመንፈስ ቅዱስ ነው፡- የሱስ በዚህ ምድር ላይ በነበረ ጊዜ እግዚአብሔር በእርሱ በኩል ለሰው ልጆች ተናገረ፣ የሱስም ወደ አብ በተመለሰ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ከእግዚአብሔር ዘንድ አጽናኝ ይሆንን ዘንድ ወደ እውነት ሁሉ እንዲመራን ተላከ (ዮሐ. 26) የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የሱስን እንደ ግል አዳኝ በሚያምኑና በሚቀበሉት ሁሉ ላይ ፈሰሰና ወደ እውነት ሁሉ ይመራናል። ስለዚህ ራሳችንን ለአብ፣ ለወልድና ለመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ እናስገዛ።
እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ይመረምራል፡ ዳዊትም ለልጁ እንዲህ ሲል ተማጸነ፡- “አንተም ልጄ ሰሎሞን ሆይ የአባትህን አምላክ እወቅ በፍጹምም ልብና በፈቃድህም አምልክ። እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ይመረምራል ሐሳብንም ሁሉ ያውቃልና ብትፈልገዉ፣ ታገኘዋለህ። ብትተወው ግን ለዘላለም ይጥልሃል” (1ኛ ዜና 28፡9)። ይህ ለንጉሥ ሰሎሞን የተሰጠው ምክር እግዚአብሔር የእኛን ምናብ እንደሚያውቅ ለእያንዳንዱ ሰው በግልጽ ይገልጣል። በሁሉም ተግባሮቻችንና ሀሳቦቻችን በጣም እንጠንቀቅ።
እግዚአብሔር አምላክ ልብን ይመለከታል፡ እግዚአብሔር ነቢዩ ሳሙኤል ዳዊትን ንጉሥ አድርጎ እንዲቀባው ነገረው ውጫዊው ገጽታ በጣም አስፈላጊው ነገር እንዳልሆነ ገልጿል። እርሱ የሚያየው ልብ ብቻ ነው (1ኛ ሳሙኤል 16፡7)።
የእግዚአብሔር ዓይኖች ሁሉን ያያሉ፡ ቅዱሳት መጻሕፍት የእግዚአብሔር ዓይኖች ሁሉን እንደሚያዩ በምሳሌያዊ ሁኔታ ይናገራል። “እግዚአብሔር ልቡ በእርሱ ዘንድ ፍጹም የሆነውን ያጸና ዘንድ ዓይኖቹ በምድር ሁሉ ይመለከታሉና።” (2ኛ ዜና 16፡9)። “ዓይኔ በመንገዳቸው ሁሉ ላይ ነው፤ ከፊቴም አልተሰወሩም፥ ኃጢአታቸውም ከዓይኔ አልተሸሸገም።”(ኤር.16፡17)። “ጆሮን የተከለ አይሰማምን? ዓይንን የሠራ አያይምን? (መዝሙረ ዳዊት 94:9)
እግዚአብሔር ክፉ ሰዎች የሚያስቡትን ያውቃል፡ “ስለዚህ ሥራቸውን ያውቃል ፥ እስኪጠፉም ድረስ በሌሊት ይገለብጣቸዋል” (ኢዮብ 34:25) ንጉሥ ናቡከደነፆር በኃይሉ ታላቂቱን የባቢሎን ከተማ በመገንባቱ ይኮራ ነበር። ቃሉ ገና በአፍ ላይ ሆኖ ሳለ ሰባት ዓመት እንደማይነግሥና ከአውሬ ጋር እንደሚኖርና እንደ በሬ ሣር እንደሚበላ ከሰማይ ድምፅ ተናገረ። (ዳንኤል 4:17–37) በኋላም ኃጢአቱን ተገንዝቦ ወደ አምላክ ተመለሰ።
እግዚአብሔር በምድር ላይ ያለውን ነገር ያውቃል፡ እግዚአብሔር አምላክ ሙሴን ከሚነደው ቁጥቋጦ ውስጥ ሆኖ ተናገረው እግዚአብሔርም ሕዝቡን ከግብፅ እንዲያወጣና ከባርነት እንዲያድን ጠየቀው። “እግዚአብሔርም አለ በግብፅ ያሉትን የሕዝቤን መከራ በእውነት አይቻለሁ ከአስገባሪዎቻቸውም የተነሣ ጩኸታቸውን ሰማሁ። ሀዘናቸውን አውቃለሁና” (ዘጸአት 3፡7)። እግዚአብሔር በምድር ላይ የሚሆነውን እያንዳንዱን ነገር ይመለከታል ። አንታክት፣ እናም በጌታ እንታመን።
እግዚአብሔር ያለፈውን ያውቃል፡ ሐዋርያው እንዲህ ሲል አረጋግጧል፡ “ሥራው ሁሉ ከዓለም መጀመሪያ ጀምሮ በእግዚአብሔር ዘንድ የታወቀ ነው” (የሐዋርያት ሥራ 15፡18)።
እግዚአብሔር በፍርድ ፍፁም ነው፡ በሰው ልጆች ላይ ለመፍረድ በእውቀት ፍጹም የሆነ እግዚአብሔር ብቻ ነው (2ኛ ጴጥሮስ 3፡7)። ሰዎች አንድ ቀን ሁሉን በሚያውቅ አምላክ ፊት መቆም እንዳለባቸው ሲገነዘቡ፣ ይህ አኗኗራቸውን እንዲገመግሙ ያደርጋቸዋል። የሱስ “ ከቃልህ የተነሣ ትጸድቃለህ ከቃልህም የተነሣ ትኰነናለህ” (ማቴዎስ 12፡37) ብሏል።
እግዚአብሔር ቃሉን ይጠብቃል፡- እግዚአብሔር ይህንን ቃል ኪዳን ለሕዝቡ ሰጥቷል። በፍጹም ልባችሁም በፈለጋችሁት ጊዜ ታገኙኛላችሁም” (ኤር.29፡13)። በፍጹም ልባችን ከፈለግነው ድምፁን እንሰማለን። እግዚአብሔር በእያንዳንዱ ሰው ልብ ውስጥ ያለውን በትክክል ያውቃል። እግዚአብሔር የሚያውቅን ከሆነ በሕይወታችን ውስጥ ምን እያጋጠመን እንዳለ ያውቃል። ብቻችንን አይደለንም አልተረሳንም። በሕይወታችን ውስጥ የሚያጋጥሙንን ፈተናዎች እግዚአብሔር ያውቃል። ፈተናዎቻችንን እና የቤተሰባችንን ሁኔታ ያውቃል፣ እናም እንደማይጥለንና እንደማይተወን ቃል ገብቷል። ዘዳግም 31:6፤ ዮሐንስ 3፡16
እግዚአብሔር ምንጊዜም ከልጆቹ ጋር ችግረኛ ነው።
ንጉሥ ዳርዮስ የባቢሎን ገዥ ነበርና ዳንኤልን የመጀመሪያ ፕሬዚዳንት አድርጎ ሾመው። ዳንኤል በእግዚአብሔር ታመነ፣ የጌታንም ትእዛዝ ተከተለ። ቀናተኛ ተቃዋሚዎች ንጉሱን አሳምነውት ሁሉም ሰው እሱን ብቻ እንዲያመልከው የሚያደርግ ህግ እንዲያወጣና ሌላ አምላክን የሚያመልክ ማንም ቢሆን በአንበሶች ጉድጓድ ውስጥ ይጣል አሉ። ዳንኤል በቀን ሦስት ጊዜ መስኮቶቹ ተከፍተው ወደ እግዚአብሔር ይጸልይ ስለነበር በእርግጥም ወደ አንበሶች ጉድጓድ ተጣለ። እግዚአብሔር አምላክ ግን ከእርሱ ጋር ነበረ የአንበሶችን አፍ ዘጋ ዳንኤልንም ጠበቀው (ዳንኤል 6፡21, 22)።
ንጉሱ ናቡከደነፆር በባቢሎን ግዛት የወርቅ ምስል ሠራ እና ምስሉን ለመመረቅ ባለ ሥልጣናትን ሁሉ ጠራ። ለምስሉ የማይሰግድ ሁሉ በሚነድድ እቶን ውስጥ ይጣላል። ለምስሉ የማይሰግዱና የማያመልኩ ሦስት ወጣት ዕብራውያን ወደ ሚነድደው ወደ እቶን ተጣሉ። ጌታ አምላክ ከእነርሱ ጋር በእሳት እቶን ውስጥ ነበረ እና አልተቃጠሉም፤ እሳቱም በእነርሱ ላይ ሥልጣን አልነበረውም (ዳንኤል ምዕራፍ 3)።
እስራኤላውያንን ከግብፅ ባርነት በመምራት ረገድ እግዚአብሔር ከሙሴ ጋር ነበር። በተአምር ለሕዝቡ ከዓለት ውኃ ከሰማይም መና ሰጣቸው። እግዚአብሔር አምላክ ባሕሩን ከፍሎ ሕዝቡ በደረቅ ምድር ተሻገሩ (ዘጸ 14፡16)። ይህ እግዚአብሔር ጠላትን በዚያው ባሕር ውስጥ አሰጥሞ ለሕዝቡ መዳንን አመጣ። ዛሬም በእኛ ፈንታ የሚሰራ አምላክ ያው ነው። እርሱ ትናንትና፣ ዛሬ እና ለዘላለም ያው ነው። (ዘጸአት ምዕራፍ 14ን አንብብ።)
ሙሴ ከሞተ በኋላ እግዚአብሔር ሕዝቡን በዮርዳኖስ ወንዝ በኩል በደረቅ መሬት አሻግሯል። የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት የተሸከሙ ካህናት በዮርዳኖስ መካከል በደረቅ መሬት ላይ ቆሙ። (ኢያሱ ምዕራፍ 3ን አንብብ።)
እግዚአብሔር ከኖህና ከቤተሰቡ ጋር ነበረ እና ከጥፋት ውሃ አዳናቸው ሁሉም እግዚአብሔርን ታዘዋልና። “እግዚአብሔርም ኖኅን አለው፡- አንተና ቤትህ ሁሉ ወደ መርከብ ግቡ። በዚህ ትውልድ በፊቴ ጻድቅ ሆነህ አይቻለሁና” (ዘፍጥረት 7፡1)። የጥፋት ውሃም በምድር ላይ አርባ ቀን ሆነ ሥጋ ለባሹም ሁሉ ሞተ ሕያዋን ፍጡርም ሁሉ ጠፋ፣ እግዚአብሔር ግን ኖኅንና ቤተሰቡን አዳነ። ጌታ ከእነርሱ ጋር ነበር።
አብርሃም ከከለዳውያን ምድር ዑር እንዲወጣ በእግዚአብሔር ተጠራ። የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ያለምንም ጥርጥር ታዘዘ እና አዲስ ሀገር ለዘሩ እንደሚሆን የገባውን ቃል ኪዳን አመነ። (ዘፍጥረት ምዕራፍ 12ን ተመልከት።) አምላክ ለአብርሃም የገባውን ቃል እንደ ጠበቀና እንደፈጸመ ሁሉ ለእኛም ቃል ገብቷል።
በዘፍጥረት 39፡1-6 ዮሴፍ በገዛ ወንድሞቹ ለባርነት ተሽጧል። ጌታ አምላክ ከዮሴፍ ጋር በባይተዋር አገር ነበር፣ በዚያም በጲጥፋራ ፊት ሞገስን አግኝቷል፣ እሱም በቤተሰቡ ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ አደረገው። በመጨረሻም እግዚአብሔር ዮሴፍን የግብፅ ሁለተኛ ገዥ እንዲሆን፣ በተለይም ለሚመጣው ረሃብ ዝግጅት ሀላፊ እንዲሆን ሁኔታዎችን መርቷል። (ዘፍጥረት 41:37–45ን አንብብ።) ዮሴፍ አምላኩ ከእሱ ጋር እንደሆነ ያውቅ ነበር።
ዮናስ በዓሣ ነባሪ ሆድ ውስጥ ሳለ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበር። ጌታ በዚያ አቆየው በመከራውም ጸሎቱን ሰማ። ከዚያም ዓሣው ዮናስን ተፋው፤ እሱም ወደ ነነዌ ሄዶ መላው ከተማ ንስሐ እንዲገባ ለማሳመን ተስማማ። ምንም እንኳን መጀመሪያ ላይ ባይታዘዝም፣ እሱ ደግሞ ከኃላፊነቱ በመራቁ ተጸጽቷል። እግዚአብሔር እንድንሠራ በሚጠይቀን በማንኛውም ሁኔታ እግዚአብሔርን መታዘዝ ያስፈልገናል፤ ቃሉን ከመታዘዝ ወደ ኋላ ማለት የለብንም።
የእግዚአብሔር ጥሪ ለእያንዳንዳችን፡ ጌታ እግዚአብሔር ከእኛ ምንም አይጠይቅም። ልባችንን ብቻ ይጠይቀናል፡- “ልጄ ሆይ፣ ልብህን ስጠኝ ዓይንህም መንገዴን ይመልከት” (ምሳ 23፡26)። እንዲሁም የእግዚአብሔርን ድምጽ ለመስማት ትእዛዛቱንና የቅዱሳት መጻሕፍትን ቃል እንድንከተል ይጠይቀናል። ከእሱ ጋር ጊዜ ማሳለፍ አለብን። ከእርሱ ጋር በሆንን መጠን ድምፁን በደንብ እናውቀዋለን። “ የእናንተ ግን ዓይኖቻችሁ ስለሚያዩ ጆሮቻችሁም ስለሚሰሙ ብፁዓን ናቸው።” (ማቴ 13፡16) በእምነት ስናድግ፣ የእግዚአብሔርን ድምፅ መስማት እንማራለን። የሱስ “በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ እኔም አውቃቸዋለሁ ይከተሉኝማል” (ዮሐንስ 10፡27) ብሏል። ከእርሱ ጋር ያለንን ግንኙነት የሚያደናቅፍ ማንኛውንም ነገር እንዲገልጥልን እግዚአብሔርን መለመንና ከዚያም እርሱን መታዘዝ አለብን። ለዚያም በቅዱሳት መጻሕፍት ላይ ማሰላሰል አለብን። በጸሎትና በአምልኮ ራሳችንን ለእግዚአብሔር ማቅረብ አለብን። አሁንም በፊቱ እንሁን። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡- “ዕረፉ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ እወቁ በአሕዛብ ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ።” (መዝ.46፡10)። ንፁህና እውነተኛ እንዲሁም ጸንተን እንኑር፣ ባህሪያችን ሰማዩ መጻሕፍት ላይ እየታተመ መሆኑን እናስታዉስ። አሜን።

በውኑ እግዚአብሔር ሁላችንም ያውቀናል?እግዚአብሔር ሁሉን ያውቃል ፡ ተመስጦ እግዚአብሔር ሁሉን አዋቂ ወይም “ሁሉን ቻይ” እንደሆነ ይነግረናል። “ልባችን የሚፈርድብን ከሆነ እግዚአብሔር ከልባ...
11/02/2026

በውኑ እግዚአብሔር ሁላችንም ያውቀናል?

እግዚአብሔር ሁሉን ያውቃል ፡ ተመስጦ እግዚአብሔር ሁሉን አዋቂ ወይም “ሁሉን ቻይ” እንደሆነ ይነግረናል። “ልባችን የሚፈርድብን ከሆነ እግዚአብሔር ከልባችን ይበልጣል ሁሉንም ያውቃል” (1ኛ ዮሐንስ 3፡20)። ይህ ማለት እርሱ ስለ ነገሩ ሁሉ ፍፁም ዕውቀት አለው ማለት ነው። እሱ ምንም መማር አይኖርበትም እንዲሁም ነገሮችን ማመዛዘን አይጠበቅበትም። የሚሆነውንና የሆነውን ሁሉ እግዚአብሔር ያውቃል። የእርሱ ሁሉን አዋቂነት ፍፁም እውቀት፣ ፍፁም ማስተዋል እና ፍፁም ጥበብ ያለው ማለት ነው። እግዚአብሔር የፍጥረት ሁሉ ማስተዋል ምንጭ ስለሆነ፣ እርሱ በባሕርዩ ሁሉ እውቀት ነው። የተፈጠርነው በእርሱ አምሳል ነው፣ ስለዚህ እርሱ ያውቀናል። እግዚአብሔር እያንዳንዳችንን ይመለከታል። “ እርሱም የምድርን ዳርቻ ይመለከታል፥ ከሰማይም በታች ያለውን ሁሉ ያያል።” (ኢዮ 28፡24)።
ከመታወቃችን በፊት አምላክ ያውቀናል፡- ንጉሥ ዳዊት “ያልተሠራ አካሌን ዓይኖችህ አዩኝ፤ የተፈጠሩ ቀኖቼ ሁሉ አንድ ስንኳ ሳይኖር በመጽሐፍህ ተጻፉ።” ( መዝሙር 139:16፣ NJV)
እግዚአብሔር ኤርምያስን እንዲህ አለው፡- “በሆድ ሳልሠራህ አውቄሃለሁ። ከማኅፀንም ሳትወጣ ቀድሼሃለሁ፥ ለአሕዛብም ነቢይ አድርጌ ሾምሁህ” (ኤር.1፡5)።
በ1ኛ ዜና 22፡9 ላይ ደግሞ የንጉሥ ሰሎሞን የሕይወት ሁኔታ በእግዚአብሔር አስቀድሞ የታወቀ እንደነበር እናነባለን።
እግዚአብሔር ኢዮስያስን ከመወለዱ 32 ዓመታት በፊት ስሙን ሰጠውና እግዚአብሔርን ከሚታዘዙት እና በፊቱ ቅን የሆነውን ነገር ከሚያደርጉ ጥቂት ነገሥታት አንዱ እንደሚሆን ስለ ሕይወቱ ትንቢት ተናግሯል (1ኛ ነገ. 13፡2)።
አብርሃም አሕዛብ ከእርሱ እንደሚወጡ በእግዚአብሔር ተስፋ ተሰጥቶት ነበር፤ ነገር ግን በዚያን ጊዜ ልጅ አልነበረውም። ሚስቱ ሦራ መካን ነበረች። የተስፋው ልጅ ይስሐቅ እስኪወለድ ድረስ 25 ዓመት ጠበቁ። ሣራ ባሪያዋን አጋርን ልጅ እንድትፀንስ ለአብርሃም በመስጠት የእግዚአብሔር ትንቢት ፍጻሜውን ለማግኘት ‘ለመረዳት’ አሰበች። ያ የእግዚአብሔር እቅድ ባይሆንም በምሕረቱ ግን በተፈጸመ ትንቢት አጋርን አጽናናት (ዘፍጥረት 16፡12)።
አብርሃም 99 ዓመት ሲሆነው አምላክ ለረጅም ጊዜ ሲጠብቀው ለነበረው ልጅ ቃል ገባለት። “እግዚአብሔርም አለ፡— ሚስትህ ሣራ በእውነት ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች። ስሙንም ይስሐቅ ትለዋለህ። ቃል ኪዳኔንም ከእርሱ ጋር ከእርሱም በኋላ ከዘሩ ጋር የዘላለም ቃል ኪዳን አቆማለሁ” (ዘፍጥረት 17፡19)።
የመጥምቁ ዮሐንስ ልደትም እንዲሁ በትንቢት ተነግሯል (ሉቃስ 1፡13)።
በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ አግኝተሻልና አትፍሪ። እነሆም፥ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ ስሙንም የሱስ ትዪዋለሽ። እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑልም ልጅ ይባላል፡ ጌታም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል” (ሉቃስ 1፡30-32)። ሁሉንም ከመወለዳቸው በፊት የሚያውቀው ጌታ እያንዳንዳችንንም ያውቃል።
እግዚአብሔር ሀሳባችንን ያውቃል፡ እግዚአብሔር ያደረግነውን ሁሉ ያውቃል፣ እንዲሁም ያሰብነውን ሁሉ ያውቃል። እግዚአብሔር ስለ እኛ ሁሉንም ነገር በፍፁም ያውቃል። መዝሙረኛው “አንተ መቀመጤንና መነሣቴን ታውቃለህ፤ አሳቤን ከሩቅ ታውቃለህ” (መዝ. 139፡2) ብሏል። ሃሳቦቻችንን ከሌሎች መደበቅ አልፎ ተርፎም ሆን ብለን በመዋሸት ስለሃሳቦቻችን ልናታልላቸው እንችላለን። ከእግዚአብሔር ግን ምንም ነገር መደበቅ አንችልም። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡- “እኛን በሚቆጣጠር በእርሱ ዓይኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተራቆተና የተገለጠ ነው እንጂ፥ በእርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረት የለም።” (ዕብ. 4፡13)።
እግዚአብሔር የእውቀት አምላክ ነው፡ የሳሙኤል እናት የሆነችው የሃና ጸሎት፡- “ከእንግዲህ በትዕቢት አትናገሩ። ትዕቢት ከአፋችሁ አይውጣ፤ እግዚአብሔር አዋቂ ነውና፥ ሥራውም በእርሱ ይመዘን ዘንድ ነውና።” (1ሳሙ.2፡3)
ንጉሥ ዳዊትም “አቤቱ፥ አንተ እነሆ የቀድሞውንና የኋላውን አወቅህ፤ አንተ ፈጠርኸኝ፥ እጅህንም በላዬ አደረግህ። እውቀትህ ከእኔ ይልቅ ተደነቀች፤ በረታች፥ ወደ እርስዋም ለመድረስ አልችልም።” (መዝሙር 139:5፣ 6)
እግዚአብሔር የወደፊቱን ያውቃል፡ የሚሆነውን ሁሉ እግዚአብሔር ያውቃል። ጌታ እንዲህ አለ፡- “በመጀመሪያ መጨረሻውን፥ ከጥንትም ያልተደረገውን እነግራለሁ፤ ምክሬ ትጸናለች ፈቃዴንም ሁሉ እፈጽማለሁ እላለሁ።” (ኢሳይያስ 46፡10)።
ስለ አብርሃም በዘፍ. 18፡18 ስለ ሶሪያዉ ንጉስ ስለ ቤንሃዳድ (2 ነገሥት 8፡9)፣ ስለ ሕዝቅያስ (2 ነገሥት 20፡1) እና ስለ ሰሎሞን (1ኛ ነገሥት 5፡5) የወደፊት ዕጣ ፈንታ ተንብዮአል። የእነዚህን ሰዎች የወደፊት ሁኔታ የሚያውቀው ጌታ የእኛንም የወደፊት ዕጣ በእርግጠኝነት ያውቃል። ስለዚህ ለጥበቡ እንገዛ።
እግዚአብሔር ጸሎታችንን ይሰማል: “ሙሴም ወደ እግዚአብሔር እየጮኸ። አቤቱ፥ እባክህ፥ አድናት አለው።” (ዘኁልቁ 12:13) እግዚአብሔር የሙሴን ጸሎት ሰምቶ ማርያም ከለምጽ ተፈወሰች።
ንጉሥ ሕዝቅያስ እስከ ሞት ድረስ ታሞ በነበረ ጊዜ፣ ነቢዩ ኢሳይያስ እንደሚሞት አረጋግጦለት፣ ንጉሡ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፣ እርሱም ራራለት ዕድሜውንም አራዘመለት (2ኛ ነገ. 20፡3-6)።
ለኢያሱ ጸሎት ምላሽ ፀሐይ ቆመ ጨረቃም ቆመ (ኢያሱ 10፡12–14)። የእነዚህን ታማኝ ሰዎች ጸሎት የሰማ አምላክ ጸሎታችንን ይሰማል።
ለሕይወት አስጊ በሆነ ቀውስ ውስጥ፣ እግዚአብሔር የአስቴርን ጸሎት ሰምቶ ሕዝቡን አዳነ።
እግዚአብሔር በስም ያውቀናል፡ እግዚአብሔር ሰዎችን በቅዱሳት መጻሕፍት ጠራ። ያዕቆብን፣ ሙሴን፣ ኢያሱን፣ ሳሙኤልን፣ የጠርሴሱን ሳኦልን ስም በነገራቸው ጊዜ ምሳሌዎች አሉልን (ኢሳ. 43፡1፤ ዘጸአት 3፡4፤ 1ሳሙ 3፡10፤ የሐዋርያት ሥራ 9፡4)።
እግዚአብሔር ለሰዎች ስም ሰጠ፡ ለአንድ ታዋቂ አበዉ እንዲህ አለዉ፡- “ስምህ አብራም አይባልም ስምህ አብርሃም ይባላል። የብዙ አሕዛብ አባት አድርጌሃለሁና” (ዘፍጥረት 17፡5)።
ሳራ፡ አብርሃም ከእግዚአብሔር ዘንድ የስም ለውጥ የተቀበለ ብቸኛዉ የቤተሰቡ አባል አልነበረም። ሚስቱም እንዲሁ ተቀብላለች። “እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፡— ሚስትህን ሦራን ግን ስሟን ሦራ ብለህ አትጥራ፥ ነገር ግን “ስሟ ሣራ ይሆናል” (ዘፍጥረት 17፡15)። የአሕዛብ እናት ትሆናለች ነገሥታትም ከእርሷ ይወለዳሉ።
ያዕቆብ፡- ያዕቆብም ከጌታ ዘንድ አዲስ ስም ተቀበለ። መልአኩም እንዲህ አለ፡- “ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ እስራኤል ይባል እንጂ ያዕቆብ አይባል፤ ከእግዚአብሔር ከሰውም ጋር ታግለህ አሸንፈሃልና።” (ዘፍ 32፡28)።
ማሕርሻላልሃሽባዝ፡- ነቢዩ ኢሳይያስ በእግዚአብሔር የተጠራ ወንድ ልጅ ነበረው፤ ስሙም የትንቢቱ ክፍል ነው። የኢሳይያስ ሚስት ወንድ ልጅ በወለደች ጊዜ፣ “እግዚአብሔርም፣ ስሙን ማሕርሻላልሐሽባዝ ብለህ ጥራ” አለኝ (ኢሳይያስ 8፡3)።
ኢይዝራኤል፡ የነቢዩ የሆሴዕ የበኩር ልጅ በእግዚአብሔር ዘንድ ትርጉም ያለው ስም ተሰጠው፡- “እግዚአብሔርም። ከጥቂት ዘመን በኋላ የኢይዝራኤልን ደም በኢዩ ቤት ላይ እበቀላለሁና፥ ከእስራኤልም ቤት መንግሥትን እሽራለሁና ስሙን ኢይዝራኤል ብለህ ጥራው” (ሆሴዕ 1፡4)።
ሎሩሃማ፡ የነቢዩ የሆሴዕ ልጅ ሌላዋ ከጌታ ዘንድ ምሳሌያዊ ስም የተቀበለች ናት፡- “ይቅር እላቸው ዘንድ የእስራኤልን ቤት ከእንግዲህ ወዲህ አልምርምና ስምዋን ሎሩሃማ ብለህ ጥራት” (ሆሴዕ 1፡6)
ሎአሚ፡ የነቢዩ የሆሴዕ ሁለተኛ ልጅ በእግዚአብሔር ስም ተጠርቷል፡- “እግዚአብሔርም። ሕዝቤ አይደላችሁምና፥ እኔም አምላክ አልሆናችሁምና ስሙን ሎዓሚ ብለህ ጥራው አለው።” (ሆሴዕ 1፡9) አለ። እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችን ስም ሲሰጠን ዓላማ አለው።
እግዚአብሔር በብዙ መንገድ ይናገረናል፡ እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ ነው። እሱ በሁሉም ቦታ የሚገኝ ነው። እሱ ሉዓላዊ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ አምላክ ለግለሰቦች፣ ለቤተሰብና ለሀገር ሲናገር በሚገልጹ ዘገባዎች የተሞላ ነው። ጥንት በተለያዩ መንገዶች ተናግሯል፣ ይህ ዛሬም እውነት ነው። እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ በፍጥረቱ ይናገራል። “የማይታየው ባሕርይ እርሱም የዘላለም ኃይሉ ደግሞም አምላክነቱ ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ ከተሠሩት ታውቆ ግልጥ ሆኖ ይታያልና፤ … የሚያመካኙት አጡ” (ሮሜ 1፡20)። “ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፥ የሰማይም ጠፈር የእጁን ሥራ ያወራል። ቀን ለቀን ነገርን ታወጣለች፥ ሌሊትም ለሌሊት እውቀትን ትናገራለች።” (መዝ. 19:1፣ 2) እግዚአብሔር በጥንት ጊዜ በመላእክት፣ በነቢያት፣ በሕልም፣ በራእይ፣ በተአምራትና በአህያም በኩል ከሕዝቡ ጋር ይነጋገር ነበር። አህያይቱም አፏን ከፍታ ለበለዓም ተናገረችው (ዘኁ. 22፡28)።

ይቀጥላል . . .

ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገርየእግዚአብሔር የራሱ ሕይወት ብልጭታ በሰው አካል ውስጥ እፍ አለበት፤ ሰውን፣ የሞራል ስጦታዎች ባለቤት፣ እና የራሱን አካሄድ የመምራት ፈቃድ ያለዉ ሕያው ነፍስ አድ...
10/02/2026

ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር

የእግዚአብሔር የራሱ ሕይወት ብልጭታ በሰው አካል ውስጥ እፍ አለበት፤ ሰውን፣ የሞራል ስጦታዎች ባለቤት፣ እና የራሱን አካሄድ የመምራት ፈቃድ ያለዉ ሕያው ነፍስ አድረገዉ። የመለኮታዊ ተፈጥሮ ተካፋይ የመሆን እድል አለው። ይህም ክፋትን ለማሸነፍ ኃይልን ይሰጠዋል፣ በዚህም መልካሙን ይወድዳል እና ይመርጣል። በእግዚአብሔር ቁጥጥር ስር ሆኖ መልካሙን የሚያፀድቅና ስህተቱን የሚያወግዝ ህሊና አለው። ከፈለገም ከእግዚአብሔር ጋር በህብረት ሊኖር ይችላል። ሄኖክ እንዳደረገው አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ማድረግና መነጋገር ይችላል። ይህንን ቅዱስ ወዳጅነት ክርስቶስን እንደ ግል አዳኙ አድርገው የሚያምን ማንም አይነፈግም።

ግልጽ ግንኙነት

ሄኖክ አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር አድረገ፣ እና ፈታኙ ሲያጠቃው፣ ስለዚያ ጉዳይ ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ይችላል። እንደ እኛ “ተጽፎአል” የሚለዉ ቃል አልነበረውም፤ ነገር ግን ስለ ሰማያዊው ወዳጁ ያውቅ ነበር። እግዚአብሔርን መካሪው አደረገው፣ ከየሱስም ጋር ጥብቅ ትስስር ነበረው። ሄኖክም በአካሄዱ ተከብሮ ነበር። ሞትን ሳያይ ወደ ሰማይ ተወሰደ። በመጨረሻው ጊዜ ሞትን ሳያዩ የሚወሰዱ እነርሱ በምድር ላይ አካሄዳቸዉን ከእግዚአብሔር ጋር ያደረጉ ይሆናሉ።
ግዚአብሔር በፈጠረው ተፈጥሮ፣ በቃሉ፣ እንዲሁም በፍቅር እንክብካቤውና በመንፈሱ አማካይነት በሚያሳድረው ተጽእኖ ይናገረናል፡፡ እነዚህ ግን በቂ አይደሉም፡፡ እኛ ደግሞ ልባችንን በፊቱ ማፍሰስ ያስፈልገናል፡፡ መንፈሳዊ ህይወትና ብርታት እንዲኖረን ከፈለግን፣ ለሰማያዊ አባታችን ጋር ትክክለኛ ግንኙነት ሊኖረን ይገባል፡፡ አሳባችን ወደ እርሱ ሊሳብ ይችል ይሆናል፤ ስለ እጁ ስራዎች፣ ስለ ምህረቱ፣ ስለባርኮቱ እናሰላስል ይሆናል፤ በዚህ ብቻ ግን ከእግዚአብሔር ጋር በሙላት ተገናኝተናል ለማለት አይቻልም፡፡ ከዚህ በተጨማሪ፣ ስለ አለንበት ትክክለኛ ሁኔታ ለእርሱ የምንናገረው ነገር ሊኖረን ይገባል፡፡
ለወዳጅ የልብን እንደሚያጫውቱ፣ ጸሎትም ለእግዚአብሔር የልብን ማጫወት ነው፡፡ የምንጸልየው ስለ እኛ ሁኔታ ለእግዚአብሔር የሚያውቀውን መረጃ ለመስጠት ሳይሆን፣ እርሱን በልባችን ለመቀበል እንዲያግዘን ነው፡፡ ጸሎት እግዚአብሔርን ወደ እኛ አያወርደውም፤ ነገር ግን እኛን ወደ እርሱ ከፍ ያደርገናል።
የሰማዩ አባታችን የበረከቱን ሙላት ሊሰጠን ይጠብቃል። ወሰን በሌለው የፍቅር ምንጭ ላይ በብዛት መጠጣት የእኛ መብት እያለን፤ ትንሽ መጸለያችን ምንኛ የሚያስደንቅ ነው! . . .
የሰማይን ግምጃ ቤት ለመክፈት ጸሎት በእምነት እጅ ቁልፍ ሆኖ ሳለ የእግዚአብሔር ወንድና ሴቶች ልጆች ለመጸለይ ለምን ቸል ይላሉ? ያለ ጽኙ ፀሎትና በትጋት የተሞላ ንቃት በይበልጥ ግደየለሽ እየሆንንና ከትክክለኛዉ መስመር እየወጣን ለመሄድ እንዳረጋለን። . . .
ክፋትን በልባችን ከሰወርን የሙጥኝ ያልነዉ የታወቀ ኃጢአት ካለ፣ አምላክ አይሰማንም፤ ነገር ግን የተጸጸተና ራሱን የሚያዋርድ ነፍስ ጸሎት ሁልጊዜ ተቀባይነት አለው። ሁሉም የታወቁ ስህተቶች ሲታረሙ፣ እግዚአብሔር ልመናችንን እንደሚመልስልን እናምን እንችላለን።
የማያቋርጥ ግንኙነት ለእግዚአብሔር ልመናችንን ለማቅረብ የማንችልበት ጊዜ ወይም ቦታ የለም፡፡ በእውነተኛ ጸሎት ልባችንን እንዳናፈስ የሚከለክለን ምንም ነገር የለም፡፡ በመንገድ ላይ ከተሰበሰበ ህዝብ መሃል ሆነን፣ ወይም በስራ ተጠምደን ባለንበት ሁኔታም ቢሆን ነህምያ በንጉስ አርጤክሰስ ፊት መጠይቁን ሲያቀርብ እንዳደረገው፣ እኛም እግዚአብሔር መለኮታዊ ምሪት እንዲሰጠን ልንጠይቀው እንችላለን፡፡ በየትኛውም ቦታ ብንሆን በስውር የምንጸልይበትን ዕድል ልናገኝ እንችላለን፡፡ የልባችን በር ዘወትር የተከፈተና የሱስም እንደ ሰማያዊ እንግዳ ሆኖ በነፍሳችን እንዲኖር ያለማቋረጥ ልናድመው ይገባል፡፡
ፍላጎታችሁን፣ ደስታችሁን፣ ሃዘናችሁን፣ ጭንቀታችሁን ወይም ፍርሃታችሁን በእግዚአብሔር ፊት አቅርቡት፡፡ የማይችለውን ሸክም በእርሱ ላይ ልትጭኑበት አትችሉም፤ ልታደክሙትም አትችሉም፡፡ የራስ ጠጉራችሁን የቆጠረው እርሱ ስለ ልጆቹ ጉዳይ ፈጽሞ ግዴለሽ አይሆንም፡፡ ‹‹ጌታ እጅግ የሚምር የሚራራም ነውና፡›› (ያዕ. 5፡11)፡፡ የፍቅር ልቡ በሰቆቃችንና ስለ ኀዘናችን በምንናገረው ነገር ይነካል፡፡ አእምሮአችሁን የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ፊት አቅርቡት፡፡ ለእርሱ ለመሸከም የሚከብደው ምንም ነገር የለም፤ ምክንያቱም ዓለማትን ሁሉ በእጁ ይዞአልና፤ በዩንቨርስ ውስጥ ያለውንም ሁሉ የሚያስተዳድረው እርሱ ነው፡፡ ለእኛ ሰላም የሚጠቅመውን ማንኛውንም ነገር ቸል ብሎ አያልፍም፡፡ ለእርሱ ለማንበብ የሚያስቸግረው የጨለመ የህይወት ምዕራፍ የለንም፤ እርሱ ሊያስወግደው የሚከብደው ጭንቀትም የለንም፡፡6

ጠይቁ ፣ ፈልጉ ፣ አንኳኩ።

“ጠይቁ።” ጥያቄው፣ የሚያስፈልግዎትን ነገር እንደተገነዘቡ ያሳያል፤ በእምነትም ብትለምኑ ትቀበላላችሁ። ጌታ ቃል ገብቷል፣ ቃሉም ለዘላለም የጸና ነዉ። በእውነተኛ ጸጸት ከመጣህ ጌታ የገባውን ቃል በመጠየቅህ ትዕቢት እንዳለብህ ሊሰማህ አይገባም። የሚያስፈልጓችሁን በረከቶች ስትጠይቁ፣ ክርስቶስን በሚመስል ባህሪይ ይሁን፣ ጌታ በተረጋገጠው የተስፋ ቃሉ መሰረት የጠየቃችሁንን ይፈጽምላችኋል። ኃጢአተኛ መሆንህ ከተሰማህና ካወቅህ ምህረቱንና ርህራሄውን ለመጠየቅ በቂ ምክንያት ነው። ወደ እግዚአብሔር ለመምጣት ቅድመ ሁኔታዉ ቅዱስ መሆን ሳይሆን ከኃጢአት ሁሉ እንዲያነጻህና ከበደልም ሁሉ እንዲያነጻህ መመኘት (ከልብህ መሻት) ብቻ ነው።
“ፈልጉ።” የእርሱን በረከቶች ብቻ ሳይሆን እርሱን ራሱንም ተመኙ። “አሁንም ከእርሱ ጋር ተስማማ ፥ ሰላምም ይኑርህ።” ኢዮብ 22፡21። ፈልጉ ታገኙማላችሁ። እግዚአብሔር እየፈለገዎት ነው፣ እና ወደ እርሱ ለመቅረብ የሚያስፈልግዎት መንፈሱ ስበት መገዛት ብቻ ነው። ለዚያ ስበት እጅዎትን ይስጡ። ክርስቶስ የተፈተኑትን፣ የተሳሳቱትንና የማያምኑትን ጉዳይ እየጠየቀ ነው። ከራሱ ጋር ወዳጅ እንዲሆኑ ሊያደርጋቸው ይፈልጋል። “ብትፈልጉት ታገኙታላችሁ” 1ኛ ዜና 28፡9
“አንኳኩ።” በልዩ ግብዣ ወደ እግዚአብሔር እንመጣለን፣ እርሱም በግብዣዉ ክፍል ሊቀበለን ይጠብቃል። . . . የእግዚአብሔርን በረከት የሚሹ የምህረትን ደጃፍ ያንኳኩ እና በፅኑ ማረጋገጫ ይጠብቁ፣ አቤቱ፣ አንተ ተናግረሃልና፣ የሚለምን ሁሉ ይቀበላል፤ የሚፈልግም ያገኛል፤ ለሚያንኳኳም ይከፈትለታል።
የሰብአዊ ዘር ታላቅ ወንድም በዘላለማዊዩ ዙፋን አጠገብ አለልን አዳኝነቱን በመቀበል ፊቱን ወደ እርሱ የመለሰውን ሰው ሁሉ ይመለከታል። ኃጢአት የሌለበት ከመሆኑ በስተቀር በሁሉም ነገር እንደ እኛ ስለተፈተነ ፍላጐታችንን፣ የት ላይ ፈተና እንደሚበረታብንና የሰው ዘር ድከመትም ምን እንደሆነ ከልምድ ያውቀዋል። “አንተ የምትንቀጠቀጥ የእግዚአብሔር ልጅ አትፍራ እርሱ ይጠብቅሃል” ፈተና ደረሰብህ? እርሱ ያወጣሃል። ደካማ ነህ? እርሱ ያበረታሃል። ደንቆሮ ነህ? እርሱ ያብራራልሃል።“ ቁስለኛ ነህ? እርሱ ይፈውስሃል። ...
ምንም ዓይነት ስጋትና ፈተና ቢኖርብህ ሁሉንም ወደ እርሱ አቅርብ። ይህን ሁሉ ለመቋቋም መንፈስህ ማበረታቻ ያገኛል።” እራስህን ከመሸማቀቅና ከችግር የምታላቅቅበት መንገድ ይከፈትልሃል። ደካማነትህንና አቅመቢስነትህን እንዳወቅህ መጠን በእርሱ ኃይል ትጠነክራለህ። ሸክምህ እንደከበደህ መጠን ይህን ሸክም በቀንበር ተሸካሚው ላይ በመጣል የምታገኘው እረፍት የበለጠ በረከት አለው።

Address

Ayat Meri Loke
Addis Ababa
1000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when SDARM Ethiopia - የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ተሐድሶ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share