31/08/2026
መንግስተ ሰማይ መንግስተ ሰማይ
እንደምን ናፍቀናል መዳኒታችንን
በአይናችን ልናይ ፊት ለፊት ልናይ
አሁንስ ጓጉተናል ከሞት ያዳንከንን
ባይናችን ልናይ ፊት ለፊት ልናይ
1⃣ #በዚያ ሀዘን የለም መከራና ለቅሶ
መከፋት መጨነቅ ያበቃል ጨርሶ
አዎን እንሄዳለን ወደ እየሩሳሌም
በደስታ በሐሴት ልንኖር ዘላለም
2⃣ #ያልበቃን ስንሆን ብቁ ሆነን ታይተን
ሕይወት ያለበስከን ሞታችንን ሞተህ
ዳግመኛ ምትመጣ ታጅበሕ በመላዕክት
መቼ ይሆን ቀኑ አንተን ምናይበት
3⃣ #ጽኑነዉ ተስፋችን ስንጠብቅህ ልናይህ እንደገና
ትመጣልናለህ አለኝታችን በክብር በደመና
አሜን ማራናታ ቶሎ ናልን አትዘግይ የኛ ጌታ
ልጆችህ ናፍቀናል ልንዳስስህ እጆችህን ልንነካ
#ኢየሱስ ሆይ ናልን ኢየሱስ ሆይ ናልን
#ኢየሱስ ሆይ ናልን ሀገራችን ዉሰደን
#ልናይህ ናፍቀናል ልናይህ ናፍቀናል
#ልናይህ ናፍቀናል ልናይህ ጓጉተናል
#ማራናታ አሜን መንግስትሕ ትምጣልን