Singer Hawi boru dido

Singer Hawi boru dido Jesus Christ is my hero

26/02/2026

ምሳሌ 18:22 ሚስት ያገኘ በረከትን አገኘ፥ ከእግዚአብሔርም ሞገስን ይቀበላል።

04/02/2026
01/12/2025

ዮሐንስ 3:16 በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።

መዝሙር 34:1-221 እግዚአብሔርን ሁልጊዜ እባርከዋለሁ፤  ምስጋናውም ዘወትር ከአፌ አይለይም።2 ነፍሴ በእግዚአብሔር ተመካች፤  ትሑታንም ይህን ሰምተው ሐሤት ያደርጋሉ።3 ኑና ከእኔ ጋር እ...
20/11/2025

መዝሙር 34:1-22
1 እግዚአብሔርን ሁልጊዜ እባርከዋለሁ፤
ምስጋናውም ዘወትር ከአፌ አይለይም።
2 ነፍሴ በእግዚአብሔር ተመካች፤
ትሑታንም ይህን ሰምተው ሐሤት ያደርጋሉ።
3 ኑና ከእኔ ጋር እግዚአብሔርን አክብሩት፤
ስሙንም በአንድነት ከፍ ከፍ እናድርግ።
4 እግዚአብሔርን ፈለግሁት፤ እርሱም መለሰልኝ፤
ከፍርሀቴም ሁሉ አዳነኝ።
5 ወደ እርሱ የሚመለከቱ ያበራሉ፤
ፊታቸውም ከቶ አያፍርም።
6 ይህ ችግረኛ ጮኸ፤ እግዚአብሔርም ሰማው፤
ከመከራውም ሁሉ አዳነው።
7 እግዚአብሔርን በሚፈሩት ዙሪያ የእግዚአብሔር መልአክ ይሰፍራል፤
ያድናቸዋልም።
8 እግዚአብሔር ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እዩ፤
እርሱን መጠጊያ የሚያደርግ ምንኛ ቡሩክ ነው!
9 እናንተ ቅዱሳኑ፤ እግዚአብሔርን ፍሩት፤
እርሱን የሚፈሩት አንዳች አያጡምና።
10 አንበሶች ሊያጡ፣ ሊራቡም ይችላሉ፤
እግዚአብሔርን የሚሹ ግን መልካም ነገር አይጐድልባቸውም።
11 ልጆቼ ሆይ፣ ኑ፤ ስሙኝ፤
እግዚአብሔርን መፍራት አስተምራችኋለሁ።
12 ሕይወትን የሚወድድ፣
በጎውንም ያይ ዘንድ ዕድሜን የሚመኝ ማን ነው?
13 አንደበትህን ከክፉ ነገር ከልክል፤
ከንፈርህንም ከሽንገላ ጠብቅ።
14 ከክፉ ሽሽ፤ መልካሙንም አድርግ፤
ሰላምን ፈልጋት፤ ተከተላትም።
15 የእግዚአብሔር ዐይኖች ወደ ጻድቃን ናቸው፤
ጆሮዎቹም ለጩኸታቸው ክፍት ናቸው።
16 መታሰቢያቸውን ከምድር ለማጥፋት፣
የእግዚአብሔር ፊት በክፉ አድራጊዎች ላይ ነው።
17 ጻድቃን ሲጮኹ፣ እግዚአብሔር ይሰማቸዋል፤
ከመከራቸውም ሁሉ ያድናቸዋል።
18 እግዚአብሔር ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው፤
መንፈሳቸው የተሰበረውንም ያድናቸዋል።
19 የጻድቅ መከራው ብዙ ነው፤
እግዚአብሔር ግን ከሁሉም ያድነዋል።
20 ዐጥንቶቹን ሁሉ ይጠብቃል፤
ከእነርሱም አንድ አይሰበርም።
21 ኀጢአተኞችን ክፋት ይገድላቸዋል፤
ጻድቃንን የሚጠሉ ይፈረድባቸዋል።
22 እግዚአብሔር የባሪያዎቹን ነፍስ ይቤዣል፤
እርሱንም መጠጊያ ያደረገ አይፈረድበትም።

The Kedus Bible is a mobile app that offers the Bible in various languages.

18/11/2025

2 ዜና 7:11-16
11 ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስና የቤተ መንግሥቱን ሥራ ጨረሰ፤ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስና ለራሱ ቤተ መንግሥት ያደርግ ዘንድ በልቡ ያሰበውን ሁሉ ካከናወነ በኋላ፣
12 እግዚአብሔር በሌሊት ተገልጦለት እንዲህ አለው፤
“ጸሎትህን ሰምቻለሁ፤ ይህንም ስፍራ መሥዋዕት የሚቀርብበት ቤተ መቅደስ እንዲሆን ለራሴ መርጬዋለሁ።
13 “ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማያትን በምዘጋበት ጊዜ ወይም ምድሪቱን እንዲበላ አንበጣ በማዝበት ጊዜ፣ ወይም በሕዝቤ ላይ ቸነፈር በምሰድድበት ጊዜ፣
14 በስሜ የተጠራው ሕዝቤ ራሱን አዋርዶ ቢጸልይ፣ ፊቴን ቢፈልግና ከክፉ መንገዱ ቢመለስ፣ ከሰማይ እሰማዋለሁ፤ ኀጢአቱን ይቅር እላለሁ፤ ምድሩንም እፈውሳለሁ።
15 አሁንም በዚህ ስፍራ ወደሚጸለየው ጸሎት ዐይኖቼ ይገለጣሉ፤ ጆሮዎቼም ያዳምጣሉ።
16 ስሜ ለዘላለም በዚያ ይኖር ዘንድ ይህን ቤተ መቅደስ መርጫለሁ፤ ቀድሼዋለሁም። ዐይኖቼም ልቤም ዘወትር በዚያ

17/11/2025

እየሱስ ክርስተቶስ ጌታ ነዉ

09/11/2025

Address

AA
Addis Ababa
AA

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Singer Hawi boru dido posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share