23/08/2026
መካኒሳ ዐዲስ ኪዳን መጥምቃዊት ቤተክርስቲያን
እሁድ ነሃሴ 17, 2018 ዓ.ም
በወንደም የኔነህ ታደሰ
የዕለቱ መልእክት አጭር ማጠቃለያ፦ የብሱ ይገለጥ!
📖 የዕለቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፦
«እግዚአብሔርም፦ ከሰማይ በታች ያለው ውኃ በአንድ ስፍራ ይሰብሰብ፥ የብሱም ይገለጥ አለ፤ እንዲሁም ሆነ።» — ዘፍጥረት 1፥9
✨ ከመልእክቱ የተወሰዱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
1. እግዚአብሔር የተዘበራረቀውን ሕይወት ያስተካክላል
በመጀመሪያ ምድር ባዶና ጨለማ ነበረች፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ቃል ሁኔታዎች ተቀየሩ። እግዚአብሔር ሲሠራ ያልተደራጀው ይደራጃል፣ የጨለመው ይበራል፣ የተዘጋውም በር ይከፈታል።
2. የተሸፈነው ይገለጣል
የብሱ ከውኃ በታች ሆኖ ለሰው ዓይን ባይታይም እግዚአብሔር ግን ያውቀው ነበር። ያልታየ ማለት የሌለ ማለት አይደለም፤ ጊዜው ሲደርስ እግዚአብሔር በሕይወታችን የተሸፈነውን ሕልም፣ አቅም እና ዕቅድ “ይገለጥ” ብሎ ያወጣዋል።
3. ከመገለጥ በኋላ ፍርያማነት ይከተላል
እግዚአብሔር የተሸፈነውን ነገር ሲገልጥልን እንድንደነቅ ብቻ ሳይሆን ፍሬ እንድናፈራ ነው (ዘፍጥረት 1፥11)።
💡 የተሸፈነው እንዲገለጥና ፍርያማ እንድንሆን ምን እናድርግ?
* ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ወዳጅ እንሁን፦ ቃሉ ሕይወታችንን ይለውጣል፣ መንገዳችንን ያበራል፣ ሚስጥርን ይገልጣል፣ ባዶነታችንንም ይሞላል።
* የጸሎት ሕይወታችንን እናሳድግ፦ ጸሎት ኃይል አለው፤ የእግዚአብሔርን ድምፅ የምንሰማበትና በመንፈስ ቅዱስ የምንሞላበት መንገድ ነው።
የቡራኬ ቃል፦
በግል፣ በቤተሰብ፣ በቤተ ክርስቲያን፣ በከተማችንና በአገራችን የተዘጋው ይከፈት፤ የጠፋው ተስፋ ይታደስ፤ የተዘበራረቀው ሕይወት ሥርዓት ይያዝ፤ የተዘራው ዘር ፍሬ ያፍራ፤ የእግዚአብሔር ዓላማ በሕይወታችን ይገለጥ!
እግዚአብሔር ይባርካችሁ!
ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ!
የጉግል ማፕ አድራሻ (Google Maps)፦ https://maps.app.goo.gl/sFcqHewKLUofJDr89?g_st=ac
መካኒሳ አዲስ ኪዳን መጥምቃዊት ቤተክርስቲያን
«እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ ...።» — 1ኛ ቆሮንቶስ 1:23
Mekanisa Addis Kidan Baptist Church
“but we preach Christ crucified...” — 1 Corinthians 1:23