18/09/2025
ደማሚት ማለት :-
ከቃሉ ትርጒም ስንነሳ የፈንጂ ዓይነት ሲሆን በዋናነት ጥቅም ላይ የሚውለው ከጦር መሣሪያነቱ ይልቅ ለልማት ሥራ መዋሉ ትኩረትን ይስባል ።
ይበልጥ በመንገድ ሥራ ቅየሳ ጊዜ የሚያጋጥሙ ትልልቅ ቋጥኞችን ለመናድና ደልዳላ ሜዳ ለማድረግ የሚያስችል አስደናቂ መሳሪያ ነው ።
የዚህ ፔጅ ስያሜም የክፉዎችን የሐሳብ ቋጥኝ በማፍረስ በእውነተኛው የቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ መሠረት የሰዎችን አእምሮ መሥራት ነውና ከዛሬ ጀምሮ
“የሰውንም አሳብ በእግዚአብሔርም እውቀት ላይ የሚነሣውን ከፍ ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳለን ለክርስቶስም ለመታዘዝ አእምሮን ሁሉ እንማርካለን፥”
2ኛ ቆሮ 10፥5 የሚለው ቃል የሕይወታችን መመሪያ እንዲሆን ተግተን ለእውነት እየወገንን ክፉ ሀሳቦችን እናፈርሳለን ፤ በፍቅራችን የሰውን አእምሮ እንማርካለን ።
ውዶች ዓላማችን ይሳካ ዘንድ ደማሚትን ያስተዋውቁ በደማሚት እናስደምምዎታለን ።