Jehovah Jireh Family

Jehovah Jireh Family Jehovah Jireh Family Litrature Team is founded in Genet Church which is created to evangelize,worship

17/04/2026
Filling blessed, its a privilege serving GOD.
12/10/2025

Filling blessed, its a privilege serving GOD.

01/05/2025

Check out ruhama_podcast’s video.

25/04/2025

አላማችንወንጌልን በሀገርና ከሀገር ውጪ በሚዲያና መድረኮች እንዲሁም በተገኘው አጋጣሚ ሰዎችን ሁሉ በመድረስ ሁለንተናዊ እድገት እንዲኖራቸው እና እንዲያገለግሉ ማብቃት #ሁላችንም የ.....

🔘 የኢየሱስ ደም ዛሬም ጠላቶቻችንን የሚያባርር ቀይ ካርድ ነው🛑✍ መቼስ ስለኢየሱስ ደም አውርተን አንጨርስም። የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ስለሃጢአታችንና ስለበደላችን የፈሰሰ ንፁህና ክቡር ደም ...
24/12/2023

🔘 የኢየሱስ ደም ዛሬም ጠላቶቻችንን የሚያባርር ቀይ ካርድ ነው🛑

✍ መቼስ ስለኢየሱስ ደም አውርተን አንጨርስም። የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ስለሃጢአታችንና ስለበደላችን የፈሰሰ ንፁህና ክቡር ደም ነው። ከአብ ጋር የታረቅንበትና በፊቱ ለመቆም ድፍረትን ያገኘንበት ደም ነው። እሱ ብቻ አይደለም ለጠላቶቻችን ቀይ ካርድ የሰጠ ለእኛ ደግሞ ስልጣንን ያጎናፀፈ የአምላክ ምህረት የተገለጠበት ታሪካችንንም ለዘላለም የቀየረ እውነት ነው። መፅሃፍ ቅዱስ የልጁ የኢየሱስ ደም ከሃጢአት ሁሉ እንደሚያነፃ ይነግረናል:-

📌“..፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።”
1ኛ ዮሐንስ 1፥7

✍ የኢየሱስ ደም ህሊናን እንኳ የማፅዳት አቅም ያለው ህያው ደም ነው።

📌ዕብራውያን 9
¹³ የኮርማዎችና የፍየሎች ደም በረከሱትም ላይ የተረጨ የጊደር አመድ ሥጋን ለማንጻት የሚቀድሱ ከሆኑ፥
¹⁴ ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም እንዴት ይልቅ ሕያውን እግዚአብሔርን ልታመልኩ ከሞተ ሥራ ሕሊናችሁን ያነጻ ይሆን?

👉በዚህ ደም ለመንፃት ግን ደሙን መቀበልና መታጠብ ይገባል። ልክ ሳሙና ፋብሪካ ውስጥ መስራት በራሱ ንጹህ እንደማያደርግ ሁሉ(በሳሙናው እስካልታጠብንበት ድረስ) ወይም ደግሞ ፀጉር ቤት መመላለሳችን በራሱ ፀጉራችንን እንደማያስተካክለው ሁሉ(ቶንዶሱ ፀጉራችንን እስካልነካ ድረስ) እንዲሁ የኢየሱስን ደም ተቀብሎ መታጠብ ከሃጢአት ለመንፃት ሌላ አማራጭ የሌለው ዘላለማዊ እውነት ነው። ሃኪም ያዘዘልን መድሃኒት እኮ የሚጠቅመን ስንወስደው እንጂ ወስደን ስናስቀምጠው አይደለም። ዛሬም ትኩስ በሆነው በኢየሱስ ደም እንታጠብና እንንፃ ከሰይጣን ባርነትም እናምልጥ መልዕክቴ ነው።🙏
♥️የኢየሱስ ደም ዛሬም ትኩስ ነው

📌“እነርሱም ከበጉ ደም የተነሣ ከምስክራቸውም ቃል የተነሣ ድል ነሡት፥ ነፍሳቸውንም እስከ ሞት ድረስ አልወደዱም።” ራእይ 12፥11

ዮናታን ወርቁ


🛑 መስዋዕት 🛑ይህን ቃል በብዙ ነገሮች ላይ እነጠቀመዋለን በሀይማኖትም፣ በፖለቲካም፣ በህይወትም በተለያዩ አግባቦች እንጠቀምበታለን ሆኖም ውጤቱን ግን አናስተውለውም። መስዋዕትነት ማለት አሳል...
15/10/2023

🛑 መስዋዕት 🛑

ይህን ቃል በብዙ ነገሮች ላይ እነጠቀመዋለን በሀይማኖትም፣ በፖለቲካም፣ በህይወትም በተለያዩ አግባቦች እንጠቀምበታለን ሆኖም ውጤቱን ግን አናስተውለውም። መስዋዕትነት ማለት አሳልፎ መስጠት ወይም መግደል ዋጋ መክፈል

“ሦስቱም ኃያላን የፍልስጥኤማውያንን ሠራዊት ቀድደው ሄዱ፥ በበሩም አጠገብ ካለችው ከቤተ ልሔም ምንጭ ውኃ ቀዱ፥ ይዘውም ለዳዊት አመጡለት፤ እርሱ ግን ሊጠጣ አልወደደም፥ ነገር ግን ለእግዚአብሔር አፍስሶ፦”2ኛ ሳሙኤል 23፥16

ዳዊት የሃያላን ደም አለበት ብሎ አፈሰሰው ለእግዚአብሔር ሰዋው ውጤቱም አያናድድም ምክንያቱም ውድ የሆነው ነገር የሚገባው እግዚአብሔር ነው። በአለማችን ላይ በጣም የሚገርመኝን ነገር ልንገራችሁ የሚበዛው እንስሳ የትኞቹ ናቸው ብዬ አሰብኩ ከዝሆንና ከበሬ የትኞቹ ናቸው እየበዛ የሚሄደው? ከሚኒሊክ ድኩላና ከበግ የትኞቹ ናቸው የሚበዙት? ሁሌ የሚታረዱት እየበዙ ነው የሚሄዱት መጥፋት ሲኖርባቸው ጭራሽ እየበዙ ነው የሚገኙት ስለዚህ የሚያስተምረን የሚሰዋው ነገር ይበዛል ጉልበታችንን አንሰጥም ብለን እቤት ቁጭ ብንል ከሳምንት በኋላ ሰውነታችን እየደከመ አጥንታችን እየደረቀ መንቀሳቀስ ሊያቅተን ይችላል ግን በሰራንበት በተጠቀምንበት መጠን ጉልበት እያገኘን እንሄዳለን።

ዋናው ነገር የማንጠቀምበት ጌታ የሰጠን አቅም እንዳይኖረን ይዘነው ወደመቃብር እንዳንወርድ እንጠቀምበት እንሰዋው አሳልፈን ለቤተክርስቲያን ለህብረት ለቤተሰብ ለሀገር ልንሰጥ ያስፈልገናል።

ተባርካችኋል እወዳችኋለሁ ❤️❤️❤️

25/09/2023

Get Ready!

Address

Zeneborik
Addis Ababa

Telephone

+251913554198

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Jehovah Jireh Family posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Jehovah Jireh Family:

Share