ፍቁረ እግዚእ ሚዲያ Fikure Egzi Media FEM

ፍቁረ እግዚእ ሚዲያ Fikure Egzi Media  FEM በዚህ ገጽ ላይ መንፈሳዊ ትምህርቶችን(ዐውደ ስብከት)፣ የስነ–ጥበብ ስራዎች፣ ያሬዳዊ መዝሙሮችንና ወቅታዊ ጉዳዮችን ያገኛሉ።
ይህ የፍቁረ እግዚእ ሰ/ት/ቤት የማህበራዊ ትስስር ገጽ ነው።

"አንተ ግን በተማርህበትና በተረዳህበት ነገር ጸንተህ ኑር ከማን እንደ ተማርከው ታውቃለህና " 2ኛ ጢሞ 3÷14🎓🎓🎓 የተማሪዎች የምርቃት መርሐ ግብር  🎓🎓🎓በ2018 ዓ.ም በተለያዩ የትምህር...
27/08/2026

"አንተ ግን በተማርህበትና በተረዳህበት ነገር ጸንተህ ኑር ከማን እንደ ተማርከው ታውቃለህና " 2ኛ ጢሞ 3÷14

🎓🎓🎓 የተማሪዎች የምርቃት መርሐ ግብር 🎓🎓🎓

በ2018 ዓ.ም በተለያዩ የትምህርት ዘርፍ
• በመደበኛ ተከታታይ ትምህርት
• በገና የዜማ መሣሪያ
• በኦርቶዶክሳዊ ቅዱሳት የሥነ ሥዕል
• የሥነ ጽሑፍ አጻጻፍ እና ትወና
• በሞካሽ ሥራ ያስተማራቸውን ተማሪዎች

🎓🗓እሑድ ጳጉሜ 1 ቀን 2018 ዓ.ም
🎓⏰ከጠዋቱ 3 :00 ሰዓት ጀምሮ
🎓💒 በሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ ያስመርቃል ።
🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓🎓

🖥🔴 የምርቃት መርሐ ግብሩ በፍቁረ እግዚእ ሚዲያ በዩቱዩብ ገጻችን በቀጥታ ወደ እናንተ እናስተላልፋለን።

https://youtube.com/channel/UCXceln4wpQhIVS42O02kAWg

" ተላዌ ጴጥሮስ (የጴጥሮስ ተከታይ)  " የተሰኘ የሙሉ ሰዓት ተውኔት ተዘጋጅቶ ቀረበ።በፍቁረ እግዚእ ሰ/ት/ቤት ሥነ ጥበብ ክፍል አጋፋሪነት የተዘጋጀው ምሴተ ጥበብ ዘፍቁረ እግዚእ " ተላዌ...
26/08/2026

" ተላዌ ጴጥሮስ (የጴጥሮስ ተከታይ) " የተሰኘ የሙሉ ሰዓት ተውኔት ተዘጋጅቶ ቀረበ።

በፍቁረ እግዚእ ሰ/ት/ቤት ሥነ ጥበብ ክፍል አጋፋሪነት የተዘጋጀው ምሴተ ጥበብ ዘፍቁረ እግዚእ " ተላዌ ጴጥሮስ (የጴጥሮስ ተከታይ) " በሚል ርእስ የተዘጋጀው የሙሉ ሰዓት ተውኔት በሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ ምእመናን በተገኙበት ቀረበ።

ተውኔቱ የብፁዕ አቡነ ሚካኤል ዘጎሬን ታሪክ የሚዳስስ ሲሆን አቡነ ሚካኤል ለሀገር እና ለቤተክርስቲያን የበረከቱትን አስተዋጽኦ እና ሀገር በጠላት ተወራ በነበረ ጊዜ ለነጻነት የከፈሉትን ዋጋ የሚያሳይ ነው።

“ከትላንት ለመማር
ዛሬን ለመኖር
ነገን ለመስራት ”

✨" ተላዌ ጴጥሮስ (የጴጥሮስ ተከታይ) " ✨

ከትላንት ለመማር ዛሬን ለመኖር ነገን ለመስራት  ዛሬ መሽት 11:00 ሰዓት አይቀርም " ተላዌ ጴጥሮስ (የጴጥሮስ ተከታይ)  "     የሙሉ ሰዓት ተውኔት አዘጋጅተናል።  📆 ነሐሴ 19 ቀን ...
25/08/2026

ከትላንት ለመማር
ዛሬን ለመኖር
ነገን ለመስራት ዛሬ መሽት 11:00 ሰዓት አይቀርም

" ተላዌ ጴጥሮስ (የጴጥሮስ ተከታይ) "
የሙሉ ሰዓት ተውኔት አዘጋጅተናል።

📆 ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ.ም
⌚️ ከቀኑ 11:00 ሰዓት
⛪️ በሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ
💵 መግቢያ :– 100 ብር

👉 ትኬቱን ባሉበት ቦታ በቴሌ ብር 09 01 04 44 44
👉 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000658449633 መቁረጥ ይችላሉ‼

✨ "አቡነ ሚካኤል ከአፈረ ዋናት እስከ ጎሬ"✨

አድራሻ፦ከፒያሳ ወደ አስኮ በሚወስደው መንገድ ላይ ራስ ደስታ ሆስፒታል አካባቢ ደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስና መካነ ጎለጎታ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን።

ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አዲስ የተመደቡትን የስራ ኃላፊዎች አቀባበል እና ትውውቅ ተደረገ።የአዲስ አበባ ሀገረስብከት አዲስ የተመደቡት ዋና ሥራ አስኪያጅ ክቡር መልአከ ብርሃን መምህር ሰሎ...
25/08/2026

ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አዲስ የተመደቡትን የስራ ኃላፊዎች አቀባበል እና ትውውቅ ተደረገ።

የአዲስ አበባ ሀገረስብከት አዲስ የተመደቡት ዋና ሥራ አስኪያጅ ክቡር መልአከ ብርሃን መምህር ሰሎሞን በቀለ እና የሀገረ ስብከቱ የየመምሪያ ክፍል ኃላፊዎች አቀባበል ትውውቅ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት መሰብሰቢያ አዳራሽ በታላቅ መንፈሳዊ ደስታና ድምቀት ተከናወነ።

በዚህ መርሐግብር ላይ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ስራ አስኪያጅ እና የሸገር አህጉረ ስብከቶች ሊቀ ጳጳስ ፣ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ፣ የክፍላተ ከተሞች ሥራ አስኪያጆች፣ የገዳማትና የአድባራት አስተዳዳሪዎችና ጸሐፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው ልዩ ልዩ ክቡራን እንግዶች በስፍራው ተገኝተዋል።

24/08/2026

እጅግ አሳዛኝ ክስተት
እጅግ አሳዛኝ ክስተት በጅጅጋ ከተማ የሃይማኖት እኩልነትና ነጻነት በተረጋገጠባት ሀገራችን፤ ዛሬ በጅጅጋ ከተማ ያልተጠበቀና አሳዛኝ ድርጊት ተፈጽሟል።

በከተማው አዲስ የተገነባው የመድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን መፍረሱ ታውቋል። ይህ ድርጊት በአካባቢው ምዕመናን ዘንድ ከፍተኛ ሀዘንን የፈጠረ ሲሆን፣ የሚመለከታቸው አካላት ስለዚህ ድርጊት አስቸኳይ ህጋዊ ማጣራት እንዲያደርጉ ማህበረሰቡ እየጠየቀ ይገኛል።
© ሶማሌ ሀገረ ስብከት

"ሁለቱም አንድ አካል ይኾናሉ ፤ ይህ ነገር ጥልቅ ፤ ረቂቅ ምሥጢር ነው ፤ እኔም ለክርስቶስና ለቤተክርስቲያን ምሳሌ አድርጌ እናገረዋለሁ፡፡" ሃይማኖተ አበው ዘስምዓት✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ሐ...
23/08/2026

"ሁለቱም አንድ አካል ይኾናሉ ፤ ይህ ነገር ጥልቅ ፤ ረቂቅ ምሥጢር ነው ፤ እኔም ለክርስቶስና ለቤተክርስቲያን ምሳሌ አድርጌ እናገረዋለሁ፡፡" ሃይማኖተ አበው ዘስምዓት

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
ሐምሌ 12/ 2018 ዓ.ም ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ከወንድማችን ደበበ ሽኩር
ጋር የጋብቻ ሥነ ሥርዓትሽን የፈጸምሽው የሰንበት ት/ቤታችን አገልጋይ ትዕግስት ሰብስቤ እንኳን ደስ ያለሽ እንኳን ደስ ያላችሁ ።

የአብርሃምንና የሣራን ፤ የይሰሐቅንና የርብቃን ጋብቻ የባረከ አምላክ አንድነታችሁን ይባርክ እመብርሃን በአማላጅነቷ አትለያችሁ ፤ ቅዱስ ዮሐንስ ከፊት ይምራችሁ ከኋላ ይከተላችሁ እያለች ፍቁሩ እግዚዕ ሰ/ት/ቤት መልካም የትዳር ሕይወት ትመኝላችኃለች።

" ጋብቻ ንጹሕ ነው የወንድና የሴት አንድ መሆንንም እግዚአብሔር አክብሮታል "
መጽሐፈ ዲድስቅልያ

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

ከትላንት ለመማር ዛሬን ለመኖር ነገን ለመስራት" ተላዌ ጴጥሮስ (የጴጥሮስ ተከታይ)  "     የሙሉ ሰዓት ተውኔት አዘጋጅተናል።  📆 ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ.ም         ⌚️ ከቀኑ 1...
23/08/2026

ከትላንት ለመማር
ዛሬን ለመኖር
ነገን ለመስራት

" ተላዌ ጴጥሮስ (የጴጥሮስ ተከታይ) "
የሙሉ ሰዓት ተውኔት አዘጋጅተናል።

📆 ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ.ም
⌚️ ከቀኑ 11:00 ሰዓት
⛪️ በሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ
💵 መግቢያ :– 100 ብር

👉 ትኬቱን ባሉበት ቦታ በቴሌ ብር 09 01 04 44 44
👉 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000658449633 መቁረጥ ይችላሉ‼

✨ "አቡነ ሚካኤል ከአፈረ ዋናት እስከ ጎሬ"✨

አድራሻ፦ከፒያሳ ወደ አስኮ በሚወስደው መንገድ ላይ ራስ ደስታ ሆስፒታል አካባቢ ደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስና መካነ ጎለጎታ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን።

በአጥቢያው የሚገኙ አቅመ ደካሞችን እና ነዳያንን የማስፈሰክ መርሐ ግብር ተካሔደ።የደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ እና መካነ ጎልጎታ ቅድስት ማርያም ቤ/ክ ምግባረ ሰናይ ክፍል ከሚያከናውናቸው ...
22/08/2026

በአጥቢያው የሚገኙ አቅመ ደካሞችን እና ነዳያንን የማስፈሰክ መርሐ ግብር ተካሔደ።

የደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ እና መካነ ጎልጎታ ቅድስት ማርያም ቤ/ክ ምግባረ ሰናይ ክፍል ከሚያከናውናቸው ዋና ተግባራት መካከል የአጥቢያውን ምእመናን በማስተባበር ነድያንን አቅመ ደካሞችን በተለያዩ መንገዶች የመደገፍ እና አጽዋማት ሲፈጸሙ የማስፈሰክ ተግባራት ይገኙበታል።

ክፍሉም ከሚያከናውናቸው ከእነዚህ በጎ ተግባራት መካከል በዛሬው ዕለት የፍልሰታ ጾም መፈጸሙን አስመልክቶ የአጥቢያውን ምዕመናን በማስተባበር ከ800 በላይ ለሚሆኑ በአጥቢያው አካባቢ የሚገኙ አቅመ ደካሞችን እና ነዳያን የማስፈሰክ መርሐ ግብር አከናውኗል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ እና መካነ ጎልጎታ ቅድስት ማርያም ቤ/ክ ምክትል አስተዳዳሪ ሊቀ ሕሩያን ቀሲስ ምስራቅ ወግደረስ ፣ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አባላት ፣የደብሩ አገልጋዮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።

በመጨረሻም ይህን በጎ ተግባር በማጠናከር እና በማስፋት ፍቁረ እግዚእ ሰንበት ት/ቤት እየሰራ ያለውን ገዳማትና አድባራትን የመደገፍ እንዲሁም በየሳምንቱ በዕለተ ሰንበት እሐድ ከቅዳሴ በኃላ ነዳያንንና አቅመ ደካሞችን ቁርስ የማብላትና በዘላቂነት የማቋቋም ስራ ምእመናን በልዩ ልዩ መንገድ በመደገፍ የበረከቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ ተላልፏል።

የቅድስት ኪዳነ ምሕረት ዓመታዊ በዓለ ንግሥ  በቶታል ፈለገ ሕይወት ቅድስት ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን በድምቀት ተከበረ ።
22/08/2026

የቅድስት ኪዳነ ምሕረት ዓመታዊ በዓለ ንግሥ በቶታል ፈለገ ሕይወት ቅድስት ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን በድምቀት ተከበረ ።

Address

ራስ ደስራ ሆስፒታል አካባቢ
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ፍቁረ እግዚእ ሚዲያ Fikure Egzi Media FEM posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to ፍቁረ እግዚእ ሚዲያ Fikure Egzi Media FEM:

Shortcuts

Share