Federal Majlis Election Board የፌዴራል መጅሊስ ምርጫ ቦርድ

Federal Majlis Election Board የፌዴራል መጅሊስ ምርጫ ቦርድ The Executive Board of EIASC Election
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠ/ም/ቤት ምርጫ አስፈፃሚ ቦርድ

ከምርጫው ጋር የተያያዘ ጥያቄና ሐሳብ አልዎት ? እንግዲያውስ 9933 ላይ ይደውሉ!

ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጁዑን !ታላቁ አባታችን የቀድሞ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ወደአኼራ ተሻግረዋል ። አላህ ( ሱ.ወ )...
19/10/2025

ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጁዑን !

ታላቁ አባታችን የቀድሞ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ወደአኼራ ተሻግረዋል ። አላህ ( ሱ.ወ ) የላቀውን የጀነተል ፊርደውስ ሽልማት እንዲያድላቸው እየተማጸንን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክርቤት የ2017 ምርጫ አስፈጻሚ ቦርድ የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ይገልጻል ። አላህ ( ሱ.ወ ) ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለመላው ህዝበ ሙስሊሙ መፅናናትና ሰብሩን እንዲሰጠው ዱዓችን ነው ።

ምርጫ ለፅኑ ተቋም
የኢ/እ/ጉ/ጠ/ም/ቤት የምርጫ አስፈጻሚ ቦርድ !

የኢ/እ/ጉ/ጠ/ም/ቤት የምርጫ አስፈፃሚ ቦርድ ለምርጫ 2017 ማጠቃለያ ጋዜጣዊ መግለጫየኢትዮጵያ ሙስሊሞች በረዥም ጊዜ የትውልድ ቅብብሎሽ የመብት ትግል ውስጥ በየሂደቱየከፈላቸው የህይወት፣ የ...
11/10/2025

የኢ/እ/ጉ/ጠ/ም/ቤት የምርጫ አስፈፃሚ ቦርድ ለምርጫ 2017

ማጠቃለያ ጋዜጣዊ መግለጫ

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች በረዥም ጊዜ የትውልድ ቅብብሎሽ የመብት ትግል ውስጥ በየሂደቱየከፈላቸው የህይወት፣ የደም፣የሞራል፣ የማንነት ዋጋ በዓለም የሙስሊም ዑማ ታሪክ ውስጥበወርቅ ተጽፎ ክስተቶች ሁሉ በትውልድ ተመዝግቦ ከአንድ ወደ ሌላኛው እየተቀባበለ እነሆ
ዛሬ ያለፈውን ታሪክ ብለን የምንዘክርበት ወቅት ላይ መድረሳችን የአላህ ጸጋ ነውናአልሃምዱሊላህ ረቢልዓለሚን፡፡

የህዝብ ሙስሊሙ ሁለንተናዊ ጥያቄዎች ጥቅል መልስ የሆነው የተቋማዊ አሠራርና ራሱተቋሙ በሙሉ መዋቅራዊ ማንነቱ መኖር ላይ የተመረኮዘ በመሆኑ በየጊዜው ይነሱ ከነበሩ
ጥያቄዎች ውስጥ አብዛኛው በኢ/እ/ጉ/ጠ/ጉባኤ (መጅሊስ) ህጋዊ ተቋም መሆንና በህጋዊ ህዝባዊተሳትፎ እና ይሁንታ የተመረጡ አመራሮች ይኑረን የሚለው የመብት ጥያቄ ምላሽ የሆነውበ2017 የኢ/እ/ጉ/ጠ/ጉባኤ ሀገራዊ ምርጫ ማረጋገጡ ሌላኛው እምርታ ሲሆን ከፍ ሲል ተቋሙራሱ እንደማንኛውም የኢትዮጵያ ተቋማት በአዋጅ ቁጥር 1207/12 ህጋዊ ዕውቅና ማግኘቱድርብ ድልና ከፍታ ሆኖ በታሪክ ተመዝግቧል፡፡

በሌላ በኩል የ2017 የመጅሊስ ሀገራዊ ምርጫን ለማካሄድ ትክክለኛ ውሳኔ ጠንካራ አቋምየያዘው የወቅቱ የመጅሊስ አመራር በተለይም የክቡር ዶ/ር ሸ/ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ ቁርጠኛአመራር በዚህ ሂደት ውስጥ ሌላኛው ባለታሪክ ሆኖ ይዘከራል፡፡

ምርጫውን ለማስፈጸም የተቋቋመው አጠቃላይ ከፌደራል እስከ መስጂድ ድረስ በየክልሉ እናከተማዎች የተዋቀረው ተዓምራዊ ተግባርን የፈጸመና የዲን እና የዑማ ተቋማዊ ተልዕኮን
በአንጸባራቂ ድል ያገባደደው ስብስብ ያለቀ አፈጻጸም እና ከግቡ ሲያመነታ ችግሮችንናመሰናክሎችን ተቋቁሞና በጥበብ አልፎ አይሆንም አይቻልም የተባለን ታላቅ ጉዳይ በአላህፍቃድ ቀጥሎ በዓላማ ጽናት ሰርቶ አሳክቶታል በውጤቱ መላው የኢትዮጵያ ሙስሊም ከጫፍጫፍ ከባህር ማዶ ከአድማስ ባሻገር ጭምር አሳትፎ በድል አጠናቋል፡፡ ለዚህም ታላቅ ክብርናምስጋና ለልዑል አላህ ይሁን፡፡

ዳግም አልሃምዱሊላህ ረቢልዓለሚን ብለናል!!!ከመስጂዶች የጀመርነውን ምርጫ በመላ ሀገሪቱ የህዝበ ሙስሊሙ ጥያቄ የነበረው “ምርጫችንበመስጂዳችን” የሚለውን ህዝባዊ ድምጽ እውን ሆኖ ለመላ ሀገሪቱ ባሉ መስጂዶችእንደተጀመረ ሁሉ መዚጊያውም ታሪካዊና የኢትዮጵያ ሙስሊም አርማ በሆነው ታላቁ አንዋርመስጂድ በታላቅ ድምቀትና ህዝባዊ ተሳትፎ ዲናዊ ሥነ ሥርዓትና ሥነ-ምግባር ተጠናቋል፡፡

ምርጫውን ከሌላ ጊዜ እና የምርጫ ዓይነቶች ልዩ ከሚያደርጉት ጉዳዮች መሀከል፡-
➢ ከአሁን በፊት ስለ መጅሊስ ምርጫ ምንም ዓይነት በዚህ ሂደት ልምድም ሠነድም
የተቀመጠ መነሻ አቅጣጫ አለመኖሩ፣
➢ ለምርጫ የተቀመጠ ጊዜ በጣም አጭር መሆንና የሚፈለገው ሀገራዊ የሆነ ምርጫ በመሆኑ
ረዥም ጊዜ የሚፈለግ መሆኑ፣
➢ ተመራጭም ምረጡኝ ብሎ ለራሱ የማይቀሰቅስ በመሆኑ ህዝበ ሙስሊሙን ማንን እና
እንዴት ለየት እርከን እንደሚመርጥ፣ ማሳወቅና ማብቃቱ ውስብስብ መሆኑ፣
➢ በቂ በጀት እና በዘረፉ የሰለጠነ የሰው ሀይል ያልነበረ መሆኑ፣
➢ በህዝበ ሙስሊሙ መሀከል በአመለካከትና በመዝሀብ ተከፋፍሎ ወትሮውንም በተለያየ ጎራ
ላይ የተሰለፉ እያንዳንዱን ክንዋኔ ከራሱ አንግልና ውክልና ብቻ በሚመለከትበት ሁኔታ ላይ
መሆኑ፣
➢ የመጅሊሱ መዋቅሮች እና የዑለማዕ ምክር ቤት መዋቅሮች በሚገባው ደረጃ ሙሉ በሙሉያልተደራጀና በየ እርከኑ ድጋፍ የሚያደርግ አካል በበቂ ደረጃ አለመኖሩ በተለይም የዑለማዕ
አደረጃጀት ሙሉ በሙሉ የለም በሚባል ደረጃ ላይ መሆኑ፣
በምርጫ ቦርዱ እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትን ጉዳዮች ሁሉንም እንደየ ሁኔታውና አመጣጡአጣጥሞ ችሎ እና አቻችሎ በመያዝ ከየትኛውም ጊዜ በተሻለሁኔታ ፈጥኖ አደራጅቶ አሰልጥኖ
በቂ የምርጫ ቁሳቁስ አዘጋጅቶ አወያይቶ በሹራ ባህል አማክሮ አስመርጦ ውጤት ለይቶየተቋሙን የመምራት ሚና ሊሚወጡ የህዝብ ተመራጮች ምርጫን በግልፀኝነት፣በፍትሃዊነት፣ በአካታችነትና በአሳታፊነት በማካሄደ ስልጣንን አረካክበዋል፡፡
ሌላው የዘንድሮን ምርጫ ልዩ ከሚያደርገው ጉዳይ የሰለጠኑ ሀገራት ዛሬ ላይ የሚጠቀሙበትንየIT ቴክኖሎጂን በምርጫ 2017 በመጠቀም በምያስደምም ሁኔታ የምርጫን ሂደት ከምዝገባእስከ ውጤት በማሳለጥ ማከናወኑ ነው፡፡
በዚህ ዘርፍ የምርጫ ቦርዱ የወሰዳቸው ቴክኒካዊ እርምጃዎች ከተቋሙ ባሻገር ለሀገርምተምሳሌታዊ ተግባር ሆኖ አልፏል፡፡ ለምርጫ ምዝገባ የሚዉሉ ቁሳቁሶችን በተመለከተ
ከ20,000,000 ባለይ የሚሆን የምርጫ ካርድና መዛግብት ታትሞ ተሰራጭቷል፡፡

የምርጫሂደቱን አሳታፊና አካታች ለማድረግ ከተለያየ አመለካከትእና መዝሃብ ጀማዓዎች፣ ተቋማትከ38 ስብሰባና ውይይቶች በላይ ተደርገዋል፡፡ ሂደቱ ከ 49,000 በላይ መሳጂዶችን በምርጫውያሳተፈ ሲሆን በዚህም ከ 13,000,000 ሙስሊም ማህበረሰብ እንደየዘርፉ በዑለማዕ፣ በምሁር፣በወጣት፣ በሴት እና በሥራ ማህበረሰብ በፍቃደኝነትና በሙሉ ተነሳሽነት ተሳተፈዋልለምርጫ ከተመዘገበው ሙስሊም ማህበረሰብ ውስጥ በአጠቃላይ እንደ ሀገር ከ 80% በላይ
ወጥቶ የመረጠ ሲሆን፡፡

 ከመስጂድ እስከ ፌዴራል ምክር ቤት በተደረጉት ምርጫዎች በአጠቃላይ እንደሀገር441,378 ተመራጮች በመስጂዶች በየዘርፉ ተመርጠዋል፡፡

 በወረዳ ላይ የተደረገ ምርጫ 9126 ተመራጮች በሀገር ደረጃ በወረዳ ም/ቤትየተመርጠዋል፡፡

 በሀገር ደረጃ ለዞኖች ም/ቤት የተመረጡ 1377 ተመራጮች ናቸው፡፡

 ሁሉም ክልሎች የራሳቸውን ምክር ቤት ለማቋቋም በተካሄደው ምርጫ ምርጫችንበመስጂዳችን በሚል መርህ መሠረት እንደሚከተለው ምርጫቸውን አከናውነዋል፡፡

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ2017 ምርጫ አስፈፃሚ ቦርድ በጠቅላይ ምክርቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ በመገኘት አዲሱን ተመራጮች ርክክብ ጨርሰው በተመደቡበት ሥራና ለተመደቡለት ...
09/10/2025

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ2017 ምርጫ አስፈፃሚ ቦርድ በጠቅላይ ምክርቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ በመገኘት አዲሱን ተመራጮች ርክክብ ጨርሰው በተመደቡበት ሥራና ለተመደቡለት እርከን ሥራ መጀመራቸውን ለማረጋገጥ የሱፐርቪዥን ሥራ አከናውኗል።

በሱፐርቪዥኑ ላይ የምርጫ ቦርዱ ሰብሳቢ አብዱልአዚዝ ኢብራሂም (ዶር) ጨምሮ ሌሎች የዘርፉ አባላት የተገኙበት ሲሆን በሱፐርቪዥናቸው የፕሬዝዳንቱ የክቡር ዶክተር ሼኽ ሐጂ ኢብራሂም እና የተቀዳሚ ም/ፕረዝዳንት ሼኽ አብዱልከሪም ሼኽ በድረዲን እና የሁለቱም ም/ፕረዝዳንቶችና ዋና ፀኃፊ እንዲሁም የሌሎች ስራ አሰወፈፃሚ አባላት ቢሮ ተጎብኝቷል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ምርጫ አስፈፃሚ ቦርድ ከትላንት ጀምሮ በተካሄደው ምርጫ ጠቅላይ ም/ቤቱን ለ5 ዓመታት የሚመሩ  ከፍተኛ አመራሮች እና ስራ አስፈፃሚ አባላት ታው...
07/09/2025

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ምርጫ አስፈፃሚ ቦርድ ከትላንት ጀምሮ በተካሄደው ምርጫ ጠቅላይ ም/ቤቱን ለ5 ዓመታት የሚመሩ ከፍተኛ አመራሮች እና ስራ አስፈፃሚ አባላት ታውቀዋል።

በዚህ መሰረት:-

1- የክበር ዶክተር ሼይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ -ፕሬዝዳንት
2- ሼይኽ አብዱልከሪም ሼይኽ በድረዲን- ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት
3- ሼይኽ ጁነይድ ሀምዛ-ምክትል ፕሬዝዳንት
4- ሼይኽ ሀሚድ ሙሳ- ምክትል ፕሬዝዳንት
5- ዑስታዝ ተምኪን አብዱላሂ- ዋና ፀሀፊ (ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ) ምሁር
6- ሸይኽ አሚን ኢብሮ-የስራ አስፈፃሚ አባል (ከድሬዳዋ )
7- ዶ/ር ሙሐመድ ሳሊህ - የስራ አስፈፃሚ አባል (ከኦሮሚያ)
8- ሸይኽ ሙሐመድ አሚን አያሽ - የስራ አስፈፃሚ አባል (ከሐረሪ)
9- ሸይኽ ሙሐመድ አህመድ ያሲን የስራ አስፈፃሚ አባል (ከአፋር)
10- ሸይኽ ኢድሪስ ደጋን- የስራ አስፈፃሚ አባል (ከአማራ ክልል)
11- ዑስታዝ ፋሪስ ግርማ- የስራ አስፈፃሚ አባል (ከደቡብ ምዕራብ) ምሁር
12- ዑስታዝ ፋይሰል ኢማም - የስራ አስፈፃሚ አባል (ከጋምቤላ) ምሁር
13- ዑስታዝ ፋሪስ ጀማል - የስራ አስፈፃሚ አባል (ከደቡብ ኢትዮጵያ) ምሁር እና
14- ሸይኽ ሽኩር ቃሲም- የስራ አስፈፃሚ አባል (ከሲዳማ ክልል)
15 ኢንጅነር አንዋር ሙስጠፋ (ትግራይ) ሆነው ተመርጠዋል።

በተጨማሪም 7 አባላት ያለው የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዑለማ ጉባኤ አባላት የተመረጡ ሲሆን

በዚሁ መሰረት፦

1 ሸይኽ አሊ መሀመድ- ሰብሳቢ
2 ዶክተር ማህሙድ ሁሴን - ምክትል ሰብሳቢ
3 ዶክተር መሀመድ ከማል- ጸሀፊ
4 ሸይኽ ኤልያስ አህመድ -አባል
5 ሸይኽ አብዱሰላም አንዋር - አባል
6 ሸይኽ ዚያድ አሊይ- አባል
7 ሸይኽ አድናን መሀመድ -አባል

የኢትዮጵያ እስላምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ2017 ማጠቃለያ ምርጫና የምክር ቤት ምስረታ መርሃ ግብር በምስል::ጉዳያችን በሹራችንምርጫችን በመስጂዳችንምርጫ ለፅኑ ተቋም!!!
06/09/2025

የኢትዮጵያ እስላምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ2017 ማጠቃለያ ምርጫና የምክር ቤት ምስረታ መርሃ ግብር በምስል::

ጉዳያችን በሹራችን
ምርጫችን በመስጂዳችን
ምርጫ ለፅኑ ተቋም!!!

የሲዳማ  ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ምስረታ እና የስራ አሰፈፃሚዎች ምርጫ በተሳካ ሁኔት ተጠናቀቀ:: ‎ሐጅ አብዱሽኩር አብዱልቃድር የክልሉ ፕራዝዳንት ሆኖ ተመርጠዋል።‎አቶ አ...
03/09/2025

የሲዳማ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ምስረታ እና የስራ አሰፈፃሚዎች ምርጫ በተሳካ ሁኔት ተጠናቀቀ::

‎ሐጅ አብዱሽኩር አብዱልቃድር የክልሉ ፕራዝዳንት ሆኖ ተመርጠዋል።
‎አቶ አብዱሽኩር አማን ምክትል ፕራዝዳንት እንድሁም አቶ ሆሴን ሪቂዋ ዎቦ የክልሉ ፀሃፊ ሆኖ ተመርጧል::

ጉዳያችን በሹራችን
ምርጫችን በመስጂዳችን
ምርጫ ለፅኑ ተቋም!!!

03/09/2025

IMALA MILKII !

የደቡብ ኢትዮጽያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ምስረታ እና የስራ አሰፈፃሚዎች ምርጫ በተሳካ ሁኔት ተጠናቁዋል:: ‎ሐጅ ያሲን ከድር አንበሴ የክልሉ ፕራዝዳንት ሆኖ ተመርጠዋል። ...
02/09/2025

የደቡብ ኢትዮጽያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ምስረታ እና የስራ አሰፈፃሚዎች ምርጫ በተሳካ ሁኔት ተጠናቁዋል::

‎ሐጅ ያሲን ከድር አንበሴ የክልሉ ፕራዝዳንት ሆኖ ተመርጠዋል። ሸህ ሚፍታ ኮማል አብደላ ምክትል ፕራዝዳንት እንድሁም አቶ ፋሪስ ጀማል ከማል ፀሃፊ ሆኖ ተመርጧል::

ጉዳያችን በሹራችን
ምርጫችን በመስጂዳችን
ምርጫ ለፅኑ ተቋም!!!

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ባካሄደው የምስረታ ጉባዔና የስራ አስፈጻሚ ምርጫ ኢማም ሃጂ አብዱልሃዲ አህመድ ቡርሃንን የከፍተኛ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት አድርጎ...
02/09/2025

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ባካሄደው የምስረታ ጉባዔና የስራ አስፈጻሚ ምርጫ ኢማም ሃጂ አብዱልሃዲ አህመድ ቡርሃንን የከፍተኛ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት አድርጎ ሰይሟል።

በዚሁ በመስራች ጉባዔ መሰረት
1- ኢማም ሀጂ አብዱልሃዲ አህመድ - ፕሬዚደንት (ከኡለማዕ)
2- ኡስታዝ ባህጃ አብዱልጀሊል ምክትል ፕሬዚደንት (ከኡለማዕ)
3- ሸህ ኡመር ሙስጠፋ - ጸሃፊ (ከምሁራን)
4- ኡስታዝ ሳዲቅ ወጌቦ አባል ከኡለማዕ
5- ሸይኽ ሙስጠፋ ጀማል አባል ከኡለማ
6- ሸይኽ ሙክታር ሀሰን አባል ከኡለማ
7- ኡስታዝ ናስር ሙሐመድ አባል ከኡለማዕ
8- አባዝናብ አባዋሬ አባል ከስራ ማህበረሰብ
9- ሸይኽ አህመድ አበቴ አባል ከኡለማ
10- ኢስማኢል ሻሜቦ አባል ከወጣቶች
11- ዙበይዳ ሀቢብ አባል ከሴቶች ተመርጠው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።

በሌላም በኩል

1-ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን
2- ሀጂ ሽፋ ሙሐመድ
3- ሸይኽ አዩብ ሙሐመድ
4- ኡስታዝ ሰኢድ ጅላሉ
5- ሸይኽ ረሻድ ከድር
6- ሸይኽ አብዱሰላም ከድር
7- ሸይኽ ሙስጠፋ ሙሐመድ
8- ሁሴን ሙሐመድ
9- አብዱረሂም ሁሴን
10- መሐመድ ሱልጣን እንዲሁም
11- ሙንተሃ ሀያቱ ክልሉን ወክለው ለፌዴራል ተመርጠዋል።

በምርጫና መስራች ጉባኤው ላይ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት የህግና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ጽ/ቤት የህግ ጉዳዮች አማካሪ ወ/ሮ መቅደስ ማቴዎስ፣ የፌዴራልና የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ምርጫ አስፈጻሚ አመራሮች፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት የስራ ሀላፊዎች፣ የዞንና የልዩ ወረዳ እስልምና ጉዳይ ምክር ቤት ስራ አስፈጻሚዎች እንዲሁም ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተሳትፈዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ምስረታ እና የስራ አሰፈፃሚዎች ምርጫ በተሳካ ሁኔት ተጠናቁዋል:: ጉዳያችን በሹራችንምርጫችን በመስጂዳችንምርጫ ለፅኑ ተቋም!!!
02/09/2025

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ምስረታ እና የስራ አሰፈፃሚዎች ምርጫ በተሳካ ሁኔት ተጠናቁዋል::

ጉዳያችን በሹራችን
ምርጫችን በመስጂዳችን
ምርጫ ለፅኑ ተቋም!!!

Address

Addis Ababa
0000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Federal Majlis Election Board የፌዴራል መጅሊስ ምርጫ ቦርድ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share