Home of God's Royal Family Internationl Church

Home of God's Royal Family Internationl Church Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Home of God's Royal Family Internationl Church, Religious organisation, piyasa, Addis Ababa.

ኑ አብረዉን የጌታን ፀጋ ይካፈሉ!
09/04/2022

ኑ አብረዉን የጌታን ፀጋ ይካፈሉ!

04/11/2021

የማለዳ ድምጽ 218
ከዚያም ከብዙ ቀን በኋላ እንዲህ ሆነ፤ የግብፅ ንጉሥ ሞተ የእስራኤልም ልጆች ከባርነት የተነሣ አለቀሱ፥ ጮኹም፥ ስለ ባርነታቸውም ጩኸታቸው ወደ እግዚአብሔር ወጣ።እግዚአብሔርም የለቅሶአቸውን ድምፅ ሰማ፥ እግዚአብሔርም ከአብርሃምና ከይስሐቅ ከያዕቆብም ጋር ያደረገውን ቃል ኪዳን አሰበ።እግዚአብሔርም የእስራኤልን ልጆች አየ፥ እግዚአብሔርም በእነርሱ ያለውን ነገር አወቀ።
ዘጸ. 2:23-25

ለአራት መቶ ዓመታት በባርነት÷ በጭቆና እንዲሁም በከፍተኛ ጭንቀት በግብጽ ምድር የነበሩት እስራኤላውያን የጉብኝታቸው ሰዓት በደረሰ ጊዜ ወደ እግዚአብሔርም ጮኹ። ጩኸታቸው የመጨረሻ÷ ምሬት የተቀላቀለበት እና ባርነት በቃን የሚል ነበር። እግዚአብሔር እየሆነባቸው ያለውን ነገር ተመለከተ÷ ኪዳኑንም አሰበ ሊያድናቸውም ወረደ።

በዚህ ጊዜ ጸሎትን ወደሚሰማ÷ ኪዳኑን ወደሚያስብ ለማዳንም እጁን ወደሚዘረጋውና ብቸኛ ወደሆነው ተስፋችን ወደ እግዚአብሔር በመጮህ እንበርታ። እርሱ ሁልጊዜ ከፍትህ ጋር የሚቆምና ጣልቃ የሚገባ አምላክ ነውና ከእርሱ ጋር እንቁም።

የሚታየውና የሚሰማው ነገር ተስፋ እንደሌለ የሚያሳይ ቢሆንም ከአምላካችን ዘንድ ግን ተስፋ አለና ለምድራችን እረፍት በተዋረደ መንፈስና በተሰበረ ልብ ወደ እርሱ እንቅረብ። በእርግጥ ለምድራችን ጉብኝት ይሆናል!!!
መላኩ ፈርሻ(መጋቢ)

05/05/2021

Paster Mele:
የማለዳ ድምጽ 38

የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ። እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን። ኢያ 24:15

እስራኤላውያን በኢያሱ መሪነት ሰላሳ አንድ (31) ነገስታትን ድል በመንሳት የተስፋይቱ ምድር ከነዓን እግዚአብሔር አሳልፎ ከሰጣቸው በኃላ ኢያሱ ህዝቡን ሁሉ ሰብስቦ :- የምታመልኩትን ምረጡ? የሚል ገራሚ ጥያቄ አቀረበ።

አስቡት ያገኙት ድል ሁሉ ምክንያቱ የእነርሱ ጦር ብርታትና ጥንካሬ ወይም የህይወታቸው ጥራት ሳይሆን እጅጉኑ የበዛው የአምላካቸው የእግዚአብሔር ቸርነትና በጎነት እንደሆነ ሳይታለም የተፈታ ጉዳይ ነው። ነገር ግን እግዚአብሔር አስቀድሞ በዘዳ.8 እንዳስጠነቃቸው ሁሉ ተሳክቶ ባሳረፍኩህ ጊዜ አምላክህን እነዳትረሳ ተጠንቀቅ ብሎ ነበር ።እናም ምንም እንኳን ለኢያሱ ኧረ እርሱን እናመልካለን ብለው ምላሽ ቢሰጡትም ረጅም ግን ሳይጓዙ ባዕዳንን ማምለካቸውን መጽሐፈ መሳፍንት ይነግረናል።

ቅዱሳን እግዚአብሔርን ለማምለክ የመጀመሪያው ምክንያት ማድረግ አለማድረጉ ሳይሆን አምላክነቱ ነው ማድረግስ ቢሆን ምን ያላደረገልን አለና? አነርሱን ከግብጽ አውጥቶ ከነዓን÷ እኛን ከሞት አውጥቶ የዘላለም ህይወት÷ እነርሱ በኢያሱ ሲመሩና ሲዋጉ ለእኛ እዉነተኛውን ኢያሱ(አዳኝ) በመላክና እርሱ ራሱ ሁሉን በመዋጋት ከጨለማው ስልጣን አድኖ አስተማማኝና ዘላለማዊ እረፍት ሰጠን...ኧረ ስንቱን ዘርዝሬ እዘልቀዋለሁ።እናማ ዕድሜ ልካችንን በሁለንተናችን እርሱን ማምለክ ይሁንልን።

በነገር ሁሉ ጌታን ስታመልኩ ዋሉ!!

03/05/2021

Paster Mele:
የማለዳ ድምጽ 36
ነገር ግን ሄዳችሁ ለደቀ መዛሙርቱ ለጴጥሮስም፡ ወደ ገሊላ ይቀድማችኋል፤ እንደ ነገራችሁ በዚያ ታዩታላችሁ፡ ብላችሁ ንገሩአቸው፡ አላቸው።
ማር.16:7
ደጆች ተዘግተው ሳሉ ኢየሱስ መጣ፤ በመካከላቸውም ቆሞ፡— ሰላም ለእናንተ ይሁን፡ አላቸው። ዮሐ.20:26

ኢየሱስ ክርስቶስ ከትንሳዔ በኃላ ለደቀ መዛሙርት በተለያየ ጊዜ በተለያየ መልኩ ተገልጧል። ዛሬ ከላይ ከተቀመጡት ሁለት ጥቅሶች በመነሳት በልቤ ያለውን ህያውና በሁላችንም ላይ የሚሰራ መልዕክቴን እንደሚከተለው አቀርባለሁ።

የመጀመሪያው ወደ ገሊላ ይቀድማቹሃል በዚያም ታዪታላችሁ የተባለውና ደቀ መዛሙርት እርሱን የትንሳዔውን ጌታ #ያዩበት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ያለ ቀጠሮ የሆነና ጌታ እነርሱን #ያየበት ነው። በዚያም ያሉበትን ሁኔታ አውቆ ደጆች ተዘግተው ሳለ በመካከላቸው ቆሞ ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዳላቸው እንመለከታለን።

ሁለት ነገሮችን ልብ በሉልኝ ጌታን ማየትና በጌታ መታየት። እርሱን ማየታቸው እንደተናገረው በሶስተኛው ቀን ከሙታን ይነሳል የሚለውን ቃል ፍጻሜ እንዲያስተውሉ ሲያደርጋቸው÷ በእርሱ መታየታቸው ደግመው ፈርተውና ደጆችን ዘግተው(በተዘጋው በር ተወስነው) ተቀምጠው ከነበረበት ያለ ገደብ እስከምድር ዳር ድረስ እንደሚወጡ የማረጋገጫን ቃል እና የእርሱን ሰላም እንዲቀበሉ አደረጋቸው።

ጌታን በማየት እንደ ቃሉ የሆነውን ታማኝነቱን ማስተዋል÷ በእርሱ ደግሞ በመታየት ካለንበት ማንኛውም ፍርሃትና ገደብ በመላቀቅ ወደ ታየልን የክብር ልክ መውጣት ይሁንልን።

ጌታን ስታዩ ÷በእርሱም ደግሞ ስትታዩ ዋሉ!!

02/05/2021

Paster Mele:
የማለዳ ድምጽ 35
ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል። ሮሜ.5:8

አንድ ሰው እንዲህ ሲሉ ሰማሁ "የይሁዳን ሐጢአት እጅግ የከፋ የሚያደርገው ከፈጸማቸው ዘግናኝ ነገሮች በላይ ኢየሱስ ለእርሱ ያሳየው ፍቅር ነው "እጅግ የሚደንቀው እውነት የሰው ልጅ የነበረበት የሐጢአት ጫፍ እንዲሁም እግዚአብሔር ፍቅሩን የገለጠበት ገደብ የለሽ ምህረት ነው።

መጽሐፍ በግልጽ እንደሚናገረው ኢየሱስ የተወለደው÷ የኖረው÷ የሞተውና የተነሳው ለራሱ ሳይሆን ለእኛ ነው። በተወለደ ጊዜ የታወጀው " ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን #ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ አሉ"(ሉቃ.2:14) ሲሆን ከሞት በተነሳም ጊዜ "ህያውን ከሙታን መካከል ስለምን ትፈልጋላችሁ? #ተነሥቶአል እንጂ በዚህ የለም።" ሉቃ 24:5 የሚል ነበር።

ስለዚህ በኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ የሚታወጀው የምስራች ነው ለሐጢአትና ለሞት የተጠየቀው ዋጋ ከበቂ በላይ በሆነው በደሙ ለዘላለም #ተከፍሏል!!! እናም በደስታ ÷በሰላም÷በእረፍት÷በፍሬ...ወዘተ መኖር ነው። እንግዲህ ስለተሰራው ድንቅ ስራ ሁሉን ሰርቶ በነጻ እንካችሁ ያለንን በብዙ እያመሰገንን ለተቀበልነው ድንቅ ስጦታ የሚመጥን ተግባራዊ የህይወት ምላሽ መስጠት ይሁንልን በማለት አበቃሁ!!!

የትንሳዔው በሆነው ህይወት ስትነቃቁ ዋሉ!!

01/05/2021

የማለዳ ድምጽ 34
በወንጌል አላፍርምና፤ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው፥ ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን ነውና።
ሮሜ.1:16
ወንጌል ስለ ክርስቶስ ነው፡፡ ድሩም፣ ማጉም፣ ቋሚውም፣ ወራጅ ምሰሶውም፣ መሠረቱም ቢሆን መሲሑ ኢየሱስ ነው፡፡ የወንጌል አንጽሮት የኢየሱስ ክርስቶስ ብቸኛ አዳኝነትና ጌትነት ነው፡፡ ወንጌልን የምንሰብከው ሌላ አማራጭ ስለሌለ ነው፡፡ "እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን...1ኛቆሮ 1:23

በኢየሱስ ክርስቶስ አምነን ከዳንን በኃላ ሁላችንም አማኞች የተጠራንለት አንድ ጥሪና አደራ አለብን ይኸውም ወንጌልን ለፍጥረት ሁሉ ማድረስ ስለዚህ ሁላችንንም ጌታ ይህንን አደራ ለመወጣት ኃይል ያብዛልን። በዕለተ ስቅለት እንደ ቤተ ክርስቲያን ፒያሳ ላይ የኢየሱስን ወንጌል አብስረናል ጌታ ይባረክ።

ሁላችንም ቢያንስ ለአንድ ሰው ኢየሱስን በቃል በኑሮ መስክረን ማለፍ ይሁንልን!!

ኢየሱስን ስታወሩ ዋሉ!!

30/04/2021

የማለዳ ድምጽ 33
የኢየሱስ ህይወት ደግሞ በሚሞተው ሥጋችን ይገለጥ ዘንድ እኛ ህያዋን የሆንን ከኢየሱስ የተነሣ ዘወትር ለሞት አልፈን እንሰጣለን። 2ቆሮ.4:11

የስቅለት መታሰቢያን በዓልን ስናከብር አይደለም በየዕለት ህይወታችን የተሰቀለውን ጌታ ማሰብ ተገቢ መሆኑ አያጠያይቅም። ለዛሬ ግን እንዲህ አሰብኩ በአደባባይ እርቃኑን በተሰቀለው በክርስቶስ ፍቅር እጅጉኑ የተነኩ ሊታዩበት ሳይሆን ሊታይባቸው ራሳቸውን ስለሰጡ ጥቂት ሰማዕታት አሰብኩ ይኸው በጥቂቱ:-

. . አንቲጳስ በጋለ ነሃስ ተጠበሰለት÷ እሲጢፋኖስ በድንጋይ ተወገረለት÷ እንድርያስ ለሶስት ቀናት በእንጨት ተሰቀለለት÷ያዕቆብ ተሰየፈለት፣ በርጠለሜዎስ በሕይወት ሳለ ቆዳው በስለት ተገፍፎ ፣ ቶማስ በጦር ተወግቶ ሞቱለት፣ ዮሐንስ ተሰየፈለት፣ ማቴዎስ ከጀርባው በሰይፍ ተወግቶ ሞተለት፣ ጴጥሮስም ለሚገድለው ገዳይ ‘’እኔን ስትሰቅለኝ ቁልቁል ስቀለኝ፡፡’’ ብሎ አይደለም በሕይወቱ በአሟሟቱ ሳይቀር አክብሮት ሰማዕት ሆነ፡፡ ብዙዎች በጎልጎታ በተሰቀለላቸውና በሞተላቸው ጌታ ላይ ባላቸው የእምነት አቋም ምክንያት በበትር ተነረቱ፣ በጅራፍ ጀርባቸው ተገሸለጠ፣ ሌሎች ብዙዎችም የሰማይን መዝሙር እየዘመሩ በደስታ በሐሴት እንባ እያመለኩት ሰማዕት ሆኑ፡፡

ስለተሰቀለውና ስለሞተው ስለተነሳውም በክብርም ስለሚመጣው ጌታ ለእርሱ መኖርን በዚህም አቅጣጫ መመልከቱ ትልቅ መባረክ ነው የተወደዳጅሁ ከላይ ከተገለጡት የእምነት አባቶች ለክርስቶስ መሰጠት በጣም እንደራቅን ተሰማኝና እባክህ አንቃን በፍቅርህ የእውነት መነካት ይሁንልን የሚለውን የእንባ ተማጽኖ ብንጋራ ብዬ ነው። በዚህ ላብቃ የኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ ፍሬዎች ጌታ ይታይብን እንጂ አንታይበት በቀረው ዘመናችን በህይወታችንም በሞታችንም ኢየሱስ ይክበር!!

የእውነት እርሱ በእኛ መኖር ሲጀምር መሞታችን ያኔ እርግጥ ይሆናል!!

በጌታ ፍቅር ስትሽነፉ ዋሉ!!

29/04/2021

Paster Mele:
የማለዳ ድምጽ 32
ማንም ወደ እኔ የሚመጣ ቢኖር አባቱንና እናቱን ሚስቱንም ልጆቹንም ወንድሞቹንም እኅቶቹንም የራሱን ሕይወት ስንኳ ሳይቀር ባይጠላ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።”
ሉቃ. 14፥26

ከላይ በተቀመጠው ቃል ላይ ጌታ ኢየሱስ እርሱን መከተል የሚወድ ሰው ቢኖር ሊኖረው ስለሚገባ የህይወት መልክ አስረግጦ ባይጠላ የሚለውን ቃል በመጠቀም ይናገራል። ይህ ባይጠላ የሚለው ቃል በዚህ ስፍራ የሚያሳየን በላጭነትንና ቅድሚያ መስጠትን እንጂ የፍቅር ተቃራኒ ስለሆነው ጥላቻ በፍጹም አለመሆኑን ልብ ይሏል።

ከላይ ለተቀመጡት አባት እናት...ወዘተ ማንም ሰዉ ቅድሚያ የሚሰጣቸው መሆኑ አገር የሚያውቀው እውነት ነው። እናም ጌታ በአጽንዖትና አድምቶ የተናገረው የእርሱ ተከታይ የሆነ ከነዚህ ሁሉ ቀዳሚና ፊተኛ እርሱን ማድረግ አማራጭ የሌለው ምርጫ መሆኑን ነው።

በህይወታችን ቅድሚያ የምንሰጠው ለማን እና ለምን ይሆን?? ለአባት÷ ለእናት እና ለመሳሰሉት ከሆነ አደገኛ ኪሳራ ውስጥ ነን ስለዚህ ከሁሉ በፊትና በላይ በእኛ ምክንያት ከክብሩ ፍቅሩን ላስቀደመ÷ የባርያን መልክ ይዞ የልጅነትን መልክ ለመለሰልን÷ ያለ ልክ ዝቅ ብሎ ያለ ልክ ከፍ አድርጎ በአብ ቀኝ ላስቀመጠንና ዘላለማችንን ለለወጠ ለእርሱ በነገር ሁሉ ቅድሚያ መስጠት÷ እርሱን ዋናና ፊተኛ ማድረግ ይሁንልን!!

ኢየሱስ ከሁሉ በልጦባችሁ ኑሩ!!! ብሩህ ቀን ተመኘሁ

16/01/2020
የቤተክርስቲያኗ ወርሃዊ ጋዜጣ
06/12/2019

የቤተክርስቲያኗ ወርሃዊ ጋዜጣ

Address

Piyasa
Addis Ababa
13145

Telephone

+251911987968

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Home of God's Royal Family Internationl Church posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Home of God's Royal Family Internationl Church:

Share