Mari ketema kalehiwot b/yn

Mari ketema kalehiwot b/yn Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Mari ketema kalehiwot b/yn, Religious organisation, Mari, Addis Ababa.

              ‎ሐዋርያት 9‎⁵ ❝ጌታ ሆይ፥ ማን ነህ? አለው። እርሱም፦ አንተ የምታሳድደኝ እኔ ኢየሱስ ነኝ፤..........❞‎‎ -ወንጌል_ቤተክርስቲያን‎በቀን 28/11 ከ7:30 ጀ...
16/07/2026


‎ሐዋርያት 9
‎⁵ ❝ጌታ ሆይ፥ ማን ነህ? አለው። እርሱም፦ አንተ የምታሳድደኝ እኔ ኢየሱስ ነኝ፤..........❞

‎ -ወንጌል_ቤተክርስቲያን
‎በቀን 28/11 ከ7:30 ጀምሮ ተዘጋጅቷል!።
➽‎በዕለቱም፦
‎ ➥የፀሎት ጊዜ
‎ ➥የቃል ትምህርት ጊዜ
‎ ➥ የአምልኮ ጊዜ
‎ ➥እንዲሁም የስነ-ጽሁፍ ጊዜ ይኖረናል
‎ እርሶ ብቻ ቀጠሮትን በቀን 28/11/2018, ከ7:00 ጀምሮ ከእኛ ጋር ያድርጉ!።

#‎አዘጋጅ፦ በኢትዮጵያ ሙሉ-ወንጌል ቤተክርስቲያን የማሪ ከተማ ሙሉ-ወንጌል አጥቢያ ቤተክርስቲያን የወጣቶች አገልግሎት።

 ወንጌላችን ጌና ድል ያደርጋል የእግዚአብሔር ቃል ገና አለምን ይዞራል በአራቱም ማዕዘን ይዳረሳልሁሉን ይለውጣል ያሸንፋል
15/07/2026


ወንጌላችን ጌና ድል ያደርጋል
የእግዚአብሔር ቃል ገና አለምን ይዞራል
በአራቱም ማዕዘን ይዳረሳል
ሁሉን ይለውጣል ያሸንፋል

 ።የሞትን ሞት እንዳትሞቱ ኑ ወደ ኢየሱስ    የድል ቀን ነው ዛሬምበለቅሶ ውስጥ እንኳ የክርስትያን ደስታ ሙሉ ነው።
14/07/2026


የሞትን ሞት እንዳትሞቱ ኑ ወደ ኢየሱስ
የድል ቀን ነው ዛሬም
በለቅሶ ውስጥ እንኳ የክርስትያን ደስታ ሙሉ ነው።

12/07/2026

"የቅዱሳኑ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው።"       — መዝሙር 116፥15   -ሥርዓትዛሬ በ5/11/2018 ዓ.ም. የመሪት አልማዝ ደመኔ የመጨረሻ ሽኝትና የቀብር ሥነ-ሥርዓት ከተለያ...
12/07/2026

"የቅዱሳኑ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው።"
— መዝሙር 116፥15
-ሥርዓት
ዛሬ በ5/11/2018 ዓ.ም. የመሪት አልማዝ ደመኔ የመጨረሻ ሽኝትና የቀብር ሥነ-ሥርዓት ከተለያዩ ቤተ ክርስቲያናት በተሰበሰቡ መዘምራን፣ በሙሉ ምዕመናን፣ በቤተሰቦች፣ በዘመዶችና በወዳጆች በተገኙበት በክብር ተፈጽሟል።
✍️እግዚአብሔር ይመስገን ወንጌል በአደባባይ በድል ተሰብኳል።
በሥነ-ሥርዓቱ ወቅት ከተለያዩ ቤተ ክርስቲያናት የተሰበሰቡ መዘምራን የመጽናኛና የተስፋ መዝሙሮችን ያቀረቡ ሲሆን፣ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችም የጸሎት፣ የቃለ ምክርና የማጽናኛ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል። ተሳታፊዎችም የሟቿን መልካም ሕይወት፣ የእምነት ጉዞና መልካም ሥራዎቿን በማስታወስ የመጨረሻ ስንብታቸውን አድርገዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙ ምዕመናንና እንግዶች ለቤተሰቡ የማጽናኛ ቃላትን በማቅረብ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከጎናቸው መሆናቸውን ገልጸዋል። ቤተሰቡም በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ለተገኙ ሁሉ እና በጸሎትና በተለያዩ ድጋፎች አብረዋቸው ለቆዩ ሁሉ ከልብ የመነጨ ምስጋናቸውን ገልጸዋል።
እግዚአብሔር ለመላው ቤተሰብ መጽናናትን ይስጥ፤ ለመ/ሪት አልማዝ ደመኔም የዘላለም ዕረፍትን ያድርግላት።

     _የተስፋን_ቃል_በማቅረብ_ሟቹን_ሸኙ።             ።  ጋር ገናናው የሆነውን የጌታን ስም ከፍ አድርገናል!!!!    #እናውጃለን፤ ለቤተሰቡም መጽናናትና የእግዚአብሔር ሰላም እ...
09/07/2026


_የተስፋን_ቃል_በማቅረብ_ሟቹን_ሸኙ።

ጋር ገናናው የሆነውን የጌታን ስም ከፍ አድርገናል!!!!
#እናውጃለን፤ ለቤተሰቡም መጽናናትና የእግዚአብሔር ሰላም እንመኛለን። በልዩነታችን ሳንጣላ በክብርና በፍቅር እንኑር።

 ‎በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን በየዓመቱ በልዩ ድምቀት የሚከበረው የሴቶች በዓል፣ በዘንድሮው 16ኛ ዙር ዛሬ 28/10/2018 ዓ.ም በማሪ ከተማ አጥቢያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ...
05/07/2026


‎በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን በየዓመቱ በልዩ ድምቀት የሚከበረው የሴቶች በዓል፣ በዘንድሮው 16ኛ ዙር ዛሬ 28/10/2018 ዓ.ም በማሪ ከተማ አጥቢያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን በእግዚአብሔር ጸጋና በታላቅ መንፈሳዊ ደስታ በድል ተከብሯል።

‎የበዓሉ መርሃ ግብር ከማለዳው ጀምሮ በጋራ ጸሎት፣ በሕብረት አምልኮ፣ በምስጋናና በዝማሬ የተከፈተ ሲሆን፣ በመቀጠልም በእግዚአብሔር ቃል ላይ የተመሠረቱ ጠንካራ መንፈሳዊ ትምህርቶች ቀርበዋል። ትምህርቶቹም ሴቶች በክርስቶስ ያላቸውን ማንነት፣ የጸሎት ሕይወት፣ በቤተሰብና በቤተክርስቲያን ውስጥ ያላቸውን ኃላፊነት፣ እንዲሁም በአገልግሎት የበለጠ ፍሬያማ እንዲሆኑ የሚያበረታቱ ነበሩ።
‎በዝግጅቱ ላይ የሴቶች መዘምራን በመንፈስ የተሞሉ መዝሙሮችን በማቅረብ ምዕመናንን ወደ ጥልቅ አምልኮ አስገብተዋል። በተጨማሪም ልዩ ልዩ መንፈሳዊ የውዳሴ ዝግጅቶች ቀርበው በዓሉን የበለጠ አድምቀውታል።

‎በበዓሉ ወቅት የቤተክርስቲያኑ አገልጋዮች ለሴቶች የማበረታቻ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን፣ በየቤተሰባቸው፣ በቤተክርስቲያንና በማኅበረሰብ ውስጥ የብርሃንና የበረከት መሣሪያዎች እንዲሆኑ አሳስበዋል። በተለይም በአንድነት፣ በፍቅርና በትሕትና በመቆም ለትውልዱ መልካም አርአያ እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል።

‎የዕለቱ ፕሮግራም በብዙ ተሳታፊዎች ታድሞ የተከበረ ሲሆን፣ ተሳታፊዎችም በቃሉ፣ በአምልኮውና በኅብረቱ በመታነጽ በብዙ መንፈሳዊ በረከት ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል።
‎በመጨረሻም 18ኛው ዙር የሴቶች በዓል በማሪ ከተማ አጥቢያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን በእግዚአብሔር ጸጋ፣ በሰላም፣ በአንድነትና በታላቅ ድል ተጠናቋል። ለዚህ የተባረከ ፕሮግራም መሳካት በጸሎት፣ በአገልግሎትና በተለያዩ ድጋፎች የተሳተፉ ሁሉ እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርካቸው።
‎"ለእግዚአብሔር ክብር ይሁን!"

 ሰበር የድል ዜና ❤😍ክብር ሁሉ በሰማይና በምድር ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ይሁን!! በወላይታ ዞን በቦሎሶ ቦምቤ  ወረዳ ዳማላ ቀበሌ ለረጅም ዓመታት በጥንቆላ ሥራ አየሳተና እያሳተ የቆዬ ...
28/06/2026


ሰበር የድል ዜና ❤😍

ክብር ሁሉ በሰማይና በምድር ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ይሁን!!
በወላይታ ዞን በቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ ዳማላ ቀበሌ ለረጅም ዓመታት በጥንቆላ ሥራ አየሳተና እያሳተ የቆዬ አንድ ግለሰብ ትናት በቀን ሰኔ 20/2018 ዓ.ም ከነሙሉ ቤተሰቡ በአጠቃላይ ከ20 በላይ በተሰብ አባላት ጋር ጌታ ኢየሱስን የግል አዳኝ አድርጎ ተቀብለዋል ።

ሰለ እርሱ እግዚአብሔርን አመስግኑ🙏 እግዚአብሔር በቤቱ እንዲተክልም ፀልዩ🤲 እንዲህ ዓይነት መንገድ ላይ ያሉትን እግዚአብሔር ወደ ቤት እንዲያመጣቸው ፀልዩ 🤲 ❤ ወንጌል ያሸንፋል 🙏

Latto Wongellay 🤲

ይህን ለዓለም ያድርጉ 😍😍😍

ሰይጣን ይጨነቅ

Humbo Press-ሁምቦ ፕረስ

 በኢትዮጵያ ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን ኦሞ ጎጀብ ቀጠና ከመላው ዳውሮ አካባቢ በመጡ ክርስቲያን አባቶች፣ እናቶች፣ ወንድሞችና እህቶች ጋር  ታላቅ አቀባበል ዳውሮ ታርጫ
27/06/2026


በኢትዮጵያ ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን ኦሞ ጎጀብ ቀጠና ከመላው ዳውሮ አካባቢ በመጡ ክርስቲያን አባቶች፣ እናቶች፣ ወንድሞችና እህቶች ጋር ታላቅ አቀባበል ዳውሮ ታርጫ

Address

Mari
Addis Ababa
ወንጌልስለልጁነው

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mari ketema kalehiwot b/yn posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share