24/05/2026
ዘጸአት 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁶ ለምድያምም ካህን ሰባት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም መጥተው ውኃ ቀዱ፥ የአባታቸውንም በጎች ሊያጠጡ የውኃውን ገንዳ ሞሉ።
¹⁷ እረኞችም መጥተው ገፉአቸው፤ ሙሴ ግን ተነሥቶ ረዳቸው፥ በጎቻቸውንም አጠጣላቸው።
¹⁸ ወደ አባታቸው ወደ ራጉኤልም በመጡ ጊዜ፦ ስለ ምን ዛሬ ፈጥናችሁ መጣችሁ? አላቸው።
¹⁹ እነርሱም፦ አንድ የግብፅ ሰው ከእረኞች እጅ አዳነን፥ ደግሞም ቀዳልን፥ በጎቻችንንም አጠጣ አሉ።
²⁰ ልጆቹንም፦ እርሱ ወዴት ነው? ለምንስ ያንን ሰው ተዋችሁት? ጥሩት እንጀራም ይብላ አላቸው።